እራሴን እንዳልገድል ቢላዋ ከለከሉኝ

ብርሃን መፅሔት ታህሳስ 1984 ቁጥር 1 :

ገና ልጅሳለሁ እግዚአብሔርን እንዲሁ እፈራዋለሁ ሃያልነቱ ታላቅነቱነና ፈዋሽነቱን  ግን አላውቅም ነበር እሱግን ቀድሞውንም ያውቀኛል ማለት እችላለሁ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ በተለያዩ በሽታዎች ተለከፍኩ በተለይ የሆድህመምና የራስ ምታት በሽታዎች ክፉኛ አሰቃዩኝ ያምሆኖ ትምህርቴን ከሞላጎደል ተከታትያለሁ ዘጠነኛ ክፍል ስደርስ ግን ራስ ህመም ከምንግዜውም በላይ ስለባሰብኝ ትምህርቴን ለማቋረጥ ተገደድኩ ከዚህም በኋላ ሆስፒታል ወሰዱኝ ይሁን እነጂ የተገኘልኝ መፍትሄ አልነበረም ቤተሰቦቼ ግን አሁንም ቢሆን እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም ምናልባት ይበጅዋል ብለው በየደብተራው በየቃልቻውና በየጠንቋዩቤት  አዞሩኝ ይህም አልሳካ ሲላቸው አዲስ አበባ አምጥተው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አስተኙኝ እዚህም ቢሆን ዶክተሮቹ መድሃኒት መዋጥ አለመቻሌንና ሰውነቴ እየመነመነ መሄዱን ሲገነዘቡ ከሆስፒታሉ እንድወጣ ነገሩኝ ሁኔታው ያሳዘናቸው ወላጆቼም በኔ ተስፋ ቆረጡ  በሽታዬን ካባባሱት ውስጥ አንዱ ደግሞ የእንቅልፍ እጦት ነው ያውም ለሶስት ወራት ያህል እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም ማለት እችላለሁ ለምናልባቱ እንኳሸለብ ያደረገኝ እንደሆነ  ግን ዙሪያዬን  ከበው የሚያስጨንቁኝ እርኩሳን መናፍስት ይታዩኛል በጣም ከመጨነቄ የተነሳ እጮሃለው ጭንቀቴን ለማስወገድ ሲባል የሚበራው ፋኖስ መሬት ወገግ እስክትል አይጠፋም ሰው ካላገላበጠኝ በቀር እራሴን በራሴ ማንቀሳቀስ አልችልም በተለይ  ስለኔ ሁሌ የምታነባው እናቴ በቀን ሶስቴ አራቴ ታገላብጠኛለች  ሶስት ወር ሙሉ ከቤት ሳትወጣ ስታስታምመኝ ከረመች የእናቴ ጭንቀት ከቀን ወደቀን እያየለ መጣ እኔም እናቴን በዚህ ሁኔታ ላይ ሳገኛት ሕይወቴን ለማጥፋት ወሰንኩ ለዚህም አላማዬመሳካት ስልም ትንሽእህቴን ጠርቼ ቢላዋእንድትሰጠኝ ጠየኳት ከሷያገኘሁት መልስ ግን ለታምሩ ቢላዋ አትስጪ ተብያለሁ የሚል ነበር በኋላ ስትጠየቅ እንዲህ ያላት ሰው የለም ከዚህ በኋላ የተሻለነገር ወደእኔ አይቀርብም  በዚህ በታመምኩባቸው  ወራት የምግብ ፍላጎት ጨርሶ አልነበረኝም ቤተሰብ ግን የተለያ ምግቦችን ሰኔ ከማቅረብ አልተቆጠቡም በዚህ አይነት በሞትና በሕይወት መካከል ሆኜ ክፉኛ ተሰቃየሁ በሶስተኛው ወር መገባደጃ ላይ የቅርብ ዘመዴ የሆነች ሴት ለራሷ ጉዳይ ወደከተማ መውጣት ፈልጋ እኔንም እግረመንገዱዋን  መጥታ ጎበኘችኝ ይህችው ዘመዴሕመሜ ጽኑመሆኑን  ስትረዳ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የተቻላትንም ያህል አጽናናችኝ ወደከተማ ሄደች ከከተማ ስትመለስ ስሜን ጠርታ ዛሬ ከተማ ሄጄ እግዚአብሄር ያድናል ይፈውሳል የሚል ቃል ሰምቻለሁ ከአሁን በፊት በየቃልቻው በየጠንቋዩ  በየደብተራው በየሼኪው ቤት ዞረሃል ፈውስ ግን ካተ እርቁዋል  እስቲ ደግሞ እግዚአብሔርን ሞክር አለችኝና  እራሴን ቀና አድርጋ  ከስሩ አዲስ ኪዳን አኖረችልኝ እኔም ስለ እግዚአብሔር ስትነግረኝ ትንሽ ትንሽ ሰላም ይሰማኝ ጀመር ድሮ ከፍርሃቴ የተነሳ እንቅልፍ በዓይኔ ዞሮ የማያውቀው ሰው ይህችው ዘመዴ ከኔ ከተለየች ከአንድ ሰዓት በሁዋላ በሶስት ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተኛሁ፡፡ወዲያውኑ ሕልም አየሁ ከፍተኛ ጦርነት በኔላይ የሚካሄድ ይመስለኛል የሁለት ነገሮች ግጭት ይታየኛል የሆነብርሃን ከግጭቱ መካከል እመለከታለሁ በዚሁ ህልምውስጥ እንዳለሁ አንድ ሽማግሌ ይመጣና እጄን ይዞ ጉዞይቀጥላል ወዴት እንደሚወስደኝ ግን አላውቅም ከረጅም ጉዞ በኋላ አንድ ትልቅ ቤት ውስጥ ገባን ሳሎኑ በጣም ሰፊ ነው የቤቱ ውበትና ቀለም በዚህ ዓለም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ነው  በቤትውስጥ ሶስት ሰዎች  በዳኝነት ወንበር ላይ ተቀምጠዋል ሰዎቹን ስመለ፤ከታቸው እጅግ ፈራሁ ከፊት ለፊታቸው ቆሜ እንዳለሁ በጣም የሚያስደነግጥ ድምፅ ታምሩን ማን አምጣ አለህ እገሌን እንጂ እሱን አይደለም አለና እኔን ባስቸኳይ ወደቦታዬ እንዲመልሰኝ ትዕዛዝ ሰጠ ሽማግሌው እጄን ይዞ ቁልቁለቱን ካወረደኝ  በኋላ ወደምተኛበት አልጋ መለሰኝ በመጨረሻም ሽማግሌው ታምሩ አሁን ተፈውሰሃል ለምልክት ያህል ራስህ ውስጥ የቀረውን በሽታህን ፈቃዱ የሚባል እጁን እራስህ ላይ ጭኖ ሲፀልይልሕ ትፈወሳለህ አለኝና ፈቃዱ የሚገኝበትን ቦታ ጠቆመኝ እኔ እስነሳ ዘመድ አዝማዱና ጎረቤቱ ዙሪያን ከቦቁጭ ብሉዋል ቅልል ብሎኝ ስለነበር ብድግ ብዬ ሰውነቴን አዝናናሁ  ራሴንም አነቃቀሁት አንዳች የሕመም ስሜት አልነበረብኝም ግራ ቢገባኝ ድርዎኑም ቢሆን ዝም ብዬ በሽተኛ ነኝ አልኩ እንጂ ለካስጤነኛ ንኝአልኩ እራሴን በራሰዬ ጠየኩኝ ወላጆቼም ጨርቄን ጥዬ ያበድኩ መሰላቸው  ሊያስሩኝ ገመድ አመጡ ቀስ በቀስ ግን እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ እንደፈወሰኝ አስረዳኋቸው ከዚያመም በኋላ ያመጡልኝን ምግብ በደንብ ተመገብኩ እነሱም በመፈወሰዬ በጣም ተደነቁ  ከመካከላቸውም ብዙዎቹ ለእግዚአብሔር ብግባራቸው  ወድቀው ሰገዱ::

በነጋታው አዲስ ኪዳኑን ይዛልኝ ወደመጣችው ዘመዴ ሰው ተላከ እርሱዋም ስለኔ ሰምታ በፍጥነት ስትመጣ ከሰዎች እኩል ቁጭ ብዬ ቡና ስጠታአገኘችን የእግዚአብሔርን ታላቅነት ካስተዋለች በኋላ በጣም ተገረመች ሽመማግሌው የነገረኝን ሁሉ ዝርዝር አድርጌ ነገርኳት ሽመግሌው ቤተክርስቲያኑ ድረስ በእግሬ እንድሄድ ስላዘዘኝ ከቤታችን እሰከካ ያለውን አስራኣምስት ኪሎ ሜትር መንገድ በእግር ጉዞ ለመጀመር ስንነሳከቤተዘመድ መሃል ግማሾቹ  በበቅሎ ይሄድ ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ዛሬ ድኖ እንዴት ዛሬዬውኑ ይሄዳል  ብለው ጭቅጭቅ አነሱ እኔግን ሽማግሌው የሰጠኝን ምክር ተቀብዬ በእግዚአብሔር ኃይል ምንም ድካም ሳይሰማኝ አስራአምስቱን ኪሎ ሜትር በእገሬ ተጉዤ ሽማግሌው በሕልሜ ያሳየኝን ቤተክርስቲያን ደረስን ወደቤተክርስቲያኑ ዘልቀን ስንገባ አንድ ወነድም ቁጭብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነብ አገኘነው ከመቀመጫው ተነስቶ ከዘመዴ ጋር ሰላምታ ተለዋወጠ ቀጥሎም ስለሁኔታው አጫወተቻቸው እሱም እግዚአብሔር አመስግኖ  አይኔን ትኩር ብሎ ተመለከተ እኔ ግን ደፍሬ እሱን ማየት ስላልቻልኩ ዓይኔን ሰበርኩ ከዚያም እግዚአብሔር ያድናል ይህን ታምናለህ አለኝ እኔም አዎ አምናለሁ አልኩት ከዚህ በኋላ ያለው ነገር አላወኩም እርሴን ስቼ ነበር ከሩብ ሰዓት በኋላ ራሴን አንድ ቦታ ቁጭ ብዬ አገኘሁ በጣም ነበር የደነገጥኩት  ምንሆኜነበር ዘመዴን ጠይቄአት እሰከምትነግረኝ በጣም ቸኮልኩ ፀሎቱን ካበቃ በኋላ ወደቤት ጉዞ ጀመርን ራሴን ስቼ በነበረ ሰዓት ምን እንደተደረገ ጠየኳት ራስህ ውስጥ ለምልክት የቀሩት 27 አጋንንት እንዴት እንደያዙህ እራሳቸውን ከገለጡ በኋላ ወጡልህ አለችኝ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ተሰማኝ  ስለእግዚአብሔር እየተነጋገርን ያንን የአሥራ አምስ ኪሎ ሜትር መንገድ በእግራችን ስናቆራርጥ ምንም ድካም አልተሰማኝም ቤት ስንደርስ ብዙ ሰዎች በእግዚአብሔር ስራ ተገረሙ ተደነቁም ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እንደግል አዳኝ ተቀበልኩ በሳምንቴ  አንዳንድ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ ብረታትና ሃይል ይሰጣል ብለው ሲነጋገሩ ሰማሁ እኔ ስለመንፈስቅዱስ  አልሞላም የሚል  ጉጉት አደረብኝ ስለመንፈስ ቅዱስ ሙላትም አብዝቼ ራሴን በጊታፊት አቀረብኩ ብዙም ሳልቆይ በመንፈስ ቅዱስ ተሞላሁ ከዚያም  በኋላ የድሮው ታምሩነቴ ተለውጦ አዲሱ እየሱሳዊ ታምሩ እንዴት እንደተተካ ሳስበው በጣም ይገርመኛል የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁንና ልጓም ፈረስን እንደሚቆጣጠረው ሁሉ እኔም መንፈስ ቅዱስ ተቆጣጥሮኛል መርቶኛል ገልጾልኛል፡፡

ብርሃን መፅሔት, ታህሳስ 1984 ቁጥር 1

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox