ፍለጋ – ቤሪያ ቁጥር 2 1996

መከራ ውስጥ ጽናት(ሪቻርድ ውምብራንድ) :

የሪቻርድ መልስ ግን ፈጠን ያለ ነበር ‹‹ሊመጣብኝ ያለውን መከራና ሥቃይ በሚገባ አውቀዋለሁ›› አለ ‹‹እናም እርግጥና ጽኑ ለሆነው ዘላለማዊ እውነት ዋጋ ብከፍል ይህ ለእኔ ክብሬ ደስታዬና አክሊሌ ነው›› በማለት አከለበት፡፡ ከዚህም በኋላ ሻምበል ግሪኩ በተባለ ትጉ ወጣት ኮምዩኒስት ባለሥልጣን ክፉኛ ተገረፈ፡ ሻምበሉም ሪቻርድን በኮሚኒስት መንግሥቱ ላይ እንዳመጸና እንደዶለተ ስለቆጠረው ወንጀሉን እንዲናዘዝና በጽሁፍ እንዲያሰፍር ያስገደደው ጀመር፡፡ ሪቻርድ ግን በእስር ቤት ውስጥ ወንጌልን ለማሰራጨት ‹‹ሞተርስ ኮድ››ን ይጠቀም እንደነበር ተነገረ፡፡ በጽሁፍ ሲያስፈርም እንዲህ አለ ‹‹ በኮምዩኒስቱ መንግስት ላይ የዐመጽንና የተቃውሞን ድምጽ አላሰማሁም እኔ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ነኝ ኢየሱስ ደግሞ ጠላቶቻችንን የምንወድበትን ፍቅር ሰጥቶናል በመሆኑም በክርስቶስ ኢየሱስ ተለውጠው ወንድሞቼ እንዲሆኑ ስለ እንርሱ እጸልያለሁ›› ሻምበል ግሬኩ መግረፊያውን በኩራት እያወዛወዘ የሪቻርድን ጽሁፍ አነሣና ማንበብ ቀጠለ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ያ የጨፈገገ የሻምበሉ ገጽታ እየፈገገ መጣ እናም ጥቂት ግር የተሰኘ መሰለ፡፡

‹‹ለምንድን ነው እንዲህ እንደምትወደኝ የምትናገረው? በእርግጥ ይህ እናንተ ክርስቲያኖች ልትጠብቁት የተገባ ትዕዛዝ እንደሆነ አውቃለሁ ሆኖም አንዳችሁም ልትጠብቁት የተገባ ትእዛዝ እንደሆነ አውቃለሁ ሆኖም አንዳችሁም ልትጠብቁት ትችላላችሁ ብዬ አላምንም ለዓመታት በእስር ቤት የተዘጋብኝን በረሃብ ያሰቃየኝንና በጅራፍ የገረፈኝን ሰው እንዴት ልወደው እችላለሁ? ሪቻርድ በፈገግታ መለስለት ‹‹ይህ ትእዛዝን የመጠበቅና ያለመጠበቅ ጉዳይ ሳይሆን የልብ መለወጥ ጉዳይ ነው፡፡ ክርስቲያን ስሆን ዳግም ተወለድሁ በዚህ ጊዜም በፍቅር የተሞላ ማንነትን ከመለኮት ተካልፈልሁ›› አለው፡፡ በመቀጠልም ለሁለት ሰዓታት ያህል ግሪኩ ከሪቻርድ ጋር ስለ ክርስትናና ስለ ኮምዩኒዝም በጥልቀት ተወያዩ፡፡ በዚህም ሳያበቃ ለሁለት ሳምንታት ያህል በየዕለቱ ግሪኩ ለጥያቄ ሪቻርድን እንደሚፈልገው በማስመሰል ወደ ቢሮው እያስጠራ ስለ ክርስቶስ ፍቅርና ይቅርታ ተገነዘበ ኃጢአቱንም ተናዞ ሕይወቱን ለጌታ ሰጠ፡፡

‹‹ከልጅነቴ በክህደት ስላደግሁ ክርስቲያን እሆናለሁ ብዬ ፈጽሜ አስቤ አላውቅም አለ ግሬኩ ከሪቻርድ ጋር ሲወያዩ ሆኖም ከተለወጠ በኋላ በጥንቃቄ ከሪቻርድ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀመረ፡፡ በኋላም ታማኝ ኮምዩሚስት ባለሥልጣን መስሎ በምሥጢር በተቻለው መጠን ሁሉ እስረኞችን ይረዳ ነበር፡፡ ብዙ ሳይቆይ ግን ይህ ድርጊቱ ስለተደረሰብት እርሱም እንደ ሌሎች ስለ ክርስቶስ እስረኛ ሆነ፡፡

ከስምንት ዓመታት ተኩል የሥቃይና የመከራ ጊዜ በኋላ ሪቻርድ ውምብራንድ በድንገት ከእስር ተለቀቀ የቆሸሸና ያደፈ ሸሚዙን እንዳጠለቀ የነተበውንና የተጨማደደውን ቁምጣ እንደታጠቀ ጠባቂ ወታደሮች እያዳፉና እየገፈተሩ የእስር ቤቱን በር ከፍተው አስወጡት፡፡ የሚስቱንና የልጁን በሕይወት መኖር ወይም አለመኖር በነጻነት ይኑሩ ወይም እስር ቤት ይሁን በመጠራጠር እያመነታ በቀጥታ መኖሪያ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ ቡካሬስት ከተማ አመራ፡፡ የመኖሪያ ቤቱን በር ከፍቶ ሲገባ ከቆመቱ ዘለግ ካለ ወጣት ጋር ተፋጠጡ፡፡ ወጣቱ የራሱ ልጅ ሚሃይ ነበር፡፡ አሁን ዕድሜው አስራ ስምንት ዓመት ሆኗል ሪቻርድ ለዘጠኝ ድፍን ዓመታት አላየውም ሚሃይ በድንገት ‹‹አባዬ!›› ብሎ ጮኾ ተጠመጠመበት ማዕድ ቤት የነበረችውም ባለቤቱ ሳቢና ድምጽ ሰምታ እየሮጠች ብትመጣ አባትና ልጅ ተቃቅፈዋል የሆነው ሁሉ ያስደንቃት ሳቢና ከእቅፋቸው ገብታ ተቀላቀለች፡፡‹‹ አንድ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር አለ›› አለ ሪቻርድ እንባውንና ሳቁን ለመቆጣጠር እየሞከረ፡፡‹‹ አሁን ከመከራ ወደ ደስታ ከሥቃይ ወደ ዕፎይታ እንደመጣሁ እንዳታስቡ ምክንያቱም በእስር ቤት ሆኜ በክርስቶስ ከማገኘው ደስታ ወደ ቤተሰቤ ወደሆነው የክርስቶስ ደስታ ነው የመጣሁት፡፡ ልዩነቱ የስፍራ ጉዳይ ነው እንጂ ደስታዬና ዕርካታዬ ፍስሃዬና ሰላሜ እስር ቤትም ሆኜ በክርስቶስ ነበር ቤተሰቤ ውስጥም በክርስቶስ ነው›› ‹‹አባዬ›› አለ ሚሃይ‹‹ብዙ ነገሮች በሕይወትህ አልፏል አንተም በብዙ ተፈትነሃል ነገር ግን በዚህ መከራና ሥቃይ ውስጥ የተማርከው ምን እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ›› ሪቻርድ ቀጫጭን እጆቹንና ክንዶቹን በልጁ ላይ በማሳረፍ እንዲህ አለ‹‹አራት ነገሮች ሁልጊዜም በልቤና በአእምሮዬ ይኖራሉ፣ በመጀመሪያ እግዚአብሔር በሕያውነቱ አለ የሚለው ነው፣ ሁለተኛው ክርስቶስ አዳኛችን ነው፣ ሦስተኛው ደግሞ የዘላለም ሕይወት አለ የሚለው ሲሆን አራተኛውና የመጨረሻው ፍቅር ከሁሉ የተሻለ ትክክለኛ መንገድ ነው የሚል ነው›› ሚሃይ እንደገባ ለማስታወቅ በአንክሮ ጭንቅላቱን ነቀነቀ በቅርቡም የቤተክርስቲያን መጋቢ ሊሆን እንደወሰነ ለአባቱ ለሪቻርድ አስታወቀው፡፡

የኮሚዩኒስት ባለሥልጣኖች ሪቻርድን በማናቸውም መንፈሳዊ ተግባራት ላይ እንዳይሳተፍ ከለከሉት፡፡ ነገር ግን እርሱ ከሚስቱ ከሳቢና ጋር በመሆን በሕቡዕ የምትንቀሳቀሰውን ቤተክርስቲያን ከመደገፍ አልቦዘኑም ፡፡ ሪቻርድም በምስጢር በተደራጁት የክርስቲያኖች ኅብረት ላይ በመስበክ በቤት ፕሮግራሞች በመምከርና በማጽናናት አገልግሎቱን ቀጠለ፡፡ የአምልኮ ነጻነትም ፈጽሞ ስላልነበር የተለያዩ ክርስቲያኖችን ልደት እንደሚያስከብሩን ሆነው ጌታን ያመልኩ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ድርጊት ብዙ ገፍቶ እንደማይሄድ ሪቻርድ ያስብ ነበር፡፡ ስለሆነም በብዙን ጊዜ ሲጸልይ እንዲህ ይል ነበር ‹‹ጌታ ሆይ አሁን እንኳ በዚያ እስር ቤት ላገልግላቸው የሚገቡ ሰዎች ካሉ ደግመህብትልከኝ ፈቅጄ ልሄድ ዝግጁ ነኝ››

ከሁለት የነጻነት ዓመታት በኋላ የምስጢር ፖሊሶች በውድቅት ሌሊት የውምብራንድን ቤት ሰብረው በመግባት ይዘውት ለሌላ አምስት የሥቃይ ዓመታት ዳረጉት፡፡ ከዚያ እንደተለቀቀ ግን እንደተለመደው በቀጥታ ያመራው በሕቡዕ ወደ ምትንቀሳቀሰው ቤተክርስቲያን ነበር፡፡ በነጻው ዓለም የሚገኙት ቅዱሳን ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ መጽሐፍትና ገንዘብ በታላቅ መከራ ውስጥ ላሉት የሮማውያን ክርስቲያኖች በመላክ ድጋፍና እርዳታ ያደርጉ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ውምብራድ በሩማኒያ መቆየት ቢፈልግም በሕቡዕ የምትንቃሳቀሰው ቤተክርስትያን መሪዎች ግን አገሪቱን ለቆ እንዲወጣና የተሰደዱት ክርስቲያኖች ድምጽ በመሆን ለቀረው ነጻ ዓለም የሩማንያን ክርስቲያኖች ተጋድሎ እንዲያሰማ ግድ አሉት፡፡ ሁለት የክርስቲያን ኅብረቶች አሥር ሺህ የአሜሪካን ዶላር በመክፈል ሪቻርድ ከቤተሰቡ ጋር የሚወጣበትን መንገድ አመቻቹ፡፡ ከመውጣቱ በፊትም የምጢር ፖሊሶች ወደ ሪቻርድ በመምጣት እንዲህ አሉት ‹‹ወደ ምዕራባውያን ሄደህ ስለ ክርስቶስ የፈለግኸውን ያህል መስበክ ትችላለህ፤ ነገር ግን በእኛ ላይ አንዳች ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ ይህን ካደረግህ ግን የእኛ ወኪሎች ያፍኑኩሃል ወይ ይገድሉሃል›› ሪቻርድም ከመሄዱ በፊት መጀመሪያ እርሱ እንዲይዝ እንዲታሰርና እንዲሰቃይ ትእዛዝ በሰጠው ኮሚኒስት ባለሥልጣን መቃብር ሥር አበባ አኖረ፡፡ ሪቻርድ እንዲህ ይላል ‹‹ የኮምዩኒስት ስርዓትን አጥብቄ እጠላላሁ ሰዎቹን ግን እወዳቸዋለሁ ኮምዩኒስቶች ክርስትያኖችን መግደል ይችሉ ይሆናልን ሆኖም ለአሳዳጃቻቸውና ለገዳዮቻቸው ያላቸውን ፍቅር ግን ሊገድሉት ፈጽሞ አይችሉም››

ውምብራንድና ሳቢና ወደ አሜሪካን ከመጡ በኋላም ‹‹የሰማዕታት ድምጽ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ቅዱስ በመላክ በማጽናናትና በማበረታታት ይደግፍ ነበር፡፡ በታኅሳስ 1989 የኮምዩኒስት አገዛዝ በሩማኒያ ከወደቀ በኋላ ውምብራንድና ሳቢ ወደ እናት ምድራቸው በመመለስ የክርስቶስን ወንጌል በብዛት ለተመሠረቱት አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀር ለመስበክ በር ተከፈተላቸው መጽሐፍ ቤቶችን በማቋቋምና መንፈሳዊ መጽሐፍትን በማቋቋምና መንፈሳዊ መጽሐፍትን በማተም ያሰራጩ ጀመር፡፡ አዲሱ መንግስትም እነ ሪቻርድ የታሰሩበትን እስር ቤት መጽሐፍና ሌሎችንም ዕቃዎች ማስቀመጫ መጋዘን አድርጎ ሰጣቸው ጌታም ስሙን ሊያከብር ይህን እንዳደረገ ላቸው፡፡

ውምብራንድ ሳቢና የኢየሱስ ክርስቶስን ይቅርታ ዐወጁ፡፡ በሩማኒያ ላሉትም ቅዱሳን ኮሚኒስቶች ይቅር እንዲሉ ያበረታቱዋቸው ነበር፡፡ ለሃያ ዓመታት ያህልም መልእክቱ ‹‹አሳዳጆችሁን ውደዱ፤ ለነፍሳቸውም መዳን ጸልዩ ለክርስቶስም ማርኳቸው›› የሚል ነበር፡፡

ቤሪያ ቁጥር 2
1996

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox