የወንጌላዊ ሽመልስ ምስክርነት

ብርሃን መፅሔት 1989 ቁጥር 29 :

በትምሕርት ቤት እያለሁ ሙሉ ጤንንት ነበረኝ አንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለሁ ትምህርት ቤት እግር ኳስ እንጫወት ነበር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገባሁ እግሬን ቁርጥማት በሽታ ያመኝ ጀመር ሕመሙ ቢጀምረኝ ብዙ አያስቸግረንም ነበር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ወደ ማጠናቀቁ ስቃረብ ግን እየጠናብኝ መጣ ይህም ሆኖ ግን እጆቼም ሆኑ እግሮቼ በደንብ ይንቀሳቀሱ ነበር ትምህርቱንም እንዳበቃሁ ወደ ሥራ ዓለም በመምህርነት ለሶስት ውራት እንደሰራሁ በሽታይ እየጠና የመጣ ቀን እጄም ጠመኔ(ቾክ) መያዝ ሲያቅተው ግራ እጄ ሥራ መሥራት አቆመ ሥራዬንም መሥራት አቁሜ ተመለስኩ ከወገቤ በታች እግሬን ያመኝ ጀመር በአንድ ወር ውስጥም እግሮቼ ደክመው መሄድ አቃተኝ ጊዜው 1955ዓ.ም ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ነበር እኔም አልጋ ላይ አራፊ ሆንኩ ለቁርጥማቱ መፍትሄ ለመሻት አንዳንድ ጥረት ማድረግ ጀመርን የኔ ቤተሰቦቼ ባእድአምልኮ አምላኪዎች ስለነበሩ ለሕመሜ መፍትሄ ለማግኝት ቃልቻ ቤት እንድመላለስ ብደረግም ሕመሜ ሊተወኝ አልቻለም በእግር መራመድ ሲያቅተኝም እዛው ቃልቻው ቤት ለአምስት ወራት ያህል እንድተኛ ተደረኩ ከዕለት ወደ ዕለትም የተለያዩ ነገሮች ይደረጉ ነበር ለመዳን ወዳጃ ማሳደር አስፈላጊ ነው ተባለ ብዙ ገንዘብም ፈሶ ሙሉ ሌሊት ይከናወን ነበር ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ምንም ዓይነት ፈውስ ላገኝ አልቻልኩም
ሐኪም ቤት ገብቼ ሕክምና ብከታተልም መፍትሔ ሊገኝልኝ አልቻለም ተመልሼም ወደ ቃልቻ ቤት ገባሁ የቃልቻ ቤቱንም ማቀያየር ተጀመረ ቀይ ሴት ፍየልም ታረደ ለውጥ ግን አልነበርም በሽታዬም እየጠነከረ መጥቶ ከወገቤ በታችያለው አካል የእኔ ይሁን የሰው እማላውቅበት ደረጃ ላይ ደረስኩ ሰው ካልዘረጋው አይዘረጋም ሰውም ካላጠፈውም በቀር አይታጥፍም ነበር እጆቼም ምንም ነገር ማድረግ ስላልቻሉ እናቴ እህቴም ወንድሞቼም ነበሩ የሚያበሉኝና የሚያጠጡኝ የምውለው አልጋ ላይ ነበር እስትንፋሴ ከእኔጋር አብሮ መሆኑን እንጂ ከሬሳ የምለይ አልነበርኩም ወደ ጠበልም እንዲሄድ ቢደረግም ምንም ለውጥ ላመጣ አልቻልኩም፡፡

ሁለት ዓመታት በእንዲህ ዓይነት ሁናቴ አለፈ የኑሮ ችግር ነበር ጊዜው የመከራ ወቅት ስለነበር ተስፋ ለመቁረጥ ሕይወት ውስጥ ገባሁ እንዲህ ሆኜ ከምኖርም ለምን ሕይወቴን አላጠፋም ማለትን ጀመርኩኝ ከጓደኞቼ ጋር ሳለሁ የነበረኝ ዓላማ ዩኒቨርስቲ ገብቼ ትምህርቴን በመጨረስ ራሴንና ዘመዶቼን ለመረዳት ነበር ያሁሉ ግን ሳይሆን ቀረ በዚያም ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ያለሁበትንና የጓደኞቼን ሆኔታ አነፃፀርኩ የሰው ሸክም መሆኔ እጅግ ስላሳሰበኝ ራሴን ለማጥፋት አሰብኩ ይህንንም ሐሳብ ያስተናገድኩት ቃልቻ ቤት ሆኜ ነበር እጄ እንኳ ገመድ ክርም መቋጠር ስለማይችል ታንቄ መሞት አልቻልኩም ሰው የእንግሊዝ ጨው ጠጥቶ ሎሜ ቢመጥ እንደሚሞት ይነገር ስለነበርና በሕክምና በኩል እውነት ለመሆኑ ሰለሰማሁ ድርቀት አሞኛል በማለት የእንገግሊዝ ጨው እንዲገዙልን ጠየኩኝ የጠየኩትም ተገዛ ሎሚ ቃልቻው ቤት ስለነበር ማስገዛት አላስፈለገኝም በነጋታው ሁሉን ለመፈጸም እያሰብኩ ሳለ አንድ ሓሳብ ወደልቤ መጣ ይህን አድርጌ ራሴን ከማጥፋት ለምን እግዚአብሔርን አልጠብቅም አልኩ ራሴን በራሴ አጥፍቼ ወደገሃነም ከምገባ ምን ለ እግዚአብሔርን ብጠብቅ ብይ አሰብኩ ከዚህም ሐሳብ የተነሳ ራሴን ላለመግደል ወሰንኩ በነጋታው የእንጊሊዝ ጨውን ሊሰጡኝ ሲመጡ አልወስድም ሆድ ድርቀት ትቶኛል በማለት መለስኩላቸው በዚያን ጊዜ ይመስለኛል እግዚአብሔር የመዳን ተስፋ የሰጠኝ በኋላ በ1957 ዓ.ም ጠንቋይ ይሁን ቃልቻ ማንኛውም ቦታ ላለመሄድ ወሰንኩ የፈጠረኝ እግዚአብሔር ነው ምንም ቢያደርገኝ እርሱን እጠብቃለሁ ብዬ ወሰንኩኝ፡፡

ሳልታመም በፊት እሁድ እሁድ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን አስቀድስ ነበር እግዚአብሔርን የመፈለግ ነገር ነበረብኝ በዚሁ ዓመት የቃልቻው ቤት ልጅ ጌታኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል መድኃኒቱ አድርጎ ተቀበለ አንድ ሰው አለ ኑና መስክሩለት በማለት ወንድም ዘለቀ ዓለሙ ጋር አብረን ስላደግን እንተዋወቃለን መሰከሩልኝ ጌታንም በዚሁ ዓመት በታኅሳስ ወር ተቀበልኩ ተጸለየልኝም እግዚአብሔር የውስጡን ሕይወቴን ነበር የለወጠው በሥጋዬ ላይ ምንም ለውጥ ባይታይም እግዚአብሔርን በእምነት ማየተት ጀመርኩ መጸለይና በተኛሁበት መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ጀመርኩ ሰባት ዓመት አልጋላይ ተኛሁ በዚህ ጊዜ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሴን ደጋግሜ አነብ ነበርና ቢያነስ አስር ጊዜ ከዳር እስከዳር ተወጣሁት ያን ወቅት ለእኔ የምድረበዳ ትምህርት ቤት እንደሆ ነው የምረዳው በሆሴዕ መጽሐፍ እግዚአብሔር ወደምድረበዳ ወስዶ እንደሚያባብል እንደተገለጸ ሁሉ ይህ ጊዜ ለእኔ ልዩ ነበር በዚህ ወቅት በእግዚአብሔር መንፈስ ተሞልቼ በጸሎትም ብዙ ተጋሁ ጌታን ተቀበልኩ ከሁለት ዓመታት በኋላ በ1959 ዓ.ም የቀኝ እጄን ትንሷ ጣት መንቀሳቀስ ጀመረች ክስቱም ብርቅ ስለሆነብኝ ቀኑን ሁሉ ሳንቀሳቅስ እውል ጀመር እናቴ ልማድ ሆንብሃል ተው ብትለኝም ለእኔ ግን ትልቅ ደስታ ይሰጠኝ ነበር ከወገቤ በታች በድን ነበረውን አካል ሰዎች ሲነከት ትንሽ ትንሽ ይሰማኝ ጀመር ከወገቤም ቀና ለማለት መሞከር ጀመርኩ የሰው ድጋፍ ግን ያስፈልገኝ ነበር በዚሁም ዓመት አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ጋር በመገናኝት አባል ሆንኩኝ በቤቴ ሆኜ ብዙ ሰዎች ይሰበስባሉ እመሰክርና መጽሐፍ ቅዱስ አስተምር ነበር በቃልቻ ቤት ያሰለፍኩትን የጨለማ ዘመን ሳስብ የንጋት ኮከብ የሆነው ጌታኢየሱስ ወደኔ መምጣቱ ታላቅ በረከት እንደሆነ አስተዋልኩ ከዚህም የተነሳ ነው ጌታን በአልጋ ላይ ሆኜ ማገልገል የጀመርኩት፡፡

በትንቢተ ኢሳያስ 35 ፤6 ላይ ‹‹አንካሳ እንደሚዳቋ ይዘላል ላል›› የሚለውን ቃል በማሰብ በሥጋ በዚህ ምድር ባልዘልም እንኳ የዘላለም ሕይወት የሰጠኝን ጌታ ዳግም ሲገለጥ ከመቃብሬም ቢሆን እዘላለሁ በማለት በአልጋዬ ጌታን አገለግለው ነበር በ1961ዓ.ም አድቬንቲስት ወደ ነበረው ዘውዲቱ ሆስፒታል አመጡኝ የሚቻለው ምርመራ ተደረገ እናቴም እኔን ለሆስፒታሉ ሠራተኞች በመተው ተመለሰች ሰድስት ዓመታት ሙሉ ተኝቼ በነበረበት ጊዜ ጎኔና ጀርባዬ ምንም አልተላጠም ነበር በዚህ ሆስፒታል ግን ገና አንድ ወር እንደተኛሁ ጎኔ መላጥ ጀመረ እንደናቴ ሆኖ ሚያስታምም ሰው ስላልነበር ነው የተጎዳሁት ምግብ የሚያጎርሰኝ አልነበረም እንጀራ ተጠቅልሎ ይመጣል ላለመሞት በአንድ እጄ እንጀራውን ተጭኜ በትንሷና በጠቋሚ ጣቶቼ በመታገዝ ለአፌም ለደረቴም የሚሆን ጉርሻ አነሳ ነበር ይህን ጊዜም ብዙ የማዝንበት ጊዜ ቢሆንም ውስጤ ግን በጌታ ደስ ይሰኝ ነበር ጎኔንም ያመኝ ስለነበር ያመጣኝን ሐኪም መልሰኝ ብዬ ጠየኩት እርሱም ልንረዳህ ስለማንችል እንመልስሃለን በማለት ከባልቻ ሆስፒታል ሐኪም አስጠርቶ አሳየኝ እርሱም በጀርባ አጥንቴ (ኅብለሰረሰሬ) ላይ እጢ እንዳለና ይህም እጢ በቀዶጥገና የማይወጣ ካልሆነ እግሬም እጄም ሽባ እንደሚሆን ተናገረ የዚህ ቀዶጥገና ጉዳቱን ባላውቅም ውስጤ እምቢ ስላለን ቀዶ ጥገናውን እንደማላደርግ ገለጽኩላቸው አብረውኝ የነበሩ ሰዎች ብዙ ተከራከሩኝ በሰው ልታመን እንደማልችል አሳወኳቸው ወደ ድሬድዋ እንድመለስ ተደረገ በተለያየ ጊዜአት ውስጥም ቀኝ እጄ ተፈታ መብላትና መጻፍ ጀመርኩ ደስ አለን ቤተሰቦቼ ደስ አላቸው 1962 ዓ.ም ላይ ቄስ ትምህርት ቤት ለምን አትከፍትም የሚል ሐሳብ መጣ እኔ ግን ሕጻናትናትን እንዴት አስተምራለሁ ብልም የእግዚአብሔር መንገድ ስለነበር በአራት ሕጻናት ማስተማር ጀመርኩ በሚቀጥለው ወር 40 ቀጥሎም 75 ሆኑ በአራተኛው ወር እንደመንግስት ትምህርት ቤት ቦታ የለኝም በማለት መመለስ ጀመርኩ በዚያን ወቅት 100ብር ትልቅ ዋጋ ነበረው እራሴንና ቤተሰቤንም መርዳት ቻልኩ እስከ 1969 ዓ.ም ድረስ እናቴን አራት ወንድሞቼን እናቴንና እኔንም በዚህ መንገድ እንድደግፍ አደለን በዚህ መንገድ እንድንደጋገፍ አደረገን በዚህ መሃል በ1965 ዓ.ም ሐረርጌ ውስጥ ዋተር የሚባል ፍልውሃ ቦታ በመሄድ ለስምት ቀናት ፍልውሃ ውስጥ እየተኛሁ እወጣ ነበር፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜም ሰው ተደግፌ መቆም ጀመርኩ የእግሮቼ ጣቶች ትንሽ ትንሽ መንቀሳቀስ ጀመሩ አብሮኝ የሄደው ልጅ ተማሪ ስለነበርና ትምሕርት ጊዜው ስለደረሰ ብዙ መቆየት ስልችል ተመለስኩኝ ሰውነቴ ለውጥ ማሳይት ጀመረ ከቀኝ ወደግራም እንደልቤ መገላበጥ ቻልኩ ቀና ማለትም እግሬንም አውርጄ መቀመጥ ቻልኩ(ባለጉማ የሰው ጋሪ) አግኝቼ ነበር ሕጻናትንም የማስተምረው በዚህ ጋሪ ላይ ተቀምጬ ነበር ደግሜ ወደዚያ ፍልውሃ በመሄድም 15 ቀናት ከረምኩ ሰውም ሳልደገፍ በምርኩዝ መራመድ ጀመርኩ ለውጥ ይታይብኝ ጀመር በዚህ ጊዜ ልጆች ሆነው ሳስተምራቸው የነበሩ ሰዎች ያለፈው ወር (ሰኔ1989) ምስክርነታቸውን ሰጡኝ ብዙ ሕጻናት አድገው ጌታን ሲያገለግሉ አይቻለሁ ዘሩ ከንቱ ሆኖ አልቀረም እግዚአብሔር ይመስገን ግንቦት 1967ዓ.ም ላይ እግዚአብሔር በድሬድዋ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለሁለት ቀናት እንዳገለግል በር ከፈተልኝ ዊልቼር ላይ ቁጭ ብዬ ነበርና ያገለገልኩት ሁለተኛ ወደዚህ ስመጣ ቆሜ እንዳገለግል ተናገርኩ ይህንንም ቃል በእምነት በተስፋ ነበር የተናገርኩት በኅዳር ወር 1968 ዓ.ም በድጋሚ እንዳገለግል ስጠራ ለ1ሰዓት ያህል ቆሜ አገለገልኩ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ወደዚች ቤተክርስቲያን እንድመጣ በልቤ ስላሳሰበኝ አባል ሆንኩ ሙሉ ጊዜ ማገልገል እንዳለብኝ ባምንም ጊዜውን እንጠብቅ ነበር በ1968 በባይብል አካዳሚ ኮንፍረስ ተካሂዶ አገለገልኩ እግዚአብሔርም አገልግሎቴን ባረከ የእርሱም ጥሪ እንዳለተገነዘብኩ የቃሉን መሞላት እየሰጠኝ ሄደ መጽሐፍ ቅዱሴን ዛሬ 42 ፡፡ጊዜ አንብቤዋለሁ ይህን ጸጋ የሰጠኝ እግዚአብሄር ነው የእርሱ ቃል ከማጥናት የበለጠ የከበረ ነገር የለም ክርስቲያኖች ለጌታ ቃል ከፍተኛ ስፍራ እንዲኖራቸው አሳስባለሁ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ጊዜያት በማገለግልበት ጊዜ አንድ ሕልም አየሁ አንድ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ከፊት ለፊቴ ሆኖና በድሬደዋ እርዳን ብሎ ሲናገርኝ ተመለከትሁ በዚያን ጊዜ ነገሩን አልገባኝም ምን አይነት አገልግሎት እንዳገለግል ሊጠሩኝ ነው በማለት ቃል ማዘጋጀት ጀመርኩ አንድ ቀን ከሐረር ወደ ድሬዳዋ ከተማ እንድመጣ መንፈስ ቅዱስ ገፋፋኝ አገልግሎት አልነበረኝም አቶ ሰለሞን የሚባሉ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ለምን ወደዚህ መጣህ ሲሉኝ እንዲሁ በማለት መለስኩላቸው እርሳቸውም ‹‹እግዚአብሔር ይመስገን›› አሉ ለምን ብዬ ስጠይቃቸው ቤተክርስቲያን ወደኔ እንደላከቻቸውና ሊያናግሩኝ እንደፈለጉ ገልጸውልኝ ወደ አንድ ክፍል አመራን ተነጋገርን ‹‹ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ጊዜህን ሰጥተህ እንድታገለግል ትፈልግሃለች አሉኝ እግዚአብሔር አስቀድሞ የተናገረኝን ነገር ስላሰብኩ እጸልይበታለሁም ሳልል ወዲያውኑ በሐሳቡ ተስማማሁ፡፡

ሐምሌ 11969 ዓ.ም በቤተ ክርስቲያኒቷ ሙሉ ጊዜዬን ሰጥቼ ማገልገል ጀመርኩ እስከዛሬ ዋዕለትም ድረስ እያገለገልኩ እገኛለሁ በጊዜው የምዕመኑ ቁጥር አነስተኛ የነበረ ሲሆን የሙሉ ጊዜ አገልጋይም እኔብቻ ነበርኩ ብቻዬን የምገፋው ነገር ስላልነበር አገልጋዮችን ማፍራት ጀመርኩ አገልጋዮችን እየመረጥኩ አሰለጥን ጀመር አዳዲሶቹን አስተምራለሁ ምክር እሰጣለሁ ጥያቄ ላለባቸው መልስ እሰጣለሁ ትምህርትም እሰጥ ነበር በዚህ ውስጥ በውስጤ ሲሠራ የነበረው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ቤተክርስቲያንም እያደገች መጣች አገልጋዮቹም እወጡ መጡ በ1967ዓ.ም እግዚአብሔር ከሰጠኝ እጮኛዬ ጋር በ1970ዓ.ም ጋብቻ ፈጸምን ዛሬ በ3 ሴቶችና በ1 ወንድ ልጅ ጌታ ባርኮናል እንደናት ሆና የምትሸከመኝን ባለቤቴን መሠረት ወንድሙን እግዚአብሔርን ስለሰጠኝ እጅግ አመሰግነዋለሁ ችግሬ ችግሯዋ አድርጋ ከእኔ ጋር ያለችው ውድ ባለቤቴነች የሁለታችንም ሕይወትና ኑሯችን በእግዚአብሔር የተጠበቀ ነውሥራ አልነበራትም ቤተክርስቲያን ልትዘጋ አሥር ቀናት ሲቀር ግን ሥራ ጌታሰጣት አገልግሎታችን እየሰፋ ሄደ እግዚአብሔር ለሚደክሙት ብርታት ለሚጠባበቁት ጉልበትና ለአግልጋዮች ኃይል ነው ‹‹ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና››(2ቆሮ12፡9)የሚለው የጌታ ቃል እውነት ነው በድካሜ የእግዚአብሔር ኃይል ይሠራ ነበር፡፡ እኔን ደካማውን ለዚህ ሥራህ ከመረጥህ ፀጋህን በውስጤ አፍስስ አልኩት እርሱም አደረገው በዚህ ሁኔታ እያለን በካቲት ወር 1974 ዓ.ም ቤተክርስቲያን ተዘጋች በዚህ ጊዜ የምዕመናን ቁጥር 120 ብቻ ነበር እኔ የነበርኩት ቤተክርስቲያን ታሽጋ አብዮት ጠባቂ ከውጪ ይቆም ነበር ብዙጊዜ ወደ ውጪ በእግሬ መሄድ ስለማልችል የምውለው በግቢው ውስጥ ነው በዚያም ሁኔታ እያለን ከቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ጋር በመሆን በየአካባቢውየመጽሐፍ ቅዱስ ቡድን ማቋቋም ጀመርን አንድ ሰው አግኝቶን እንዲወጣ የሚፈቀድለት ለ5ደቂቃ ብቻሥራ እንሥራ ነበር በአንድቀን ሠላሳ የተለያዩ አገልጋዮች ወደቤቴ መጥተው ተመልሰዋል በዚህ ሁኔታ እያለን ጥበቃው ላላ ማለት ጀመረ በር ላይ አብዮት ጠባቂ እየጠበቀ በበርሜል ውሃ ሞልተን 6 ነፍሳት አጠመቅን ይህን የእግዚአብሔር ጥበቃ ነበር 9ወራትያህል በዚህ ቤት ተቀምጬ ሳበቃ ቤት እንዲሰጡኝ እጸልይ ነበር ስድስት ቤቶች ካስመረጡኝ በኋላ አሁን ያለሁበት ቤት ልገባቻልኩ በዚህ ቤት ውስጥ ብዙ አገልግሎት አካሄድን የአውራጃው ተጠሪ የሕዝብ ደኃንነት ኃላፊውና የርዮት ዓለም ተጠሪዎቹ በቶች አጠገቤ የነበሩ ቢሆኑም ከጌታ ጥበቃ የተነሳ አንደም ነገር ሊገጥመን አልቻለም ነበር፡፡

ቤተክርስቲያን ሲከፈት ጌታ አብዝቶ ን2000 ያህል ሆነን ነበር ዘመኑን የጨለማ ሳይሆን የብርሃን ጊዜ ነበር የምለው ሰዎች ቤትን ዘጉ የጌታን ቤት ግን አልዘጉም የእግዚአብሔር ሥራ ሊያዝ ስለማይችል እጅግ ሰፊ ሆነ አገልጋዮችን ማፍራት ጀመርን የእግዚአብሔርን ቃል ተክተው የሚያገለግሉ አገልጋዮችን ማፍራት ጀመርን መነሳት ትልቅ አገልግሎት ነው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ‹‹ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ›› ይለዋል አሁንም ለአገልጋዮች የማስተላልፈው መልእክት አገልጋዮችን ለማፍራት ብዙ እንዲጥሩ ነው ይህንም በማድረግ ሸክምን መከፋፈል እንችላለን አገልግሎታችንን ሞትን ጨምሮ በተለያየ ምክንያቶች ልናቆም ስለምንችል ለመንጋው መጠንቀቅ ይኖርብናል ሁሉን የሚያስችለውን እግዚአብሔርን መታመንና በፊቱም መውደቅ እጅግ አስፈላጊያችን ነው አገልጋይም ሰለቸኝ ማልተ የለበትም ጌታ እየሱስ በዩሐንስ አራት በሥጋው እረፍትን በፈለገበት ጊዜ ነበር ሳምራዊቷን ሴትና ሌሎቹን የከተማይቱን ነዋሪዎች ወደ ዘላለማዊው እረፍት ያመጣል ዛሬ አንነቴ ትንሽተደልድሎ ቆሜ እሰብክ የነበረወ ቁጭብዬ ማስተማር ጀመርኩ ይህም ምንም አያሳስበኝም እግዚአብሔር ፈቅዶታል አሁንም አንድ ትልቅ ተስፋ አለኝ ከአልጋ ላይ አንስቶ ያቆመኝ እግዚአብሔር ዱላዬን እንደሚያስጥለኝና ምስክር እንደሚያደርገኝ አምናለሁ ተስፋዬ በእርሱ ላይ የጸናነው ፍቃዱ ከሆነ ያደርገዋል ዝም ብዬ እርሱን እጠብቃለሁ ከዚህም በሰፋ ሁኔታ ጌታን እንደማገለግለው አምናለሁ እስከዛሬ ድረስ ብዙ ፍሬዎችን ጌታ ሰጥቶኛል ጌታ እየሱስ‹‹ያለ እኔ ምነም ልታደርጉ አትችሉምና›› እንዳለ ሁሉ ከእርሱ ጋር የተጣበቀ ከሆነም ምን ጊዜም ፍሬ የሚያፈራ ነው የሚሆነው አገልጋይ ሁሉ ጌታ ኢየሱስን በጌትነቱ በሕይወታቸው የሚያነግሱት ከሆነ ሥራውን እርሱ ይሠራል ኢየሱስ ጌታ ያልነረበት አገልግሎት ፍሬ አልባ ነው በእግዚአብሔር ጸጋ ውስጥ ሆኖ ከጌታ ጋር የተያያዘ አገልጋይ ግን የራሱ ሕይወት የተጠበቀና ፍሬ የሚያፈራም ይሆናል የእኔ ሕይወት በዚህ መንገድ እንዳለፈ አውቃለሁ ከጌታኢየሱስ ጋር ከተገናኘሁ በኋላ በመንፈሳዊ በረከት በጤንነት በኑሮ ባርኮኛል፡፡

እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን መናን ሰጣቸው በእኔ ደግሞ እውን ሆኖ መርቶኛል በሁሉም መስክ በሕይወቴ እውን ሆኖ ሠርቷል ኢየሱስ ክርቶስ ታማኝ ጌታ ነው እስከሕይወቴ መጨረሻም በደስታም ይሆን በኃዘን ላገለግም ቆርጩአለሁ ቢሆንልኝ ጌታን እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ በሞቱም እንድመስለው እመኛለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን አገልግሎ ለእርሱ ከመኖር የበለጠ ነገር የለም ሁላችንም ጌታን እንመልከት በታማኝነትም እናገልግለው በክብሩ ሲመጣ ለዘላለም አብረነው እንሆናለን ጌታ ኢየሱስ በሕይወታቸው ላነግሳችሁ ደግሞ ለነፍስም ለስጋም እውነተኛ ተስፋ እንደሆነ እመኑት ጠንቋይ ሆነ ባለመድሃኒቱ ምንም አይጠቅምም ማናችንም ብንሆን ብቻውን ተስፋ የላችሁም ብሎ ማለት የሚችለውን እግዚአብሔር እንታመን በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

ብርሃን መፅሔት
1989 ቁጥር 29

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox