ጋብቻ ባዶ ሲሆን

አብሪ መፅሔት ፣ ግሩም መልዕክት :

ሁለቱም ተጋብተው ለጥቂት ጊዜ አብረው ኖረዋል የግብረ ሥጋ ግቡኝነትም አድርገዋል ይሁን እንጂ ፍቅራቸው ተሟጦ አልቋል የዚያ ምክኒያት ብዙ ሊሆን ይችላል ምናልባት ከመጀመሪያው አንስቶ እነዚህ ሰዎች ፍቅር የላቸውም አሊያ በልጅነት ጋብተው ፍቅራቸውን ሊያዋህድ ጥንካሬ ጎሏቸዋል ወይንም የፍቅራቸውን እሳት ይበልጥ እንደማቀጣጠል በግል ሥራ ተጠምደው ባትለዋል ወይም ልጃቸውን ብቻ በመንከባከብ ጊዜአቸውን እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ጋብቻ ላይ አደጋ ነው የሚፈጥረው እውነቱን ለመናገር ማንኛውም ጋብቻ ክፉ ሳይጠናወተው ፈጽሞ ሊወድቅ አይችልም ያም በሽታ በአንድ ቦታ ተወስኖ የሚቀር ዓይነት አይደለም ብዙስፍራዎች ይበክላል ተጋቢዎቹ በቃላት ይወረፋሉ በድርጎት ይጨካከናሉ ይህም በመካከላቸው ልዩነት ይፈጥርና አንድነታቸውን ይገልጠዋል መጽሐፍ ቅዱስም መተው አንድ መሆን እና መጣበቅ የሚላቸው ውህዶች ሊነጣጠሉ ባለመቻላቸው ምክንያት አንደኛው ላይ የሚፈጥረው ችግር ሌሎቹንም መበከል ይጀምራል በዚህም ሰበብ ወብድየው ከሚስቱ የበለጠ የምትንከባከበውን ሴት መፈለግ ኢቀጥል ሚስትም በበኩሏ አብዝቶ የሚያስደስታቸውንና ምቾትዋን የሚጠብቅላትን ወንድ ታስሳለች ያም ርምጃ ዝናትን ያቀጣጥላል እንደ እውነቱ ኮሀነ በሁለት ተጓዳኞች መካከል የግብረ ሥጋ ግኑኝነት አለመተማመን የሚያመጣው ካለመተሳሰብ አለመታማመን በኋላ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አያሌ ጸሐፊዎች ጋብቻ ፍቅርን ይገላል በሚል የተሳሳተ ግምት ተሞልተዋል በዚህም አሳባቸው ብዙ ሰዎች የፍቅር ሕይወት ከጋብቻ ውጪ ነው ብለው እንዲያምኑ አድርገዋል ይህ ግምት ፈጽሞ የተሳሳተ ነው፡፡ ጋብቻ ፍቅር አይገድለውም የፍቅር አለመኖር ግን የጋብቻብ ሕልፈት ያፈጥነዋል እውነቱን ለመናገር ከጋብቻ ውጪ ያለ ፍቅር በቀላሉ የሚወድም እንደ ገለባ እሳት የሚቆጠርና ሁለቱንም ሰውች ጉዳይ ላይ የሚጥል ነው፡፡ ጋብቻ በፍቅር በግብረ ሥጋ ግንኝነት ላይ ብቻ መመሥረቱ አይበቃም ‹‹መተው›› የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ አሳብ መጨመር አለበት አለበለዚያ ግንኙነቱ ሕመምተኛ ነው፡፡ የሞሆነው በውስጡም ተስፋ መቁረጥና ብልሹ ኑሮ ይከተላል በብዙ አገሮች እንደታየው በሦስቱ ቋሚ መሠረቶችን ሥር ሳታልፍ የምታረግዝ ሴት ልጅ ውጤቱ መጥፎ ይሆናል ማርገዟ ወዲያው እንደተገነዘበች ተፋጥነው ግብቻቸው ይፈጽማሉ

በዚህ መንገድ የሚፈጸም ጋብቻ ደግሞ አብዛኛው በፍቺ ይፈርሳል

ከእንደዚህ ዓይነቱ ጋር የሚፈጠሩ ልጆችም በወላጆቻቸውን አብሮ የመኖር የጋብቻ መከታ የሚያጡ ይሆናሉ የጋብቻቸውም ጣራ ክፍተት ስሚሆን ዝናብ ያስገባና ያበሰብሳቸዋል እርሱም ከለላ ብቻ ሳይሆን አባታቸውን ጭምር ያጣሉ፡፡

በትክክል ለመናገር በፍቅር ውስጥ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት ከሌለ ጋብቻ ይፈርሳል እንደዚሁ ጋብቻ ከሌለ ፍቅር የግብረ ሥጋ ግቡኝነት እርስበእርሳቸው ጠላቶች ይሆናሉ፡፡ሌላው ሁለት ሰዎች በሕግ ተጋብተው ከአሥር እስከ ሃያ ዓመት አብረው ኖረዋል ስለሚዋደዱም የመፋታትን ነገር አስበውት አያውቁም ያም ሆኖ ግንኙነታቸው አጥኒና የተሟላ አይደለም፡፡ ወንድየው ወደ እኔ ይመጣና ‹‹ሚስቴ ቀዝቃዛ ናት አድራጎትዋን በተገቢው መንገድ አትፈጽምም ስሜቷን አፍና በመያዟ ፈጽማ አትጋብዘኝም ደስታም አይሰማትም ይለኛል ሚስትየውም በበኩሏ ‹‹ባለቤቴ በጣም ችኩል ነው፡ አያስገድሰኛል ይወቅሰኛል ማንም አይበቃውም ሌላኛዋም ይህን የመሰለና ከዚህም የተቃረነ ነገር ትናገራለች ለምሳሌ ዘወትር ይደክማል እኔ እፈልጋለሁ ነገር ግን ጀርባውን አዙሮ ይተኛል›› በማለት ስሞታዋን ታሰማለች ይህን ተናግሬ ሳበቃ በቤተክርስትያን ውስጥ ያሉት ሁሉ ሳቃቸውን ለቀቁት፡፡ እውነት ለመናገር በግብረ ሥጋ ግኑኝነት ረገድ ያለ በሽታ በተጋቢዎች መካከል ከፍ ያለ ችግርን ይፈጥራል የግብረ ሥጋ ግኑኝነት እንዳይኖር የተደረገ እንደሆነ ከሁለቱ አንዳቸው ወይም ሁለቱ ተስፋ የመቁረጥ መንፈስ ያድርባቸውና አንዳቸው አንዳቸውን ከእኔ ጋር የፍቅር ስሜት የለህም አሊያ የለሽም በመባባል ይወቃቀሳሉ በዚህም ሁኔታ መሰለቻችት ይፈጥራል ፍቅራቸውም እየቀዘቀዘ ይሄዳል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ሲፈጠር ውጪ ሄዶ የሥጋ ፍላጎትን የማርካት ስሜት እየጠነከረ ይሄዳል በዚህም የጋብቻ አቋም አደጋ ላይ ይወድቃል በመጨረሻም መባለግን ያስከትላልና ወደ መፍታት ያመራል በሽታው በወቅቱ እንዲድንም ካልተደረገ ጋብቻውን ይገድለዋል፡፡ እንገዲህ እራሳቸውን ለጋብቻ የሚያዘጋጁ ሁሉ ወደ ጋብቻ ዓለም የሚገቡበትን ምነገድ ጠንቅቀው ማወቅ አለባቸው ያም መንገድ በመተው በመጣበቅ /ፍቅር/ ና አንድ ሥጋ በመሆን በኩል ብቻ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ ልጅ ለማግኘት በሚለው አሳብ ወደ ጋብቻ የሚዘልቅ አንድ ሰው ወዲያው ወደ ግብረ ሥጋ ግኑኝነት ማዕዘን ያመራል ይህም የሚሆነው የግብረ ሥጋ ግኑኝነት በልጅ መወለድ ስሜት አካባቢ ብቻ ተወስኖ በመገመቱ ነው፡፡ በዚህም የፍቅር ማሰዳያው ማዕዘን ፈጽሞ ተንቆ ተነስቷል ይህም ሁኔታ በተጋቢዎችና በቤተሰባቸው መካከል ግጭትን ወደሚፈጥር አቅጣጫ የሚያመራን አደጋ ይፈጥራል፡፡ እዚህ ላይ የአንድ አይሁዳዊ ወተት ነጋዴና የሚስቱን ታሪክ ተናግሬ ላብቃ ሰውየው ቴቭ ሚስቱ ደግሞ ጉልዴ ትባላላች ወደ ጋብቻ ዓለም በጋብቻ መስመር የገቡና መልካም ምሳሌዎች ሊሆኑ የሚችሉ ባልና ሚስት ናቸው ከሃያ አምስት ዓመት የጋብቻ ዘመን በኋላ እርስ በርሳቸው ይዋደዱ እንደሆነ እንዲህ ተጠያየቁ፡፡

• ጎልዴ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ለመሆኑ ትወጂኛለሽ?
• ጅል ነህ እንዴ
• መሆኔን አውቃለሁ ግን ትወጂኛለሽ?
• እንዴት ትወጂኛለሽ? ብለህ ትጠይቀኛለህ ለሃያ አምስት ዓመት ሙሉ ልብስህን በማጠብ ምግብሕን በማዘጋጀት ቤትህን በማጽዳት ለልጆችህ ወተት በመስጠትና ላሞችን በማለብ እያገለገልኩህ ኖረን ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው ስለመዋደድ የምታወራው?
• እኔ እ አንቺ እኮ የተገናኘነው በጋብቻችን እለት ነበር በዚያ ፈርቼአለሁ፡፡
• እኔ እፍረት ይዞኛል
• ግልፍ ይለኝ እንደነበር አስታውሳለሁ
• እኔም እንዲሁ
• አባትና እናቴ መፈቃቀር እንደምንችል ይነግሩኝ ነበር አሁን የምጠይቅሽ እንደምትወጂኝ ለማወቅ ነው ትወጂኛለሽ?
• ሚስትህ እኮ ነኝ፡፡
• መሆንሽን አላጣሁትም ግን ትወጂኛለሽ?
• እወድሃለሁ ለሃያ አምስት አመት አብሬህ ኖሪአለሁ ተጣልቼሃለሁ አብሬህ ተርቤያ ለሃያ አምስት ዓመትም አልጋዬ አልጋህ ነው ታዲያ ይህ ሁሉ ፍቅር ካልሆነ ምን ሊሆን ይሆን?
• ትወጂኛለሽ ማለት ነዋ!
• እወድሃለሁ ብዬ ነው የማስበው
• እኔም እወድሻለሁ ብዬ እገምታለሁ
• ምንም ያህል ሁኔታው ባይለወጥም ከሃያ አምስት ዓመት በኋላ እርስ በርስ መፈቃቀርን ማወቅ ጠቃሚ ይመስላል፡፡
አብሪ መፅሔት

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox