መንፈስ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ያሉ ብልሹ እሴቶችን ማስወገድ ይፈልጋል

በርት ኤም. ፋርያስ :

በ 2002 ረዘም ባለ የ ጾም እና የጸሎት ጊዜ ዉስጥ በነበርኩበት ወቅት ከእኔ በላይ ከመስታወት የተሰራ ጣራ አይ ነበር፤ በአገልግሎቴ የምፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ሞገስ፣ ቅባት፣ ሃይል፣ የተከፈቱ በሮች፣ ተጽዕኖ እና ሌሎችም ከሌላኛው በኩል ነበሩ። ነገር ግን እኔ ጣራ ጣራውን ሳይ እግዚአብሔር አምላክ ወደታች እንዳይ እያመለከተኝ ስለቆምኩበት መሰረት እና ስለ ባህሪዬ ይናገረኝ ነበር። በወቅቱ ጽፌው ስለነበረው መጽሃፍ ሊፈትነኝ ነበር የመጣው።

በቅርቡ የሞቱ ብዙ ታዋቂ አገልጋዮች ከእነሱ መካከል አንዳንዶች በሃጢያት ሕይወት እና በመጥፎ ባሕሪ ለተሸነፉ ይህ ጥሩ ማስታወሻ ነው።እግዚአብሔር ሰዎችን ይቀባል፤ ሰዎችም ባህሪያቸው ለአገልግሎታቸው የተገባ እንዲሆን ያደርጋሉ። (1ኛ ጢሞቲዎስ 3 ያንብቡ)። ሰዎች በቅባት፣ በስጦታ፣ በካሪዝማ፣ እና በችሎታ ይማረካሉ ይሳባሉም። እግዚአብሔር ግን ለባህሪ ቅድሚያ ይሰጣል። እሱን ለመምሰል የምትፈልጉ ከሆነም በዚህ ይፈትናችኋል።

በእምነት አባቴ የሆነው እና አሁን በሕይወት የሌው ኬኔዝ ሄገን በሕይወት ዘመኑ ብዙ ሽህ መጋቢዎችን እና ቤተክርስቲያናትን አገልግሏል። ከነዚህ መካከል እጂግ ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ለአገልግሎት ብቁ የሆኑት ይለን ነበር። ከዚህም አልፎ በእነርሱ ሕይወት ምክንያት የልጆቻቸው ሕይወት እንዴት ሊበላሽ እንደሚችል ተንብዮ ነበር። የእርሱ ትንቢት 100 ፐርሰን ትክክል ነበር። ባህሪ በሕይወት እና በአገልግሎት የመጀመሪያውን ቦታ ሊይዝ ይገባዋል። 

ትዳርህ እና ልጆችህ ከቁጥጥር ውጭ ሆነው የአንተ ስጦታ እና ቅባት ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ አትንገረኝ። የራስህን ዝሙት እና ሱስ ሳታሸንፍ አለምን እንዴት ለታሸነፍ እንደሆነ አትንገረኝ። ዛሬ ዛሬ አገልጋዮች በዝሙት ወይም በሌላ ባልተገባ ድርጊት ተይዘው በአገልግሎት ሲቀጠሉ፤ ምስኪን ተከታዮቻቸውም “መፍረድ አይገባም” እያሉ ሲከላከሉላቸው እና እንደ ጣኦት ሲያመልኳቸው ማየት የተለመደ ነገር ነው። 

እኔ በግሌ በፍረድ ላይ ያለን የተሳሳተ እይታ በአሁን ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉት አደገኛ ነገሮች አንዱ ነው ብዪ አስባለሁ። ቤተክርስቲያን ውስጥ ላለው የቆሸሸ እና የረከሰ አገልግሎትም ምክንያት ነው። ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅ ፍርድ በእርግጥ ቁልፍ ነገር መሆኑን ያውቅ ነበር። 

“ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? በዓለምስ ላይ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ስለሚሆን ነገር ልትፈርዱ አትበቁምን? የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን? እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ የፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን?” (1 ቆሮንቶስ 6:2-4).

በቤተክርስቲያን ለመፍረድ አቅም የሌላቸው “አትፍረድ” የሚሉ ናቸው። 

እንደዚህ በጽድቅ ለመፍረድ አቅም ማጣታችን ተንበርክከን የክርስቶስ አካል ላለችበት አሳዛኝ ሁኔታ እንድንጸልይ ሊያደርገን ይገባል። ስለምን እንደ እግዚአብሔር ባልሆነ ስኬት እና ዝና የምንነዳ ሆንን? ስለምን ሰዎችን በሚያተልቅ አገልግሎት፣ መድረክ፣ ደማቅ መብራቶች፣ እና ማይክ የምንሳብ ሆንን? ኢየሱስን ስለማናውቀው አይደለምን? ከእርሱ ጋር የግል የሆነ ሕይወት የለንም። በጓዳችን እሱን አናውቀዉም። 

በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ሐዋርያው ጳውሎስ በቤተክርስቲያን በመሪነት ማገልገል ለሚፈልጉ ሰዎች አስፈላጊ የሆኑ ባህሪዎችን ለይቶ ያስቀምጣል። (1 ጢሞቲዎስ 3፥ 1 – 7) የወንጌል አገልጋዮች ፣ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን መጋቢዎች እና ሽማግሌዎች መጽሃፍ ቅዱሳዊ ካልሆነ ስኬት ከመነዳት ይልቅ ከእነዚህ ባህሪዎች ጋር ራሳቸውን ሊያስተዋዉቁ ይገባቸዋል። ዲያቆናትም እንኳን ቢሆኑ ከተፈተኑ እና ያለነቀፋ ከተገኙ በኋላ በቤተክርስቲያን ለማገልገል የተወሰኑትን ባህሪዎች የሚያሟሉ መሆን ይገባቸዋል።           

“እነዚህም ደግሞ አስቀድሞ ይፈተኑ፥ ከዚያም በኋላ ያለ ነቀፋ ቢሆኑ በዲቁና ሥራ ያገልግሉ።” (1ኛ ጢሞቲዎስ 3:10).

ያለነቀፋ! ያ ማለት የሚነቀፍበት ባህሪ ሊኖረው አይገባም ማለት ነው። ስለምን ዛሬ በቤተክርስቲያን ይህንን መለኪያ ችላ አልነው?  

ሰዎች  “ማንም ፍጹም አይደለም፤ ሁላችንም ድካም እና ጉድለት አለብን፤ በህግ ልትመራ አትችልም” ይላሉ። ደግሞም “አትፍረድ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ነው” ይላሉ።     

ታዲያ ስለምን እነዚህ ባህሪያቶች በቃሉ ውስጥ ተቀመጡ? ጳውሎስ ምክንያቱን እንዲህ በማለት ያስረዳል፥   

 “ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ። ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።”  (1ኛ ጢሞቲዎስ 3:14-15).

ሐዋርያው ጳውሎስ ወጣቱ ጢሞቲዎስ በደንብ እንዲረዳው የፈለገው ነገር ቤተክርስቲያን በዓለም ውስጥ ታላቋ የእውነት ጠባቂ መሆኗን ደግም ይህ ቤተክርስቲያን የምትጠብቀው እውነት ፋይዳው ታላቅ መሆኑን ነው። አንድ ጽሁፍ እንዲ ይላል ፥  “ይህ ከእግዚአብሔር ሰው መሆን ጋር በምድርም መጥቶ ከፈጸመው ስራ ጋር ግንኙነት አለው።”  (ቁጥር 16)  በሰማይ ጥልቅ የሆነ መገረምን ያጫረው ስራ፤ ይህንንም የሚናገረው እውነተኛ አስተምህሮ በሰዎች ዘንድ ሊጠበቅ ይገባዋል።  

ይህ ታላቅ አስተምህሮ በሰይጣን ተጽእኖ የሚካድበት  ፣ እውነትም የሚበርዝበት እና የሚቀየጥበት ጊዜ እንደሚመጣ በማሳየት፤  ይህ ታላቅ እውነት በሚቀጥለው ምዕራፍ በሰፊው ተብራርቷል (1ኛ ጢሞቲዎስ  4)። አሁን ይምንኖረው በዚያ ዘመን ነው። አስተምህሮ እና ባህሪ ለዘላልም የተሳሰሩ ሆነው ይኖራሉ። 

እነዚህ የባህሪ እሴቶች በቤተክርስቲያን አመራር ውስጥ በጣም መሰረታዊ ናቸው፤ ምን ያህል ከእነርሱ እነደራቅን ሳስብ በእጅጉ እገረማለሁ። ዛሬ ላይ ወደ ህዝቡ እና ወደ እውቅና ማማ በፍጥነት የሚወጡ ወጣት አገልጋዮች ጉዳይ ያሳስበኛል። ብዙዎቹ እንደ ትወርዋሪ ኮከብ ናቸው፤ ዛሬ እዚህ በሚቀጥለው ቀን ደግሞ ሌላ ቦታ።    

በስጦታዎች እና በችሎታዎች ሳይሆን በተለወጠ ባህሪ የሚያበራ ኮከብ መሆን እለት እለትም በማብራት መጨመር የሚበልጥ ነገር ነው። ብዙዎች የስጦታዎች እና የችሎታዎች መኖርን ከእግዚአብሔር ፍቃድ እና ለአገልግሎት ብቁ ከመሆን ጋር ያሳስቷቸዋል። እንደዚህ ግን አይደለም ስጦታዎች እና ችሎታዎች ለጥሪአችን  የታጠቅናቸው ናቸው። እግዚአብሔር አምላክ በስጦታዎቹ እና በቅባቱ ያስታጥቀናል፤ ነገር ግን በባህሪያችን ራሳችንን ለአገልግሎት ብቁ የምናደርገው እኛው ራሳችን ነን። ለባህሪ ቅድሚያ ካልሰጠን ለመታለል ቅርብ እንሆናለን።

ቀደም ብዬ በነገርኳችሁ ረዘም ባለው የ 2002 የጸሎት ጊዜ፤ ከኢየሱስ የመጣ አንድ ሬማ ቃል ሕይወቴን ቀይሮታል። እንዲህ ነበር ያለኝ “እኔ እንድከፍትልህ የምትፈልጋቸውን በሮች ያልከፈትኩልህ ከእኔ ጥበቃ የተነሳ ነው። እንዚህን በሮች ብከፍትልህ ትታለላለህ እንደልቤ መኖርም አትችልም “ ( ይህን ምስክርነት “ጉዞ ወደ እርሱ ቅድስና” በሚለው ማስታወሻዬ ላይ አስፍሬዋለሁ)። እንደዚህ ሲለኝ እንደ ሕጻን ነበር ያነባሁት፤ እራሴን ከእራሴ እንደጠበቀኝ ስረዳ ፍቅሩ ከምቋቋመው በላይ ነበር።           

ከዛ በኋላ የሰዎችን አገልግሎት ውደምፈልግበት ሳይሆን የሱን ልብ ወደማውቅበት ፍቃዱንም ወደምፈጽምበት ስፍራ ነበር የወሰደኝ። ይህ በሰው ልብ ውስጥ ባለው የአመጻ ሚስጥር ምክንያት ትልቅ የለውጥ ተአምር ነበር።  

እግዚአብሔር በህይወታችን እንዳለው ጥሪ በታላቅ መንገድ ሊጠቀምብን ሁሌ ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ እኛ በባህሪ ለአገልግሎት የተገባን እና ዝግጁ አይደለንም። እናም በራሳችን ተተኩሰን እሱ ለእኛ ያለውን ፍጹም የሆነውን አላማ እና ግብ ሳንኖር እንቀራለን።   

እነዚህን የካትሪን ኩልማን የጠቢብ ቃላት አድምጡ፥ 

ወደላይ እያየሁ ጮክ ብዬ “ኦ ውዴ ኢየሱስ፣ ስለምን ይህን ሁሉ ነገር የ 16 አመት ልጅ እያለሁ አላደረክም? ያኔ አልደክምም ነበር፣ ሌሊት እና ቀን እየዞርኩ መስበክ እችል ነበር። ያኔ እንቅልፍ በማልፈልግበት በወጣትነት እድሜዬ ለምን እንዲሆን አላደረክም? ኢየሱስ ሆይ ስለምን ብዙ መጠበቅ አስፈለገህ?” አልኩ።    

ጮክ ያለ ድምጽ አልነበረም፤ ነገር ግን ተናግሮኛል፤ እንዲህ ነበር ያለው። 

“ካትሪን ያኔ ሰጥቸሽ ቢሆን ኖሮ ሁሉንም ነገር ታበላሽው ነበር።” 

ምን ማለቱ እንደሆነ በሚገባ አውቅ ነበር። አባት ለልጁ ምርጡን ያውቃል። እናንተ በባህሪያቸሁ ላይ ስሩ፤ ፍቃዱን በትክክለኛው ጊዜ መግለጥን ለእርሱ ተውለት።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox