በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ 3 ስህተቶች

በርት ኤም. ፋሪስ :

በቅርቡ አንድ የቴሌቪዥን ሰባኪ እንዲህ ሲል ሰማሁት “እግዚአብሔር አሜሪካ ላይ የሚፈርድ ከሆነ ኢየሱስን ይቅርታ መጠየቅ ይኖርበታል።”

ነገር ግን ቃሉ እንዲህ ነው የሚለው፥ “የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።” (1 ጴጥሮስ 3:12).

“ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል።” (2 ጴጥሮስ 2:9).

በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚታየው የመጀመሪያው ስህተት የእግዚአብሔርን ፍርድ እና ቁጣ በተመለከተ ያለው ቸልተኝነት ነው።  

  1. የእግዚአብሔርን ፍርድ አለመረዳት

የጠቀስኩት ሰባኪ መረዳቱ ሚዛናዊነት እና የእግዚአብሔር ሃሳብ እውቀት ይጎድለዋል። ኢየሱስ የሁላችንን ፍርድ ስለተሸከመ እግዚአብሔር በአሜሪካም ላይ ሆነ በማንም ላይ አይፈርድም ይላል። እውነት ለመናገር፥ ይህ አይነቱ የዕምነት ስረዓት የማያምኑ ሁሉ ይድናሉ ከሚለው አስተሳሰብ ጋር ተመሳሳይነት አለው ።

እንደዚህ ነው የሚለው፥ ኢየሱስ የሁሉንም ሰው ፍርድ በመስቀል ላይ ስለተሸከመ ማንም አይፈረድበትም። ሁሉም ሰው ሰላም ነው። በመጨረሻ ሁሉም ሁሉም ሰው ይድናል። በእርግጥ ይህ ታዋቂ እይታ ነው በቤተክርስቲያን ውስጥ መታለል እንዲበዛ ትልቅ በርን የከፈተው። ይህ በአማኞች ዘንድ ስንፍናን ፈጥሯል፣ ቅዱስ የሆነ ፍርሃትም እንዲጠፋ አድርጓል።  

በእርግጥ ሮሜ 1 አሜሪካ አሁንም እንኳን ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ስለመሆኗ ማረጋገጫ ይሰጠናል። 

 “እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤” (ሮሜ 1፥18) 

የእግዚአብሔር ቁጣ እየተገለጠ ነው፤ አሁን። በሌላ አነጋገር የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማየት እስከ ፍርድ ቀን መጠበቅ አስፈልገንም። አሁን እየተገለጠ ነው። ይህን ለመረዳት ቀጣዮቹን ቁጥሮች ማየት ያስፈልጋል።  

“እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤”(ሮሜ 1፥24)

“ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤”(ሮሜ 1፥26)

“ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤”(ሮሜ 1፥28)

እነዚህ ቁጥሮች የሚናገሩት ከስርአት ስለወጣ የወሲብ ልምምድ ነው፤ በተለይም ደግሞ የግብረሰዶማዊነት ሃጢያጥ። በእጠቃላይ የወሲብ አብዮት ተብሎ የሚጠራው የእግዚአብሔር ቁጣ ውጤት ነው። አሜሪካ ላለፉት ብዙ አስርት አመታት ከእግዚአብሔር ቁጣ በታች ትገኛለች። የኤድስ ተጠቂዎችን እንደጀግና ብናሞግሳቸውም፤ እውነታው ግን እርሱ ለሃጢያታቸው የተቀበሉት ቅጣት መሆኑ ነው።(ሮሜ 1፥27)        

በእርግጥ ሞት የሚገባውን ሃጢያት የሚያደርጉ ሰዎች በማያደርጉም ጭምር ሲበረታቱ ይህ በማህበረሰብ ላይ የተገለጠ የእግዚአብሔር ቁጣ የመጨረሻው ምልክት ነው። ቤተ-ክርስቲያን ሆይ ንቂ! አንዳንድ ሰባኪዎች ምን እያሉ ነው? አሁን እየሆነ ያለው ምንድን ነው? የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ህጋዊ ፍቃድ አግኝቷል፣ የትኛውም አይነት ውርጃም እንደዚሁ፤ ቀጣይ ደግሞ ምን እንደሚፈጠር ማን ያውቃል። የእግዚአብሔር ፍርድ እና ቁጣ በዚህ ነው ያለው! ማምለጥ ይችላሉ? አዎ ማምለጥ ይችላሉ። ከልብ ከሆነ ንስሃ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሱ አሁንም ምህረቱን መቀበል፣ መዳን እና ነጻ መዉጣት ይችላሉ። ብዙዎች ግን ይህንን አያደርጉም። 

  1. በቅድስና ላይ ያለ ልክ ያልሆነ እይታ 

ሁለተኛው በአሁን ዘመን ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያለው ልክ ያልሆነ እይታ ደግሞ ቅድስና ላይ ያለ ፍጹም ስህተት የሆነ መረዳት ነው። በእርግጥ ጌታ እግዚአብሔር ይህንን በተመለከተ አጋነንታዊ የሆነ ዝምታ እንዳለም ተናግሮኛል። በባህላችን ውስጥ ያለውን የሞራል ግራ መጋባት ለመፈወስ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ወደሆነው ቅድስና መመለስ ትልቁን ስፍራ እንደሚይዝ አምናለሁ። አለም የምትሄደው ቤተክርስቲያን ወደሚትሄድበት ነውና። በቤተክርቲያን ውስጥ ለተበራከተው አለማዊነት አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት በቅድስና ላይ ያለን ልክ ያልሆነ እይታ ነው። 

እውነተኛው ቅድስና በመጥፎ እይታ ነው የሚታየው፤ ልክ ጊዜው እንዳለፈበት አሁን ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለው። ነገር ግን አንድ ነገር ልንረዳ ያስፈልገናል፥ እርሱም መጥፎ ልምምድ ወይም የተሳሳተ አስተምህሮ ከእግዚአብሔር የሆነውን ቅድስና ትርጉም እና አስፈላጊነት ሊያጠፋው እንደማይችል።

አማኞችን በተመለከተ ደስ የሚለኝ የቅድስና ትርጉም አለ እርሱም፥ “ቅድስና ንጹህ ለሆነ የአስተሳሰብ፣ የቃል፣ የስሜት፣ እና የስራ ሕይወት ያለ ሞራላዊ ታማኝነት እና አቋም ነው።” የሚል ነው። በዚህ ትርጓሜ ውስጥ ለእግዚአብሔር መለየት ይሚል ሃስብ አለ። በሌላ አባባል፥ የአለምን ሃሳብ መልክ እና መለኪያ ልንመስል ሳይሆን እግዚአብሔርን ልንመስል ፍቅዱንም ልናደርግ ይገባናል።    

ነገር ግን ከዚህም በላይ ቅድስና እኛ የማን ነን የሚል ሃሳብንም ይይዛል። ታማኝነታችን፣ ፍቅራችን፣ አና ተገዥነታችን ለማን ነው? ቅዱስ መሆን ማለት፥ እኛ እና የእኛ የሆነው ሁሉ የእኛ ሳይሆን ለእግዚአብሔር እና ለአላማው የተለየ ነው ማለት ነው። ለመጀመሪያዎቹ ቤተ-ክርስቲያናት የተጻፉት መልእክቶች ዋና ሃስባቸውም ይህ ነበር። ታዲያ ዛሬ እንዴት አማኞች አገልጋዮችም ጭምር ይሄን ችላ ይላሉ?     ልክ ያልሆነ የቅድስና አረዳድ ወይም ደግሞ እሱን ወደ ጎን መተው የእግዚአብሔርን እውነተኛ ፍቅር እንዳንረዳ ጥላ አጥልቶብናል። እግዚአብሔርን እንደሚወድን ብቻ ከእኛ ምንም አይነት የሕይወት ጥራትን እንደማይፈልግ ፍቅሩ ከቅድስናው በላይ እንደሆነ ተደርጎ ሲታይ ሰዎች በዛ እምነታቸው የኖራሉ፤ አፈንጋጭነት እና ያልተገደበ የሃጢያት ልምምድም በቤተክርስቲያን ውስጥ ስፍራን ያገኛል። ይህ ደግሞ በሶስተኛነት ወዳስቀመጥኩት ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ወዳለው ሌላኛው ስህተት ይወስደናል እርሱም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ላይ ያለ ልክ ያልሆነ አረዳድ ነው። 

2. በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ያለ ልክ ያልሆነ እይታ ዛሬ

ዛሬ ዛሬ በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ እና ክርስቲያን ተብለው በሚጠሩ ሰዎች ዘንድ ከእውነተኛው የእግዚአብሔር ፍቅር የጎደለ ስሜታዊ እና ለስላሳ ፍቅር መሰል ነገር ይስተዋላል። ይህ ፍቅር በእውነት ላይ የተመሰረተ አይደለም።

ለምሳሌ በወቅቱ አነጋጋሪ ከሚባሉት ነገሮች አንዱ አስቅድሞ የተጠቀሰው ግብረሰዶማዊነት ነው። በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ብዙዎች እየተቀበሉት እና ድጋፋቸውን እየሰጡት ይገኛል። አብዛኞቹ ቤተ-እምነቶች እንዲህ አይነት ልምምድ ውስጥ ያሉ ሰዎችን በአገልጋይነት እየሾሙ ይገኛሉ። ይህ የሚደረገው በፍቅር ስም ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አስረግጦ ይሄ እርግማን እንደሆነ በቤተክርስቲያንም ውስጥ ቦታ ሊኖረው እንደማይገባ ይናገራል። 

ይህ ማለት እንደዚህ አይነት ሰዎችን መውደድ ማቆም አለብን ማለት ነው? አይደለም፥ የበለጠ ልንወዳቸው ይገባናል ምክንያቱም ትልቅ ይሆነ አደጋ ውስጥ ናቸውና። ነገር ግ ን ይህን ስናደርግ በርህራሄ፣ በጥበብ፣ እና በፍቅር ያሉበትን ሃጢያት ልንንገግራቸው ደግሞ ይገባል። ሆኖም ብዙዎች ለዚህ ኢየሱስን እንደጠሉት ይጠሏችኋል።  

 “ማንም ሰው ከኢየሱስ በላይ ሰውን ሊወድ አይችልም። ሆኖም የእርሱ ፍቅር እንኳን ሰዎችን አስቆጥቷቸዋል። የእርሱ ፍቅር ፍጹም ነበር፤ ታላቅ እና ቅዱስ የሆነ ፍቅር፤ ነገር ግን ያ ፍቅር እንኳ ሰዎችን አስደንግጧቸዋል። እንዲህ አይነቱ ፍቅር እጅግ ይከበረ ነው ልንቋቋመው ይማንችለው።”(አር.ሲ. ስፕራውል፥ የእግዚአብሔር ቅድስና)   

አያችሁ፥ ፍቅር መጽሃፍ ቅዱሳዊ ደርጃን ለማሟላት ከእውነት እና ከቅድስና ጋር መሆነ አለበት ። ዛሬ ላይ ከእኛ ወይም ከወዳጃችን ህይወት ጋር የማይስማሙ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ወደ ወደድነው እንቀይራቸዋለን። ብዙዎች የእግዚአብሔርን ፍርድ እና ቁጣ፣ ቅድስና፣ እና ገሃነምን ከመጽሃፍ ቅዱስ አውጥተዋል። ይህ እየኖርንበት ያለነው ክፉ የዘመን መጨረሻ አንድ ምልክት ነው።

በአለም ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር እንደወደድን ልንናገር እንችላለን ነገር ግን የእግዚአብሔርን ክብር እና ብዙዎቻችን የጸለይንበትን መነቃቃት ማየት የምንፈልግ ከሆነ ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ይጀምር ዘንድ ይገባዋል።  

“ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?”(1 ጴጥሮስ 4፥17)

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox