የማበሻውን ጨርቅ እናንሳ _ ዴቪድ ዊልከርሰን ጽፎት ናን ኤልኤዘር እንደተረጎመው

ዴቪድ ዊልከርሰን ጽፎት ናን ኤልኤዘር እንደተረጎመው :

መደረቢያውን አኑሮ የማበሻውን ጨርቅ በማንሳት የደቀሙዛሙርቱን እግር አጣጥቦ ካበቃ ቡኋላ እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን መተጣተብ ይገባችሁዋል በማለት ነበር ማንኛችንም ልንቀበለውና በሕይወታችን ሰርፆ ሊገባ የሚገባውን መልዕክት ክርስቶስ ለተከታዮቹ ያስተላለፈው፡ አንዳንድ ክርስትያኖች ይህን ክፍል ቃል በቃል አሊያ ጥሬ ትርጉም ብቻ ላይ ስለሚያተኩሩ ‹‹ እግር መተጣጠብ›› የሚለውን ጽንሰ ሃሰብ ልማዳዊ ሥርአት ብቻ እያደረጉት መጥተዋል እንገዲህ ጥልቅ የሆነው የክርስቶስ ትዕዛዝ በዚህ ልማዳዊ ድርጊት ማትም አንዱ የአንዱን ሥጋዊ እግር በማጠብ የሚቀጥል ከሆነ መንፈሳዊ መልዕክቱ እየደበዘዘ መክሰሙ አይቀርም፡፡ቃሉ እንደሚነግረን ክርስቶስ እግር የማጠብ ተግባሩን ካከናወንና መደረቢያውን ለብሶ ከተቀመጠበት በኋላ የሚከተለውን ጥያቄ ሰነዘረ ‹‹ምን እናደደርግ ሁላችሁ አስተዋላችሁን›› በሌላ አባባል ‹‹እግር የማጠቤ መንፈሳዊ ሚስጥር ምን እንደሆነ ልብ ብላችሁዋልን? እንደኔ እምነት በዚያን ወቅትና በዚያ ስፍራ የሰነዘረው ጥያቄ በዚህ ትውልድ ያለነውንም ሁሉ የሚያጠያይቅ ይመስለኛል፡፡ በዚያ ክፍል ክርስቶስ ጠንካራና ጥልቅ የሆነ መልዕክት ለማስተላለፍ እንጂ ስለተራ የመተጣጠብ ሥርዓት ሊናገር እንዳልፈለገ ምን ያህሎቻችን ልብ ብለነው ይሆን? ስለዚሁ ክርስቶስ በተግባር ስላከናወንነው ጉዳይ የቤተክርስትያን አባቶች ግንዛቤና አመለካከት ለማወቅ የመጽሐፍ ቅዱስ አንድምታዬን ማገላበጥ ጀመርኩ ሁሉም በአንድ ሐሳብ ዙሪያ የተኮለኮሉ ይመስላል ‹‹ራስ ማዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ›› በሚለው መረዳት ሥር የኔ የእይታ ግን ከዚህ ያልፋል ትሁት የመሆንን ምሳሌነትማ ከክርስቶስ ያሳየን ክብሩን ጥሎ በወረደበት ወቅት ነበር ለዚህም ነው በዚህ ሥፍራ ላይ ከዚ ስለተለየ አሳብ ያወሳል ብዬ መናገር የምፈልገው የማበሻውን ጨርቅ ስለ ማንሳት አሳብ፡፡

ከቃሉ እንደምናነው ክርስቶስ በንግግሩም ሆነ በድርጊቱ በግጽ ያስቀመጣቸው አንዳንድ ጉዳዮች ካሉበት ሁኔታ በላቀ መንገድ ሊናገሩ የሚያስችላቸውን ታላላቅ ምስጥራት አዝለዋል ‹‹መስቀልን ተሸክሞ የመከተል ሕይወት የአሳነካዩ እጅ መቆረጥና የአሰናካዩ ዓይን መውጣት ሂደት ጠፍሬው መውደቅና መሞት ምሳሌ የሁለተኛውን ምዕራፍ መራመድ ግዴታ›› እነዚሁሉ ከጥሬፍቺያቸው ባሻገር ብዙ የሚናገሩት ጥልቅ እውነት አላቸው የማበሻውን ጨርቅ ማንሳት ሂደትም ቢሆን በዚህ ሁኔታ ነው ሊጤን የሚገባው በረጅም ዘመን የአገልግሎት ዘመኔ በርካታ ምዕመናን ወደ እኔ እየመጡ ‹‹ክርስቶስ እንዳደረገውና አድርጉ ብሎ እንዳዘዘው እርስ በእርሳችን የማንተጣጠበው ለምድነው?›› በማለት ይጠይቁኛል እኔም ‹‹ክርስቶስ አካላዊውንና ውጫዊውን ሥርዓት ሳይሆን መንፈሳዊ ምስጥሩ ላይ ነው እንድናተኩር የሚሻው ስል›› እመልስላቸዋለሁ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን መልስ በምሰጥበት ሰዓትም እንኳን ቢሆን ስለዚህ ጠለቅ ስላለው መንፈሳዊ ምስጢር ምንም ዓይነት መረዳት አልነበረብኝም ስለዚህ ሳይሆን አይቀርም ዘለግ ላሉ ዘመናት የዚህ የክፍል ብር መልዕክት ብዥ እያለብኝ የከራረመው በቅርቡ በጸሎት ላይ እንዳለሁ ሦስት የተለያዩ ቃላትን መንፈስ ቅዱስ ወደልቤ አመጣ እነዚህም ቀላት ‹‹የማበሻውን ጨርቅ ማንሳት›› ስለሚለው ጽንስ አሳብ ግልጽ የሆነ መረዳት እንዲኖረኝ አገዙኝ፡፡

በደልን ማጥራት
በቁጥር አሥራ ሁለት የነበሩት ደቀመዛሙርት በክርስቶስ የተወደዱ ልበ ቅኖችና ከመምህራቸው ጋር ፍጹም ሕብረት የነበራቸው ቢሆንም ያሁኔታ በእግሮቻቸው ላይ ትቢያን ተሸክመው ከመሄድ አላገዳቸውም፡፡ ለዚህም ይመስላል ክርስቶስ የተቀረው ክፍላችሁ ንጹህ ነው እግሮቻችሁ ግን አይደለሉም፡፡ በእየለቱ ጉዞኣችሁ የሚሰበሰቡትን ብናኝ አለ ስለዚህ እግሮቻችሁን እንጂ መላው አካላችሁን መታጠብ አያሻችሁም በማለት የተናገረው፡፡ ክርስቶስ ሲያስገነዝባቸው የፈለገው ተፈጥሮአዊ ስለሆነውና በእግራቸው እየሰበሰቡ ስለሚመጡት የአቧራ ብናኝ አይደለም፡፡ የማበሻውን ጨርቅ የሚያነሱ እውነተኛ አጽናኞችናመንፈስ ቅዱስም የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡

ስለ ኃጢአት ብናኝ ነው ስለ መተላለፍና ውድቀት ብናኝ ነው ወደ ፈተና ሮጠን በመግባታችን ስለምንጎትተው የበደል ብናኝ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በኢየሩስ ኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ስለሚንከባለለው አቧራ የማውራትም ሆነ ዓላማዬ ብሎ እግር የማጠብ እቅድና ውጥን አልነበረውም፡፡ ገላትያ ስድስት አንድ ላይ ‹‹ወንድሞች ሆይ! ሰው ማናቸውንም ስሕተት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳዊያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዓይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት ነገር ግን አንተም በዚህ ዓይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ›› የሚል ቃል ሰፍሯል በዚህም ስፍራ ‹‹ስሕተት›› ተብሎ የተጠቀሰው ቃል በግሪኩ ልሳን ‹‹ውድቀት›› ኃጢአት መተላለፍ ..›› በተሰኙ ቃላት ሊተከጃ ይችላል ስለዚህ ማንኛውም ክርስትያን በየትኛውም ስሕተት ውስጥ ቢገኝ ከጥፋቱ የመመለስ ቅን ልብ እስካለው ድረስ በየዋህነት ልንደግፈው ይገባል እንዲህ ጠለቅ ያለው እግር የማጠብ ምሳሌነት ይህንኑ ነው የሚያመለክተን፡፡ በናንተ በኩል ወንድሞቻችሁ ላይ የሚታየውን ጉድፍ እንዴት አድርጋችሁ እንደምታጠሩ አላውቅም ሆኖም በክርስቶስ አገልግሎት ውስጥ የማበሻውን ጨርቅ ሲነሳና የሌሎችን ጉድፍ ለማራገፍ ጥቅም ላይ ሲውል ነው የምናስተውለው፡፡

ግልጽ ሆኖ መናገር ቢያስፈልግ አንዳንድ ክርስትያኖች ርህራሄ የሌላቸውና ክፉዎች ናቸው እንዲያውም በዓለም ናቸው እያልን ከምንዘልፋቸው ሰዎች በላቀ ደረጃ ጨካኞችና በጥባጮች ሆነው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ የዚህ ዓይነቱ ባህሪ ይዘው እንደሚጓዙ ጌታም ያውቃል እኛም ስለዚህ ሰዎች በጽድቅ ማነስና በኃጢአት መቆሸሽ የምንሰጠውን ፍርድና የምናሰማውንም ሐሜት በዚያው ልክ ያጠየነዋል፡፡ እርግጥ ስጋውያን የሆኑ ክርስትያኖች የወንድሞቻቸውን ጉድፍ ፈጥኖ የማመልከት ባህሪ እንዳላቸው አይካድም ይሁን እንጂ የሌላውን ጉድፍ እየመዘዙ ለተቀሩት የማዳረስና በየሥፍራው የመበተን ሕመም ደግሞ ከሌሎች ሁሉ የከፋ የኃጢአትን አቧራ መሆኑን በዚያው ልክ አያጤኑም፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ልጅ እግር ከሆነ መጋቢ ጋር ተገናኝተን የሥነምግባር በደል መፈጸሙን በማመን ለቤተክርስትያን ካሳወቀ በኋላ ሥራውን ያስረክባል ምነም እንኳ እግሩ በኃጢአት ትቢያ ቢበከልና ልቡ በኃዘን ቢመታም ለክርስቶስ ለክርስቲያኖችና ለእግዚአብሔር ቃል ያለው ፍቅር ዛሬም አልቀነሰም ቀርቤ አጽናናሁት ልቡ እንዳይወድቅ አበረታሁት፡፡ በኃጢአት መውደቁና ከሥራ መሰናበቱን እንደሰማሁ ወደ እሱ ፈጥኜ እንድሄድ መንፈስ ቅዱስ ነበር ያመላከተኝ በዚያ ሁኔታ ላይ እያለ እንኳ የልቡ ገርነት አልተለየውም መቼም በቅጽበት ጊዜ ውስጥ በኃጢአት እንዳልወደቀ ይገባኛል ያመ ሆኖ በዚያ በደል ለመቀጠል እልከኝነት አይታይበትም፡፡ ያውቃቸው የነበሩ ወዳጆቹ ራቁት ወንድም እገሌ እንወድሃለን ሲሉ ውዳሴ ከንቱ ሲያዘንቡለት የከረሙት ሁሉ አንዳች ተላላፊ በሽታ እንደወደቀበት ሕመምተኛ ይርቁት ጀመር ከሁሉም የከፋው ያመልክበት የነበረው ቤተክርስትያን መሪዎች በዝርዝር ጉዳዮች ንስሐ የገባበትን ቪድዮ በየአካባቢው ማሰራጨታቸው ነበር፡፡

የማበሻ ጨርቄን አንስቼ እንዲህ አይነቱን ሰው ቀረብኩት ወዳጄ ከልቤ እንደምወድህ ልንገርህ እፈልጋለሁ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ገና ብዙ ያላለቀ ሥራ አለው ዛሬም እንኳ የሚመለስ ልብ ካለህ ክርስቶስ ሊቀበልህ ዝግጁ ነው እኔም ከጎንህ ቆሜ እደግፍሃለው የሚለውን መልዕከክት አስቀመጥኩለት የማበሻውን ጨርቅ ለማንሳት ፈቃደኛነትና ራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠትን ፈጽምና ባለው የውስጥ ኃይል የሌለው ጉድፍ ለማጠብ የመብቃትን ብርታት ይጠይቃል ‹‹ የእኔ ወንድም በክርስቶስ ውስጥ ጸንተህ እንድትኖር ለቤተሰብህ የሚገባውን ላደርግ የእግርህን ጉድፍ ላጥራና በንስሐ እንድትመለስ ልርዳህ እስመጨረሻው ከጎንህ ለመቆም እፈቅዳለሁ የሚለውን የማበረታቻና የድርጊት ቃል ለመፈጸም የሚያበቃንን ጸጋ ማግኘትን ይጠይቃል፡፡ ይህ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የመጋቢው ወዳጅ ስልክ ደወለልኝና ‹‹ ዳዊት ያንተ ድጋፍ ለጉዋድኛዬ ምን ያህል ድጋፍ እንደሰጠው ምናልባት አሁን ላይገባህ ይችል ይሆናል ነገር ግን እነዚያ ከአንደበትህ የወጡት ውብ ቃላት ለጉዋደኛዬ በረከት ሆኖታል ብርታት እንዲያገኝ ረድቶታል ብቻውን በነበረበትና ማንም ሊደርስለት ባልፈለገበት ወቅት አዲስ ተስፋን በውስጡ አስቀምጠዋል›› በማለት አወጋኝ፡፡

መጽሐፍቅዱስ ማንም በበደል ቢገኝ በዳዩን ሰው በፍቅር ልናገለግልና ወደ እግዚአብሔር ፍርሃት ልናስጠጋው እንደሚገባን በግልጽ ይነግረናል ይሁን እንጂ የብዙዎቹ ጥያቄ ‹‹እንደምን አድተርገን ይህን መፈጸም እንችላለን?›› የሚለውን ነው፡፡ እኔ ግን ‹‹አሁንም ቢሆን የምሕረትን ፎጣ በማሳት ልቡ ወዳዘነበት ሰው እናምራ ኃጢአቱን ገሃድ ለማውጣት አካባቢውን አንቆፍር ክርስቶስ ባሳየን የፍቅር ልክ ማበሻውን ይዘን እንቅረበው ወዳጁ እንሁን በርህራሄ እየገሰጽን በደሉን እናርም በእግዚአብሔር ቃልም እናጽናናው የሚለውን እውነት ነው መናገር የምፈልገው ይህ ድርጊት ኃጢአትን ማባባልና ክፉውን መልካም አሰኝቶ መጥራት አይደለም እየተናገርኩ ያለሁት በበደል ውስጥ ስላሉና በበደላቸውም ስለተጸጸቱ ያም ሆኖ ተስፋ ስለተሟጠጠባቸው ጻድቃን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ጌታን ማሳዘናቸው የገባቸው ቢሆንም በፍርሃት በበደለኝነት ስሜትና በመገለል ውስጥ ነው ያሉት፡፡

ደግሜ ያነሳሁት ፍሬሐሳብ ሁለቴና ሦስቴ አሊያም ከዚያበላይ ምህረት ተደርጎላቸው በእልከኝነት ስለጸኑ ሰዎች አይደለም እንደዚህ ዓይነቶቹን ‹‹አማኞች›› የተቀረው ጉባዔ ሁሉ እግዚአብሔርን እንዲፈራ ያለርህራሄ ልንገስጻቸው ከዚያም አልፎ በፍጹም ልብ እስኪመለሱ ድረስ ከኀብረት ልናግዳቸው ይገባል በደላቸውን የተገነዘቡ ኃጢአታቸውን የጠናዘዙና ፈጽሞ የተውት ግን ምሕረትን የሚያደርግ በደልን የሚያብስና ቁስልን የሚፈውስ ፎጣ ያስፈልጋቸዋል ከጥቂት ዓመታት በፊት የአንድ ቤተክርስትያን ተባባሪ ፓስተር ዓይኖች እንባ እንደገቱ ‹‹ዳዊት ልቤ በሀዘን ድመቷል በዚህ ሳብያ በማገለግላቸው ሰዎች ፊት አንገቴን ቀና አድርጌ መራመድ አልቻልኩም›› በማለት አዋየኝ ምክኒያቱ ይሄ ነበር የዚህ ፓስተር ሴት ልጅ ከጋብቻ ውጪ ታረግዛለች ይህን የሰማው ዋና ፓስተር ረዳት የፓስተሩ በመእምናን ፊት ቆሞ ሴት ልጁ የሰራችውን ኃጢአት እንዲናዘዝ ያስገድደዋል ተባባሪው ፓስተር የተባለውን ሁሉ ፈጸመ ይሁን እንጂ በዚያ ሁኔታ በጉባዔ እንዲ ለፍፍ የተደረገው የበደል ኑዛዜ የፓስተሩን ሴት ልጅ ቅስም ሰበረ የቤተሰቡ ልብ አደማ፡፡ እንገዲህ በዚህ ድርታችን ነው የእግዚአብሔር ምሕረት የሚያስፈልገን እግሮቻቸው ላይ ትቢያ የተነሰነሰውን ወገኖቻችንን ለማስለቀቅ ማፈሪያ ለማድረግ ስለምንሮጠው አሳፋሪ ሩጫ ነው የምህረትን ፎጣ በማንሳት የሌሎችን ጉድፍ መጥረግ የምንማረው? በወንድሞቻችንስ ላይ የተጣበቀውን ትቢያ እየዘገንን በአየር ላይ ከመነስነስ በመታቀብ ሕይወታቸውን ከሞት እንታደገው

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox