ለትዳር ጥንቃቄ

ከፀጋው ምንጭ፡- ሪነዋል ማጋዚን 1996 :

የልጆቻቸውን ዕድገት የማይወዱ ወላጆች የሉም በትክክለኛው ጎዳና መራመዳቸውንም እርጠኛ መሆን ይፈልጋሉ ፡፡

ከዚህም የተነሳ በልጆቻቸው ትዳር ውስጥ እንኳ በመግባት ሊመሯቸውና ሊቆጣጠሩአቸው የሚዳዳቸው ጥቂቶች አይደሉም በመሰረቱ ትዳር ሁለት ተጋቢዎች በጋራ በመሰማማትና በመረዳዳት የሚመሩት ሕይወት እንጂ ብዙ ሰዎች የሚያስተዳድሩትና አመራር የሚሰጡበት ድርጅት አይደል ቤተሰብ የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለው አይካድም ሆኖም ውሳኔዎች መተው ያለባቸው የተጋቢዎቹ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ጋብቻ አማካሪነት የ25 ዓመት ተሞክሮ ያላቸውን ዶ/ር ዊላርድ ሃርሌ በትዳር ውስጥ አለመግባባትን ከሚፈጥሩ ጉዳዮች ሁለቱን ከገጠመኞቻቸው ጋር ለምሳሌ ያህል እንዲህ አቅርበውታል፡፡ ወደ ቢሮ ወጣት ባልና ሚስቶች መጥተው ያገጠማቸውን ችግር እንዲህ ሲሉ ገልጸውልኛል ሄለንና ዮሐንስ ይባላሉ፡፡ የሄለን ወላጆች ለብዙ ዓመታት የሚያልኩበት ቤተክርስቲያን አባል እንዲሆኑ ሄለንና ዮሐንስን ወደ ወላጆቿ ቤተክርስቲያን እንዲሄድ ግድ ትለዋለች በእጮኛምነት ዘመናቸው ሁለቱም ዮሐንስ ወደሚያመልክበት ቤተክርስቲያን አዘውትረው ይሄዱ ነበር አሁን ከተጋቡ በኋላ ግን ድንገት በባለቤቱ ወላጆች አስገዳጅነት አባል እንዲሆኑ የተወሰነበት ቤተክርስቲያን ግን ዮሐንስ ፍፁም አልወደደውም ለዓመት ይህል እያጉረመረመ ቢመላለስም ነገሩ ደስ ስላላሰኘው የምናምልክበትን ቤተክርስቲያን ወላጆችሽ ሊመርጡልን የሚገባ አይመስለኝም ወትሮ በእኔ ቤተ ክርስቲያን አብረን ስናመልክ ደስተኛ እንደነበርን ታውቂያለሽ ስለዚህ ከአሁን በኋላ እያዘንኩ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ስማልፈልግ ወደሚመቸኝ ቤተክርስቲያን መሄድ ራሳችን መርጠን እንሄዳልን ሲል ውሳኔውን ያሰውቃታል በዚህ ደስ ያልተሰኘችው ሄለን አይሆንም ከወላጆቼ መቀያየም አልፈልግም በዚህ ችግር ውስጥ እያሉ ነበር ከነጥያቄአቸው ወደ ቢሮዬ የመጡት እኔም ሄለንን እንዴት እንዲህ ያለ ራስ ወዳድ ውሳኔ ትወስኛለሽ? ለወላጆችሽ ደስታ ስትይ የባለቤትሽን ፈቃድና ስሜት እንደተረማመድሽበት አታስተውይም? ወላጆችን ደስ ማሰኘት ቢገባም የእናንተን ውሳኔ እነርሱ እየወሰኑላችሁ በመኖር አይደለም በማለት በዚህ ጉዳይ ላይ ጸልየው ተስማምተው ወደፈቀዱት ቤተክርስቲያን እንዲሄዱ መክሬአቸው ተለያየን ተለያን ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሁለቱም ልባቸው የረፈበትን ቤተክርስቲያን እንዳገኙና እዚያ አባል እንደሆኑ ደስተኞችም እንደሆኑ መጥተው ነገሩኝ፡፡

በባልና ሚስት የግል ውሳኔ ውስጥ የሚገቡ ወላጆች በተጋቢዎች ፍቃድና ስሜት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚጨምሩ ሊዘነጉ አይገባም ‹‹ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ስለዚህ ወላጆችም ልጆቻቸውን ለራሳቸው ውሳኔ ቢተውአቸው መልካም ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የባልን ወይም የሚስትን ጓደኛ ከሚገባው በላይ መቅረብ የሚያስከትለው ችግር ነው፡፡ ሳይታወቅ መቀራረቡ ወደ መፈቃቀር ደርሶ ትዳር የታወከባቸውም ሆኔታዎች አሉ ለረጅም ዓመታት በመልካም ጉርብትና የኖሩ ሁለት ክርስቲያን ቤተሰቦች ከደረሰባቸው ችግር የተነሳ ልምክር ወደ እኔ ይመጣሉ አንደኛው ቤተሰብ ጡረታ ስለወጡ ቤት ገዝተው ቀሪ ዘመናቸውን ለማሳለፍ ወደ አንድ የገጠር አከባቢ ይጓዛሉ፡፡ ከዓመት በኋላ ጎረቤቶቻቸው የነበሩትም ባልና ሚስት በጡረታ ሲገለገሉ እነርሱ አጠገብ መረት ገዝተው ቤት ሠርተው እንዲኖሩ ይመክሩአቸው እና በሃሳቡ በመስማማት የቀድሞ ጎረቤቶቻቸውም አጠገብ መጥተው ጎን ለጎን ቤት ሠርተው መኖር ይጀምራሉ፡፡ የሁለቱ ሰዎች ሚስቶች በጣም የተቀራረበ ጓደኝነት ስላላቸው አንዳቸው ሌላይቱን ቤት በመሄድ ይጽናኑ ነበር መቸም ሞት አይቀርምና ድንገት ኋላ የመጡት ቤተሰብ አባወራ ይሞታሉ፡፡ በዚህ ወቅት በአጠገባቸው ማንም ስላልነበረ ጎረቤቶቻቸው እያጽናኑአቸው ሴትየዋ ይበረታሉ አባወራው ሲሞት የሚያጎድለው ነገር አለና የሚስታቸውን ጓደኛ ለማጽናናት አጥራቸውን ለማጠባበቅ የሚሰራ የወንድ ሥራ ካለ ለመርዳት ሚ/ር ቶማስ ጎረቤታቸው ጋ መመላለስ ያዘወትራሉ፡፡

ለካስ ቀስ በቀስ ሁለቱንም ፍቅር ይዟቸው ኖርዋል፡፡ ይህንን የሚ/ር ቶማስ ባለቤት ይደርሱበትና በባልና በሚስቱ መሃልና በጓደኛሞቹ መካከል ከፍተኛ ችግር አለመግባባት ይፈጠራል በዚህ ወቅት ነበር ሚ/ር ቶማስ ከባለቤታቸው ጋር ምክር ለመጠየቅ የመጡት፡- ታሪኩን ካዳመጥኩ በኋላ ሚ/ር ቶማስ በል እንገዲህ ለዚህ ሁሉ ያበቃህ ከባለቤትህ ጓደኛ ጋር ከገደብ ያለፈ መቀራረብ መጀመርህ ነውና ጥፋትህን አምነህ ባለቤትህን ይቅርታ ጠይቅ አልኩት በዚህም ተስማማ ነግር ግን ዘላቂ መፍትሄ እንደማይሆን ስለተገነዘብኩ ዘወትር በጥርጣሬ እንዳይኖሩ ‹‹ቤታችሁን ሽጡና ራቅ ወዳለ ቦታ ሄዳችሁ ቤት ግዙ›› አልኳቸው በመጀመርያ ሚ/ር ቶማስም ሆነ ባለቤታቸው ሀሳቡ ከበዳቸው ሆኖም ውሎ አድሮ በነገሩ ስላመኑበት ቤታቸውን ሸጠው ወደ ሌላ ከተማ ሄደው መኖር ጀመሩ የትዳር ሕይወታቸውም እንደገና እንደታደሰ ሰማሁ፡፡ ለረጅም ዓመታት የኖረ የጓደኝነት ሊኖረን ይችላል፡፡ ጓደኞቻቸውንን እጅግ ልንወዳቸው እንችላለን፡፡ ሆኖም ይህ መቀራረብና መዋደድ በትዳራችን መካከል መግባት የለበትም ለሁሉም ተገቢ የሆነ ገደብ ልናበጅለት ይገባል፡፡ ክርስቲያን ስለሆንን ብቻ እንደዚህ ዓይነቱ ችግ አያጋጥመንም ብለን ድምዳሜ ላይ መድረስ አይገባንም፡፡

ለትዳር እንቅፋት የሚሆኑ ልናስወግዳቸው የሚገቡ ነገሮችን ሥር ሳይሰዱ ማስወገዱ አስተዋይነት ነው ሲሉ እኚህ የትዳር አማካሪ ያሳስቡናል ለትምህርት የሚሆነንን ለራሳችን እናስቀር፡፡

ከፀጋው
ምንጭ፡- ሪነዋል ማጋዚን 1996

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox