በዚህ አጋንንታዊ ስሜት ላይ በሩን ለመዝጋት የሚረዱ 4 እርምጃዎች

ክሪስ ቨሎተን :

ቅናት ንፁህ ክፋት ነው፡፡ ከማንኛውም ኃጢአት በላይ በሕይወታችን ውስጥ ለአጋንንታዊ መናፍስት በሩን ይከፍታል፡፡ 

ቅናት ቃየን አቤልን እንዲገድል አነሳሳው ፣ የዮሴፍ ወንድሞች ለባርነት እንዲሸጡት እና ንጉሥ ሳኦልን ታላቅ እና በጣም ታማኝ ወታደር የሆነውን ዳዊትን ለማጥፋት እንዲፈልግ አነሳሳው ፡፡ በጎዳናዎች ላይ ተሰልፈው እንደዘመሩት ሴቶች ፣ “ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር” (1ኛ ሳሙ 18፡7)፣ ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው ከእኛ በላይ የበለጠ ትኩረትን ሲሰጠው ወይም ታዋቂ ከሆነ ቅናትን ይነሳሳል፡፡ የሳኦል ቅናት በሕይወቱ ውስጥ የእብደት እና የግድያ መንፈስ በርን ከፍቷል (1 ሳሙ 18 ይመልከቱ)፡፡ በአንድ ወቅት ትሑት የሆነ አንድ የገበሬን ልጅ ወደ ጅምላ ነፍሰ ገዳይነት ቀየረው፡፡ 

ሐዋርያው ​​ያዕቆብ እንደ ጻፈው፡፡ “ቅናትና ራስ ወዳድነት ባለበት በዚያ አለመግባባትና ክፉ ነገር ሁሉ አለ”፡፡ በህይወቴ አብዛኛውን ጊዜ በቅናት ስሜት እታገለ የነበረ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ምን እንደ ነበር ለመለየት አልቻልኩም ምክንያቱም ቅናት ብዙ ጭንብሎችን ስለሚለብስ ነው ፡፡

አንዳንድ ጊዜ እራሱን ማስተዋል ብሎ ይጠራል፡፡ የተጠቂዎቹን ልብ እየፈተሸ እነሱን ለማሳጣት ምክንያቶች ይፈልጋል ፡፡ በቅናት መንፈስ የተቀባው የማስተዋል ስጦታ ግን ጥርጣሬ ነው ፡፡ ጥርጣሬ የማስተዋል ክፉ የእንጀራ እህት ነው ፡፡ ይህ ጠማማ የማስተዋል ስሪት ነው ፤ እናም ብዙ ጊዜ በስጦታቹ ውስጥ የምትሰሩት ይህ ከሆነ ፤ ምናልባት ዛሬ ወደ ለውጥ ግብዣዎ ይሆናል ፡፡

ስጦታቹ በቅናት መንፈስ ፋንታ በመንፈስ ቅዱስ እንዲቀባ ስትፈቅድ በአካባቢያቹ ባሉት ሰዎች ሕይወት ላይ ያለውን ሞገስ ማስተዋል ትጀምራላቹ!

ቅናት ምንም ጓደኞች የሉትም

ምንም እንኳን ቅናት ብዙ ፊቶች ቢኖሩትም ጓደኞች የሉትም! ከቅናት ጋር መተባበር ወደ ብቸኝነት ጎዳና ወደ መለያየት ፣ ተስፋ መቁረጥ እና ወደ መናቅ ይመራቹሀታል ፡፡ ቅናት ድርጊታቹን እንዲቆጣጠር ስትፈቅዱለት ዛሬ አንድን ሰው ስቶዱት እናም በቀጣዩ ቀን እንደ ስጋት ስታዩት እራሳቹን ታገኙታላቹ ፡፡ ከእነሱ የበለጠ ተወዳጅ ፣ የላቀ ችሎታ ወይም የበለጠ ኃይል እስኪሰማቹ ድረስ ከፍ ታረጉቸዋላቹ  ፣ ነገር ግን የዛ ሰው ዕውቀት ፣ ሞገስ ፣ ተሰጥኦ ወይም ስልጣን ከእናንተ በሚበልጥበት ሰአት ፣ ጦርነቱ ይጀምራል ፡፡ 

ቅናት ሌሎችን ለማሳነስ እንድንሞክር ፣ ድክመታቸውን ለማጉላት ፣ እነሱን ለመቆጣጠር መዋቅሮችን እንድንሰራ ፣ በእነሱ ላይ ክስ እንድንመሰረት እና / ወይም እነሱን ለማሳደድ ብዙ ሰዎችን እንድናነሳሳ ያደርገናል ፡፡ ቅናት ቆንጆ ቤተመንግስት ሊገነባ ይችላል ፣ ነገር ግን አጥፊው በመሬት ወለሉ ውስጥ ከእይታ ርቆ ተጠቂዎቹን ለመጣል ሴራ እየጠነሰሰ አጋጣሚ እየጠበቀ ነው ፡፡ 

ቅናትን ለማሸነፍ 4 እርምጃዎች ስለዚህ ምን እናድርግ? ቅናትን ለማሸነፍ አራት እርምጃዎች፡

  1. ችግሩን መጋፈጥ፡ በመጀመሪያ ፣ ቅናት እንዳለን አምነን መቀበል አለብን ፣ እናም ኃጢያታችንን መቅረፅ ማቆም አለብን! አንድ ነገር ዳክዬ የሚመስል ከሆነ ፤ እንደ ዳክዬ ከጮሕ እና እንደ ዳክዬ የሚሄድ ከሆነ ፤ ዳክዬ ነው ፡፡ ያቄምንበትን ሰው ምን ያህል እንደምንወደው ወይም እንደምናደንቀው ለሰዎች መናገር እውነት አይደለም እናም ኃጢያት ነው፤ ይህም በሕይወታችን ውስጥ ወደ ጭራቅነት እንዲቀየር ያስችለዋል ፡፡
  2. በምትቀኑበት ሰው ላይ ኢንቨስት አድርጉ፡ ከዚያ የእነሱ ድል የናንተ ድል ይሆናል ፡፡ በቅናት መንፈስ ላይ የሚደረግ ጦርነት።
  3. አለመቀበል ፤ እምቢ ማለት! እራሳቹን ከሌሎች ጋር እንዲያነፃፀር ለአዕምሯቹ አትፈቀዱለት ፡፡ ይልቁን እውነተኛ የምስጋ ልብን አዳብሩ።
  4. እናንተ ማን እንደሆናቹ እና የማን እንደሆናቹ አስታውሱ፡ አባታችን ብዙ ፍቅር ፣ አቅርቦት ፣ ዝና እና የመሳሰሉት ለልጆቹ ሁሉ እንዳለው መርሳት የለብንም ፡፡ አንድ ሰው የምንጓጓለትን ነገር ሲያገኝ አሁንም ለእኛ የሚሆን ብዙ ይቀራል ፡፡ የአንድ ሰው ከፍታ የሌላ ሰው ዝቅጠት አይደለም ፡፡ ግን የሌሎችን ድሎች ማክበር ካልቻልን ጌታ የራሳችንን እንዲኖረን አይፈቅድልንም ፡፡ በሌላ በኩል ፣ እራሳችንን ዝቅ ካደረግን እርሱ በተገቢው ጊዜ ከፍ ከፍ ያደርገናል!

አክብሩ በረከትንም አምጡ ማክበር ለርስት ክፍት በር እንደሚያመጣል ስንገነዘብ ፣ እነሱን ከማሳደድ ይልቅ የምንናፍቀውን ስጦታዎች ካላቸው ሰዎች ለመቀበል ልቦናችንን ማዘጋጅት ቀላል ነው ፡፡ ቅናትን ማሸነፍ ውድድር አይደለም ፡፡ ይህ እራስን ስለማሳየት አይደለም ፡፡ ይልቁንም እንድታድጉ ፣ ብስለት እና ብልጽግና የሚያስፈልጋቹ ነገር ሁሉ እንዲደርሳቹ እግዚአብሄር ካለው ጊዜ ጋር መላመድ ነው ፡፡ በዙሪያቹ ላሉ ስዎች ስኬት ልባቹን በ ምስጋና ሙሉ እና በራሳቹ ሕይወት ውስጥ የበረከትን ምላሽ ታገኙታላቹ።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox