6 የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን የተሃድሶ ምልክቶች

ራየን ልስትሬንጅ :

እኛ በተሐድሶ ዘመን ውስጥ ነው ያለነው። መንግሥተ ሰማይ በመንግሥቷ የግንባታ እቅዶች የታጠቁ አዳዲስ ግንበኞችን እየላከች ነው።

በመንፈሴ እንዲህ የሚል ቃል ሰማሁ፣ “ለተከታዮቼ እና ጸንተው ለሚቀጥሉት አዲስ የህንፃ እቅድ እሰጣቸዋለሁ!” እነዚህ በሰማይ ተልዕኮ ያላቸው ግንበኞች በግንባር ቀደምትነት እንዲጠሩ ከቶ ያላሰቡ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህም ልክ እንደ ዳዊት በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን ክብር የሚፈልጉ እና የሚጠብቁ ሰዎች ይሆናሉ።

ነህምያ 2፡18 ላይ የ አሁኗ ቤተ-ክርስቲያን የመነሳት እና የመገንባት ወቅት ላይ ትገኛለች። ይህም ወቅት የሚገለፀው በእነዚህ ስድስት መንገዶች ነው።

አዲስ እየወጡ ያሉ ሐዋርያዊ ወታደሮችን ተመልከቱ። አዲስ መንግስቱን የሚገነቡ አዲስ ዝርያዎች እየተነሱ መሆናቸዉን አምናለሁ። እነርሱም አዳዲሶቹን ሞዴሎች፣ ቡድኖች፣ ቤተ-ክርስቲያኖች፣ የመሰብሰቢያ ቦታዎች እና አዳዲስ እንቅስቃሴዎችን ይገነባሉ። ግልጽ ለማድረግ ያህል፣ ይሄ የያለፉት መሪዎች ምትክ ሳይሆን፣ እነርሱ አስቀድሞ የገነቡት ላይ የሚጨመር ቅጥያ ነው።

ይሄ አዲሱ ዘር ታድያ፣ ልክ የቀደሙት ሓዋርያት ሲያደርጉ እንደነበሩት፣ ሀሰተኛ ትምህርትን ብሎም የባሕሪ ጉድለትን ለማረም ፍቃደኛ የሆነ መሆኑ ግድ ነው። ይሄም ለእግዚአብሔር ቤተሰቦች ካለን እዉነተኛ ፍቅር ይመጣል። እነዚህ ጉድለቶች የሚስተካከሉበት ተገቢ ደንብና አሰራር አለ። ሐሰተኛ ትምርቶች፣ መጥፎ ልማዶችና የተለያዩ የማታለል ሴራዎች በመካከላችን እየተፈፀሙ የሐዋርያዊ መሪዎችን ዝምታ ለመቀበል አቅሙ የለንም። ብዙዎች በቦታዎች የመስበክ እድልን፣ ዝናን፣ ክብርን ወይም ተከታዮችን ላለማጣት ፈርተው ይሆናል፣ ነገር ግን ስለንፁህነትን ወይም ቅድስና፣ ስለታማኝነትን እና ስለሁለንተናዊ አንድነት እግዚአብሔር በዚህ ግንባታ ውስጥ ወቀሳን ያመጣል።

ብዙዎች የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር ተጠርተዋል። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት፣ ስብስቦች ወይም የአገልግሎት ማዕከላት ያልተለመደ መገለጥ፣ ኃይል እና ተግባር አላቸው። መፈወስን፣ መዳንን እና ሙላትን ለመቀበል መሄድ የሚቻልባቸው እንዲህ አይነት ቦታዎች እንደነበሩ አስታውሳለሁ። በዚህ ዘመን እንደነዚህ አይነት ቦታዎችን ማግኘት ቀላል አይደለም። ሆኖም እነዚህ ቦታዎች በሚያሳዝን ሁኔታ ደንበኛ መር መዋቅር ባላቸው ቤተ ክርስቲያኖች ይህም ማለት፣ የሰው ልጅ ጥበብና ሓሳብ ላይ የሚያተኩሩ፣ ከ መንፈስ ልምምድና ሃይል ይልቅ በጉባዔዉ ቁጥር ብዛትና የወንበር ሙላት በሚጨነቁ ተተክተው ይገኛሉ።

ቤተ-ክርስቲያን ያለዉን የተሃድሶ ሂደት ለማስቀጠል ፊት ለፊት መጋፈጥ ይኖርታል ይህ ወቅት በቤተ-ክርስቲያን ለረጅም ጊዜ የቆዩ የሴሰኝነት፣ እድሜን ያማከለ አድሎና የዘረኝነት ድርጊቶች በጋሃድ የሚጋለጡበትና የሚስተካከልበት ጊዜ ነው። ይህ ካለፈው ደረጃ በበለጠ የተዋቀረና በክትትል ስር ያለ መንፈሳዊ፤ ወታደራዊ ጦርነት ነው። ይህም በማናቸውም የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ የሚሰራ ሲሆን ያልተጠበቀ ከባድ ምላሽ ይሰጣል። ለዉጥ ከመታየቱ በፊት ነገሮች ይዛቡ እናም ይወሳሰቡ ይሆናል፣ ነገር ግን ጠንካራ ፍጥጫ አስፈላጊ ነው። ብዙ ስብስቦች እና ክስተቶች በዓለም አቀፍ ትንቢታዊ ማኅበረሰብ ዉክልና ስም ቢነገዱም ከተለያዩ ዘር የተውጣጡ አገልጋዮች ሲያገለግሉ አይስተዋልም። እግዚአብሔር ይህንን የሚያጋልጥ ደፋር እና ጠንካራ ድምጾችን እያነሳ ነው። የኤርምያስ 1 ትዕዛዝ፤ ከመገንባት በፊት ማፍረስ ነው።

ታላቅ አዋጅ እናመንግሥቱን ተልኮ መረዳት እየተስፋፋ ነው። በብዙ ሁኔታዎች፣ በመንፈሳዊ መስቀለኛ መንገድ ላይ ቁመናል። በተለያዩ ዉሳኔዎች መካከል፣ ቀጥሎ የሚሆነውን ነገር እየፈለግን አለን። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት፣ ሀይልና ውስብስብ ስለሆነዉን መንፈሳዊ እውነት መረዳት ቀጣዩን ርምጃችን ለማወቅ ቁልፍ ነው። በተደጋጋሚ ወደ አንድ ተመሳሳይ ነገር በሚጠቁሙ ትንቢታዊ ልምምዶች ተውጠናል ሆኖም በህይወትና ሞት መካከል ተጨምተን እንድንጠባበቅ ሆነናል። ብዙ ጊዜ፤ ቀድሞም የመንግስቱ ዜጎች በመሆናችን ብቻ የእኛ የሆነውን ነገር እንደገና ስንጠብቅ እንታያለን።

“ሸማር” ነብያቶች እየተነሱ ነው። ወደፊት የሚያስጠነቅቁ፣ የሚመለከቱ እና የሚያጋልጡ ነቢያት በብዛት ይጨምራሉ። ይህ የእግዚአብሔር ሕዝብን ከስህተት ለመቆጠብ ወሳኝ የሆነ ነገር ነው። “ሻማር” ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ መከታተል፣ ጠብቆ ማቆየት፤ ጠባቂ ሰው መሆን ማለት ነው።

ማሕልየ መሓልይ 3፡3 እንዲህ ይላል፣ “ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፤ ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም”።

ጌታ በመለኮታዊ ሀይሉ፣ የበሰሉና ጥበብ ያላቸው ነብያትን እና አዲስ ከሚነሱ ሐዋርያት ጋር ሲያጣምር ተመለከትሁ። ስራውን ለመከላከል እና ለዚህ ሰዓት የሚሰጠውን ቅባት ለመጠበቅ እርሱ የመንግሥቱን መዋቅር በመመስረት ላይ ይገኛል። ነብያቶች በሃዋርያዊ እቅዶች እና ተልዕኮዎች ውስጥ በመንፈስን እንደ ጠባቂዎች ሆነው ያገለግላሉ። እንደ አስፈላጊነቱም ይገልጣሉ እናም ያስጠነቅቃሉ። በሐዋርያቶችና በነቢያት መካከል አለመተማመንና የባሕሪ ጉድለት ከተፈጠረ፣ ይህ አይነቱ ሥራ ፈጽሞ አይሳካም።

የፈውስ እና ተአምራዊ አገልግሎት ወደ ነበረበት ተመልሷል ፈጥኖም እያደገ ነው ጌታ የተአምረኞችን ጉዞ ወደነበረበት እንደገና ሲመልስ፣ ለተወሰኑ ግዜዎች ግልፅ የሆኑ ህልሞችን አይቻለው። ኢየሱስ እርሱ ባደረገው ነገሮች ተጽእኖው እንደፈጠረ ሁሉ፣ በተናገረውም ተጽእኖን አድርጓል። በትናንሽ እንቅስቃሴዎች ስንወያይ እና ስናስተምር ብዙ ሰዓታትን አሳልፈናል፤ አሁን ግን ተራው ጥልቅ የሆነው የተዓምራዊ ኃይል እና ድንቅ የሆነ ጊዜ ነው።

እኚ አስደሳች ጊዜያት ናቸው። እግዚአብሔር ህዝቡ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ይፈልጋል። እንነሳ፤ ለእሱ ያለፍርሀትም እንታዘዝ። ደግሞ ለእግዚብሔር ክብር እንጠንቀቅ፣ አዳዲስ እንቅስቃሴዎችን እንገንባ፤ እናም ንጉሱን፣ መንግሥቱን እና መላው ክብሩን አናውጅ።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox