ኢየሱስ በአስገራሚ ሁኔታ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልምምዶችን የእግዚአብሔርን ቃል በመጥቀስ የሚያደርጉ ሰዎች ያጋጥሙት ነበር። ይህንንም በጊዜው የነበሩት የአይሁድ መሪዎች በማርቆስ ወንጌል 7 ፥ 9 – 13 እናትን እና አባትን መርዳትን በቁርባን መስዋእት ሲቀይሩ ተገልጦ እናየለን።
መጽሃፍ ቅዱሳችንን ስናጠና ሰይጣንም እራሱ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያውቅ እና ለራሱ እንደሚመቸው ሲጠቅስም እናያልን። (ሉቃስ 4፥9 – 12)።
በክርስቶስ አካል ውስጥ እንዳለ አንድ ታዛቢ እኔም እራሴ ይህንን ባህሪ በተደጋጋሚ ተመልክቻለሁ፥ ሰዎች እውነተኛ ሃሳባቸውን ለመደበቅ፣ ከተጠያቂነት ለመሸሽ፣ ሌሌችን ለመጠቀም፣ ወይም ለሌሎች የሚያሳዩትን ያልተገባ ባህሪ ጥፋት እንዳልሆነ ለማሳየት እግዚአብሔርን ሲጠቀሙ ወይም ከእርሱ ጀርባ ሲደበቁ አስተውያለሁ።በዚህ ሁለት ክፍሎች ባሉት ጽሁፍ የሚከተሉትን ሃሳቦች አነሳለሁ፥
ሰዎት መልካም ላልሆነ ባህሪያቸው እግዚአብሔርን ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙባቸው አስር መንገዶች
ሴቶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በሚደርስበት እና ባልተገባ መንገድ በሚያዙበት አለም እንደሚኖር አንድ ፓስተር, የተወሰኑ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በተገቢው ሁኔታ ሳላብራራ አላልፍም። ሚስቶች ለጌታ እንደሚገዙ ለባሎቸቸው እንዲገዙ የሚያስተምረውን የጳውሎስን መለዕክት ሳካፍል (ኤፌሶን 5)፤ ያንን ቦታ ከተቀረው የመልዕክት ክፍል ነጥዪ ብቻውን አየር ላይ ልተወው አልችልም፤ “ለያንዳንዳችሁ የተገዛችሁ ሁኑ” ብሎ የሚናገረውንም (ከ 5፥ 21 ጀምሮ ያለውን ሃሳብ የሚጠቀልለው ይህ ክፍል ባሎችም ለሚስቶች እንዲገዙ የሚል ሃሳብም ይኖረዋል፤ ባሎች ሚስታቸውን እንዲወዱ የሚያዘው ክፍልም እናዳለ ሆኖ 5:25)።አለመታደል ሆኖ ስጋዊ እና ተንኳሽ የሆኑ ባሎች ሚስታቸውን ለመጨቆን እና እንደፈለጉ ለማድረግ ይህንን ክፍል በጌታ ስም ይጠቀሙበታል (እነዚህ ባሎች የኤፌሶን 5፥ 21 – 25ን ሙሉ መልዕክት ሳይሆን የሚመቻቸውን ብቻ መርጠው ይወስዳሉ።) እናንተ ኤፌሶን 5፥21ን ብቻ ሳይሆን ሙሉ መልዕክቱን ለመስበክ የታዘዛችሁ ሁኑ።
2. የፈለጉትን ለማድረግ “እግዚአብሔር ተናገረኝ” ይላሉ፥
እንደ መጋቢ የወደዱትን ለማድረግ እና ሃላፊነት የጎደለውን ባህሪያቸውን ለመሸፋፈን “እግዚአብሔር ተናግሮኛል” የሚሉ ብዙ ሰዎችን ሰምቻለሁ። ሰዎች እንደዛ ብለው ለኔ ሲነግሩኝ ቀይ መብራት ነው የሚመጣልኝ ምክንያቱም ያ የሚያሳየው ከፍ ሲል የዛን ሰው አለማደግ ካልሆነም ደግሞ ሰዎችን ለራስ መጠቀም ማሰብ ባስ ሲልም ልክ ያልሆነን ድርጊት ልክ እንደሆነ ለማድረግ መፈለግን ስለሆነ ነው።
እግዚአብሔር ሰዎችን እንደሚናገር በእርግጥ አምናለሁ፤ ትልልቅ ውሳኔዎች ግን በሳል የሆነ ምክር እና ከልብ ሸክም በተጨማሪ የሌሎች ምስክርነት ባለበት ሁኔታ መውሰን ይኖርባቸዋል። (በክርስቶስ ብዙ ባደኩኝ ቁጥር እንደ ድሮው አብዝቼ “ጌታ ተናገረኝ” አልልም። ) አሁን እያወራሁላችሁ ይለኋቸው ሰዎች ግን ምንም እንኳን ከእግዚአብሔር ባይሰሙም “ጌታ ተናገረኝ” ብለው ሃሳባቸውን በሌሎች ላይ ከማራመድ ወደ ኋላ አይሉም። እንዲህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ የልባቸው ፍላጎት ባህሪያቸው በ “እግዚአብሔር ምሪት” እንደመጣ አድርጎ ማሳየት ነው።ሌላው መጋቢ ብዙ ጊዜ ሊሰማው የሚችለው “የኔ ጊዜ አልፏል” የሚል ነው፤ ይህም አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያንን ለመልቀቅ ውይም ከአገልግሎት ለመውረድ የወሰኑ ሰዎች እንደምክንያት የሚጠቀሙበት ነው። በአብዛኛው እዉነቱ ግን እንደፈለጉት እውቅና ስላልተሰጣቸው (ዝናን ስላላገኙ)፣ ያሰቡት ስላልሆነ ውይም በሌላ ቤተ-ክርስቲያን የተሻለ አማራጭ አለ ብለው ስላሰቡ ነው። እውነተኛውን ምክንያት ተናግሮ በግልጽ መሄድ ሲቻል ስለምን “የኔ ጊዜ አልፏል” በሚል በእግዚአብሔር ማሳበብ ያስፈልጋል።
3. ነገሮችን በመታዘዝ ማድረግ ሲገባቸው እነርሱ “ይጽልያሉ”
አንድን ሰው የሆነ ነገር እንዲያደርግልኝ ስጠይቅ “በጉዳዩ ላይ ልጽልይበት” ካለኝ በቤተ – ክርስቲያን ቋንቋ አይሆንም ማለቱ እንደሆነ ይገባኛል። (እኔን ፊት ለፊት አይሆንም ለማለት ስላልደፈሩ ለዉሳኔያቸው እግዚአብሔርን ተጠያቂ ማድረግን ይመርጣሉ።) ለምን በቀጥታ አይሆንም አይሉም? እኔ ዝም ብለው እንጽልይበት ከሚሉኝ ይልቅ በቀጥታ አይሆንም ቢሉኝ እመርጣለሁ።
በእርግጥ ሰዎችን በሆነ ጉዳይ ላይ እንዲጽልዩልኝ ወይም እንዲያስቡበት ጠይቄ አውቃለሁ፤ በተለይ ደግሞ ትልልቅ ውሳኔውች ሲኖሩ። ከብዙ አመታት በኋላ ሰዎች “እንጸልይበት” ሲሉኝ በእውነት ለመጽለይ በማሰብ እንደሆነ እና እንዳልሆነ መናገር እችላለሁ።ከዚህ በተጨማሪ ሃዋሪያው ያዕቆብ (በምዕራፍ 2 ላይ) የተራበን እና የሚለብሰው ያጣን ሰው የሚያስፈልገውን ነገር ከመስጠት ይልቅ ‘እሳት ሙቅ ጥገብም’ ለሚል ሰው እርምትን ሲሰጥ እናያለን፤ ይህ አንዳች ነገር ማድረግ ሲኖርባችሁ ልጽልይበት ብሎ ከመመልስ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ይህ ከሃላፊነት ለመሸሽ እግዚአብሔርን እና ጽሎትን የመጠቀም ሌላኛው ምሳሌ ነው።
4. ቤተሰቦቻቸውን እና ሌሎች ሃላፊነቶችን እስከሚረሱ ድረስ ከመጠን ባለፈ ‘ያገለግላሉ’
በየምሽቱ በጸሎት ስብሰባዎች ላይ በመገኘት “መንፈሳዊ ውጊያን” ማድረግ የ 16 አመት ታዳጊን አመለካከት ከመቅረጽ ይቀላል ብዪ ብዙ ጊዜ እናገላለሁ። እንደመጋቢ ወደቤት ገብተው የቤተሰባቸውን እና የትዳራቸውን ውጣ ውረድ ከመጋፈጥ ይልቅ በስራቸው መጠመድን የሚመርጡ ሰዎችን አውቃለሁ (ይህ በቤተ-ክርስቲያን ያሉ መጋቢዎችንን እና በስራ ቦታ ያሉ መሪዎችን ያጠቃልላል።) “አስቀድማችሁ መንግስቱን ፈልጉ” (ማቴዎስ 6፥ 33) የሚናገረው ስለ ቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት ነው ብለው የሚያስተምሩ መጋቢዎችም ነበሩ። ባለቤታቸውን እና ልጆቻቸውን ችላ ያሉት ‘የጌታን ስራ’ እየሰራሁ ስለነበር ነው ብለው ምክንያት ያቀርባሉ፤ (ለዚህ ነው ብዙ የአገልጋይ ልጆች ከቤተ-ክርስቲያን የጠፉት – ለወላጆቻቸው ከቤት መጥፋት ቤተ-ክርስቲያንን እና እግዚአብሔርን ተጠያቂ ያደርጋሉ)።
5. ለሌሎች ጻድቅ መስለው ለመታየት የእግዚአብሔርን ቃል ይጠቀማሉ፥
ማቴዎስ 18፥ 15 – 18 ላይ ያለውን ቃል በመጥቀስ ከበዳላቸው ሰው ጋር በአጭር ንግግር በማድረግ ሰዎች ስለበደሏቸው ቤተሰባቸውን ጨምሮ ከእነርሱ መራቃቸውን ልክ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ።
ከልብ ለመታረቅ ከመሞከር ይልቅ፣ ህብረት ያቋረጡት ይህንን የእግዚአብሔር ቅል በመከተል እንደሆነ ለመናገር ይሞክራሉ።. (በእርግጥ ማቴዎስ 18፥ 15 -18 ግጭት ሲኖር መሪዎችን ወደ ጉዳዩ ማስገባት እንደሚያስፈልግ ይናገራል፤ ብዙዎች ግን ከተጠያቂነት ለመሸሽ ይህንን የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ቆርጠው መትውን ይመርጣሉ) ሌሎች ከማያምን ጋር አለመጠመድን በተመለከተ 2 ቆሮንቶስ 6 ፥ 14 በመጥቀስ ትዳራቸውን ማፍረሳቸው፣ ልጆቻቸውን ችላ ማለታቸው እና አያምኑም ብለው ካሰቧቸው ሰዎች መራቃቸው ልክ መሆኑን ለማሳየት ይሞክራሉ። ነገር ግን ይህ ክፍል ማቴዎስ 7፥1 ላይ ባለው አውዱ ስጋን እና መንፈሥን ከሚያረክስ እንደ ጣኦትን ማምለክ ካለ ነገር ራሳችንን ስልማንጻት እንጅ ካማያምኑ ሰዎች ሁሉ መራቅ አንዳልሆነ ያሳየናል።
ይህንን ጳዉሎስ በ 1 ቆሮንቶስ 5 ፥ 10 ላይ አማኞች ከማያምኑ ጋር ህብረት ማድረግ የለባቸውም ወይም አማኞች የማያምኑ ባላቸውን ወይም ሚስታቸውን መተው አለባቸው ብሎ እንደማያስብ በመናገር ግልጽ ያደርጋል (1ቆሮንቶስ 7 ፥ 12 – 15 አማኞች የማያምን ባላቸውን ውይም ሚስታቸውን እነርሱ ካልፈቷቸው በቀር አብረው እንዲኖሩ በግልጽ ይነግረናል) ኢየሱስ ብዙውን ጊዜ ህብረት ያደርግ የነበረው ከሃጢያተኞች እና ከማያምኑ ጋር ነበር፤ እርሱን በትልቁ ይፈትኑት የነበሩት ግን ለመጥፎ ተግባራቸው ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ ጀርባ መደበቅን የሚመርጡት የሀይማኖት አቀንቃኞች ነበሩ።
Copyright Hiyawkal © 2025
Leave a Reply