ሐና በትክክል መሲሑን አገኘችው እናም በዚህ ምክንያት ስለ መምጣቱ ቤዛን ለሚሹ ሁሉ የመናገር ፍላጎት ተሞላች፡፡ ኢየሱስን ያገኙት ሴቶች ታላላቅ ሰባኪዎች እና መነቃቅዮች ናቸው፡፡ በሐና ቅባት የተሞሉ በዘመናችን ያሉ ሴቶች ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት ጊዜአቸውን ያሳልፋሉ የእርሱን ግርማ እየተመለከቱ፣ የከበረ መገኘቱን እየተላመዱት እና በጸሎት በኩል የልብ ምቱን እያዳመጡ፡፡ በሐና ቅባት የተሞሉት የኢየሱስን ፍቅር እውነታ በሚነድ ፍቅር እና ቅንዓት ያካፍላሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት የተጠመቁ ሴቶች የክብር ተሸካሚዎች ይሆናሉ፡፡ እነሱም በምልክቶች እና በሚከተሉ ድንቅ ነገሮች ሁሉ ወንጌልን ይሰብካሉ፡
እነዚህ ሴቶች ከሚያነጻው እሳት ጋር ስፍር ቁጥር የሌለው ሰዓት ስለሚያሳልፉ ልዩ የቅባት አገልግሎት ያገኛሉ ፡፡ ፍቅር ፣ ንፅህና እና ኃይል ከውስጣቸው ይወጣል፡፡ “እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር” (ትንቢተ ዘካ 2፡5)፡፡ የእግዚአብሔር መገኘት በተአምራዊ ሁኔታ ከእነሱ ጋር ይሆናል ፣ እሳቱም በእነሱ ውስጥ ይለቀቃል፡፡ እነሱም በፍቅር ተነሳስተው የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሰው ልጆች ለማሳየት የፅድቅ ሰባኪዎች ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ሴቶች በጨለማ ኃይሎች ለተጠመዱ ሰዎች መዳንን እና ፈውስን ያመጣሉ፡፡
የዘመናችን ሐና ዓለምን ትወዳለች እንጂ አትኮንንም (ዮሐ 2፡16-17)፡፡ ቤዛን የሚፈልግ ትውልድ አለ እናም እግዚአብሔር ለሥቃያቸው መልስ ይሰጣል፡፡ ሴቶች ለእግዚአብሔር ክብር በሰዋች ልብ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ጌታ በተአምራዊ ኃይል እያጎናጸፍቸው ነው፡፡ እርሱ ለእኛ ሲል የሚሰራ አፍቃሪ አምላክ መሆኑን ለማሳየት ተዓምራቶችን ይለቃል፡፡ መለኮታዊ የሆነ ፈውስ የእግዚአብሔር ርህራሄን ያሳያል ይህም ብዙዎች ወደ እርሱ እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል፡፡ በሉቃስ 7፡16ለ ውስጥ ኢየሱስ የመበለቲቱን ልጅ ከሞት ሲያስነሳ ሰዎቹ እንዲህ አሉ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐበኘ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ”፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአንድ እውነተኛ አምላክ ማመንን ለመደገፍ እና የመልእክተኛው መልእክት ሊያረጋግጥ ይመጣል፡፡ (1ኛ ተሰ 1፡5-6) እንዲ ይላል “ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ፡፡ ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ”
ብዙዎች ሴቶች ሰባኪዎች በመሆናቸው በጭራሽ አይስማሙም ይሆናል ነገር ግን የጌታ እጅ በህይወታችን ላይ እንዳይወርድ መከልከል አይችሉም፡፡ በእርሱ እጅ ታላላቅ ፈውሶችን እና ነፃነትን እንድንፈጽም የእግዚአብሔር እጅ ኃይል ይሰጠናል፡፡
የጋለ የኢየሱስ ፍቅር
“እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና፡፡ ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው፡፡ ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም፥ ፈሳሾችም አያሰጥሙአትም፤ ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል፡፡” (ዘሰ 8፡6-7)
በዛሬው ጊዜ ለሴቶች ብቸኛው መፍትሄ ኢየሱስ ነው፡፡ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ ተስፋ ነው፡፡ ከምንሠራው እና ከምንናገረው ነገር ሁሉ በስተጀርባ ኃይል የሚሆነን ኢየሱስ እና የሱፍቅር ነው፡፡ ኢየሱስ የደህንነት ስፍራችን ነው፡፡ ፍቅሩ ልባቹን ይፈውሳል፡፡ ጠላት በሴቶች ላይ አባት መሰል የግፍያ መንፈስን ልኳል ነገር ግን ጌታ ይህንን ጠላት ለማጥፋት እና ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ የጋለ ፍቅሩን በመልቀቅ ላይ ነው፡፡
የኢየሱስን ፍቅር በልባችን ላይ እንደ ማኅተም የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ እርሱ ድል አድራጊ ንጉሣችን ነው፡፡ የእሱ የፍቅር ማኅተም ለጥሪያችን ስልጣን ይሰጠናል፡፡ በድሮ ጊዜ ንጉስ በጣም አስፈላጊ ሰነድ ላይ የሰም ማኅተም ያሳርፍበታል ከዚያም ሰነዱ የንጉሱን ምልክት በያዘ ቀለበት ይታተማል፡፡ እነዚህ ሰነዶች የንጉሱን ስልጣን እና የባለቤትነት መብት በሚወክለው በንጉሱ ማኅተም የተጠበቁ እና የተረጋገጡ ናቸው፡፡ በዘመናችን ያሉ ሐናን የሚመስሉ ሴቶች በሕይወታቸው እና በአገልግሎቶቻቸው ላይ የንጉሶች ንጉሥ ማኅተም ይኖራቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ይጠብቃቸዋል እናም የመንግሥቱን አጀንዳ ለማራመድ የሰማይ ሀብቶችን ሁሉ ለነሱ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ለእኛ በቂ መሆን አለበት፡፡ ከወንዶችንም ሆነ ከኅብረተሰቡ ተቀባይነት ለማግኘት መፈለግ የለብንም፡፡ እሱን ለመውደድ እና እሱን ለማስደሰት መኖር አለብን፡፡ እኛ በተስፋው መንፈስ ቅዱስ ታትመናል፡፡ (ኤፌ 1፡13)
የሐና ቅባት:
የድፍረት ፣ የኃይል እና የጥንካሬ ሴት ሁኑ
ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በምድር በተገለጠበት ጊዜ እግዚአብሔር የጾም እና የጸሎት ጸጋን በሐና ላይ ተለቀቀ ፡፡ የኢየሱስ በምድር መገለጥ ለዳግም ምጽአቱ እግዚአብሔር ትውልድ ሙሉ ሴቶች ላይ ጸጋን በመልቀቅ ላይ ነው እንደ ሐና በተመሳሳይ ዓይነት የቅባት አገልግሎት የሚሰሩ ሴቶች፡፡
ይህ መጽሐፍ በምድር ሁሉ እየተሰራጭ ለጸሎት እንቅስቃሴ መነሻ ይሆናል በምድር ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ መነቃቃትን ያመጣል፡፡
የዲቦራ ቅባት:
ጥበበኛ እና አስተዋይ ሴት የመሆን ጥሪን መቀበል
ብሉይ ኪዳን ዲቦራን እንደ ዳኛ፣ አማላጅ፣ ነብይት፣ የእስራኤል እናት እና በወታደራዊ ስልት አንድ ኃያል ቅንጅት እንደሆነች ይገልጻታል፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘመን እግዚአብሔር የዛሬዎቹን ሴቶች ከእራሳቸው በላይ ወደሆነ ዓላማ እየጠራቸው ነው፡፡ የዲቦራ ቅባት ምንም እንኳን በወግ ወጥመድ ውስጥ ብትያዙም በባህላዊ እና በጾታዊ ጭፍንነት ውስጥ እንደ እስር ቢቆለፍባቹም እነዚህን መሰናክሎች ሰብራቹ እንድትወጡ እግዚአብሔር እንደሚፈልግ ያሳየናል፡፡ የአላማቹን ሙላት ለመቀበል ጊዜው አሁን ነው!
በሥራ ቦታቹ ፣ በቤታቹ ወይም በቤተክርስቲያናቹ ውስጥ የምታሳድሩት ተጽዕኖ ምንም ይሁን ምን የዘመናችን ዲቦራ የመሆንን ፈታኝ ጥሪ ተቀበሉ ለእግዚአብሔር ቁሙ እና በድፍረት ሌሎችን ወደ እርሱ ምሩ!
የአስቴር ቅባት፡
የጸሎት፣የድፍረት እና የተጽዕኖ ሴት መሆን
አስቴር ለሕዝቧ ደህንነትና ስለ እግዚአብሔር እቅድ ስትል ህይወቷን አደጋ ላይ ለመጣል ፈቃደኛ ነበረች፡፡ በእግዚአብሔር ስልታዊ ቦታ ተጽዕኖ ባለው ስፍራ የተቀመጠችው አስቴር እግዚአብሔር ማንንም እንዴት ሊጠቀም እንደመሚችል ኃይለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ ናት፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሪ ምላሽ ሰጠች እናም ዝግጁ ለመሆን በአካላዊ እና በመንፈሳዊ የዝግጅት ጊዜ ውስጥ አለፈች፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን እንደነበረው እግዚአብሔር በዛሬው ጊዜ ሴቶችን ይሾማል እናም የእሱን የክብር ባህል እንዲያነሳሱ መለኮታዊ ዕድሎችን ይሰጣቸዋል፡፡
የአስቴር ቅባት ሴቶችን ታላቅ የሚያደርጋቸውን ባሕርያት፣ተጽዕኖን የመፍጠር ኃይል፣ለተሰጣቹ ስራ የእግዚአብሔርን ሞገስ ለማግኘት ቁልፉን እና የአስቴር የስኬት ሚስጥርን ጨምሮ ያሳየናል፡፡ የመጣቹበት ቦታ ወይም ያላቹ ችሎታ እና ተሰጥኦ ምንም ለውጥ የለውም፤ከፈቀዳቹለት እግዚአብሔር ሕይወታቹን ለክብሩ ሊጠቀም ይችላል!
የሐና ቅባት፡
ጠንካራ፣ስኬታማ እና ፍሬያማ ሴት መሆን
በሐና ቅባት ላይ ሚሸል ማክሊን-ዋልተርስ ተደጋጋሚ ተስፋ አስቆራጭ እና የጠላት መሳለቅ ፊት የማያመነታ አንድ ልዩ መንፈሳዊ ሀይልን ገልጣለች፡፡
በልዩ እና ኃይል ሰጪ ትንቢት ማክሊን-ዋልተርስ በሴቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ እና ዓላማ ላይ የሚያጋጥሟቸውን ጉዳዮች እና ሌሎች ጉዳዮችንም ታነሳለች፡፡
እነዚህ ሴቶች ናቸው በህይወታቸው እና በመጪዎቹ ትውልዶች ውስጥ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚመለከቱ፡፡
የሩት ቅባት፡
የእምነት፣በጎነት እና ለአላማ የተጠራች ሴት መሆን
ከታላቅ ኪሳራ በኋላ ተሐድሶ አለ፡፡ የተሰበረ ልብ ሊጠገን ይችላል፡፡ እና የጠፉ ሕልሞች ትልቁ የተስፋ ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ግን ከዚህም በላይ ብዙ የሩት ታሪክ አለ፡፡
ሩት የመጽናኛ ቀጠናዋን ለመልቀቅ እና አዳዲስ አጋጣሚዎችን ለመቀበል አትፈራም፡፡ እርሷ ስኬታማ ህይወት ለማግኘት ያለችበትን ባህላዊ ገደቦች በድፍረት ጥሳ አለፈች፡፡ ሁሉንም አደጋ ላይ ለመጣል እና ለመዘርጋት ፈቃደኛ ነበረች፡፡
የሩት አስገራሚ ሕይወት በዛሬው ጊዜ ላለችው ቤተክርስቲያን ትንቢታዊ ምሳሌ ነው፡፡ በሩት እና በቦዓዝ ታሪክ በኩል የተነገረው የሚያምር የመቤዠት ምስል በሕይወታቹ ውስጥ የአባታችንን የመቤዠት ሥራ ይተነብያል፡፡ ድንበሮችን ለመስበር እና አዳዲስ ግዛቶችን ለማሸነፍ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ጀግና፣ደፋር፣በእምነት የተሞላቹ እና እንደ ሩት ቆራጥ የማያወላውል፣ አቅኚ ወኔ ይኑራቹ፡፡ ከእርሷ ታሪክ ከሩት ቅባት ተማሩ፡፡
Copyright Hiyawkal © 2025
Leave a Reply