ከሶስት አመት በፊት፣ የነበሩኝ አብዛኛዎቹ ትንቢታዊ መልዕክቶች ተፈጽመው አልፈዋል። የእግዚአብሔር መንግስት ይስፋፋና የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በክብር ይልቅ ዘንድ፣ ጌታ ተጨማሪ የትንቢት መልዕክቶችን በህይወቴ እንዲያመጣ በጸሎት እጠይቀው ነበር።
በቅዱስ ቃሉ እንደተጻፈው፤ “ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና” (1 ቆሮ 13:9)። ትንቢት ድርሻ ነው። የመጀመሪያው ድርሻ የትንቢት ተናጋሪ ሰው፣ የመልዕክትን ቃል ማድረስ ሲሆን፤ ሁለተኛው ድርሻ ደግሞ የእኛ በጸሎት፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመተባበር፣ የትንቢት ቃሉን ትርጉም መረዳት የሚያስችለንን ጸጋ በመቀበል በነፃነት እንዲገለጥ መፍቀድ ነው።
ለምሳሌ ባለጠጋ እንደምንሆን የትንቢት ቃልን ብንቀበል፣ በዝምታ ቁጭ ብለን 1ሚልየን ብር ከሰማይ እንዲወርድ ወይንም ደግሞ የሆነ ሰው ትልቅ መጠን ያለው ቼክ እንዲጽፍልን መጠበቅ የለብንም። ይልቁንስ መንፈስ ቅዱስ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን፣ የቢዝነስ ስልትንና አዳዲስ ግኝቶችን እንዲያሳየን እርሱን በጸሎት መቅረብና መጠየቅ ይኖርብናል። ብዙውን ጊዜ ባለጸጎች የምንሆነው ጌታ እንዲኖረን በፈቀደው ሃብት ለመባረክ የሚያስችለንን መንገድ እንዲያሳየን እርሱን በመፈለግ ላይ ሳለን ነው።
የትንቢት ቃሉ መወራት ሲጀምር ጦርነት ይነሳል። ቃሉ በመንፈሳዊው አለም እንደተለቀቀ፣ ተቃዋሚው እና አበሮቹ በህይወታቹ በተነገረው ትንቢት ላይ አመጻን ለማወጅ መሞካራቸው አይቀሬ ነው። ስለዚህ እኛም በተቃርኖ፣ ጦርነትን በማወጅ መቃወምና የሚመጣውን መልዕክት ለማጥቃት የሚንቀሳቀሰውን ሁሉ በስልጣን መቆጣጠር ይገባናል። ቃሉንም በኃይል መቀበል አለብን! “መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል” (ማቴ 11:12)። በዘመናዊው የኢንግልዘኛ ትጉርም “መንግሥተ ሰማያት በኃይል ተስፋፍታለች፥ በኃይልም ብርቱዎች ይናጠቋታል” ይላል። እኛ ታድያ ብርቱዎች በመሆን ያን የተመኘነውን ነገር በኃይል፣ በጸሎት፣ በማወጅና በኢየሱስ ክርስቶስ ባገኘነው ስልጣን መቀበል ይኖርብናል።
ኢየሱስ እና አብ በነገሮች ላይ ስልጣንን በመውሰድ ለመፍጠርና ህያው ለማድረግ ተናገሩ (Speak Out, የሚለውን መፅሐፌን ተመልከቱ)። ድምፃችንን በማሰማት መፀለይና ቃልን በማውጣት መናገር አለብን። ኢየሱስ ሥልጣን ሰጥቶናል፣ እናም ድምጻችንን በማሰማት በመጸለይ እና የትንቢት ቃላችንን ወደ መገለጥ እንዲመጡ በመናገር ይህንን ስልጣን መቀበል ያስፈልገናል። ያለ ምንም ተግባር በዝምታ ተቀምጠን ነገሮች በታዕምር እንዲገለጡና እንዲከሰቱ አንጠብቅ፤ ይሁን እንጂ ይህ ሊሆን እንደሚችል ግን አምናለው።
የትንቢት ቃላቶቻቹን መግለጥ
እኔ የትንቢት ቃላቶቼን ከፊቴ በመጠበቅ እና በላያቸውም ተፈላጊነትን በማድረግ በተገቢ ሁኔታ ገልጫለው።
በክርስቶስ ያላቹን ሥልጣን ማወቅ እና ድምፅን በመስማት መጸለይ የትንቢት ቃላቶቻችሁን ለመግለጥ በጣም አስፈላጊ ናቸው። በ ኤ.ኤል. ጊል የተጻፈው Destined for Dominion መጽሐፍ ስለሥልጣን የሚያብራራ ጥሩ መጽሐፍ ነው። መንፈስ ቅዱስ፣ ትንቢታዊ ቃላትን በእኛ ላይ እንዳይፈጸሙ ሲል ሰዎችን አይጠቀምም። እሱ ሐሰተኛ ተስፋን ሊሰጠን ፍቃዱ አይደለም። ተስፋ እንድንቆርጥም አይፈልግም። ቃላቱ እስኪገለጡ ድረስ በትዕግስት እና በቁርጠኝነት እንድንቆይ ሲል እነዚያን ቃላት ሰጠን። ብዙ የትንቢት ቃላት ያለምንም ስራ ዝም ብለው ተቀምጠዋል ብዬ አምናለሁ፣ ምክንያቱ ደግሞ የክርስቶስ አካል ሰንጥቀው ወደ ፊት እንዲመጡ መጥራት ላይ ስለ ደከመ ነው። እኛ ትንቢታዊ ቃላችንን በማንጸባረቅ መጫወት የሚገባን ድርሻ አለን። በአለም የእናንተ ትንቢቶች እንዲገልጡ ይጠበቃል ለዚህም ጌታ ወደ ፊት እንድትገሰግሱ ጥሪ ያደርጋል። ይህችን ዓለም ለኢየሱስ ክርስቶስ ለማብቃት፣ ሁላችንም ትንቢቶቻችን በሙሉ በአንድ ላይ ተገልጠው ማየት እንፈልጋለን። ተነሱ! ንቁ! እነዚህን ቃላት አውጡ!
Copyright Hiyawkal © 2025
Leave a Reply