መንፈስ ቅዱስ ሃጥያተኛዋን አለም የሚወቅስበት 7 መንገዶች

ዶ/ር ጆሴፍ መቴራ :

በዚህ ጊዜ አብዛኛው የክርስቶስ አካላት፣ የመንፈስ ቅዱስን ተግባራት በሚያስቡበት ጊዜ፣ ተሃድሶን፣ ታላቅ መነቃቃት፣ እና የእግዚአብሔር ኃይል መገለጥን ያስታውሳሉ።

ምንም እንኳ ሁላችንም ስለ ቤተክርስቲያን መነቃቃት እና እድሳት ማውራት የምንወድ ቢሆንም፣ መንፈስ ቅዱስ ለቤተክርስቲያን ብሎም ለዓለም ወሳኝ የሆኑ ሌሎች በርካታ ተግባራቶች እንዳሉት መገንዘብ ይኖርብናል። በርግጥ ዛሬ ባሉት ማራኪ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ፣ መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ልብ ላይ ወቀሳን የማምጣት ተልእኮ በአብዛኛው ቸል የተባለ ይመስላል።

ብዙ ሰባኪዎች የቤተ ክርስቲያናቸውን አባላትን ለማበረታታትና ለማነሳሳት ብቻ ይሞክራሉ። ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ፣ በተደጋጋሚ ለቤተክርስቲያኖቻቸው ወቀሳን ለማምጣት ፍላጎት አለው፤ ምክንያቱም ከትዛዙ ያፈነገጡ የሕይወት ዘይቤ ምርጫዎች፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በነጻነት እንዳይንቀሳቀስና እንዳይባርክ ያደርሉና ነው።

በዮሐንስ 16፡8 ላይ፣ ኢየሱስ እንደተናገረው፣ “መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ፣ የኃጢአትን አለም፣ ጽድቅንና ፍርድን ይወቅሳል”። የዚህ ስራ አስፈላጊነት ሊታለፍ አይገባም! በኃጢአተኛው ሁኔታችን ላይ የሚያበራው መንፈስ ባይኖር ኖሮ፣ የወደቁ ፍጡሮች አዕምሮአቸው ታውሮውና አስተሳሰባቸው ጨልሞ ሃጥያታቸውን እንኳ ባልተረዱ ነበር  (2 ቆሮ 4፡4 እና ኤፌ 4: 17-19 ተመልከቱ)።

እናም፣ የእኛን ኃጢአተኝነት ሳናውቅ፣ አዳኝ እንደሚያስፈልገን እምነት ሊኖረን አይችልም። ይህም ማለት ደግሞ፣ ከኃጢአታችን ፈጽሞ ንስሃ አንገባም እናም ህይወታችንን ለጌታ ኢየሱስ አንሰጥም ማለት ነው። በርግጥ፣ በ “ወቀሳ” እና “ኩነኔ” መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።

መንፈስ ቅዱስ ኃጢያተኛ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር የማስታረቅ ግልጽ ዓላማ ይዞ ይወቅሳቸዋል። ነገር ግን ሰይጣን ዓላማው ሰዎች ከእግዚአብሔር እንዲሸሹ ስለሆነ ኩነኔን ያደርጋል።በዚህ ጽሑፍ ውስጥ፣ መንፈስ ቅዱስ የኃጢአትን ዓለም እንዴት እንደሚወቅስ ላይ ለማተኮር እፈልጋለሁ።

  1. የመንፈስ አንድነትን በመጠበቅ (ኤፌ 4: 3)

ሐዋርያው ጳውሎስ፣ እንደ አማኞች ያለብንን ኃላፊነት፣ በሰላም ሰንሰለት የመንፈስን አንድነትን በጥብቅ መጠበቅ አለብን ሲል በኤፌሶን ያለውን ጥልቅ ቃል ጠቅሷል። በቤተክርስቲያን አንድነት እና ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ አላማ እንደመሆኑ መጠን የክርስቶስ ተከታዮች ቤተክርስቲያንን በመከፋፈል አላማ ውስጥ ሆነው ሲንቀሳቀሱ በፅኑ ይወቅሳቸዋል። ሰዎች በመካከላቸው የመረረ ጥላቻ፣ ቂም እና በቀል አይሎ በሀሜት፣ በማንቋሸሽ እና ሰዎችን እርስ በርሳቸው በማጋጨት ሕይወት ሲኖሩ እርሱ መንፈስ ቅዱስ በፅኑ ይወቅሳቸዋል።

 ኢየሱስ በዮሐንስ ምዕራፍ 17፡20-23 ላይ፤ አለም እርሱ ከአብ እንደተላከ ልታምን የምትችለው፣ ቤትክርስቲያን በፍጹም አንድነት ውስጥ ስትሆን ብቻ ነው ብሏል። ደግሞም አንዳችን ሌላውን ስንወደው እኛ የእርሱ ደቀ መዛሙርት መሆናችንን በዚህ ያውቃሉ (ዮሐንስ 13፡35)። ስለዚህ አለም በኢየሱስ ክርስቶስ እውነት ተጠቅልላ የተለያየ ዘር እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ያላቸው ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በአንድነት እውነተኛ ፍቅርን ሲመሰክሩና እስኪለማመዱት መንፈስ ቅዱስ አለምን ይወቅሳል።

2. ለምድራዊ ገዥዎች በመመሥከር

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ፣ ኢየሱስ ለጲላጦስ ያደረገውን ምስክርነትና የተነገረውን ትረካ እናነባለን (ዮሐንስ 18: 36-38 ተመልከቱ)፣ ጳውሎስም ለሦስት የሮሜ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሲመሰክር ማለትም: ለአገረ ገዢ ፊሊክስ፣ ለፊስጦስ እና ለንጉሥ አግሪጳ (ሐዋ 24-26 ተመልከት) እናያለን። ወንጌልን ለምድራዊ ገዥዎች በምስበክ፣ መንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆኑ፣ ለወንጌል በሮችን መክፈት በሚችሉ ብሎም በእምነታቸው ወንጌል ወደ በባህላቸው ስርፆ እንዲገባ  እና ለቤተ ክርስቲያን ሞገስን መስጥት እንዲችሉ መሪዎችን ይወቅሳል። 

3. በአጠቃላይ የወንጌል ስብከት

እርግጥ ነው፣ በማንኛውም ጊዜ የኢየሱስን ወንጌል በምንሰብክበት ወይም በምንጋራበት ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ በሚያዳምጡት ልብ ውስጥ እምነትን ያነሳል (ሮሜ 10፡17 ተመልከት)። በ 1ኛ ዮሐንስ 5፡6-11 ላይ እንዲሁ ሐዋርያው ዮሐንስ፣ መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ልብ ውስጥ የእግዚአብሔርን ልጅን እውነተኝነት እንደሚመሰክር ያሳየናል።

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አማኞች ዝም ሲሉ፣ መንፈስ ቅዱስ አንደበታችንን እንዲቀባ እና ለዓለም ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ወቀሳን እንዲያመጣ እድሉን አይሰጡትም። ለዚህ ነው “አንድ ሰው ያለ ሰባኪ እንዴት ማመን ይችላል?” ብሎ ጳውሎስ የሚጠይቀው (ሮሜ 10 14 ተመልከቱ)።መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ሥጋ ውስጥ ስለፈሰሰ (ሐዋ 2፡17 ተመልከቱ) ዓለም እጅግ በጣም የሚያስፈልገውን የተቀባ ጸጋ እና ቆራጥ ወንጌል ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ይህንን፤ ሰዎችን ለሚዋጁበት ቀን ለማዳን፣ ለመለወጥ እና ለማቆየት ሊጠቀምበት ይችላል (ኤፌ 1 : 13,14 ተመልከቱ)።

4. የእግዚአብሔርን ውበት በኪነ ጥበብ፣ በሙዚቃ እና በተፈጥሮ በመግለፅ

እግዚአብሔር ዉበቱን በአምሳሉ፤ ምስሎቹን (ዘፍ 1፡27 ተመልከት) በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስቶ፤ ከእርሱ ጋር በጋራ በመፍጠር ውበቱን ያሳየናል፣ ይሄንም በኪነ ጥበብ፣ በሙዚቃ፣ በስነ ጽሑፍ፣ በፊልም እና በሳይንስ ማለትም በሥነ ጠፈር፣ በጂኦሎጂ፣ በባዮሎጂ፣ በፊዚክስ እና ከዚያም በላይ በሆኑ የተፈጥሮ ሕግ እና ተፈጥሮ ጥናት በኩል  ይገልፅልናል። እነዚህ ሁሉም ከተፈጥሯዊ እና ከመንፈሳዊ ክስተቶች በስተጀርባ ያለውን የአስተሳሰብ ጥበብን ንድፍ የሚያመለክቱ ናቸው። ለዚህም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔር ሥራ በእሱ ደስ በሚሰኙ ሁሉ መጠናት አለበት የሚለን (መዝ 111፡2 ተመልከቱ) እንዲሁም ተፈጥሮ ለዙህ ነው የእግዚአብሔር ክብርን የምታውገጀው (መዝ 19)፣ ይህም በራሱ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ባሕሪና ኃይል እውነተኝነት እንዲያረጋግጥ በቂ ማስረጋ ነው (ሮሜ 1 19-21 ተመልከቱ)።

5. በቅድስና ህይወት በመመላለስ

የክርስቶስ ተከታዮች በቅድስና ህይወት ሲኖሩ፣ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ፍሬን ሲያፈሩ፣ መንፈስ ቅዱስ ይህንን በመጠቀም አማኝ ወዳልሆኑት የሃጥያት ወቀሳን ያመጣል፣ (በሉቃስ 5፡8 ላይ ከኢየሱስ ጋር በለመሆኑ በጴጥሮስ ላይ  የመጣን ወቀሳ በሉቃስ ዘገባ ተመልከቱ)።በተጨማሪም በህይወት ውስጥ፣ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ እየፈለገ የነበረው እንደ የእግዚአብሔር ሰው  ስሚዝ ዊግልስዎርዝ አይንት ሰው አጠገብ፤ በባቡር ዉስጥ ወይንም መናፈሻ ወንበሮች ላይ ስለተቀመጡ ሰዎች ስለሐጥያታቸው የተወቀሱበት የተለያዩ ጽሁፎችን አንብቤያለሁ። በተጨማሪም፣ የቻርልስ ፊኒ የግል ህይወት ታሪክ ውስጥ፣ በአንድ ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ ፋብሪካ፣ በአጋጣሚ እግሩ በረገጠበት ጊዜ ስለሚያደርገው ወንጌላዊ ስብሰባዎች  ይተርካል፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከኀጢያታቸው መወቀስ የተነሳ በብዙ ሲያዝኑና ሲያለቅሱ፣ የፋብሪካው ባለቤት ሥራውን ዘግቶ ሃይማኖታዊ አገልግሎት መስጠት ጀምሮ እንደነበር ይተርካል።

6. በቤተ-ክርስቲያን ፍትሕን በመስራት

የኢየሱስ ተከታዮች፣ የተራቡትን በመመገብ፣ ለማያውቋቸው ሰዎች እንክብካቤ በማድረግ፣ የታሰሩትን በመጠየቅ፣ የተቸገሩትን እና የታመሙትን ሰዎችን በመርዳት፣ እርሱን እንዲመስሉ፣ ለተከታዮቹ ነግሯቸው ነበረ (ማቴ 25 ተመልከቱ)። በተጨማሪ ሚክያስ 6: 8 ላይ ሲያስታውሰን፤ እግዚአብሔር ህዝቡ ፍትህን እንዲያደርግ እንደሚፈልግ፣ በምሕረት በመኖር እና ከእርሱ ጋራ በትህትና እንድንመመላለስም ነግሮናል። ስለሆነም፣ የክርስቶስ ተከታዮች እንደዚህ ዓይነት ህይወት ሲኖሩ፣ መንፈስ ቅዱስ በታላቅ ባርኮት የሚኖሩ ህዝቦችን ያሳየናል (ማቴ 5 1-16 ይመልከቱ)። ይህም በሰማይ እንደሚኖረው ህይወት በምድር ላይ እንዴት መለማመድ እንደሚቻል ልክ እንደ ቅምሻ ነው (ሉቃ 11 2-4 ተመልከቱ)። በዚህም መንፈስ ቅዱስ፣ ኃጢያተኞችን እና የማያምኑትን ዓለም ለመውቀስ ይጠቀምበታል።

7. ኢየሱስን እንደ ጌታ በቃልና በድርጊት በማምለክ

ኢየሱስ፣ ተከታዮቹን በከንፈራቸው ብቻ ከመውደድ ይልቅ የእርሱን ፈቃድ እንዲታዘዙ እንደሚጠብቅ ግልጽ አድርጓል (ማቴ 7:21፣ ማር 7 13,14)። ስለሆነም: እጅግ በጣም ብዙ የሆኑት የክርስቶስ ተከታዮች ትእዛዛቱን በመታዘዝ ኢየሱስን ሲያመልኩ (ዮሐ 14:15) እና እሑድ ብቻ ሳይሆን፣ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ድረስ እርሱን በመታዘዝ ህይወት ሲኖሩ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ውስጥ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አጥብቆ ይወቅሳል በዚህም ዓለም፣ ኢየሱስ በእውነትም የዓለም ጌታ እና አዳኝ እንዲሆን በአብ የተላከ ንጉስ እንደሆነ እንድታውቅ ነው!

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox