ተሐድሶ ሲሳሳት

ኤዲ ሃያት :

መንፈስ-መር ተሐድሶ(መነቃቃት) ወደ ሥጋዊ ስሜት ሲለወጥ እንዴት እናውቃለን? ለእኔ፣ አንድ ለመስበክ ዕቅድ በተያዘልኝ ሞቅ ባለ “የተሐድሶ” ቤተ-ክርስቲያን ዉስጥ ተከሰተ፤ በምስጋና እና በአምልኮ አገልግሎት ጊዜ፣ ሰዎች በፈንጠዝያ ስሜት እየጮኹ፣ ባንዲራዎችን እያውለበለቡ እና በመተላለፊያዎች ላይ እየሮጡ ነበር፤ እኔ ግን በጸጥታ እያመልክሁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር፤ “የማታለል ምሽጉ ኩራት ነው” ሲል ሰማሁ።

ወድያውኑ ለጉባዔው ማስተላለፍ የነበረብኝን ሀሳብ ተረዳው። እርሱም፣ በመንፈሳዊ የተሐድሶ ወቅት ኩራት እንዴት ሾልኮ እደሚገባ፤ ምክንያቱ ደግሞ ከእግዚአብሔር ሀይል እና በረከት የተነሣ እንደሆነ ነው። ግለሰቦች እና አብያተ-ክርስቲያናት በህይወታቸው በተገለጠው በእግዚአብሔር ባርኮት ምክንያት የራሳቸውን የተለጠጠ የበላይነት ሃሳብና ምስል ይጨብጣሉ። ይህ ኩራት የኋላ የኋላ ለአጋንንትን ማታለል እና መሸሸጊያ፤ መግቢያ በር እንዲሁም ምሽግ ይሆናል።

በዚያን ዕለት ማለዳ መልዕክቴን ከጨረስኩ በኋላ፣ በጉባኤው ከፍተኛ የሆነ ጸጥታ ሰፈነ። ከባርኮቱ ስነ ስርዐት በኋላም ሁሉም ሰው ለመናገር እጅግ በጣም የፈሩ በሚመስል ሁኔታ በፀጥታና በሹክሹክታ ነበር ከጉባዔው የተከናወኑት። ቅድሞ ከነበረው የፌሽታ ስሜት ጋር ሲስተያይ ከፍተኛ ለውጥ ከመኖሩ አንፃር የተወሰነ ሃሳብ ገብቶኝ ነበር።

አገልግሎቱ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ በጉባኤው የነበረውን ሞቅታ አላቀዘቀዝኩትም ብዬ ተስፋ አድርጌ እንደነበር ከቤተ-ክርስቲያኗ መጋቢ ጋራ ሃሳብ ተከፋፍለን።

“ኧረ በጭራሽ፣ እንዲያውም ኢላማህን መትተሃል” ሲል መለሰ። “እንዲያውም ዛሬ አንተን እንደ ቅጥረኛ ተኳሽ በማምጣቴ እከሰስ ይሆናል” አለ።

ከዚያም በዚያን ጠዋት ተናግሬ የነበረው ሃሳብ እንዴት በጉባኤ ውስጥ እየተከሰተ እንደቆየ አካፈለኝ። በማነቃቃት ውስጥ፣ ከዳኑ ከአንድ አመት በታች በሆናቸው ግለሰቦች እንዴት የእርሱን አመራር እንደፈተኑትም ተናገረ። ምክኒያቱ ደግሞ በተቀበሉት የእግዚአብሔርን መገኘትና ኃይል በራሳቸው በተለጠጠ የራስ ክብር ሲለማመዱት፤ ምንጩ ግን ከእግዚአብሔር ቸርነትና ጸጋ የተነሳ መሆኑን ስላልተገነዘቡ ነበር።

የኩራት ችግር

ጎርደን ሊንሰይ በ 1940 ዎቹ እና 50 ዎች ውስጥ ካሉት ዋነኞች የተሐድሶና የመዳን መነቃቃት መሪዎች መካከል አንዱ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ “አንድ ሰው ከመንፈሳዊ ሀይል እና ከመባረክ እየላቀ እና በከፍተኛ መጠን እየተጨመረለት እንደመጣ፣ እሱ ደግሞ ዝቅ ብሎ ወደ ታች፣ ታች እና ዝቅተኛ ለመሆን መሻት አለበት።”

ይህ አባባል የተወለደው ከህዝቡ ፈውስ እና ነጻ መውጣት አገልግሎት ውስጥ በከፍተኛ ኃይል ከእግዚአብሔር ሲጠቀሙ የነበሩ የተወሰኑ ወንድሞችን ህይወት እና አገልግሎቶችን በሚያሳዝን ሁኔታ መፈራረስና መበላሸትን በመመልከት ነው። በእያንዳንዳቸው ሁኔታ፣ የሰይጣን ወደ ግለሰብ ሕይወት መግቢያ በር፣ ከልክ በላይ የተወጠረ የራስ የበላይነትና ኩራት ይመስላል።

በአምላክ ፊት ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ ከማድረግ ይልቅ በራሳቸው ስኬት በደስታ ተሞልተዋል። ታላቅ የሆነውን የእግዚአብሔር ክብርና ኃይል ከማሳየት ይልቅ፤ በኩራትና ትዕቢታቸው ምክንያት ወደ ታች ተጥተዋል። አንደኛ ጴጥሮስ 5፡5 እንዲህ ይላል፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”

ለበርካታ ዓመታት፣ ከ 1947 ጀምሮ ሊንሰይ፤ በ1940 ዎች ዓመታት እና በ1950 ዎቹ ውስጥ በስፋት የታወቀ የፈውስ ወንጌል ሰባኪ የዊልያም ብራንሃምን አገልግሎት በሃላፊነት ሲመራ ነበር። ብራንሃም በጸልት ጊዜ ውስጥ አንድ መልአክ ተገልጦለት ለዓለም ህዝብ ሁሉ የሚሆን የፈውስ ስጦታ እንዲቀበል በታዘዘ ጊዜ በታላቅ ተአምራዊ እና አስደናቂ በሆነ አገልግሎት ውስጥ ተውጦ ነበር።

ፈውስ እና ተአምራቶች በመኖራቸው ምክንያት በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የእርሱን አገልግሎት ይካፈላሉ። እነዚህን ትላልቅ ዘመቻዎች የተደራጁት በሊንሰይ ሲሆን ስብሰባዎችንም በቀዳሚነት ይመራል እንዲሁም በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ያስተምር ነበር።

ብራንሀም በምሽት አገልግሎት ውስጥ ለመስበክ እድሉ ሲደርሰው፣ ሊንሰይ በአነስተኛ ደረጃና በትህትና ያስተዋቀው ነበር። ደግሞም እግዚአብሔር ወንጌላዊውን በሚያስደንቅ መንገድ እየተጠቀመበት መሆኑን በማረጋገጥም ጭምር ነበር።

በአንድ ወቅት ሊንሰይ ወጣ ባለ ጊዜ “ወንድም ባክስተር” በስብሰባዉን በመክፈት ብራንሃምን አስተዋወቀ። በብዙ አድናቆትና ፈገግታ ብራንሃምንም ልዩ “የመጨረሻ ዘመን የእግዚአብሔር ነቢይ” በማለት ጠቅሶም ነበር። ሊንሰይ ተመልሶ ሲመጣ፣ ብራንሃም እንዲህ አለ፣ “ወንድም ሊንሰይ፣ ከአሁን በኋላ ወንድም ባክስተር በመድረክ እንዲያስተዋውቀኝ እፈልጋለሁ” አለ። (እነዚህ እውነታዎች ባለፉት ፍሬዳ ሊንሰይ፣ በጎርደን ሊንሰይ ሚስት፤ ሁሉን ዝርዝር ጠንቅቀው በሚያዉቁት በኩል ተላልፎ ወደ እኔ ደረሰ።)

ብራንሃም ራሱን ኩራት በሚመግቡትና የመጨረሻው ዘመን ነቢይ በሚል እንደ ሃውልት ክበው ይህን በሚነግሩት አይነት ሰዎች መክበብ ጀመረ። ሊንሰይ ሊያስጠነቅቀው ቢፈልግም፣ ዳሩ ግን ምክሩ እንዲያው ሳይሰማው ቀረ። ሊንሰይ፣ ብራንሃም ከባድ የሆነ ስህተትን በፀጋ የተቀበለ መሆኑን ሲመለከት፣ ከ”ብራንሃም አገልግሎት” እራሱን በማግለል፣ ዛሬ “ክራይስት ፎር ዘ ኔሽን” ተብሎ የሚጠራውን የፈውስ ድምጽ አቋቋመ።

በመጨረሻም ብራንሃም በሚልክያስ ምዕራፍ 4፡5 ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ተስፋ ፍፃሜ እንደሆነ አምኖ ነበር፣ “እነሆ፡ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ” አለ። በተጨማሪም ራዕይ ምዕራፍ 3፡14 ከተመዘገበው ከሰባተኛው ቤተክርስቲያን መልአክ ጋርም እራሱን አመሳስሎ አቀረበ።

ብራንሃም እንግዳ የሆኑ ልዩ ትምህርቶችን በመቀበል እና በማስተማር ህይወቱን ቀጠለ። የእሱ የእባቡ ዘር አስተምሮ፤ የሔዋን ኃጢያት ከእባቡ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነትን በክስተቱ ከተባረሩ በዚህም ለጋህነም እሳት የታጩ ሰዎችን ያከተተ ነው ይላል። የእርሱን ትምህርቶች የሚቀበሉ ደግሞ በእነዚያ የእግዚአብሔር ዘርና የክርስቶስ ሙሽራ ለመሆን የታጩ ይሆናሉ ይላል።

ሐሰተኛ ትምህርቶቹ ከርሱ ዘንዳ ቢፈራረቁም እንኳ ግንኙነቶቹ ውስጥ ተአምራት መፈጸማቸው አላቆመም ነበር። እግዚአብሔር መሐሪ ነው!

በ 1963 ኬኔት ኢ. ሄገን ወደ ሊንሰይ ቢሮ በመሄድ የጻፈውን ትንቢት በእጁ አስረከበው። ትንቢቱም እንደ ሚያመለክተው ነፃ የመውጣት መነቃቃት/ተሐድሶ መሪ መንገዱን ስቷል፣ ብሎም በቅርቡ ከእይታም ይወገዳል።

ሊንሰይ ባለቤቱ ፍሬዳ ባለችበት ድምፁን ጮክ ብሎ አነበበው። ከዚያም ከጠረጴዛው ስር ባለው ሳጥን ዉስጥ አስገብቶት ቆለፈበት። ፍሬዳም “ስለ ማን ነው የሚያውራው?” ብላ ጠየቀች። ሊንሰይ በከፍተኛ ጭንቀትና ሃሳብ እንዲህ በማለት መለሰላት: – “እርሱ ስለ ብራንሃም እያወራ ነው፤ እርሱ ከትክክለኛው መንገድ ወጥቶአል ኤልያስ ነኝም ብሎ ያስባል።”

ከሁለት ዓመታት በኋላም ሊንሰይ ከክልል ውጪ የሆነ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰው። በስልክም ከመኪና አደጋ በኋላ ከባድና ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ ለነበረው ሰው ለብራንሃም እንዲመጣና እንዲጸልይ ጠየቁት። ሊንሰይ ቀድሞ በነበረው ልምድና ታሪክ ምክንያት ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር እጅ ትቶ፣ ወደ ብራንሃም አልሄደም ነበር። ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ብራንሃም ሞተ።

ምንም እንኳ ታሪኩ አሳዛኝ ቢሁንም፣ ብራንሃምን ያጋጠመው ክስተት በቤተክርስቲያን ታሪክ ዉስጥ ልዩና ያልተለመደ አይደለም። በተደጋጋሚ፣ እግዚአብሔር ለህዝቦቹ ጸሎት ምላሽ ሲሰጥ፣ ኩራት በጎን ሾልኮ ወደ ውስጥ ገብተዋል፣ በዚህም ምክንያት መነቃቃቱና ተሐድሶው ተዳክሞና ተበታትቶ ይታያል፣ ይህ ደግሞ ዛሬም እየሆነ ያለ ነገር ነው።

የትህትና መፍትሔ

በምስራቅ የባህር ዳርቻ ላይ በትልቅ ከተማ ውስጥ እያገለገልኩ ሳለ በዋነኝነት ጴንጤቆስጤዎችን እና የመንፈስ ቅዱስን ድርሻ የሚያጎሉትን አማኞችን የሚመለከት ሆኖ ሊታይ የሚችል መጽሔት አገኘውና ተመለከትኩት፤ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትና አገልጋዮች በተለጠፉት ማስታወቂያ ውስጥ ከወደር ያለፈ ኩራትና እራስን ማግዘፍ የሚታይበት ከመሆኑ የተነሳ በእጅጉ ተገረምኩ።

የመንፈስ ቅዱስን ድርሻ የሚያልቁ ነብያት፣ ሐዋሪያትና ኤጲስ ቆጶሶች ብቻ አልነበሩም፤ ነገር ግን “ጠቅላይ ሐዋርያ”፣ “ቀዳሚ ሐዋርያት”፣ “ሕግ ተርጓሚ ሐዋርያት”፣ “የጳጳሳት አለቃ”፣ “የሃይማኖት መሪ” እና እንዲያውም አንድ ግለሰብ እራሷን ከፍ ከፍ በሚያደርግ “ታላቋ ሊቅ ሐዋርያ” በሚል ስም እራሷን እስከመሾም ድረስ ተደርሷል።

ሳስበው፤ እነዚህ ግለሰቦች፣ እራሱን ዝቅ ዝቅ ላደረገው፣ የእርሱን ተከታዮች፣ በዚያች ግዛት ባህል በባሮችና በቤት ሰራተኞች ብቻ የሚደረገውን፤ እግር ዝቅ ብሎ ያጠበው ለእርሱ ተከላዮች መሆን ይቻላቸው ይሆን? በማቴዎስ 23፡8-12 ላይ፣ በራስ ላይ ከሌሎች አማኞች እራሳቸዉን ለይቶ የሚያወጣ እራስን በማወደስ ስሜት መጠሪያ ቅጥያ ወይም ርዕሥ እንዳያወጡና እንዳይወርሱ ላስጠነቀቃቸው ለርሱ ተከላዮች መሆን ይችላሉን?

“እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል። ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” (ማት 23፡8-12)።

ታድያ አለም ኢየሱስን የማያይበት ምክንያት ለምን ይገርመናል። ኢየሱስን ለኛ ሊያዩት እንኳ ተስኗቸዋል። ሃገራዊ መንፈሳዊ መነቃቃት የማንመለከትበት ምክንያትም ግልፅ ነው። በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 7፡14 መሰረት እንደዚህ ላለው አይነት መነቃቃት የመጀመሪያው መስፈርት፣ የእግዚአብሔር ህዝቦች “እራሳቸውን ትሁት ማዲረግ ነው”።

ከተወሰኑ አመታት በፊት በ“ተሐድሶ አሁን” ኮንፍረንስ ውስጥ ተቀምጬ ሳለው፣ በጌታ ፊት እንድሰግድ፣ የሚገፋፋ ስሜት ተሰማኝ። ነገር ግን ማንም የተንበረከከ ሰው ስላላየው፤ እንዲያውም ሰዎች ቁመውና ለመንፈስ ቅዱስ አዲስ ግንኙነት ፀሎትን ለመካፈል ወደ ፊት እየወጡ እንደሆነ ስለተመለከትኩ፣ ቁጭ ብዬ ማድረግ ያለብኝን ነገር አሰላስል ነበር።

ሆኖም፣ ይሄ እራሴን ከጌታ ፊት ዝቅ እንዳደርግ በሚገፋፋኝ ስሜት ውስጥ እንዳለው፣ በመጨረሻ ተሸንፌ ባለሁበት ዝቅ ብዬ ተንበረከኩ። ልክ ጉልበቶቼ መሬትን እንደነኩ፣ መንፈስ ቅዱስ በልቤ በጥራትና በደመቀ ሁኔታ ሲናገር ተሰማኝ።

“ከዚህ ብኋላ በሚመጡት ግዜአት በሙሉ ታላቅን ነገር አደርጋለው። እናም የኔን ሃይል እና ክብር በምትመለከትበት ጊዜ፣ ይሄ ሁሌም የአንተ ቁመና ይሁን። አንተ ዝቅ ብለህ የአለማትና ፍጥረታት ሁሉ ገዢ የሆነውን ሉዐላዊ ጌታ ታመሰግን እና ትሰግድለት ዘንድ ይገባሀል” አለኝ።

እውነት ነው፣ ኩራት የማታለል ምሽግ ነው። ለዚህ ነው ታድያ በተደጋጋሚ ስለ እኛ ሳይሆን ስለ እስርሱ እንደሆነ መገንዘብና እውቅና መስጠት ያለብን። ደግሞ በዚህ ውስጥ የጴጥሮስን ማበረታቻ ቃል አስታውስ፡ “እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” (1 ጴጥ 5፡5)።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox