ትንቢታዊ ቃል፡ ተራሮቻቹን ለመውረስ ጊዜው አሁን ነው

ብራየን እና ካንዲስ ሲመንሰ :

ብዙ የተራራ ሕልም እያየሁ እንደነበር በሀምሌ ወር መጨረሻ ላይ ተገነዘብኩ፡፡ በተራሮች ላይ ባንዲራዎችን እተክል ነበር ፣ የተራራ ጫፎችን ፈልጌ ሳስስ እና በተራሮቹ ላይ ስቧርቅ ራሴን አየሁ፡፡ በወቅቱ ስብሰባዎች ላይ ስለነበርኩ በተራሮች ላይ እየተጓዝኩ መሆኔን በጭራሽ ቆም ብዪ አልተገነዘብኩትም፡፡ ስለዚህ በእርግጥም ቃሌ በዚህ ወር ከተራሮች ጋር ይያያዛል፡፡

በአንድ ህልም ጌታ “ወደ ተራራው ለመውጣት ጊዜው አሁን ነው” ሲል ሰማሁ፡፡ በሌላው ደግሞ “ተራሮቹን ለመውረስ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ወደ ላይ መውጣትና ማሸነፍ ጊዜው አሁን ነው!” ሲል ሰማሁ፡፡

ተራሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለያዩ ነገሮችን ሊያመለክቱ ይችላሉ ነገር ግን በአጠቃላይ ተራሮችን ከአምልኮ እና ከፀሎት ጋር እናቆራኛለን፡፡ በዮሐንስ 4 ውስጥ ሴቲቱን አስታወሳቹ? ሰዎች ለማምለክ ወዴት መሄድ አለባቸው ብሎ እንደሚያስብ ኢየሱስን ጠየቀችው፡፡ ኢየሱስም የምናመልክበት ቦታ ሳይሆን ፣ ነገር ግን የምናመልከው ነው ብሎ ነገራት፡፡ 

ወደ ተራራው ለመውጣት ጊዜው አሁን ነው!

ስለዚህ የምናመልከው ማን ነው እና የምንፀልየውስ ለማን ነው? ፊቱን በደንብ ለመመልከት ጊዜው አሁን ነው፡፡ በውኃ ጉድጓዱ አጠገብ እንደነበረችው ሴት እንዳደረገው ኢየሱስ ዘወትር ወደ ልባችን ይመጣል፡፡ እውነት ማን እንደሆነ ፊቱን በመጨረሻ ባየች ጊዜ ህይወቷ ለዘላለም ተለወጠ፡፡ ወደ ውብ ፊቱ በመመልከት ልባችን በእግዚአብሔር የተራራ መንግሥት ውስጥ የሚኖርበት ጊዜው አሁን ነው! 

ዛሬ ፣ ጌታ እንድንነሳና ከእርሱ ጋር እንድንሄድ ፣ እንድናገለግለው ፣ ልባችንን ለማረጋጋት እና ድምፁን እንዳዲስ እንድንሰማ እየጠራን ነው፡፡ በቀኝ እና በግራ በዙሪያችን ሁሉ ችግሮች አሉብን እና ሊያናግረን ይፈልጋል፡፡

በዚህ ወር አሜሪካ ውስጥ ሁለት አሰቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ነበሩን ፣ እና በመላው ምድር ዙሪያ አስከፊ ክስተቶች አሉ፡፡ ግን ልባችን በፍርሀት እንዲመራ እና እንዲሞላ መፍቀድ የለብንም፡፡ የእኛ ትኩረት እርዳታችን ከሚመጣበት ወደ ጌታ መዞር አለበት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያጽናናን አምላክ ነው እናም ሰይጣንን ከእግራችን በታች የሚደመስስ የሰላም አምላክ ነው! ትኩረታችንን ወደ እርሱ ለማድረግ መወሰን አለብን፡፡

“የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፡፡ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን” (2 ቆሮ 1፡3-4) 

እርሱ እኛን የዕርገት ሕዝብ አድርጎናል፡፡ ወደ መንፈስ ቅዱስም ዓለም በቀጥታ እንመጣለን እናም በቀን ውስጥ ለሚያስፍልገን ሁሉ ወደ አብ ፊት እንቀርባለን፡፡ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የምንነሳበት ጊዜ ነው፡፡

“ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ፡፡እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም” (መዝ ዳዊ 121፡1-3)

ዓለም ሁል ጊዜ አስደሳች ቦታ እንደሚሆን ቃል አልተገባልንም፡፡ በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲ ይላል በፍጻሜው ዘመን (ያ አሁን ነው) ፣ “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ” (ማቴ 24፡6)፡፡ ግን በክርስቶስ በእርሱ በሰላምና መፅናናት መመላለሳችንን መቀጠል እንችላለን፡፡ 

“በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” (ዮሐ 16፡33)

ማዘን እና ከሚያለቅሱ ጋር ማልቀስ ትክክል ነው ፣ ግን የበለጠ ማድረግ አለብን፡፡ ሀሳባችን እና ህይወታችን ወደ ከፍታ እንዲፈስ ለማድረግ መምረጥ አለብን፡፡ የእግዚአብሔር ወንዝ ጌታ ወደሚቀመጥበት ተራራ ከፍ ብሎ ይፈሳል፡፡ እርሱ ነው ራሳችንን ከፍ የሚያረገው (መዝ ዳዊ 3፡3)፡፡ በክብር ዙፋን ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን በሰማያዊ እይታ እና አጀንዳው ወደ ምድር ክብ ሲመልከት እኛም ከእሱ አጠገብ መቀመጫችንን እንድንወስድ ተጠርተናል፡፡

የእርሱን ጥበብ ለማግኘት እና ተግባራዊ ለማድረግ በ ዙፋን ክፍል ጸሎት ውስጥ ከእርሱ ጋር ለመቀላቀል ጊዜው አሁን ነው፡፡ መጽሓፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እጅግ ታላቅ ኃይል በቅዱሳዊ አማኝ በልባዊ ጸሎት ይለቀቃል፡፡ (ያዕ 5፡16) ይህ ለሀገራችን ፣ ለሌሎች ሀገራት ፣ ለህይወታችን እና ለሌሎችም ልቡን እና መፍትሄውን ይሰጠናል፡፡

በዳንኤል 12፡3 ያሉት የሚያበሩት የሚነሱበት ጊዜ አሁን ነው እኛም ከነሱ መሆን አለብን “ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ”

ስለዚህ ኑ እንውጣ! በተራራ ላይ ለመኖር ተፈጥራቹዋል፡፡ ከእርሱ ጋር በህብረት እና በአንድነት እንድቶኑ ተፈጥራቹዋል፡፡ የእግዚአብሔር ተራራ ስማቹን ይጠራል!

ተራሮችን ለመውረስ ጊዜው አሁን ነው!

ጌታ “ወደ ተራራው መውጣት ጊዜው አሁን ነው” ብሎ ሲናገር ብቻ አልሰማሁም ነገር ግን “ተራሮችን ለመውረስ ጊዜው አሁን ነው” ሲልም ተናግሯል፡፡ ሰዎች በተራሮች አናት ላይ የራሳቸውን የግል ባንዲራዎች ሲተክሉ አየሁ፡፡ እነዚህ ተራሮች የእግዚአብሔር ተራራ አይደሉም ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰጣቹ ህልሞች እና በህይወታቹ የእግዚአብሔርን መልካም እና ፍጹም ፈቃድ ከመከተል ወደኋላ የሚከለክሏቹ ፍርሃቶችን ሊወክሉ ይችላሉ፡፡ ምናልባት ተራራቹ አዲስ ንግድ ለመጀመር ፣ መጽሐፍ መፃፍ ፣ አዲስ ሥራ ማግኘት ፣ አገልግሎትን መጀመር ፣ ወይም ደግሞ የዕዳ ተራሮችን ማሸነፍ ፣ የድብርት ወይም የድሮ ልምዶችን ማሸነፍ ሊሆን ይችላል፡፡ 

ጌታ ኢያሱን “ብርቱ እና ደፋር ሁን” አለው፡፡ እንደ ካሌብ እኛም በውስጣችን ሊያልፍን የሚችል ያንን የድሮ “የአንበጣ አስተሳሰብ” መጣል አለብን፡፡ እኛ በክርስቶስ ቃል ወደተገባልን ምድር  ገብተናል እናም ሁሉንም  “ውሸቶች” የምናስወግድበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ “እስከዚድረስ በቃ ከዚ አታልፍም” የሚለንን የጠላት ውሸት የምንዘጋበት ጊዜ ነው፡፡ ያንን ተራራ ለመውጣት ጊዜው አሁን ነው ምክንያቱም እኛ በክርስቶስ ነፃ ወጥተናል፡፡ አዲስ ቀን ነው እናም እኛ ወደ ላይ እየወጣን ነው!

“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ፡፡ የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ “ (መዝ ዳዊ 46፡10-11)

“ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ፡፡ “ (ኦሪት ዘኍ 13፡30)

ስለዚህ ዛሬ የሚያጋጥማቹ ነገር ሁሉ አብ “በእርግጠኝነት ማድረግ ትችላላቹ” እያላቹ ነው፡፡ ኢያሱ ተራራውን በለቀቀለት ጊዜ ካሌብ 85 ዓመቱ ነበር፡፡ ካሌብም ጠላትን ከምድሩ አባረረ ፤ ምድሪቱም ዐረፈች፡፡ ዛሬ እናንተ መነሳታቹን አውጃለው! ድል ለመቀዳጀት እና ከዚያ እስከሚቀጥለው ድላቹ ድረስ ለማረፍ በእናንተ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ፍርሃት እየተባረረ ነው፡፡

ባንዲራቹን በእዚያ ተራራ ላይ ስተክሉ አየሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር በድፍረት እና በልበ ሙሉነት ስለሚሞላቹ ነው፡፡ እሱ ከፍርሃት ሁሉ ነፃ እያወጣቹ ነው እናም ከአንበጣ አስተሳሰብ እየተላቀቃቹ ነው፡፡ ሁሌም ማን እንደሆናቹ ወይም እንዳልሆናቹ አታስቡም ነገር ግን እሱ በውስጣችሁ ያለው ማን እንደሆነ ታስባላችሁ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለመነሳት የእናንተ ቀን ይህ ነው! የዘመናችን ተራራን የሚይዝ ካሌብ የሚነሳበት ቀን ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጣቹን ተስፋዎች ለመኖር ጊዜው አሁን ነው እነዚያ ተስፋዎች በጭራሽ አይጠፉም እነሱ ተስፋዎች እነሱን ለመከተል በቂ እምነት እንዲኖራችሁ እየጠበቁ ነው፡፡ ወደዚያ ተራራ ለመውጣት ተዘጋጁ ተራሮችን ለማንቀሳቀስ (ማር 11፡23) እና በተራሮች ላይ ለመዝለል ተዘጋጁ (ዘሰሎሞን 2፡8)! ኃይል በሚሰጣቹ በክርስቶስ ሁሉን ማድረግ ትችላላቹ፡፡

በፍርሃት ከመሸበር ይልቅ ትኩረታችን በአምላካችን ላይ የምናረግበት ጊዜ ነው፡፡ ወደ ፊት መመልከት እና ለእኛ ባዘጋጀው ድል መደሰት አለብን!

“ለርስቱ እኛን መረጠን” (መዝ ዳዊ 47፡4)

ዛሬ በሕይወታቹ የሚያምኑበት ዘገባ የማን ነው? የ ጌታን ቢሆን ይሻላል፡፡ ተራሮቻቹን ለመውረስ ጊዜው አሁን ነው! እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው!

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox