መነቃቃት እንዲመጣ ምን ይጠይቃል

ዴሪክ ፕሪንስ :

መነቃቃት እንዲመጣ ምን ይጠይቃል? በደቡብ አፍሪካና ናሚቢያ ውስጥ ናማኳላንድ የሚባል አንድ ልዩ ቦታን የሚመለከት ምስል ላካፍላቹ። ናማኳላንድ የተለመደ ስፍራ አይደለም ምክንያቱም ለብዙ ወሮች ከሌሎች በተለየ ሁኔታ ምንም ዝናብ አያገኝም። መሬቱ በሙሉ ደረቅ፣ እርባታና እፅዋት የሌለበት ሥፍራ ነው። ይሁን እንጂ የበልግ ዝናብ በሚጥልበት ጊዜ ይህ ክልል በተዋቡ አበቦች ያሸበረቀ ይሆናል። ምንም እንኳ በሺዎች የሚቆጠሩ የአበቦች ዘር በመሬቱ ግፅታ ውስጥ ተቀብሮ ያለ ቢሆንም፤ ፈክቶ እንድዲያብብ ግን ዝናብ መኖሩን ይጠይቃል።

ዛሬም ቢሆን አብዛኛዎቹ ቀደምት የክርስቲያን ሀገሮች እንደ ናማኳላን ናቸው ብዬ አምናለው። እጅግ በጣም የደረቁ እና ምንም ሕይወት በውስጣቸው ያለባቸው እንኳ አይመስሉም። ነገር ግን ከወለሉ በታች እውነተኛው የወንጌል ዘር፣ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በእነዚህ ሀገሮች ተቀብሮ ይገኛል። እግዚአብሔር በእነዚህ በአንቀላፉ ዘሮች ላይ ቅዱሱ መንፈሱን ቢያፈስስ፣ የለውጥ ሕይወትንና ዉበትን በምልከታ እናያለን።

ድርሻችን ምንድነው?

የመንፈስ ቅዱስ ዝናብ በመፍሰስ ሂደት ውስጥ እኛ የምንጫወተው ሚና ምን ይመስላል? ይሄን ጥያቄ ለመመለስ የተመሰቃቀለ ምስል አሳይቶን የሚነሳውን የኢዮኤልን መጽሐፍ መመልከት ይቻላል። እህሉ ጠፍቶአል፣ እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፣ በምድሪቱም ፍሬ የለም። ሁሉ ነገር ደርቆ ወድሟል። ለሕዝቡ እንዲሁም ለእንስሳቶቹ የሚሆን ምግብ አልነበረም። ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ ይህን እናነባለን

“አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ። የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?” (ኢዮኤል 2፡12-14)።

ከሰዎች ምን ይጠበቃል? መማጸን ነው።

ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤ በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበክላቸው ይገኛሉ (ኢዮኤል 2፡28-32)።

ይሄ ክፍል፣ “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን” ማለቁን በግልፅ ያስረዳናል። ለምንድነው “የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” የተባለው? ምክኒያቱም መንፈስ ቅዱስ በመፍሰስ ላይ ስላለ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ሲፈስ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሲፈልሱ እንመለከታለን።

አስቸኳይ የፀሎት ጥያቄ

በአስቸኳይ ምላሽ ልሰጡት የሚገባ ጥያቄ ላቀርብላቹ እወዳለው። በ1950ዎቹ በለንደን ከተማ ዉስጥ በማገልገል ላይ ሳለው፣ በብሪታንያ መነቃቃት እንዲመጣ በየሳምቱ እንጸልይ ነበር። ምንም እንኳ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ቢሆነውም፣ እኔ በግሌ እነዚያ ጸሎቶች እንዲያው ሳይሰሙ አለፉ ብዬ አላምንም። ይህ ታድያ ለበርካታ ዓመታትና በብዙ ሃገራት ታማኝ አማኞች መነቃቃት እንዲመጣ የጸለዩትን ሕዝቦች ሁሉ ይጨምራል። ይሁን እንጂ የመጨረሻዎቹ መልሶች የመማጸን ጸሎት ያስፈልገዋል።

ሌላ ተስፋ እንደሌለ፤ ከእውነታው ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ጣልቃ ካልገባ ሀገራት ጨርሶ ይጠፋሉ፤ እናም እግዚአብሔር የመማጸኛ እንባን ይጠብቃል። እኛ በራሳችን ተስፋ ለመቁረጥ መሞከር ጥቅም አልባ ነው። የፀጋና መማጸንን መንፈስ ሊያፈስብን የሚችለው እርሱ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።

ጥያቄዬ እንደዚህ ነው፣ በግልጽም ልጠይቃቹ እፈልጋለው። ከመመለሳቹ በፊት የመንፈስ ቅዱስን ምሪት እንድትጠይቁ ተስፋ አደርጋለሁ። የመማጸንን ጸሎት እንድትጸልዩ ዘንድ፣ መንፈስ ቅዱስ እናንተን በማነቃቃትና በማብቃት ሂደት ውስጥ እራሳቸውን በመስጠት ከቆረጡት ወገን እንደምትሆኑ እንድጠይቃቹ እግዚአብሔር በልቤ አስቀምጧል ብዬ አምናለው። እንዲህ ባለ መማጸን በመጸለይ ወደራሳቹ ማብቂያ ለመድረሳችሁ እውቅና መስጠትን ይጠይቃል።

እኔ የሰጠዋችሁን ፈተና በጥንቃቄ ያስቡበት። ለእግዚአብሔር ላይ ላዩን ምላሽ እንድትሰጡት ፍላጎቴ አይደለም። ነገር ግን፣ መንፈስ ቅዱስ “በሃገራቹ መነቃቃት እንዲመጣ መማጸን ትችሉ ዘንድ እንዳደርግ ፈቃደኛ ነቹ? በህይወትዎ ውስጥ እንድሻግራቹ፣ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚያስፈልገውን ተቀዳሚ እንዳደርግ፣ እና አስፈላጊ ከሆነ፣ ከሰማይ ሰማያት ዝናቡን ሲዘንብ እስከምታዩ ድረስ፣ በኔ ፊት በየቀኑ ወለሉ ላይ በግንባራቹ እንድትወድቁ አደርጋቹ ዘንድ ፍቃደኛ ናችሁን? ” በማለት መንፈስ ቅዱስ ሲጠይቅ ትሰማላቹ ብዬ ተስፋ አደርጋለው።

እንዲህ ዓይነቱ ጸሎት መንፈስ ቅዱስ ለሚመራቸው ሰዎች ጥሪ ነው። ይህ ለሁሉም ሰው አይደለም። የመማጸን ሮሮ ከተፈጥሮ በላይ ነው፤ እናም ከመንፈስ ቅዱስ ይወጣል። እናንተ ለዚህ እደተጠራቹ ባይሰማቹ፣ በራሳቹ ጉድለት ምክንያት እንዳይደለ ልትረዱ ያስፈልጋል። ይህ ከመንፈስ ቅዱስ የመጣ ጥሪ ሲሆን በውስጣችን ባለ ምንም አይነት ችሎታ ላይ የተመሰረተ አይደለም። እርሱ ይህንን በልባቹ ውስጥ ካላስቀመጠ፣ ለአንተ የሚሆን ሌላ ነገር ስላለው ነው።

ስለዚህ፣ ለአንድ አፍታ አሁኑኑ መንፈሱን ያዳምጡት። እግዚአብሔር በዚህ መንገድ ሊጠቀምባቹ እንደሚያስብ ካመናቹ፣ በቀጣዩ የጸሎት ጊዜአቹ በዚህ ጥሪ ውስጥ እርሱን ለመከተል ፈቃደኝነታችሁን በቀላሉ ግለጹ፡

አባት ሆይ፣ በመገኘትህ ውስጥ በአድናቆት እቆማለሁ። ወደ እኔ ስለመጣው የቃልህ ፈተና አመሰግናለሁ። ለሕዝቤ ምህረት ወደ አንተ እጮኻለሁ። እግዚአብሔር ሆይ ማረን! በፍርድህ ውስጥ በምልጃ አስበን። በጸሎቴ ውስጥ ስኬትን እንድለማመድ በጸጋ እና ቅዱሱ መንፈስህ አብቃኝ – በመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ ውስጥ በመጠማት ለመጸለይ እንድንችል ይህን ሕዝብ ወደ ራስህ መልሰው እንድትጎበኛቸው እጠይቅሃለሁ። አባ ሆይ፣ በምድራችን መነቃቃት ይመጣ ዘንድ በቅዱስ መንፈስህ ተንቀሳቅሰህ እንድሰራ እጸልያለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox