እርኩሳን መናፍስትን ከቤታችሁ እንዴት ታስለቅቃላችሁ?

ካቲ ዴግሮ :

እርኩሳን መናፍስት ወደ ቤታችን ሾልከው ገብተው በመንፈሳዊ ውጊያን በመክፈት እንዲከብደን፣ እረፍት እንድናጣ፣ እና ድብርት እንዲሰማን ያደርጋሉ። እነዚህ እርኩሳን መናፍስት በመንፈሳዊ እርምጃችን ወደ ፊት እንዳንጓዝ ያደርጉናል እንዲሁም በስሜት እስራት ውስጥም ያስገቡናል። አጋንንቶች በተለያዪ መንገድ ወደ ቤታችን ሊገቡ ይችላሉ፥

  • በፊልም
  • በዘፈን
  • አዲስ በተገዙ እቃዎች
  • አለቃ መናፍስት
  • ከቤተሰብ የሚመጡ መናፍስት
  • በምንጠቀምባቸው እቃዎች
  • በጭቅጭቅ
  • በበሽታ
  • በመለያዬት
  • በጓደኞች፣ በዘመዶች፣ እና በእንግዶች
  • ከዚህ በፊት ቤት ውስጥ በመግባት እና በመኖር

ቤታችንን ከአጋንንቶች መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ቤታችንን በመንፈስ ማጽዳት ወደፊት ሊመጣ ከሚችል መንፈሳዊ ፍላጻ ይጠብቀናል፤ መንፈስ ቅዱስም ያለ መከልከል ይሰራ ዘንድ ይፈቅድለታል።

ወደ ቤታችሁ ሾልከው የገቡ መናፍስታን እንዴት ማስለቀቅ ትችላላችሁ?በሚከተሉት መንገዶች ቤታችሁን በመንፈስ ማስለቀቅ ትችላላችሁ፥

  1. መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ሁልጊዜ መክፈት፥ መዝሙር መጽሃፍ ቅዱሳዊ አዋጅ ነው። ለውስጥ ሰውነታችሁ የሚሆን እንጅ የማያውካችሁን መዝሙር በመክፈት፤ መዝሙር የተባለ ሁሉ ቅዱስ እና ክርስቲያናዊ ላይሆን ይችላል። 
  2. በቤት ውስጥ መጽሃፍ ቅዱስን ድምጽን ከፍ አድርጎ ማንበብ፥ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን እና የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እየቀያየሩ መስማት።
  3. እያንዳንዱን ክፍል በዘይት በመቀባት መጽለይ፥ የቤታችሁን መውጫ እና መግቢያ ሁሉ በዘይት ቀቧቸው፤ ሁሉንም ክፍሎች ለእግዚአብሔር እየለያችሁ እና በዘይት እየቀባችሁ የእግዚአብሔር ማገኘት ያለባቸው እና ለሚገባባቸውም ሁሉ ሰላምን የሚሰጡ ናቸው እያላችሁ ተናገሩባቸው።

በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ መጸለይ

  • በመኝታ ክፍሎች፥ የዝሙት፣ የእርኩሰት፣ እና የ ግለ ወሲብ መናፍስት ለቀው እንዲወጡ እዘዟቸው።በዚህ ክፍል አጋንንቶች አስፈሪ ህልም እና ቅዠት አይፈጥሩም እንዲሁም በሌሊት መጥተውም ሰውን አይገናኙም ብላችሁ በተእዛዝ ጸልዩ። የጣፈጠን እንቅልፍ እተኛለሁ በማለት ተናገሩ አውጁም።
  • በመጸዳጃ እና በመታጠቢያ ክፍሎች፥  የህመምን እና የበሽታን ጉልበት፤ የሆድ እና የአንጀትን ችግሮች እሰሩ ገስጹም። የያንዳንዱ ሰው አንጀት እና ሆድ እቃ ሁሉ ሙሉ ጤናማ ይሆን ዘንድ እዘዙ። ራስን የመጥላት፣ የከንቱነት፣ እና የመታበይ መንፈስ ሁሉ ይወጣ ዘንድ ጸልዩ። ሰዎች ራሳቸውን በመስታወት ሲመለከቱ በእግዚአብሔር አምሳል እንደተፈጠሩ እንዲያስተውሉ የእርሱንም ፍቅር እንዲያውቁ ተናገሩ።
  • በማዕድ ቤት፥ የምግብ መመረዝ አይኖርም እያላችሁ ተናገሩ፤ ጤናማ ያልሆንን ውፍረት እና ያልተስተካካለን አመጋገብ የሚያመጡ በሽታዎችን እና የ መናፍስት አሰራሮችን እየተቃወማችሁ ጽልዩ። የአልኮልን፣ የአነቃቂ እጾችን፣ የጣፋጭ ነገሮችን ሱስ የሚያመጡ መናፍስትን ተቃወሙ እሰሩም። ሰዎች ጥሩ ባልተሰማቸው ቁጥር ሁሉ ምግብን እንደመፍተሔ እንዲውስዱ የሚያድርጉ የስሜት ቀውሶችን ሁሉ በመቃወም ጸልዩ።

o በመመገቢያ ክፍል፥ የጥላቻን እና የመለያየትን መንፈስ ሁሉ አስወጡ። የእግዚአብሔር ፍቅር የሞላበት የቤተስብ ሕብረት ይኖር ዘንድ አውጁ። በምግብ ጊዜ የሚነሱ ወሬዎች ሁሉ ለሰው ጥቅም ለእግዚአብሔርም ክብር ይሆኑ ዘንድ ጸልዩ።

o በሳሎን፥ በቴሌቪዝን በኩል ሾልከው የገቡ መናፍስትን፣ ልቅ ንግግሮችን፣ ስሜት ቀስቃሽ፣ እና የእርኩሰት ምስሎችን ተቃወሙ፤ የኤሌክትሮኒክስ ሱሰኝነትን ተቃወሙ። አካባቢውን ያስለቅቁ ዘንድ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ክፈቱ። ጥሩ ባልሆኑ የቴሌቪዥን ዝግጅቶች በኩል አጋንንቶች ይገባሉና እንደዚህ አይነት ይዘት ያላቸውን ዝግጅቶች አትክፈቱ። 

o በመሞቂያ ክፍል፥ አጋንንቶች ብዙ ጊዜ እዚህ ክፍል ይደበቃሉና ከዚህ በፊት እዚህ የኖሩ ቤተሰቦች ባለማወቅ ለአጋንንት ፈቅደው ቢሆን እርኩሳን መናፍስት ሾልከው እንዳይገቡ ጸልዩ። በዘይት እየቀባችሁ አጋንንቶች ይለቁ ዘንድ በኢየሱስ ስም ገስጿቸው።

o የእቃ ማሰቀመጫ ክፍል፥ ከሌላ ቦታ በመጡ እቃዎች ተጠቅመው አጋንንቶች በቤታችሁ ስጋትን እና ሁከትን ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ከጉዞ የተመለሱ እቃዎች እና ሻንጣዎች ላይ ጥንቃቄ አድርጉ። በስጦታ በመጡ እና ከቤተሰብ ከተላለፉ ለብዙ ጊዜም ክተቀመጡ እቃውች ጋር አጋንንቶች ሊጣበቁ ይችላሉ።

o ሰዎች፥ እግዚአብሔርን የማያከብር ሕይወት የሌላቸው፣ እንዲጫጫናችሁ እና እንዲከብዳችሁ የሚደርጉ ሰዎች ቤታችሁ ደርሰው ሲመለሱ ጸልዩ። አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት ስዎች ከወጡም በኃላ እንታወካለን ደስታችንም ይቀንሳል። አብራችሁ በምታልሳልፉበት ጊዜም ሊከብዳችሁ፣ ሊደብራችሁ፣ እና ጭንቀት ሊሰማችሁ ይችላል። “እንደ እግዚአብሔር ያልሆነ ምንም አይንት ሕብረት አይኖረኝም፣ በኢየሱስ ስም አጋንንቶች ሾልከው አይገቡም” እያላችሁ ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ።

ቤታችሁን ከክፍ መናፍስት ካስለቀቃችሁ ወደ ፊት ሾልከው እንዳይገቡ እንዴት መከላከል ትችላላችሁ?

የሚከተሉት ነጥቦች ሕግን ለመፈጸም ሳይሆን ቤታችሁን ለጌታ እንድትሰጡ ይረዷችኋል።

* ግድግዳ ከመቀባታችሁ እና ወለል ካማንጠፋችሁ በፊት የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጻፉባቸው።

* እያንዳንዱን ክፍል በዘይት ቀቡ።

* በቤታችሁ መግቢያ በር ላይ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ጽፉ።

* በቤታችሁ ሁሉ መንፈሳዊ ዝማሬችን ክፈቱ፤ ስራ ላይ በምትሆኑበትም ጊዜ ሁሉ። ምሽትም ላይ ቢሆን በማይረብሽ ድምጽ ይከፈት።

* በቤታችሁ ዙሪያ ምልክትን አድርጉ፤ በቤታችሁ እና በግቢያችሁ ዙሪያ በአራቱም አቅጣጫ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ያለባቸውን ምልክቶች አድርጋችሁ በመሬት ውስጥ ቅበሯቸው።

* በቤታችሁ ውስጥ እና ውጭም ሁሉ እይተንቀሳቀሳችሁ ጸልዩ።

እነዚህ ድርጊቶች እንደዚሁ የሚደርጉ፣ ከፍርሃት የመነጩ እና ሕግን ለመፈጸም የሚደረጉም አይደሉም፤ ነገር ግን በቤታችሁ የሰላምን አየር የሚፈጥሩ፣ቤታችሁም በክርስቶስ መሰረት ላይ የተገነባ እንደሆነ እና ለእርሱም የተሰጠና የተለየ እንደሆነ የሚያውጁ ናቸው።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox