ትንቢታዊ ሕልም: በክርስቶስ አካል ውስጥ ያሉ ሰዎች የድንገተኛ አደጋ እንክብካቤ

ጆ ጆ ዳውሰን :

በቅርብ ትንቢታዊ ሕልም አየው እሱም እኔና ባለቤቴ ወደ ድንገተኛ አደጋ የጥበቃ ክፍል ውስጥ ስንገባ ነበር ፡፡ ይህ የድንገተኛ አደጋ ክፍል እንክብካቤ በሚጠብቁ ሰዎች ተሞልቷል ፡፡ 

እኔና ባለቤቴ በክፍሉ ጥግ ላይ ተቀምጠን እየተመለከትን ነበር ፡፡ ከዛ ድንገት አንድ ሰው ወደ ተጠባባቂ ክፍል ገብቶ አንድ ሰው አወጣ ፡፡ ከዚያም አንዲት ሴት ገብታ ሌላ ሰው አወጣች ፡፡ ከዚያ አንድ ቤተሰብ ገብቶ ሌላ ሰው አወጣ ፡፡ 

ከእንቅልፌ ስነሳ ጌታ የሕልሙን ትርጓሜ ይሰጠኝ ጀመረ ፡፡ ስንት ሰዎች በመንፈሳዊ የድንገተኛ አደጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሆኑ ይሰማቸዋል? በክርስቶስ አካል ውስጥ ያሉ ስንት ሰዎች የድንገተኛ አደጋ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል? እግዚአብሔር በሕልም ያሳየኝ ነገር ታዛዥ ስንሆን እና እንድናደርግ የጠራንን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ስንወጣ ሰዎችን ከድንገተኛ ሁኔታ እያወጣን እንደሆነ አምናለሁ ፡፡

 የ ማስታወሻ ጽሁፍ በሰራቹ ቁጥር የአምላክን ፍቅር በምታሳዩበት ጊዜ ፣ መጽሐፍን ወይም የመወያያ ሀሳቦችን በምትጽፉበት ጊዜ ፣ ስብከት በምትሰብኩበት ወይም ለአንድ ሰው በምትፀልዩበት ጊዜ ከድንገተኛ ሁኔታ እየወጡ ነው ፡፡ በክርስቶስ አካል ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ሰዎች ለተጠሩበት ዓላማ እና ዕጣ ፈንታ ሙሉ በሙሉ የሚሄዱ ከሆነ ፣ ከዚያ ጥቂት ሰዎች ብቻ እራሳቸውን የመንፈሳዊ ድንገተኛ አደጋ ሁኔታ ውስጥ ያገኛሉ ፡፡ 

ወዳጆቼ ሆይ ፣ አዳምጡ ፣ ዓለም እግዚአብሔር እንድታደርጉት የሰጣችሁን እንድታደርጉ ያስፈልጋታል ፡፡ ምክንያቱም እናንተ ብቻ ልደርሱባቸው የሚችሉ ሰዎች አሉና ፡፡ አንድ በውጭ የሚኖር ሰው የሚፈልገውን መገለጥ እና ማስተዋል አላቹ እና ወጥታቹ ድምጳቹ የሚሰማበት ጊዜ ነው!

ሌሎች መስማት ፣ ማየት ፣ ማንበብ ወይም ማዳመጥ የሚያስፈልጋቸውን እግዚአብሔር በውስጣችሁ ያደረገው ምንድን ነው? በውስጣችሁ ያለውን ውስጣችሁ የሆነውን ከዓለምና ከክርስቶስ አካል ምን እየዘረፋችሁ ነው? እግዚአብሔር በውስጣችሁ ያስቀመጠውን ሁሉ ማግኘት ያስፈልጋል ፤ እሱንም ማውጣት ያስፈልጋል ፡፡ ወደ ዕጣ ፈንታቹ ገብታቹ ሰዎችን ከመንፈሳዊ የድንገተኛ አደጋ እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡

አገልጋይም ፣ መጋቢም ፣ ቄስም ፣ የትምህርት ቤት መምህርም ፣ ዶክተርም ፣ የቤት እመቤት ወይም አያትም ብቶኑም ጥሪያቹ የሌላውን ሰው ዕጣ ፈንታ ለመክፈት ቁልፍ ነው ፡፡ አንድን ሰው ከድንገተኛ አደጋው ውስጥ ባወጣቹ ቁጥር አንዱን ሰው በመንካታቹ ምክኒያት ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሌሎች ህይወቶችን እየለወጣቹ ነው ፡፡

በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ አስፈላጊ ናቹ ፣ እናም ይህ በስንፍና ዝም ብሎ የመቀመጥ ጊዜ አይደለም ፡፡ የድንገተኛ አደጋ ሁኔታ ውስጥ ያሉት ሁሉ እንዲድኑ እግዚአብሔር በውስጣችሁ ያስቀመጠውን ነገሮች ወደ ዓለም ለማምጣት በትጋት የመሞላት ወቅት ነው!

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox