ዓይኔ ቢታወርም

ብርሃን መፅሔት ቁጥር 32 :

የትውልድ ሥፍራዬ ክልል 11 ከፊቾ ዞን ኮዳ ቀበሌ የሚባለው ምነደር ነው በሕጻነቴ ዓይኔን ሕመም ስሰቃይ ቆይቼ በ7ዓመቴ ሁለቱም ዓይኖቼ አብጠው ፈነዱና ፈሰሰ ወላጆቼም ለሚያመልኩት ቃልቻ (ውቃቢ) ‹‹ዳማሰንዶ ለሚባለው ብዙ መስዕዋት አቀረቡ በሕክምናም ብዙ ደከሙ ገንዘባቸው ባከነ ተስፋም ቆረጡ ዕድሜዬ ለአቅመ አዳም እስከሚደርስ ድረስ በዚህ ዓለም ርኩሰት ተሞልቼ መጠጥ በመጠጣት በመዝፈን ኖርኩ በአካባቢያችን ባህል መሠረት ትዳር እንድመሰርት ተገፋፋሁ ትዳርም መሠረትኩ ወደጌታ እንድመጣ ምክኒያት የሆነኝ ነገር ተፈፀመ ቤተሰቦቼ ሚስትህ ከአንተጋር እንድትኖር ከፈለክ ከቃልቻ ዘንድ ገንዘብ አምጥተህ ልብስ ገዝተህ ካላለበስካት ትሄድብሃለች በቃልቻ ገንዘብ የተገዛ ልብስ ለብሳ መሄድ ስለማትችል ካንተ ጋር ትቀመጣለች አሉኝ ከወላጅ እናቴ ጋር ወደ ባለውቃቢው ዘንድ ሄድን ከሰውዬው እግር ሥር ሰግደን ልመናችንን አቀረብን እርሱም አምላካችሁ ወርዶ ካልፈቀደ አሁን የምሰጣችሁ ገንዘብ በእጄ የለም እርሱ ሲፈቅድ ነው አሁን ግን ወደመጣችሁበት ሂዱ ብሎን ባዶአችንን ሸኘንብዙ መንገድ ተጉዘን ስለደከምን እናቴ የምታውቀው ሰው ቤት ለምነን ልናድር ወሰንን ይህ ሰው የእግዚአብሔር ሰው እንደሆነ እናቴም አታውቅም ማታ እራት ከመብላታችን በፊት እዚያው ቤት ውስጥ አንድ ወንጌላዊ የቤተሰብ ጸሎት አስጀመረ የእግዚአብሔርን ቃል አስተማረ ከዚያም መዝሙር ዘመሩ በዚያን ጊዜ ውስጤ ተሰበረ እንዴት አድርጌ ወደዚህ እምነት እንደምገባ በልቤ አሰብኩና ፈራሁ ለእናቴም ይህን ሳጫወታት ልጄ ቃልቻው ይህንን ከሰማ ይገድልሃልና ይህንን ሃሳብ ከልብህ አውጣ ብላ ተቆጣችኝ ከእራት በኋላ የቤቱን ባለቤት ከየት እንደመጣን ጠየቀን እኛም የመጣንበትንና ምክኒያቱን ነገርነው የእግዚአብሔርን ቃል ነገረንና ዝም ብለን አደርን ወደ ቤታችን ሄድን፡፡

እኔም እቤት እንደደረስኩ እሁድ ዕለት ጠዋት በልቤ ወሰንኩኝና አንድ ሕጻን ልጅ መርቶኝ በቀበሌያችን ውስጥ ወዳለው የቃል ሕይወት ቤ/ክ ጌታን እንደግል አዳኜ አድርጌ ተቀበልኩ ከዚህ የተነሳ ወዲያውኑ ከቤተሰቦቼ ስደት ደረሰብኝ ወንድሜ ማንም እቤታችን አይጸልይም አለኝ የምኖረው ከእናቴ ጋር ስለነበር አንተ ራስህ ይህን የቃልቻ ዕቃ ከእናቴ ቤት አውጣ ብዬ በቤት ውስጥ ሲመለክባቸው የነበሩትን ዕቃዎች በሙሉ አውጥቼ ወደ ውጭ ወረወርኩ ከዚህ የተነሳ ታላቅ ወነድሜ ቦታው የእኔ ስለሆነ ከእኛ ጋር መኖር አትችልም ብሎ ከባለቤቱ ጋር ከቤቱ አስወጣኝ እኔም ባለቤቴን ይዤ ሽኮ ወደሚባል ወረዳ ከቤተሰብ ርቄ ለመኖር ወሰንኩ እዚያ እንደደረስኩ ቤት ተሠራልኝ የሚያውቁኝ አንዳንዶች አማኝ መሁኔን ሲያውቁ ድሮ ጥሩ ዘፋኝ ነበረ አሁን ተበላሽቶ በሰልባጅ ተለውጦ መጣ ብለው ጠሉኝ እኔም እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ ዝም ብዬ መኖር ቀጠልኩ፡፡ በነበርኩበት አካባቢ ቤ/ክ ስለሌለ መንፈሳዊ ሕይወቴ እየደከመ ሲመጣ ጌታ ቤ/ክ ያለበትን ቦታ እንዲመራኝ እጸልይ ጀመር አንድ ጓደኛዬ እየመራኝ ባዥቃ ከሚባል መንደር ወደ ሸኮ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ መመላለስ ጀመርን ሁልጌዜ እሁድ እሁድ ቤ/ክ ስለምንሄድ በአካባቢው ያሉ ሰዎች የእኛን መመላለስ ጀመርን ሁልጌዜ እሑድ እሑድ ቤ/ክ ስለምንሄድ በአካባቢው ያሉ ሰዎች የእኛን መመላለሰ ጠልተውኝ በባለቤቴ ላይ ስደት አነሱባት ምድነው እውር ባል እየጎተትሽ የምትመላለሸው እያሉ አስጨነቋት እሷም ስድቡን መቋቋም ስላልቻለች ተነስታ ጠፋች አንድቀን ባለቤቴ ግዝሬት በሚባል ቦታ አለች ሲባል ሰምቼ አመጣታለሁ ብ ሳስብ ወድያውኑ እንደሄደች ባል አግብታለች ተባለ፡፡

አንድ ቀን ሌሊት ተንበርክኬ እንዲህ ብዬ ፀለይኩ ‹‹ጌታ ሆይ ለምን ክንድህ እዚህ ወረዳውስጥ አይሰራም ብዬ ፀለይኩኝ አንድ ቀን እህቴ ወንድሙ ነእኛ አትዘንብን እኛ ጋ እየመጣህ ቡና ጠጣ አለችኝ እኔ ፀልዬ የማልጠጣበት ቤት እልሄድም ስላት እኛ እኮ እግዚአብሄርን እንጠራለን ፀልይና ጠጣ ነገር ግን እናንት ኢየሱስ የመትሉት አይገባንም አለኝ እኔም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ልገራችሁ እርሱ ስለ እኛ ኃጥያት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቷል እናንተ ይህንን የመዳን መንገድ ማወቅ አለባችሁ ብዬ መሰከርኩላቸው ልባቸው ተነካ እነርሱም እንዲህ አሉኝ እስቲ የእህትህን ልጅ ታማ የምትሰቀየውን ወስደህ ፀልየህ አድናት አሉኝ ልጅቷም በጣም ታማ ሰውነትዋ በሙሉ በቁስል ተመትቶ ነበርና ከፈቀዳችሁልኝ እሷም ካመነች እግዚአብሔር ያድናታል ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም አልኩ እህቴም ልጀዋን ለማዳን ብዙ ባክና ስለነበር ብዙ ቦታ እየዞርኩ ከምትሞት አንድ እግዚአብሔርን አምና ብትሞት ይሻላል ብላ ፈቀደች እኔም ልጅቷን አባትሽንአስፈቅደሽ ነይና ወደ ቤተ/ክ እንሂድ ልኳት አባቷን ስትጠይቅ ጴንጤ ጋ ቀርቶ ገደልም ግቢ አላትና ወደኔ መጣች እኔም ከእግዙአብሔር ቃል በልቤ ያለውን ሃሳብ አጠንክሬ ነገርኳትና አደፋፈርኳት ወደ ቤ/ክ አብረን ሄድን ቤ/ክ ስንደርስ ተዘግቶ ስለነበር አንኳኳን ከአገልጋዮቹ አንዱ መጣና ሲያያት ለማኝ መስለናቸው ተጠራጠሩን ለምን እንደመጣን ጠየቁን እኔ ይህችን ልጅ ጌታን እንድትቀበል መስክሬላት አምጥቼ ነው ጸልዩላት አልኩት ለበሽታዋም ጸለዩላት ጌታም በድንቅ ሁኔታ ፈወሳት እኔም ለትንሽ ጊዜ ወገኖች ጋር ተቀምጣ ሽማግሌውች እንዲጸልዩላትና መጽሐፍ ቅዱስ እንዲስተምሩዋት ነግሬያቸው ወደ ወርጎ ተመለስኩ በሣምንቱ የወሰድኳት ልጅ ድና ሰውነቷ በሙሉ ተለውጦ መጣች ከእሷ ጋር ወደ ሸኮ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ስንመለስ እቤት ቁጭ ብዬ የእህቴን ልጆችና የመንደር ልጆች አንድ ላይ ሰብስቤ መዝሙር እዘምርላቸው ነበር አንድ ቀን አማቼ እንዲህ አለኝ ባለቤቴ ብዙ ጊዜ እየታመመች በየቃልቻው በየጠንቋዩ ቤት ዞሬ ደክሜ ተስፋ ቆርጫለሁ እህትህን ከጭንቋ ለማትረፍ ያልሄድኩበት ሥፍራ የለም ሃኪም ቤትም ወስጃት ምንም መፍትሄ አጥቻለሁ አለኝ እኔም እንግዲህ መፍትሄው ጌታን መቀበል ነው አልኩት እሱም በሃሳቤ ተስማማ መጽሐፍ ማንበብ ስለሚችል መጽሐፍ ቅዱስ አምጥቼ ለአማቼ ሰጠሁት ማንበብ ጀመረ የጌታንም ነገር እየተረዳ መጣ በዚህ መሐል እናቱ በህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ለቅሶ የሚመጡ ዘመዶቹ ቃልቻ አምላኪዎች ስለነበሩ እምነቱን ለማስቀየር ሲሞክሩ እኔም ማታ በጌ ፊት ተንበርክኬ ክፉ መንፈሱን አጥብቄ በቃወም ሃሳቡን እንዳይቀይር ጸለይኩ እግዚአብሔር ም ጸሎቴን ሰማ ከለቅሶ በኋላ ከባለቤቱ ጋር ወደ ቤ/ክ ለሄድ ፈቀደ እሷም ጌታን ተቀበለች በሳምንቱ እርሱም ጌታን ተቀበለ በቤት ውስጥ አራት እኔም እያስተማርኳቸው ለተወሰነ ወራት ስንመላለስ የቤ/ክ ሽማግሌዎች እቤታቸው የጸሎት ፕሮግራም እናደርጋለን አሉ መጥተውም በቤት ውስጥ ላሉ ልጆች በሙሉ ጸለዩ ቤተሰቡ በሙሉ በጌታ አመኑ እኔም ማንበብና መጻፍ ባችልም ጌታ ካስተማረኝ ካለ በልቤ ያለውን እያስታማርኩ እየመከርኩ እየጸለይን መኖር ጀመርን አገልጋዮች መጥተው በተጨማሪ ወንጌልን ሰበኩ በአካባቢ ያሉ ሰዎችም ጌታን መቀበል ሲጀምሩ በመንደራችን ያሉ ባለውቃቢ ባላባቶች ተቃውመው ስደት አስነሱብን ጌታን የተቀበሉትን ሰዎች እንዲህ አሉአቸው ‹‹እናነተ ይህን እውር የሚመራው አዲስ ሐይማኖት እንዴት ዓይን እያላችሁ ትከተላላችሁ በጣም ተሳስታችኋል ወንድሙ የሚበላውን ሰው ደግሞ ከወንዝ ማዶ ወስደን እንወረውረዋለን ከዛ በኋላ እምነታችሁ ይቀራል እያሉ ዛቱብን ወገኖችን አስፈራሩ የአማቼም ዘመዶች ደግሞ በወስጥ ተቃውሞ አቸውንአሰሙ ጌታ ግን ሞገስ ሰጠን በእኛ ላይ የተነሳውን ስደትና ተቃውሞ ጌታ በታላቅ ኣመታት መታ ነፍሳትም ዕለት ዕለት ወደ ጉባዔያችን ተጨምሩ እኔም የወጡትን እያስተማርኩ ዛሬ በዥተን ከ200 በላይ ሆነን ጸሎት ቤት ሠርተን ጌታን እናመልካለን፡፡

አሁን በኅብረታችን ጌታን የማገለግለው በምስክርነት በምክር በፀሎት ሲሆን የመማር ዕድል ጌታ ቢሰጠኝ ለወደፊት የጌታን ቃል አንብቤ በእግዚአብሔር ቃል ለማገልገል ትልቅ ምኞት አለኝ እግዚአብሔር አንስቶኝ የመንግስቱ ወራሽአድርጎኛል ስለዚህ ከፍተኛ ደስታ ሰላም ትልቅ የአገልግሎት ፍቅር አለኝ ይህ ሥጋዊ ዓይኔ በመታወሩ ምንም ሀዘን አይሰማኝም ምክኒያቱም እኔ ዓይን ቢኖረኝ በዓለም በጣም አስቸጋሪ እንደምሆን ይሰማኛል ይህንን ሕይወት የማገኝም አይመስለኝም ሥጋዊ ዓይን እያላቸው የእግዚአብሔርን መንገድ ለማያውቁና የልብ ዓይናቸው ያልበራላቸው ሰዎች ጌታን አምነው ያለመዳናቸው በጣም ያሳዝነኛል እኔ ዓይን ባይኖረኝም ጌታ ከእኔ ጋር ስለሆ ያለምንም ጭንቀት እኖራለሁ ሁልጊዜ ደስ ይለኛል ጊዜዬን የማሳልፈው በከንቱ አይደለም ሁልጊዜ እጸልያለሁ ደግሞም ስለጌታ እመሰክራለሁና ያለኝን የጸሎት ጥያቄ የዓይነ ሥውራን ት/ቤት ገብቼ ተምሬ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ እንድችል ነው ጌታ ይባርካችሁ፡፡ አሜን

ከወንድሙ ገብሬ_ብርሃን መፅሔት, ቁጥር 32

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox