3 ኢየሱስ እንደ ሊቀ-ካህንነቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት

ጀንቲዘን ፍራንክሊን :

የኣካል ብቃት የ27 ቢልየን ዶላር ኢንደስትሪ ነው። በየ ዓመቱ መስከረም ሲጠባ በሰውነት ማጎልመሻ ቤቶች አባል የሚሆኑ ሰዎች ብዛት በእጅጉ ይጨምራል። ነገር ግን አባል ሆነው አካላቸውን ለማብቃት ከተቀላቀሉት መካከል 80% ያክል የሚሆኑት ጥቅምት በገባ በሁለተኛ ሳምንቱ ቁርጥ አድርገው ያቆማሉ። ብዙዎቻችን ብቁ ሆኖ የመታየትን ሃሳብ እንወደዋለን፣ ነገር ግን በተጨባጭ ብቁ ለመሆን የሚጠይቀው ቆራጥነት ይጎድለናል።

በ ዘሌ 16፡21፣ እግዚአብሔር ብቁ የሆነን ሰው ሲፈልግ እናያለን፡ “አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዝዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል።”በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ እግዚአብሔር ሃጥያትን ከሕዝቡ የሚያስወግድበት ስርዓት ነበረው። በየ ዓመቱ የስርየት ቀን ሲደርስ፣ ሊቀ-ካህኑ ሶስት ነገሮችን መምረጥ ይኖርበታል፡

  1. የጌታ ፍየል። ይሄ ፍየል ለሃጥያት እንደ መስዋዕት ሆኖ ይቀርባል። የሃጥያት ይቅርታ ደም ሳይፈስ ከቶ አይገኝም። በዚያን ዓመት ለተፈፀመ ሃጥያት በሙሉ፣ የጌታ ፍየል እንደ ሃጥያት ሆኖ ሞቶ መስዋዕት መቅረብ ነበረበት።
  2. የሚሰደድ ፍየል። የስርየት ቅን በተቃረበ ጊዜ ባሉት ቀናት፣ ሁሉም ቤተሰብ ወደ ሊቀ-ካህኑ በመሄድ ባለፈው ዓመት የተፈጸሙትን ሃጥያት ጮሆ ይናዘዛል። የሁሉም ኑዛዜ ከተሰማ ብኋላ፣ ካህኑ ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዝዛል።
  3. ብቁ ሰው። ብቁ የሆነውም ሰው የህዝቡ ሃጥያት ያደረበትን ፍየል ይዞ፣ ፍየሉ ከመንገዱ ርቀት የተነሳ መመለስ እስኪያቅተው ድረስ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል። ምናልባት ፍየሉ ተመልሶ መምጣት ከቻለ በህዝቡ ላይ ርግማንን ያደርጋል። ይሄን ጉዞ ለማድረግ ታድያ የተለየ አይነት ሰው ይጠይቃል።

ስለዚህ፣ የሃጥያት ይቅርታን ለማግኘት የአንድ ፍየል ደም ፈስሶ መሞት፣ ህዝቡን ከሃጥያት ለመለየት ደግሞ አንድ ፍየል መኖር አለበት። ካህኑ በየዓመቱ በዚህ ተመሳሳይ ስርዓት ውስጥ በተደጋጋሚ ያልፋል። ኑዛዜው፣ መስዋዕቱ፣ ተሰዳጁ ፍየልና ብቁ የሆነው ሰው ከዓመት ዓመት ይፈለጋል። 

የሆነው ሆኖ ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ ሁሉኑን ቀየረ።

የኢየሱስ ሞትና ትንሳዔ ሃይል አለው። እርሱ የጌታ ፍየል ነው፤ እኛ የሃጥያት ይቅርታን እናገኝ ዘንድ የእርሱ ደም ፈስሶ ሞትን ቀመሰ። እርሱ ተሰዳጁም ፍየል ነው፤ ምክኒያቱም ከሶስት ቀን ብኋላ ሞትን ድል ነስቶ ተነስቷልና። እርሱ የሞተዉን እና በሕይወት የሚኖረውን ፍየል ቦታ ይይዛል።  እርሱ ብቁውም ሰው ነው፣ ሃጥያታችንን ከቶ እንዳይመለስ አርቆ አስወግዷል። ከኢየሱስ የተነሳ ለሃጥያታችን ይቅርታን ከማግኘት አልፎ ከእስራቱ ሰንሰለትም ነፃ ወጥተናል።

በኢየሱስ ሞትና ትንሣዔ በኩል፣ ሐፍረትን፣ ራስ ወቀሳን፣ ጭንቀትን እና ፍርሃትን ማስወገድ ይቻላል። ከመጠጥና የተለያዩ ሱሶች እንዲሁም ከስነ፟-ምግባር ጉድለት ነፃ ያወጣል። ሃጥያታችን ይቅር ከመባል አልፎ ነፀነትን ተቀናጅተናል። ሃሌሉያ! ይቅርታን ለማግኘት በመጸለይ መጠየቅ እና ዳግመኛ ተመልሶ ተመሳሳይ ሃጥያት ዉስጥ እንድንማቅቅ የእግዚአብሔር ፍቃድና እቅድ አይደለም። ድኅንነት ከቀድሞ የአኗኗር ሁኔታ መለየትን ይጠይቃል።

ልባችንን ለጌታ አሳልፎ እንደ መስጠትና ለሃጥያታችን ይቅርታን እንደ ማግኘት የሚያስደስት ነገር የለም። ታዕምር ነው። ነገር ግን ተመልሰን ስናደርግ በነበርነው ተግባር ከቀጠልንና ኑሮአችንን ካላስተካከልን ድህንነትን በሙላት መለማመድ ይከብደናል። ድኅነትን ሲገኝ፣ መለያየትም ግድ ይላል። ህይወታቹን ሊለቁ የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ይኖራሉ። የዳናቹት ወደ ተነሳቹበት አስከፊ ቦታ እንድትመለሱ አይደለም። መቆራረጥ አስፈላጊ ነው።

አስተውሉ፣ ኢየሱስ ለዘላለም ብቁው ሰው ነው። ከዚህ ወዲያ ፍየሎች አያስፈልጉም። ኢየሱስ አንዴ፣ ለሁሉምና ለዘላለም ዋጋን የከፈለ በግ ነው። ሃጥያታችንን ሊሸከምና መስዋዕት ለመሆን ብቁ የሆነው እርሱ ብቻ ነው። እርሱ ያለ በደልና ያለ ነቀፋ ነው። እርሱ ብቻ ነው ሕይወቱን አሳልፎ ለእኛ ሕይወትን የሰጠን። ህይወቱን መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ትክክለኛና ብቁ የሆነ ከእርሱ ሌላ የለም።

ኢየሱስ ብቁ ስለሆነ፣ ሃጥያታችን ሊደመሰስና ይቅርታን ልናገኝ ችለናል። በርሱ አዲስ ፍጥረት ሆንን። የዱሮው ሰው ጠፍቷል፣ ብቁው ሰው በእኛ ውስጥ ይኖራል። እርሱ ትክክል ለሆነው “እሺ” ላልሆነው ደግሞ “እንቢ” እንድንል ብቁ ያደርገናል። በራሳችን ነጻ ፍቃድ ብቻ ላይ ተመስርተን ብቁ ልኖን ጨርሶ አይቻለንም። በራሳችን “መልካም ሰው” ሊያስብለን የሚያስችል ጥንካሬም የለንም። ዳግመኛ መወለድ ያስፈልገናል። ብቁው ሰው በልባችን ሊኖርም ይገባናል።

በትክክል የመለወጫ ሂደት፣ ከውስጥ ጀምሮ ወደ ውጭ የሚሄድ ነው። መጀመሪያ ብቁውን ሰው በልባቹ አኑሩት፤ እርሱ መሆን ያለባቹ ያደርጋችኋል። እርሱ በትልቅ ደረጃ ያሳድጋችኋል። ህይወታችሁን ይለውጣል። አመለካከታችሁን ይቀይራል። ቤተሰባችሁንና ሁኒታዎችን ያስተካክላል። እርሱ ለዓላማው ብቁ እና ለበጎ ስራ ሁሉ ዝግጁ ያደርጋችኋል።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox