በመባል የሚታወቅ የወፍ ዘር ነው ታላላቅ ነገስታት ንስርን ለተለያዩ ነገሮች መግለጫነት እንደ ምሳሌ ተጠቅመዋል ለነጻነት ለሥልጣን ለግርማና ለመሳሰሉት በዚህ ጹሑፍ ለግርማና ለመሳሰሉት በዚህ ጹሑፍ ግን የምናተኩረው አስገራሚ የሆነ መመሳሰል በንስር ባሕሪና በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ መኖሩን ነው በዚህች አጭር ጹሑፍ ውስጥ አምስት ነጥቦችን ብቻ እንመልከታለን፡፡
የተለያ አዕዋፍና አራዊት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተዛመደ መልኩ ጎጆዋቸውንና ስፍራቸውን በመተው ወደሌላ ቦታ ይሰደዳሉ ይህም ፍልሰት በመባል ይታወቃል ኀይለኛ ፍልሰት በመባል ይታወቃል ኃይለኛ የክረምት ወቅት ሲመጣ ብዙዎቹ ወደ ሌላ አካባቢ እስከ እረጅም እርቀት ድረስ በመጓዝ ሀገር ሁሉ አቋርጠው ይሰደዳሉ ንስር ግን እንደዚህ አይደለም ክረምት አልፎ በጋም እንደሚመጣ ያውቃል በመሆኑም በብዙ ድካምና ጥረት የሠራውን ጎጆውን ጥሎ አይሸሽም እንደምንም ብሎ በጎጆው ውስጥ በመሆን ያን የክረምትን ወራት ያሳልፋል ንስር የክረምት ወራት ያሳልፋል ንስር ክርስቲያኖችም እንደዚህ ናቸው ወጀብ አውሎ ንፋስ ስለበዛባቸው ብቻ እግዚአብሔርን ካስቀመጣቸው ቦታና ከሰጣቸው ስፍራ ተነስተው አይሄዱም ጌታ ወጀቡን ጸጥ በማድረግ እንደሚያሻግራቸው ያውቃሉ በሆኑም በስፍራቸው ጸንተው ይቆያሉ(ናሆም 1፡3)
ንሰር አንድ ጠላት ብቻ አለውያም እባብ ነው ንስር ቤቱን የሚሰራውከፍ ባለ አለት ላይ ስለሆነ ከእባብ ሌላ ምንም ሊደርስበት አይችልም እባብ ግን ተስታኮ ወደ ጎጆው ሊያመራና የንስርን እንቁላሎች ወይም ጫጩቶችን ሊጎዳ ይችላል ከዚህም የተነሳ ሴቷ ንስር እንቁላሎች ወይም ጫቹቶችን ሊጎዳ ይችላል ከዚህም የተነሳ ሴቷ ንስር እንቁላሎችዋንም ሆነ ጫጩቶቿን በትጋት ነው የምትጠብቀው እባቡ ወደ ጎጆዋ ሲመጣ በከፍተኛ ፍጥነት በአፏ እና በጥፍሮቿ ትይዘውና ወደላይ ትበራለች ከዚያም አለት ፈልጋ በአለቱላይ እባቡን ትለቀዋለች እባቡም በአለቱላይ ተፈጥፍጦ ይሞታል የክርስቲያን ጠላት የቀደመው እባብ የተባለው ዲያብሎስን ነው ረእ 12፡9 ክርስቲያንም ዲያብሎስን የሚቀጠቅጠው በአለቱ በክርስቶስ ነው በክርስቶስ ዲያብሎስ ድል ተነስቷልና
ንስር አንዳንድ ጊዜ ይታመማል በተለይ የተበከለ ምግብ ከበላ ይታመማል በሚታመምበትም ጊዜ ተዘርግቶ በደረቱ ይተኛና ዓይኑን ወደ ፀሐይ ቀና በማድረግ ፀሐይን በቀጥታ በዓይኖቹ ይመለከታል ፈውስንም ከፀሐይ ብርሃን ያገኛል ንስር የተለየ ዓይን ስላለው ፀሐይን በቀጥታ አይቶ ሳይታወር የሚቀር የተለየ ፍጥረት ቢሆን ነው የዓይኑ አፈጣጠር የተለየ እስከ 40 ኪ.ሜ ድረስም አሻግሮ ማየት ይችላል ንስር ክርስቲያኖችንም በሕይወታቸው ችግር ሲገጥማቸው ድካም ሲይዛቸውና ፈተና ሲያንገላታቸው በቀጥታ ወደ ክርስቶስ በመመልከትና እርሱን ደጅ በመጥናት እንደ ፀሐይ ከሚያበራው ፊቱ ፈውስን ብርታትና ኃይልን ይቀበላሉ ንስር አንዳንድ ጊዜ ካልተፈወሰ እዚያው ፀሐይን እያየ ሞቶ ይቀራል ክርስቲያን የመጣው ቢመጣ ጌታውን እያየ ይሞታታል እንጂ ጌታውን ትቶ አይሄድም ሮሜ 8፡38-39 ንስር እስከ 40 ኪሜ ድረስ ከርቀት አሻግሮ እንደሚያይ ሁሉ ንስር አስቀድሞ ከርቀት የሚያዩበትና የሚያስተውሉበትን መንፈስ ከጌታ ተቀብለዋል፡፡
ንስር በማለዳ ተነስቶ ሁልጊዜ ከአፉ በሚወጣ ፈሳሽ ቅባት መሰል ነገር የክንፎቹን ላባዎች ይቀበል ይህም ቀን በሚበርበት ጊዜ ክንፎቹን የንፋሱን ግፊት ለመቋቋም ጥንካሬ እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል ይህንንም ተግባር ባለማቋረጥ በማለዳ ተነስቶ ያደርጋል ንስር ክርስቲያኖችም ዕለት ዕለት በማለዳ በመንቃት በጸሎት ቃሉን በማንበብ ለየዕለቱ ፈተናን ውጣውረድ የሚያስፈልጋቸውን ኃይልና ብረታት ከጌታ ይቀበላሉ ይህንን ያልተለማመዱ ክርስቲያኖች ግን ብዙ ጊዜ ሽንፈት ቢገጥማቸው አያስደንቅም ንስር ክርስቲያኖች ግን እንደዚህ አይደሉም ከእንቅልፍ ይልቅ የጌታቸውን ፊት ይናፍቃሉ በማለዳም ወደእርሱ ይገሰግሳሉ ፊቱንም ይፈልጋሉ ጌታም ፊቱን በላያቸው ላይ ያበራል የቀኑንም ክፋት ሁሉ በድል ይወጣሉ፡፡
ንስር ለጫጩቶቿ የምታደርገው ፍቅር በጣም አስደናቂ ነው ጫጩቶቿ በሚፈለፍሉበት ጊዜ የጎጆው እንጨት እንዳይጎረብጣቸው በደረቷ አካባቢ የሚገኘውን ስስ የገላዋን ክፍል በመንጨት ትጎዘጉዝላቸዋለች ጫጩቶቿም በምቾት ደስ ብሏቸው አካሏ ቁራጭ ላይ ይተኛሉ ይሞቃቸዋልም የክርስቶስ የሆኑትም ተመሳሳይ ፍቅር ለሌሎች እንዲያሳዩ ይጠበቅባቸዋል ለአዳዲሶችም የምናሳየው እንክብካቤ ፍቅርን የተላበሰ ሊሆን ይገባል፡፡
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም ኢሳ 40፡31
ትርጉም ተድላ ሲማ
ብርሃን መፅሔት
1989 ቁጥር 29
Copyright Hiyawkal © 2025
Leave a Reply