አብዛኛውን ግዜ ከአውድ ውጭ የሚቶረገሙ 7 ገናና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ታሊዛ ቤከር፡

ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ በአስደናቂ አነጋገር የተሞላ ቢሆንም ፣ የተወሰኑ ጥቅሶች በ ፖፕ ባሕል መሰረት በቀናተኛ መንፈስ
ላይ ይነሳሉ። ሰዎች የሚወዷቸውን ጥቅሶችን በሚጠቅሱ በኪነጥበብ ፣ በኩባያ ፣ በጋዜጣዎች ፣ በአለባበስ ወይም ንቅሳት ላይ
ኢንቨስት ያደርጋሉ ፡፡ ሆኖም ፣ በጣም ገናና ከሆኑት ጥቅሶች መካከል አንዳንዶቹ በሚያሳዝን ሁኔታ ከእውነተኛ የቅዱስ ጽሑፋዊ
አውዳቸው በተቃራኒ የተረዱ ናቸው ፡፡
የቅዱሳት መጻሕፍትን አለአግባብ መጠቀም አደገኛ ነው ፡፡ ሥነ-መለኮትዎ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ስሜቶች ላይ የተመሠረተ
መሆኑ ያመኗቸው “ተስፋዎች” የማይፈጸሙ ሲሆኑ ግራ መጋባትን ሊፈጥርብዎት ይችላል ፡፡ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር በተሻለ
ለመረዳት ሰባት በተሳሳተ መንገድ የተረዱ ጥቅሶችን እንደገና እንገልፃለን ፡፡

  1. ኤርሚያስ 29 ፡11 (N IV):- “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው
    እንጂ የክፉ ነገር አይደለም”። ይህ ጥቅስ በዚህ ዝርዝር ውስጥ በመጀመሪያ ላይ የተጠቀሰው በተደጋጋሚ ከአውድ ውጭ
    ስለሚወሰድ ነው ፡፡ ያስተውሉ ፣ ይህ ጥቅስ የተጻፈው እግዚአብሔር ለዛሬው የዘመናችን አንባቢ በቀጥታ በሚናገርበት
    አውድ ውስጥ የተፃፈ አይደለም ፡፡ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሕዝቦች ሁሉ የሚሰጠው ቃል ነው እንጂ፡፡ በኤርምያስ ውስጥ
    እግዚአብሔር በባቢሎን ለተያዙት ዕብራውያን ነፃነትን እንደሚያመጣላቸው ተስፋ ሰጣቸው ፡፡ እዚህ ያለው ብልጽግና ስለ
    ተግባራዊ አካላዊ ፍላጎቶቻቸው ነው ፡፡
    የዘመናችን አንባቢዎች አምላክን በማመናቸው ብቻ በድግምት ሀብታም እንዲሆኑ አይደለም ፡፡ ይህ ጥቅስ ከአውድ ውጭ
    በሚቶረገምበት ጊዜ አደገኛ ጎን ሊኖረው ይችላል ሥር የሰደደ ህመም ያለው ሰው ፣ ይህ ጥቅስ ምትሃታዊ ፈውስ እንዲያመጣለት
    ሊታዘዝለት ይችላል ። ሆኖም ፣ በተሳሳተ መንገድ የተረዳነው ተስፋ ሳይፈፀም ሲቀር የሰዎችን እምነት ሊያዳክም ይችላል ፡፡
  2. ፊልጵስዩስ 4፡13 :- “ኃይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ ፡፡” ይህ ጥቅስ በአትሌቲክስ አከባቢዎች ውስጥ
    በብዛት ይዘወተራል ፣ ከስቴፍ ከሪ ጥቅሱን በጫማዎቹ ላይ መፃፍ እስከ ቲም ተቦው የፊት ተለጣፊዎች ድረስ ይህንን ጥቅስ
    ይጠቅሳሉ ፡፡ የዚህ ሀሳብ መልዕክት ፕሮፌሽናል አትሌቶች በእየሱስ በማመናቸው ተወዳዳሪ ይሆናሉ የሚለው ሀሳብ ነው ፡፡

ሆኖም ፣ ከዐውደ-ጽሑፉ አንጻር ፣ ጳውሎስ ይህንን ፅሁፍ የፃፈው የፍርድ ሂደትን በመጠባበቅ ላይ እያለ የእየሱስን ትንሳኤ
ለመስበክ አስቦ ነው ። ይህን ጥቅስ ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያንን የፃፈው ሞትን ድል ያደረገው የክርስቶስ የኃይል ምንጭ
መሆኑን በማስታወስ ስቃዩን እንዲቋቋሙ ለማበረታታት ነው ፡፡ በአትሌቲክስ ወይም በሙያዊ ውድድር ጣሪያ በመድረስ ወይም
በአስማት በመባረክ ሳይሆን መንፈሳዊ ውጣ ውረድን በመቋቋም ውስጣዊ ጥንካሬን መፈለግ ነው ፡፡

  1. ማቴዎስ 7:1 (M EV ):- “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ።” ሰዎች ይህንን ጥቅስ “እኔን ሊፈርድብኝ የሚችለው እግዚአብሔር
    ብቻ ነው” በሚለው ሊተረጉሙት ይችላሉ ፣ ማንም ሰው ትክክል የሆነ እና ትክክል ያልሆነ ስህተት እንዳለው የማረጋገጥ
    ስልጣን የለውም ማለት ነው ፡፡ ሆኖም ፣ “እኔን ሊፈርድብኝ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው” የሚለው ከመጽሐፍ ቅዱስ
    የመጣ ሳይሆን ከቱፓክ የተወሰደ ነው! ይህ ስንኝ ሰዎች እርስ በርሳቸው መፋረዳቸውን ማቆም አለባቸው የሚል ትርጉም
    ካለው ፣ የፍትሕ ስርዓታችንን ማቆም አለብን ፣ እናም እግዚአብሔር ጣልቃ በመግባት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን ይቀጣል ፡፡
    በእርግጠኝነት ፣ ህብረተሰባችን ምን አይነት ባህርይን መታገስ እንዳለበት እና ምን ማስወገድ እንዳለበት የሚመሩ ህጎችን
    በማፀደቅ ረገድ ጠንካራ ነው ፡፡

ብዙ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን የሚርቁበት አንዱ ምክንያት በምእመናን መካከል ያለው ግብዝነት እና ራስን በማድነቅ ችግር
ስለሚጨነቁ ነው ፡፡ ምስክሮቻችንን ለማጠንከር በአብያተ ክርስቲያናችን ሁሉም ሰው ተቀባይነት እንዳለው በግልፅ በማስቀመጥ
“ከአንተ ይልቅ የተቀደስኩ” ነኝ የሚሉ አመለካከቶችን ማስወገድ አለብን ፡፡

  1. መዝሙር ዳዊት 46 ፡10 :- “ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ
    ከፍ ከፍ እላለሁ።” “ዝም በሉ” ወይም “ዝም ብላችሁ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ እወቁ” የሚሉ ፅሁፎችን በክርስትናን
    መምሰል እና መታመን ውስጥ ማግኘት እጅግ ቀላል ነው። ይህም ከእግዚአብሄር ጋር ጥልቅ ሰላምን ለማግኘት በፀጥታ ውስጥ
    ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገን አመላካች ነው ፡፡ እግዚአብሔርን በዝምታ ማድመጥ ትልቅ ሀሳብ ቢሆንም ይህ ጥቅስ ግን
    ይህንን የሚያበረታታ አይደለም ፡፡
    የበለጠ ኃያል መልእክትን ለማግኘት ማንበብዎን ይቀጥሉ። ይህ ጥቅስ በክፍሉ ውስጥ ለተገለለ ለአንድ ሰው ብቻ የተነገረ ሳይሆን
    ለሁሉም የእግዚአብሔር ሕዝቦች የወጣ ቃል ነው ፡፡ ከብሔርዎ እና በመላው ምድር ዳርቻ ካሉ ሰዎች ጋር በሰላም አንድ ይሁኑ
    በማኅበረሰብዎ ውስጥ ፣ የእግዚአብሔር ዕቅድ ራሱን ለሁሉም ሰው ሊገልፅ መሆኑን ይወቁ ፡፡
  2. ያዕቆብ 5፡15 :- “የእምነትም ጸሎት ድዌውን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።”
    የታመሙ ሰዎች በክርስቶስ ላይ በቂ እምነት ማጣት ይታይባቸዋል በሚል የተሳሰተ ዕይታ ሰዎች ይህንን ጥቅስ ሊተረጉሙት
    ይችላሉ። በእርግጥ የእነሱ መከራ በራሳቸው ጥፋት የተነሳ ነው ፡፡ ሆኖም ፣ ይህ በተሳሳተ መንገድ የተተረጎመ ጥቅስ ከባድ
    ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል ፡፡ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ተአምራዊ ፈውስ የማድረግ ችሎታ ያለው ቢሆንም ፣ ሁላችንም
    አካላዊ ሳቃይ ሊደርስብን በመጨረሻም ወደ ሞት ሊወስደን የሚችል ነገርን መጠበቅ እንችላለን።
    ይህን ቁጥር በማመን “መዳን” እና ከ ውድቀት “መነሳት” እንደምንችል ጥቅሱ ቃል ገብቷል ፣ ይህ ምን ማለት ነው? ብዙ ሰዎች
    በሚሰቃዩበት ጊዜ ጥልቅ ፍቅርን ፣ የበለጠ ጥበብን እና የተሻለ ሰላምን ያገኛሉ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ መንፈሳዊ እና ሥነ-
    ልቦናዊ ግንዛቤዎች በመጀመሪያ በሽታን ሳይቋቋሙ መቆየት የማይቻል ናቸው ፡፡ ክርስቲያኖች በበሽታ ሲሰቃዩ ሥቃያቸው
    እንዲለቃቸው ለመጸለይ በመሞከር ላይ ብቻ አያተኩሩ ፡፡ በችግር ውስጥ ሊነሱ የሚችሉትን የማዳን ግንዛቤዎችን በመረዳት ከእነሱ
    ጋር ወደዚ ሥቃይ ዘንበል ይበሉ፡፡
  3. ወደ ሮሜ ሰዎች 13 ፡1 ፦ “ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤
    ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።” ሰዎች ከአውድ ውጪ በዚህ መልኩ ይህንን ይተረጉማሉ በእነሱ
    በኩል እንዲሠራ እግዚአብሔርን በመተማመን ማንኛውንም የፖለቲካ መሪን በጭፍን መከተል አለብን ማለት ነው፡፡ ሆኖም
    ባለሥልጣናት ስልጣናቸውን ህብረተሰቡን ለመጉዳት ሲጠቀሙበት ምን ይሆናል? ግብፃውያን ዕብራውያንን በባርነት ሲገዙ
    እግዚአብሔር ሙሴን በማስነሳት ይህንን አገዛዝ እንዲያፈርስ ኃይል ሰጠው ፡፡ ንጉሥ ዳርዮስ በዳንኤል በእግዚአብሔር አምልኮ
    በጣም በመበሳጨቱ ዳንኤልን በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ በሞት ቀጣው፡፡ የተቀደሱ የአምልኮ ሥርዓቶችን ለማትረፍ
    በሚሞክሩ የኢኮኖሚ መሪዎች ኢየሱስ ተቆትቷል ፡፡

ታላላቅ የክርስቲያን መሪዎችን ጨቋኝ መንግስታዊ ስርዓቶችን በመቃወማቸው እናከብራቸዋለን ፡፡ የክርስቲያን የባርነት
ተከራካሪዎች ባርነትን ለማስቆም አግዘዋል ፡፡ ቄስ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር የሲቪል መብቶች ንቅናቄን ከፍ በማድረግ መራ ፡፡
የደቡብ አፍሪካን አፓርታይድ ለማስቆም ሊቀ ጳጳሱ ዴዝሞንድ ቱቱ ረድተዋል ፡፡ የመንግሥት እርምጃዎች ለአምላክ ተጋላጭ በሆኑ
ሕፃናት ላይ በሚወድቅበት ጊዜ መተግበር የ እኛ ኃላፊነት ነው ፡፡

  1. 1 ቆሮንጦስ 13 ፡4 (E S V):-“ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም’’ ፡፡
    ይህንን የፍቅር ጥቅስ የማይወድ ማነው? በግንኙነት ውስጥ ላሉት እንደ መመሪያ ሆኖ የሚያገለግል እና በተጨማሪ የሠርግ
    ዋና መዓድ ነው ፡፡ በእርግጥ ይህ ጥበብ ለባለትዳሮች ጠቃሚ ቢሆንም ፣ እዚህ ያለው ግልጋሎት በጣም ሰፊ ነው ፡፡ ጳውሎስ
    ይህን ምክር ለቆሮንጦስ ቤተክርስቲያን በሙሉ ነው የጻፈው ፡፡ ያላገባን ወይም ያገባን ሰዎች ፣ በዚህ የፅሁፍ አካሄድ
    በአካባቢያችን ያሉትን ሁሉንም ሰዎች መውደድ አለብን ፡፡

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox