ክርስቲያኖች ምልካም ላልሆነ ባህሪያቸው እ/ርን ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙባቸው 5 ተጭማሪ መንገዶች (ክፍል 2)

ዶክተር ጆሴፍ ማቴራ :

ኢየሱስ በአስገራሚ ሁኔታ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልምምዶችን የእግዚአብሔርን ቃል በመጥቀስ የሚያደርጉ ሰዎች ያጋጥሙት ነበር። ይህንንም በጊዜው የነበሩት የአይሁድ መሪዎች በማርቆስ ወንጌል 7 ፥ 9 – 13 እናትን እና አባትን መርዳትን በቁርባን መስዋእት ሲቀይሩ ተገልጦ እናየለን።

መጽሃፍ ቅዱሳችንን ስናጠና ሰይጣንም እራሱ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያውቅ እና ለራሱ እንደሚመቸው ሲጠቅስም እናያልን። (ሉቃስ 4፥9 – 12)።በክርስቶስ አካል ውስጥ እንዳለ አንድ ታዛቢ እኔም እራሴ ይህንን ባህሪ በተደጋጋሚ ተመልክቻለሁ፥ ሰዎች እውነተኛ ሃሳባቸውን ለመደበቅ፣ ከተጠያቂነት ለመሸሽ፣ ሌሌችን ለመጠቀም፣ ወይም ለሌሎች የሚያሳዩትን ያልተገባ ባህሪ ጥፋት እንዳልሆነ ለማሳየት እግዚአብሔርን ሲጠቀሙ ወይም ከእርሱ ጀርባ ሲደበቁ አስተውያለሁ።

6. ሰዎች ተግባራዊ ሕይወታቸውን ወደጎን ብለው የማይጨበጥ ልምምድ ውስጥ ሲገቡ፥

“ecclesia of God” ብሎ እማነትን በማወጅ ጻድቅ መንግስት በምድር ላይ በእርግጥ መመስረት ይቻላል ብለው የሚያስቡ አንዳንድ መሪዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ።ጸሎት እና ምልጃ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ውጊያን የምናሸንፍበት ትልቅ ስፍራ እንደሆነም አምናለሁ(በኤፌሶን 6፥12 ላይ ውጊያችን ከድም እና ከስግ ጋር አይደለም እንደሚል) ነገር ግን መሪዎችን ሳይመርጡ እና በህብረተሰብ የመሪነት በሮች እንዴት መቆም እንደሚችሉ ሳያሰለጥኑ በር ዘግቶ መጸለይ ብቻውን ተራ መንፈሳዊነት ነው።  ይህ አማኞች ስለፍትህ፣ ጽድቅ እና ነጻነት እንዲሰሩ የሚናገሩትን የመጽሃፍ ቅዱስ መልዕክቶች ሁሉ ችላ ያለ ነው።(የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል መጽሃፈ ምሳሌን፣ አሞጽን እና እንደ ኢሳይያስ 58 ያሉትን ክፍሎች ይመልከቱ)

7. ሰዎች አገልግሎታቸው “ከእውነተኛው ማንነታቸው” ሳይሆን ሲቀር፥

ልናምን ከምንፈልገው በላይ, ሁላችንም እግዚአብሔር አምላክን የምናገለግለው ካልተለወጠው፣ ለእግዚአብሔር እጅ ካልሰጠው፣ ካልተሰበረው እና ከሚያታልለን የሕይወታችን አካል ነው። ሁላችንም በአገልግሎታችን የምናደርገው ለእግዚአብሔር ክብር እንደሆነ እንድናስብ አድርጎ ያታልለናል፤ እውነታው  ለራሳችን ስም፣ እውቅና እንዲሁም ውስጣችን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ሆኖ ሳለ።እሱን ወደመምሰል መለወጥ የምንችለው ግን የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ነፍሳችንን እና መንፈሳችንን እንዲለያይ ስንፈቅድለት እና ጨለማውን ማንነታችንን አልፎ ሲገባ ብቻ ነው። (2 ቆሮንቶስ 3፥18 ፣ እብራውያን 4:12 -13 ይመልከቱ)።

8. ሰዎች ምኞታቸውን ለማሳካት ትልልቅ ነገሮችን ለማድረግ ሲነሳሱ፥

በሕይወታችን ያየናቸው ብዙ አስደናቂ አገልግሎቶች ከጌታ ምሪት እና ከእርሱ ክብር ሳይሆን ከአገልጋዩ ምኞት እና ፍላጎት የተነሳ የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። ምናልባት ይህ ብዙ መሪዎች እና አገልጋዮች ለምን በፈተና እና በውጊያ ስዓት ጸንቶ መቆም እንደሚያቅታቸው ሊነግርን ይችላል። (1 ቆሮንቶስ 3፥10 -15 ይመልከቱ) እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሰራተኞች በከንቱ ይደክማሉ(መዝሙር 127 ይመልከቱ)።

9. ሰዎች ከቤተ-ክርስቲያን ማዕረጎች ጀርባ ሲደበቁ

በ 2006 ቢሾፕ ሆኘ ስለይ ብዙ ሰዎች ወደ እኔ እየመጡ ስለ አዲሱ “ሹመትህ” እንኳን ደስ አለህ ለማለት ይመጡ ነበር! ሰዎች ይህን ሲሉ በጣም ነበር የደነገጥኩት ምክንያቱም በመንግስቱ የክርስቶስ አገልጋይ ሆኘ ዝቅ እንዳልኩ እንጅ “ሹመት” እንዳልተቀበልኩ ተርድቼ ስለነበር።(ዮሃንስ 13 ያንብቡ) እኔ ልክ አንድ ድርጅት ለሰራተኛው እድገት እንደሚሰጥ እና የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጥ አይነት ቦታ አስቤው አላውቅም ነበር። ይህ ምን ያህል ብዙ ሰዎች የቤተ-ክርስቲያንን ማዕረግ እንደ ጥቅም ማስከበሪያ የስልጣን ተዋረድ አድርገው እንደሚያስቡ አሳይቶኛል። (በእርግጥ ሁሉም አገልጋይ እንደዚህ የተሳሳተ አመለካከት አለው ብዪ አላስብም፤ እግዚአብሔርን ከልባቸው በታማኝነት እና በተዋረደ ማንነት የሚያገለግሉ ብዙ ቄሶችን እና መጋቢዎችን አውቅለሁ)።

ሰው በቤተ-ክርስቲያን ያለን ስፍራ እና ማዕረግ ለማግኘት ሲናፍቅ የእግዚአብሔር የሆነውን ነገር የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት እና ለክብሩ ሳይሆን የራሱን ፍላጎት ለማሟላት ሊጠቅምበት ይችላል።

10. ሰዎች ሁሌ በሌሎች ሲፈርዱ፥

በማህበራዊ ሚዲያዎች ጽሁፎችን ስታዩ እና ክርስቲያኖች አምርረው እርስበርስ አንዱ ሌላውን ሲኮንኑ ስታዩ በማን መንፈስ ነው ይህንን የሚያደርጉት ብላችሁ ልትጠይቁ ይገባል።

ሰው ወደ ክርስቶስ ሲመጣ፣ እውነተኛ ያልሆነው ማንነት የልብ ኩራት፣ ቁጣ፣ መራራነት፣ እራስ ወዳድነት፣ ልክነኝ ባይነት ከውስጥ ካልተወገደ ፈራጅ ማንነት ለእግዚአብሔር አገልግሎት እይሰጠ እንዳለ ወደ ማሰብ ወጥመድ በቀላሉ ይያዛል። (ዮሃንስ 16፥2 ይመልከቱ)።

እንደ ክርስቲያን፣ እግዚአብሔር ከፍቅር፣ ከመሰበር፣ ከርህራሄ፣ ከምህረት፣ ከመልካምነት፣ እና ከተዋረደ ማንነት ጋር የተያያዘውን የውስጥ ማንነት እንዲቀይር ሳይፈቅዱ የመጽሃፍ ቅዱስን የሞራል እና ይማህበረሰብ እሴቶች ብቻ ተቀብሎ መኖር ይቻላል። (በተራራው ስብከት ኢየሱስ ያነሳቸውን የማህበረሰብ፣ የባህል እና የግንኙነት እሴቶች ይመልከቱ፤ በተለይም ማቴዎስ 5፥1 – 16)።

ለማሳያነት – ላውረን ዴግል በኤለን ዲጀነረስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በቀረበች ጊዜ ከብዙ ክርስቲያን ነን ባዮች ውግዘት እና ትችት ደርሶባታል። ይህንን ሳይ ምን ያህል ሃይማኖተኝነት አሁንም አለምን እንደሞላ ያጋለጠ ስለነበር በጣም ነበር ያዘንኩት።ስለምን ባልተለወጡ ሰዎች ፊት ስለ ኢየሱስ ለመዘመር በዚህ ሾው ላይ አትገኝ? በእርግጥ እኔም እራሴ ከቲቢኤን፣ ከ ጋድ ቲቪ፣ ከደይእስታር እና ከሌሎችም የክርስቲያን ቻናሎች ይልቅ በኤለን ፕሮግራም ላይ መገኘትን እመርጣለሁ፤ ምክንያቱም የምወደውን እና የማምነውን ኢየሱስን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ክርስቲያን ላልሆኑ ሰዎች እንድገልጥ እድል ስለሚሰጠኝ።

ኤለን ኢየሱስ በእርሷ ሾው ላይ እንዲኖር ብትጋብዘው (ኢየሱስ ከ 2000 አመት በፊት ሳይሆን ዛሬ በምድር ላይ እንደተመላለሰ በማሰብ) ያልምንም መጽሃፍ ቅዱሳዊ እምቢታ ይመጣ እንደነበር አምናለሁ፤ በጊዜው መስፈርት ጻድቅ አይደሉም ከተባሉት ጋር ይበላ እና ሕብረት ያደርግ ስለነበር። በእርግጥም መጽሃፍ ቅዱስ ከሃጢያተኞች ጋር ይበላ እና ይጠጣ ነበር ይለናል። (ሉቃስ 7፥34 ይመልከቱ)።

በሚያሳዝን ሁኔታ ላዉረን ላይ ይንን ትችት ያወረዱ ሁሉ ትችታቸውን በእግዚአብሔር እና በቃሉ ላይ ለማስደገፍ ይሞክሩ ነበር።(ይህ ዝም ብሎ የራስን አሳብ ከመናገርም ይባሰ ነው)። በተቃራኒው በዚህ ክርስቶስን የማያውቁ ሰዎች በሚኖሩበት አለም በመኖር ማንነታችንን ሳናጣ እና የእነርሱን ሕይወት ሳንመስል የኢየሱስን ማንነት እና ፍቅር ለሰዎች እናሳያለን። 

በመጨረሻም ጸሎቴ ይህ ነው ይህን ያነበቡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል፣ ቤተ-ክርስቲያንን፣ እና የእርሱን ባህሪ ለተሳሳተን ተግባር እና እንደ እግዚአብሔር ቃል ላልሆነ ባህሪ መጠቀም እንደሚቻል እንዲያውቁ እና ከዛም ይጠበቁ ዘንድ ነው።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox