እውነተኛ ተሃድሶ በሚያስፍልጋችሁ ሰዓት መረዳት ያለባችሁ 5 እውነታዎች

ዶ/ር ኬሮል ፒተርስ-ታንክስሊ :

ቃልኪዳንን በማፈረስ የሚጠፋ ጋብቻ፡፡ የሚመራው ማህበረሰብ የጣለበትን እምነት የሚከዳ የህዝብ መሪ፡፡ ወሲባዊ ወይም የገንዘብ እንዝላልነት ውስጥ የተያዘ ፓስተር፡፡ ተሃድሶ የሚቻል ነውን? ተሃድሶ ምን ይመስላል? ወደነበረበት ለመመለስ ምን ያስፈልጋል? 

የወንጌል መልእክት የኢየሱስ አጠቃላይ አገልግሎት ተሃድሶ የሚቻል እንደሆነ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ እርሱ የመጣው ማንንም ዞር አላደረገም፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ኢየሱስ መገኘት የገባ ማንም ከጽድቅ ውጭ ሌላ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት አለው ብሎ አያስብም፡፡

በምንዝር እንደ ተያዘችው ሴት ታሪክ (ዮሐ 8፡2-8)፤በቤተሳይዳ በውኃ ገንዳ የነበረው የሽባ ሰው ታሪክ   (ዮሐ 5፡2-14) እና ጴጥሮስ ኢየሱስን ከከዳው በኋላ ያለው ታሪክ (ዮሐ21፡15-19) ኢየሱስ ከኃጢአተኞች ፈጽሞ እንደማይሸሽ ያሳየናል፡፡ በእውነት እስከመጨረሻው እንዲለወጡ እድል ሰጣቸው፡፡  

ተሃድሶ እንደሚያስፈልጋቹ የሚሰማቹ ከሆን የሚቻል መሆኑን እወቁ! የሆነ ነገር አጋጥሞአቹ ወይም ራሳቹ ነገሮችን አመሰቃቅላቹ አሊያም ሁለቱም ከሆነ ኢየሱስ ለወደፊቱ ያዘጋጃል፡፡ በቅርቡ ሰዎች ተሃድሶ በሚያስፈልጋቸው ተሃድሶን በሚጠይቁበት በተሃድሶ ሂደት በተበሳጩበት በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ነበርኩ፡፡ የዚያ ብስጭት አንዱ ክፍል ተሃድሶ ማለት ነገሮች ተመልሰው ወደነበሩበት ይመለሳሉ ማለት ነዉ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ተሃድሶ ማለት ግን ይህ ማለት አይደለም፡፡

እና ነገሮች ልክ እንደቀድሞው እንዲሆኑ ትፈልጋላቹ? የመጋለጥ ህመም እና ምናልባትም የሚሰማቹ እፍረት በጣም የሚያሳቅቅ ቢሆንም ወደዚህ ችግር ውስጥ የገባቹት “ነገሮች በነበሩበት ሁኔታ” ነው፡፡ ተሃድሶ ማለት ለውጥ ማለት ነው፡፡ 

ስለ ተሃድሶ ይበልጥ በትክክል ስናስብ በደንብ “ወደ ኋላ” ተመልሰን አናይም፡፡ የተበላሸን ዓይነተኛ መኪና መጠገን ቀለም መቀባት አይደለም ነገር ግን መጀመሪያ ወደተፈጠረበት መንገድ መመለስ ማለት ነው፡፡ አሁን የተሰማቹ እፍረት ሳይሰማቹ በፊት እንደነበረው እንድትመለሱ ሳይሆን ነገር ግን እሱ ወደ ፈጠራችሁ መንገድ መመለስ ይህን ነው እግዚአብሔር የሚፈልግላቹ፤ውጫቹ ብቻ የሚያብረቀርቅ ሳይሆን ነገር ግን ውስጣቹም አዲስ እና የከበር እንዲሆን፡፡ ከወንጌል አውታር እውነተኛው ተሃድሶ ምን እንደሚመስል እነሆ፡

  1. የአእምሮዎ (አስተሳሰብ) ለውጥ

ንስሐ ማለት ይህ ነው፡፡ ጠላታችን የውሸት ጌታ ነው፡፡ አትያዙም በሚል ሀሳብ ውስጥ ይጠምዳቹሃል፡፡ “ያን ያህል እኮ መጥፎ አይደለም” እና በሞከራቹበት ቅጽበት በላያቹ ላይ እፍረትን ይከምርባቹሃል፡፡

ንስሐ መግባት ማለት ነገሩ ያን ያህል መጥፎ እንደሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምታቹሃ ማለት ነው፡፡ ተቀባይነት ያለው የእግዚአብሔር የጽድቅ መስፈርት ብቻ ነው፡፡ እና ነገሮች ተበላሽተዋል፡፡ ኩራታቹ፣ስግብግብነታቹ፣ምኞታቹ፣በሰዎች ደስ መሰኝታቹ፣ፍርሃታቹ ወይም አንተንም ሆነ ሌሎችን ክፉኛ የጎዳቹ ነገር፡፡ እና ከአንድ ድርጊት ወይም ከተከታታይ ድርጊቶች በላይ የናንተ ተፈጥሮ ጉድለት አለው፡፡ ነገሮችን የምታዩበት መንገድ ትክክል አይደለም፡፡ እናንተ በጸባያቹ ብቻ ሳይሆን በእውትም በባህሪያቹም ኃጢአተኛ ናቹ፡፡ በራሳቹ ምንም የተለየ ነገር ለማድረግ ሙሉ በሙሉ አቅመቢስ ናቹ፡፡ በባህሪ የተለየ መሆን ብቻ ሳይሆን እናንተም መለወጥ እንደሚያስፈልጋቹ ወደ መቀበል ትመጣላቹ፡፡ እናም በዚህ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሃሳብ እና ጸጋ እንዲሁም የሌሎችንም አገልግሎት ለመቀበል ፈቃደኛ ትሆናላችሁ፡፡

2. የልብ (አመለካከት) ለውጥ

ከአዲሱ ልብ የበለጠ ታላቅ ተስፋ የለም፡፡ “አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ፡፡ መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ፡፡” (ትን ሕዝ 36፡26-27)

ስለእናንተ አላውቅም እኔ ግን ኢየሱስ ባገኘኝ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በየትኛውም ጉዳይ ፣ በስብራትም ሆነ በሱስ ትግል ውስጥ ለዘላለም መኖር አልፈልግም፡፡ ያ ስቃይ ይሆን ነበር! ይቅርታ ካለፈ ነገር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ተሃድሶ ወደ ፊት ከሚሆን ነገር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ተሃድሶ ማለት ከመጋለጣቹ በፊት ወደነበራቹበት መንገድ መመለስ ማለት ሳይሆን እግዚአብሔር ወደ ፈጠራችሁ መንገድ መመለስ ማለት ነው፡፡

አዲስ ልብ የከበረ ነገር ነው፡፡ በድህነት ቅፅበት የሚመጣ አዲስ ልብ አለ፡፡ ነገር ግን አዲሱ ልብ እያደገ እንደ ክርስቶስ ልብ ለመሆን የሚያደርገው ሂደትም አለ፡፡ በተለየ ሁኔታ ለመስራት ውስጣቹም የተለየ መሆን አለበት፡፡ ኢየሱስ የሚፈልገው ነገር እናንተን ከውስጥ ወደ ውጭ መቀየር ነው፡፡ ያ ጊዜ ይወስዳል፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ ብዙ መሆን ይጠይቃል፡፡ ከሌሎች ላይ ግብረመልስን፣በሚያነቃቃ ሚዲያ መረስረስን፣የድሮ ቁስላችንን መክፈት እና መፈወስን እና ተጨማሪ ነገሮችንም ይጠይቃል፡፡ 

3. የጸባይ ለውጥ

አእምሯቹ እና ልባቹ ሲቀየ ማስረጃው በጸባያቹ ውስጥ ይታያል፡፡ በእግዚአብሔር መንገድ መመላለስ የዕለት ተዕለት ምርጫ ሆኖ የሚቆይ ቢሆንም ኃጢአትን ላለማድረግ ጥርሶቹን መንከስ ማለት ግን አይደለም፡፡ ሌላ ሰው ስኬታማ ሲሆን በእውነት ደስተኛ ትሆናላቹ፡፡ ጥበቃ በማይደረግባቹ ሰአት የወሲብ ሐሳባቹ የትዳር ጓደኛቹን ብቻ ያካትታል፡፡ ውሳኔ በሚያጋጥማቹ ጊዜ የመጀመሪያ ምላሻቹ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ነው፡፡

ይህ ፍጽም ከመሆን ጋር ወይም ከሕጋዊነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እንደተናገረው “ከእንግዲህ በኋላ ኃጢአት አለማድረግ ” ነው፡፡ ከውጭ እየተመለከተ ያለ አንድ ሰው ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ እናንተን ይገልጻቹሃል፡፡ እናንተንም ምንም የምደብቁት ነገር እንደሌላቹ “እንደ የፀሐይ ብርሃን ግልጽ” ናቹ፡፡በዚህ የተሃድሶ ደረጃ ውስጥ በራሳቹ ላይ አንዳንድ እውነተኛ ልዩነቶችን ታስተውላላቹ ሌሎች ግን ሊያስተውሉት  ወይም ላያስተውሉት ይችላሉ፡፡ እናንተ ያው እንዳልሆናቹ ታቃላቹ ሌሎች የሚናገሩትም ሆነ የሚያደርጉት ምንም ይሁን ምን ከእግዚአብሄር ጋር ወደፊት እየተጓዛቹ ነው፡፡

4. የባህሪ ለውጥ

ከጊዜ ጋር, ሌሎች ሌዩ መሆናቹን ለማየት ይገደዳሉ፡፡ ይህ ስለ ይቅርታ አይደለም፡፡ ዶ/ር ሄንሪ ክላውድ እንደገለጹት ይቅርባይነት ካለፈ ነገር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አሁን እያወራን ያለነው በእውነትም እምነት የሚጣልበት ስለመሆን ነው ይህም ወደፊት ነገሮች የተለዩ እንደሚሆኑ ማረጋገጫ ያሳያል፡፡ 

ከፀጋ የወደቁ እነዚ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ሌሎችን “ይቅርታ” በሚሉበት ቅጽበት ሌሎች በተለየ እይታ እንዲመለከቷቸው ይፈልጋሉ፡፡ እዚያ ካልጀመራቹ በስተቀር ምንም ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን ሌሎች በናንተ ላይ እምነት መጣል ሚችሉት በብዙ ጊዜ ሂደት ውስጥ ባህሪያቹ የተለየ መሆኑን በማስረጃ ስታሳዩ ነው፡፡ 

ሌሎች እናንተን የሚያዯበትን እይታ መቆጣጠር አትችሉም፡፡ እናንተን ማየት የሚመርጥ ማንኛውም ሰው በእውነት እናንተ ልዩ መሆናቹን ማየት እንዲችል በሚያደርግ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ መኖር ትችላላቹ፡፡ ያህ ብዙ ሰዎች ከሚገምቱት በላይ ብዙ ጊዜ ይወስዳል፡፡ እና የትዳር አጋራቹ እንደገና እናንተን ሊያምኗቹ ወይም ላያምኗቹ ይችላሉ፡፡ የምትመሯቸው ሰዎች ምናልባትም እንደገና እናንተን ሊያምኗቹ ወይም ላያምኗቹ ይችላሉ፡፡ ቀደሞ የነበራቹ ተጽዕኖ ወደ ነበረበት ቦታ ሊመለስ ወይም ላይመለስ ይችላል፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ህመም ሊኖር ቢችልም እግዚአብሔር እናንተን የሚመለከትበት መንገድ እንጂ ሌሎች እናንተን የሚመለከቱበት መንገድ ወደ ማያሳስባቹ ስፍራ ትደርሳላቹ፡፡ 

5. የተልዕኮ ለውጥ

የቀደሙትን እርምጃዎች እስክታልፍ ድረስ በእዚህ ስኬታማ መሆን አትችሉም፡፡ ከክህደት በኋላ ትዳራቸውን እንደገና ለማደስ የሚፈልጉ ባሎች ወይም ሚስቶች እንደ አዲስ ትዳርን መፍለግ አለባቸው ምንም እንኳ ከቀድሞ የትዳር አጋራቸው ጋር ቢሆንም፡፡ ከጥቂት ወራት የምክር አገልግሎት በኋላ “የድሮውን” የጋብቻ መልክ ለመመለስ መሞከር አይሆንም፡፡ የቀድሞው ጋብቻ አልሆነም፡፡ የመስራት ዕድል ያለው ብቸኛው ነገር አዲስ ጋብቻን መመስረት ነው፡፡ 

እንደዚሁም የተዋረደ ፓስተር ወይም መሪ ምሳሌነቱን እንደገና መልሶ መገንባት አለበት፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ፓስተር ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ መመለስ ለፓስተሩ፣ለቤተሰቡ እና ቤተክርስቲያኒቱ ከባድ የስህተት እርምጃ ይሆናል፡፡ በመሪሆች ባህሪ እና በተልእኳቸው ውስጥ አዲስ መሠረት ቀስ በቀስ መገንባት አለበት፡፡ 

እዚ ደረጃ ላይ ስትደርሱ ነው ሌሎች ሰዎች እናንተን ስለሚመለከቱበት መንገድ “መጨነቅ” መጀመር ያለባቹ፡፡ ተልዕኮቹ ከበፊቱ የተለየ ሊሆን ይችላል፡፡ እና ያ ጥሩ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ 

ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን በምንዝር የተያዘችው ሴት ናት ብለው የሚያምኑት መግደላዊት ማርያም (ዩሐ 8፡2-8) ከትንሳኤው በኋላ ኢየሱስን በህይወት ያየች የመጀመሪያው ሰው ሆነች፡፡ ኢየሱስን የካደው ጴጥሮስ ከቀድሞዋ ቤተክርስቲያን መሪዎች መካከል አንዱ ሆኗል፡፡ እግዚአብሔር ለእናንተም ተልእኮ አለው፡፡

በተሃድሶ ሂደት ውስጥ የትም ብትሆኑ አታቁሙ! እናንተ ከእሱ ጋር መሄዳቸውን ካላቆማቹ እግዚአብሔር የተሃድሶ ሂደቱን አያቆምም፡፡

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox