አስክሬኑ አፈር ከለበሰ አንድ ጀንበር ዞሯል በርካታ ባለውቃቢዎች አስማተኞች ጠንቋዮች እንዲሁም ከሃምሳ የሚበልጡ የሀገር ሽማግሌዎች ተሰባስበው የሟች መንፈስ ከቤተሰቡ በአንደኛው ላይ እንዲያርፍ በሁለቱ መቅደሶች ትይዩ ቆመው ተማፅኖአቸውን ያሰማሉ ሕዝቡ ጦሩን እንደሰነገለ የ‹‹ኮይ›› ምላሽ በፍርሃት ይጠባበቃል ከአዋቂ እስከ ደቂቅ ያለው የቤተሰቡ አባል ከትቢያ ተደፍቶ ‹‹የመንፈሱ ቀልብ የሚያርፍበት ማይሆን የሚለውን ጥያቄ ያወጣል ያወርዳል እንግዲህ መንፈሱ ያረፈበት ሰው ከሁለቱ መቅደሶች አንደኛውን ይመርጥና መሥዕዋት ካቀረበ በኋላ ሕዝቡን ማስደግደግ ይጀምራል ሕዝብ ይገብራል መንፈሱ ያስገብራል ሕዝብ ያርዳል መንፈሱ ያሳርዳል ሕዝብ ይገዛል ተረኛው እስኪተካ እንዲህ ነው ሕይወት የሚቀጥለው፡፡ ተማጥኖ ቀጠለ ኮይ ግን ምላሽ አልሰጠም ጀንበሯ ከአናት ወርዳ ወደ ምዕራብ መራመዷን ቀጠለች ከመቅደሱ አፃር ያሉት ‹‹አዋቂዎች ኮይ ሆይ ስማን የሚለውን ጩኸት አላቆሙም ሕደዝቡ እያደገደገ ሀዴዎ የተሰኘውን ቃል ያስተጋባል አሜን ይሁን እንደማለት የሟች ባለቤት ማለትም የበላይ ሺባብ እህት ከባለውቃቢው የሚወለዱ ስምንት ልጆች አሏት እሷ በአገሩ ላይ ፈላጭ ቆራጭ የሆነው የባለ ዛሩ ሚስት ስትን በላይ ደግሞ ክርስቲያን ነው ያውም ያማሩ እግሮች አሉት ተብሎ የተመሰከረለት የወንጌል መልዕክተኛ አራት ቀናት ቀደም ብ የአማቹን መታመም ይሰማና ጥየቃ ሄደ፡፡
በዚያም ለእህቱ ለልጆቿ አልፎም ለባለቤትዋ የወንጌልን ቃል ማሰማት ጀመረ ባለቤትዋ ማለትም ባለውቃቢው ቃሉን ሲሰማ ፈጽሞ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ሞተ ታዲያ አስክሬኑ ተቀብሮ አንድ ቀን እንዳለፈ የውቃቢያን ጉባዔ ተሰበሰበ ጩኸቱ ልመናው ጭፈራው ጭብጨባውና ግስፈቱ አካባቢውን ቁና አደረገው ከክፉዎች ጉባኤ ጀርባ ተሸሽጎ ያለው በላይ ከወንድሙ ጋር ቀኑን ሙሉ በግንባሩ ተደፍቶ ወደ አምላኩ ይጸልያል የክፋትን ሠራዊት ይዋጋል ጉባዔያቸውን ይገስጻል ፀሐይ ወደ ምዕራብ ተዳፋች ኮይ ምላሽ አልሰጠም ያልተለመደ ሁኔታ በመሆኑ ሕዝቡ ግራ ተጋባ ድንገት ኮይን ከሚማጠኑት ሰዎች መካከል እነድ ወጣት እመር በማለት አቅራቢያው ወዳለው ጎጆ ገሰገሰ ብዙም ሳይዘገይ አንድ ሌላ ሰው ከጎጆው ወጥቶ ከጉባዔው ጀርባ ወደሚጸልየው በላይ አመራና ወጣቱ እንደሚፈልገው ገለጸለት አሁን ድረስ የሕዝቡን ጩኸትና ጭብጨባ ጎልቶ ይሰማል በላይ እስፍራው እንደደረሰ አስገራሚ ጉዳይ ገጠመው እሱ ስለሆነ ለሰይጣን ልገዛ አልፈልግም እብካህን ጌታ እቀበላለሁና ጸልይልኝ ሲል ወጣቱ ተማጸነው በላይ እጁን መጸለይ ሲጀምር ክፉ መንፈስ ከወጣቱ ውስጥ እየጮኸ ወጣ ወዲያው በጉባዔተኞቹ መካከል ሽብር ነገሠአሳባቸው ተከፈለ ቋንቋቸው ተመሰቃቀለ ሁካታው ሁሉ በጸጥታ ተዋጠ ፀሐይ ወደ ምዕራብ አድማስ ተጠጋች አንዳንዶች ጴንጤዎች በመካከላችን ስለገቡ መንፈሱ መውረድ አልቻለም በማለት ስለተናገሩ ሥርዓ ለነገ ጀንበር እንዲቀጥል ቀጠሮ ተያዘ፡፡ልመናው በማለዳ ተጀመረ ሥፍራው በሰዎች ተሞልቷል ዛሬ የመጣው ደግሞ ከትላንቱ በቁጥር ላቅ ይላል ጩኸትና እሪታው አካባቢውን ያምሰዋል በላይ እንደተለመደው ከሕዝ ጅርባ ሆኖ ሊጸልይ ሥፍራውን ያዘ በሌላ ቦታ ያሉ ወገኖችን በጸሎት ያግዙታል ሕዝ ኮይን ይማጠንና ይለምን ቀጠለ ድምጽሕን አሰማን ታምራትህን አሳየን ጩኹቱ ቀጥሏል ጥቂት ቆይቶ አምልኮ ተጀመረ፡፡
በተለመደው ሥርዓጥ መንፈሱ ወንዶች ላይ ብቻ ነው ማረፍ የሚገባው ዛሬ ግን እንስቶች መካከል እየገባ ያመሳቅል ጀመር ሕዝቡ ተረበሸ ፀሐይ ወደ ምዕራብ ተጣደፈፈች ኮይ ምላሽ ነፈገ ጠንቋዮችና ቃልቻዎች ተሰባስው ወደ ጓሮ በመዞር ወደ ኤልያስ አምላክ በመጸለይ ላይ ያለውን በላይን ሰማህ. . . ይህን ሥፍራ ለቀህ ተነስ እኛ እንደሆን አንተን አልተቃምንም ለምንድነው አንተ እኛ የምትቃወመን በማለት ጥያቄአቸውን አቀረቡ፡፡ ወዴት እሔዳለሁ ሲል መለሰ ከዳሱ በስተጀርባ ግባ ነበር መልሳቸው ምቹ ሥፍራ ይዞ ጸሎቱን ቀጠለ የኮይ መልስ ግን አልመጣም ምሽቱ ጥላውን ዘረጋ ሰው መበተን ጀመረ አንዳንዶች ተስፋ በመቁረጥ ብንለምንህ እንቢ ብልሃል እንግዲያውስ የማትመልስ ከሆነ. . . ሲሉ ምሬታቸውን አሰሙ ጊዜው ላይን ያዘ በላይሽባብ በተበተነው ሕዝብ መካከል ቆመፐ የጌታን ቃል ማሰማትና መመስከር ጀመረ፡፡ ሦስተኛ ቀን፡፡ ኮይ ልመና የወጣ አልነበረም የሟች ሚስት እንዲጸልይላት በላይን አስጠራችው እንደደረሰ በቤቱ ውስጥ በርካታ ሰዎች ተሰባስበዋል ዩሐኝስ 8÷16 ገልጦ መስበክን ጀመረ የሴትየዋን የመጀመሪያ ልጅ ስብከቱን ተቃወመ ዛተም በላይ ግን በእምት መስበኩን ቀጠለ በመጨረሻም ሰዎች ክርስቶስን እንዲያውቁ በመድኃኒታቸው መሆኑንም እንዲረዱ ደግሞም ወደ እርሱ እንዲመጡ ጥሪ አቀረበላቸው ከ32 በላይ ሰው በአንድ ጊዜ ብድግ አለ ተቃዋሚውም ልጅ እጁን ለክርስትቶስ ሰጠ እንዲያውም ሚስቴን ላምጣና እሷም ክርስቶስን ትቀበል ሲል ለመነ አመጣት ጌታንም አገኘች፡፡ የሟች ዘመዶች ተሰባስበው ይህን የውቃቢ ቤት አፍርሱልን አሉ እናም በአንደኛው እሁድ ቅጥሩን ነቀሉ መቅደሱንም አፈረሱ በውስጡም ያሉትን ልዩ ልዩ የመሰዊያ ዕቃዎች በእሳት አቃጠሉት ወንጌልንም ተቀጣጠለ በሰዎች ልብ የነገሰው ኢየሱስ የኮይን አለቅነት ሻረ የክርስቶስ ጌትነት በሕዝብ ዘንድ ተሰማ አምላክነቱ ጎልቶ ወጣ ሰዎች ወደ ጌታ መምጣት ጀመሩ በፈረሰው መቅደስ አናት ላይ መስቀል ተተከለ ዛሬ ከ32 በላይ ቤተሰቦችና አዝማዶች የውሃ ጥምቀት ወስደው ወደ ቤተክርስቲያን ተጨምረዋ ለመሆኑ የዛሬው ወንጌላዊ የዚህ ታሪክም አካል የሆነው በላይ ሽባብ እንደምን ኢየሱስን ሊያገኝ ቻለ እንዲህ ይተረከዋል፡፡ መምጣት ጀመርኩ የዚያን ጊዜ ሁኔታዬን ሳስብ ምን እባላለሁ ብዬ እንደወጣሁ የጥገርመኛል ዘመዶቼን ከፍተውብኝ ስንቅ እንኳ ከልክለውኝ ነበር፡፡
ይሁንና ጠላት እነሱንም ሆነ ያካበበውን ሕዝብ አስሮ ስሊያስጨንቅ ድንጋጤም ስላሳደረባቸው አለቀስና አዝን ነበር፡፡ ይህን ሁሉ ያደረግሁት መጽሐፍ ቅዱሴን አንብቤ ባገኘሁት እውቀት እን ማንም እንዲህና እንዲያ ነው በማለት መንገዱን ያሳየኝና የመከረኝ ሰው ስለነበር አይደለም ሚዛን የተሰኘው ከተማ እኔ ካሁበት 18 ኪ.ሜ ይርቃል በዚያም ቤተክርስያን መኖሩን ሰምቼ ወደዚያ ወረድኩ በስፍራውም ከወገኖቼ ዘንድ አምል ተካፋየየ ቃሉንም ሰምቼ ከመመለስ በስተቀር የጸለየልኝ ሆነ ቃል ኪዳን እንድገባ ያገዘኝ ሰው አልነበረም ይሁንና ቤቴ በመምጣት ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነን አንተን ተቀብያለሁ ስል እነርሱ እንደሚያደርጉት ንስኃ ገባሁ፡፡ የቤተሰቦቼ ጥላቻ ጨመረ ሊገድኝ ተማማሉ እም ጸሎቴን ቀጠልኩ በዚህ ሁኔታ እያለሁ ሕመም ያዘኝ ይሞታል ባዩ በዛ እናቴ ጠንቋይ ቤት ስለምዘወትር ከዚያ ይዛ የመጣችው ወሬ የእኔን መሞት የሚገልጽ በመሆኑ ሁሉም ሰው የመሞቻየየን ቀኔን ነበር የሚጠብቀው ታዲያ ተኝቼ ቢሆን መጸለዬን አላቋረጥኩም ብቻዬን ነበርኩ በአካባቢው ከአውሬ በስተቀር ዝር የሚል ፍጡር አልነበረም ለሊት ላይ ተኝቼ እያሉ ዙሪያየ ብብርሃን ተሞላ ድምጽ ሰማሁ በላይ ይሕን ቤት ትሠራለህ ቤቱም የጸሎት ቤት ይሆናል ከእንቅልፌ ነቃሁ ቤቱን ጨለማ ውጦታል ያለሁት ግን ያው የሠራሁት የሣር ጎጆ ውስጥ ተነሳሁና መጸለይ ጀመርኩ እንዴት እሠራዋለሁ? የሚል አሳብ አእምሮዬን ሞላ ተንበርክኬ አለቀስኩ በነጋታው ሥራ ላይ ሆኜ ነገሩን አወጣና አወርድ ጀመር ወንድሞቼ ተቃዋሚዎች በመሆናቸው እንዴት ተደርጎ ይሠራል? ብቻዬንስ እንደምን እወጣዋለሁ? የሚለው ጥያቄ አስጨነቀኝ ወዲያው አንድ ነገር ወደ ልቤ መጣ ‹‹ትንህርት ቤት እየሠራሁ ነውና አግዙኝ እናንተም ፊደል አስቆጥራችኋለሁ›› ብላቸው ቤቱን ይሠራሉ ከዚያም ወንጌልን መስበክ እጀምራለሁ ስል አሰብኩ ውጥኔንም ነገርኳቸው ተስማሙ እኔ ጋ ድርሽ ብለው የማውቁት ሁሉ እንጨት ቆርጠው የቤቱን ሥራ ያፋጥኑት ጀመር ትልቁ አዳራሽ ተሰርቶ አለቀ መስቀል ተከልኩበት ፊደል ገዛሁና ማስተማሬን ልቀጥል መስቀል ተከልኩበት የሚገባበት ጠፋ ሁሉም ጰየንጤ ዘንድ አንገባም ሲሉ አደሙ ምንም ማድግ ስላልቻልኩ መጸለዬን ቀጠልኩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ወላጅ እናቴ ልጄ ታሞ ጫካ ውስጥ ብቻውን ስለሆነ እጠይቀዋለሁ ስትል ሦሥ ሕፃናትን አስከትላ መጣች ልጆቹን ፊደል አስቆጠርኳቸው ወንጌልንም መሰከርኩላቸው ከዚያም ሌሎች ሲያደርጉ እንዳየሁት እጄን ጭኜ ጸለይኩላቸው በቋንቋችንም መዝሙር አስጠናኋቸው አባቴ ከሞተ ጀምሮ አሁን ከሠራሁት ቤት ጎን ያለው የውቃቢ ቤቱ እንዳለ አለ፡፡
ዝግ ነው የመሥዕዋት ዕቃዎቹና የቃልቻ መሣሪያዎቹ በመላ በሳጥን ተከተው ተቀምጠዋል ቤቱን ላፈርስና እቃዎቹን ላጠፋ አሰብኩ ጸለይኩበት ለእናቴ ቤት እሠራለሁ ስል ወንድሞቼን ቀሰቀስኩ በሉ መጀመሪያ ይህን ቤት እናፍርስ ስል ፍርሃት ገባቸው ጥቂቶቹን ይዤ ቤቱን አፈረስኩ እቃዎቹን በሙሉ አወጣሁና ሰበርኩ ግማሹን ጣልኩ የተቀረውን አቃጠልኩ የነበሩትን መቀመጫዎች ግን ወደ ጸሎት ቤት ውስጥ አገባኋቸው ሰው ሁሉ በላይ ከዛሬ ነገ ይሞታል በማለት መጠባበቅ ጀመረ እናቴ ስጋት ገባት ቀን ቀንን ተካ ሞት ግን ወደ እ ሊመጣ አልቻለም በዚህ ሳቢያ ወንድቼን እህቶቼንና የእንጀራ እናቴን ጨምሮ 16 ሰዎች ጌታን አገኙ አባቴ 48 ልጆች ነው ያሉት ከ8 ሚስቶቹ የወለደው ሃያዎቹን በሽታና መንፈሱ ጨርሷቿል እንግዲህ ከተረፉት መካከል ነው 16ቱ ወደ ጌታ የመጡት እነርሱን ሰብስቤ ማስተማር ጀመርኩ፡፡ውስጤም የቃልቻውን መንፈስ በመበቀል ቅናት እየተሞላ መጣ መንፈሱን ማጥፋት አለብኝ ስል በጌታ ተማመንኩ ብዙ ሰዎች ወደ እኔ መምጣ ጀመሩ ቃልቻው ኃይል እንደሌለው በማስረዳት የወንልን ቃል አስተማርኳቸው ጌታን መቀበል ጀመሩ በቁጥርም እያደግን መጣን ኅብረትን መሠረትን እኔም ፕሮግራም እየመራሁ ቃልንም እየሰበኩ በምድሪቱም በመዘዋወር እየተመሰከርኩ የወንጌላዊነት ሥራዬን ቀጠልኩ፡፡ ብዙ ተቃውሞ ነበር፡፡ ሆኖም መስበኬን አላቋረጥኩም፣በዚህ መሀል በመንግስት ሥራ ሳቢያ ማለትም ለ1ዓመት ያህል ግብርና ሥልጠና ለመከታተል ሄድኩ፡፡ ከዚያም ሆኜ ልቤ ወደ ወንጌል ሥራ ነበር የሚጎተተው ውስጤ ይቀጣጠል ጀመር ‹‹እግዚአብሔር ሆይ ለዚህ ምድር›› በረከት አድርገኝ የሚለው ጸሎት አልተቋረጠም፡፡
ትምህርቱን ጨርሼ እንደወጣሁ በከብቶች ሕክምና ላይ ተሰማራሁ በተለያዩ ቀበሌዎች እየተዘዋወርኩ በማከምበት ወቅት የከበቶቹን ባለቤቶች በመሰብሰብ ወንጌልን እነግራችኋለሁ ብዙዎቹንም ምርኮ በማድረግ እግዚአብሔር ሰጥቶኛል መንፈሳዊ ልጆቼም በጣም ብዚ ናቸው ብዙ ናቸው፡፡ ከሦስት ዓመት በኋላ እግዚአብሔር ለወንጌል የመውጣትን ጥሪ ወደ ሕይወቴ አመጣ እንግዲህ ከሥራ የመልቀቂያ ወቅት መድረሱ ግድ ሆነ፡፡ መሥሪያ ቤቴን ለቅቄከመውጣቴ በፊት ስለክርስቶስ አዳኝነት ያልመሰከርኩላቸው የሥራ ባልደረቦቼ አልነበሩም በዚያም እግዚአብሔር ብዙ ምርኮ ሰጥቶኛል ሆኖም የወንጌል ሸክም ውስጤን ስለሞላ እዚያ መቆየት አልቻልኩም ስለዚህ በሳላምና በፍቅር ተሰናበትኩ ከዚያም ሙሉ በሙሉ ለወንጌል ሥራ ራሴን ሰጠሁ ጌታም ብዙ ሥራዎችን በእኔ አከናወነ አስካሁን ወንጌል በደረስኩባቸው ቦታዎች አብያተ ክርስያናት ተተክዋል ይሄን እን አሁንም እንኳ ወንጌል ያልደረሳቸው በር ካታ ሥፍራዎች እንዳሉ አቀወቃለሁ ብዙዎች በቃልቻ እሥራት ውስጥ አሉ ወደነሱ ለመሄድ ሰፊ ልብና መነሳሳት አለ፡፡ ታላቅ ወንድሜ በአባቴ ላይ የነበረው የቃልቻ ምንፈስ እንዲወርድበት የጋለ ፍላጎት አለው መንፈሱን ወርሶ ምድሪቱን ሊገዛ ይመኛል መንፈሱ ከወረደበት ደግሞ ያባቴ ለወለዳቸው ልጆች የሚመጣውን ጥሎሽ ጨምሮ ያባቴን ገባሮችም ይወርሳል ማለት ነው እንግዲህ ወንድሜ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ላይ እያለ ነበር ወደ ጌታ የመጣሁት እናም ከፍተኛ ጠላት ሆኖ ተነሳብኝ ደግሞም የክርስቶስን ነገር ስለማወጅ ጥላቻው ጨመረ ሊገድለኝም አሸመቀብኝ ጉዳዩ እናቴ ጆሮ ስለደረሰ አንተ ካልጠፋህ የቃልቻው መንፈስ ሊሰራ እንደማይችል ስላወቀ ነፍስህን ይፈልጋታልና ተጠንቀቅ ስትል ነገረችኝ መንፈሱን የመቀበል ስሜት ውስጤ ሞላ እግዚአብሔርም አነሳሳኝ እናም የሰይጣንን አሰራርን መቃወም ከጀምርኩ ጭራሽ ባሰበት ጦርና ገጀራ ይዞ ከመንገድ ይጠብቀኝ ጀመር ከአንድ ማሕጸን የወጣን ብንሆንም አምስት ዓመት ሙሉ ሰላምታ ሰጥቶኝ አያውቅም በተቃራኒው ለእርሱ ያለኝ መውደድና ፍቅር እየጨመረ መጣ አጥብቄ ጸለይኩላት ደብዳቤም ጻፍኩለት ይሁንና የምልክለትን ደብዳቤ ሳያነበው ያቃጥለዋል በኋላ ግን እግዚአብሔር መንገድ አዘጋጀልኝ፡፡ ከብቶችን ለማከም ወደ መንደራቸው ወጣሁ የአካባቢው ሰዎች ከነከብቶቻቸው ሲመጡ እሱ ግን ከብቶቹን ይልክና ይቀራል እኔ እያለሁ እዚያ ይቆምም ለዓይን ይጠላኛል ከዚህ የተነሳ የታመሙበትን ከብቶች አክሜና የተጎዱበትንም ረድቼ ሰድለታለሁ ቀስ በቀስ ፍቅር አሳየው ጀመር፡፡
አንድ ቀን ወደ መንደሩ ስሄድ አንድ አሳብ ወደ ልቤ መጣ ጴጥሮስ ክርስቶስን ስለበደል ሲጠይቀው ምህረት ሰባ ጊዜ ሰባት እንደሆነ ነበር ያሳውቀው ታዲያ ወንድ ሊገድልኝ እንኳ ቢያስብ ይቅር ልለው እንደሚያሻ ወደ ቤቱም ሄጄ ያን ላደርግ እንደሚገባኝ አመንኩ በጉዳዩ ላይ ጸለይኩበት በአንደኛው የእግዚአብሔር መንፈስ ውስጤን ሲያነቃቃኝ ይታወቀኛል በረታሁ ስደርስ ቤቱ ዝግ ነው፡፡ ተኝቷል በሩን አንኳኳሁ ደጃፍ ዝር ካልኩ አምስት ዓመት ሆኖኛል ወደ ውስጥ ዘ፤ልቅሁ ከእንቅልፉ ተነስቶ አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለ፡፡ በፍቅር አናገርኩት ወንድ ሆይ አንተን በድያለሁ እስካሁን ድሰረስ በክርስቶስ ምክንያት እንዲህ ተለያይተን አለን፡፡ እኔ ደግሞ እወድሃለሁ ስል እግሩ ሥር ወደቅሁ ደንግጦ ተነሳ ከዚያም እኔ እኮ ነኝ የበደልኩህ አንተ መቼ በድለኸኝ ታውቃለህ ልገድልህ እንኳ የተነሳሁት እኔ አይደለሁም? ይቅር ብዬሃለሁ አለኝ ተቃቀፍን እንባዬ ወረደ ባለቤቱ በላይ ምን ሆነህ ነው የምታለቅሰው? አለችኝ መልስ አልሰጠኋትም እያለቀስኩም ስለጌታ ነገርኩት እንዲያድንህና እረፍት እንድታገኝ ብየየ እንጂ ለሌላ እኮ አይደለም ስል ገለጥኩለት ወደ ቤተክርስቲያን መጣሁ ከዚያም ወንድሜ ከዚህ ጉባዔ ጋር እንደሚቀላቀል በእምት መናገር ጀመርኩ፡፡ ታናናሽ ወንድሞች አሉኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው የሚያገለግሉት ታድያ በአንደኛው ዕለት ለወንጌል አገልግሎት እንደወጣሁ ታላቅ ወንድ እነዚህን ልጆቹን አስጠርቶ እንዲመሰክሩለት ፈለገ በጣም ፈሩ የሚገድላቸው መሰላቸው እናም ለሌሎች ሰዎችን ጠርተው አብረው ሄዱ እጅ ጭነውለት መጸለይ ሲጀምሩ በውስጡ ያለው አጋንንት ጮኸ በክርስቶስ ስም ገሰጹት ለቅቆ ወጣ በዚያን ዕለት እሱን ጨምሮ ሳበት ሰዎች ጌታን አገኙ እግዚአብሔር አስደናቂ ምርኮ ሰጠን ወሬውን እንደሰማሁ ከማገለግልበት ቦታ በደስታ እየዘለልኩ ወደ ቤቴ ሄድኩ አልቅሼ ሳምኩት ወደ ቤተክርስቲያናችን መጣ ድኅነትን አስተምረው ጀመር በትምህርቱም ውስጥ ከዚህ ቀደም ብዙ ሰዎችን በድለሃል ስለዚህ ይቅርታ መጠየቅ አለብህ ስል ነገርኩት ልክ እኔ እንዳደረግሁት ሁሉ በየቤቱ እየዞረ ባስቀየማቸው ሰዎች እግር ሥር በመውደቅ ይቀርታ ለመነ ከእናቴም ጋር የነበረውን ጸብ በዚህ መንገድ አስተካከለ ከዚያ በኋላ ሕይወቱን በመንፈሳዊ ነገር መቅረጽ ጀመርኩ በመጨረሻም አጠመቅሁት ያ አሳዳጅ ዛሬ የመቤተክርስቲያን መሪ ሆኖ ያገለግላል ለብዙዎች ይጸልያል ከዚያም አልፎ እኛም እንኳ በጌታ ቃል ይመክረናል ያስተምረናልም፡፡
በአካባያችን የውቃቢ አምል ይበዛል እናቴ በባሏም ሆነ በአባቷ በኩል በዚህ አምልኮ የተተበተበች ናት በዚያ ላይ ታላላቅ ወንድሞቿ ባላባትም አስገባሪም በመሆናቸው የነርሱ ትምክህት ፊቷን ወደ ክርስቶስ እንዳትመልስ አድርጓታል በዚህም መሃል ከእናቴ ጋር የሚኖረው ታናሽ የሆነው ልጅ ድንገት ይታመማል ሊሞት ሲቃረብ ልከው አስጠሩኝ ቤት ስደርስ ወገኖች እየጸለዩለት ነበር ተዝለፍልፎ ቃሬዛላይ ተዘርግቷል ሆስፒታል ሊወስዱት አስበው ስለደከመ ነበር የተውት በእምነት እንዲጸልዩለት ነገርኳቸው ቤተዘመዶች ያለቅሳሉ የአካባቢው ሰዎችም ቤቱን ሞልተውታል ሁሉ እንዲሰሙ ድምጼን ከፍ አድርጌ ጌታን የምትቀበሉ ስ አወጅሁ አንዳንዶች ቀስ ብለው መውጣት ጀመሩ በዚህ መሃል አንድ ወንድም ወደ እናቴ ዘወር ብሎ እማማ ከእኛ ጋር መጸለይ ስለማይችሉ ውጪ ይቆያሉ? ወይስ ያምናሉ? ሲል ጠየቃት እሷም እኔ ጌታ እየሱስ ብዙ ነገር ሲያደርግ አይቻለሁና ከእናንተ ጋር እጸልያለሁ እሱንም እቀበላለሁ በማለት ተንበረከከች ወዲያው እጅ ጭኜ ጸለይኩላት ከክርስቶስም ጋር ቃል ኪዳን አስገባኋት ጌታንም ተቀበለች ቤቱ በእልልታ ሞላ ከዚያም በኋላ ወንድሜ ቢሞት እንኳ ግድ አልነበረኝም ምክንያቱም እሱ ወደ ጌታ ነው የሚሄደው እናቴ ግን ከዘላለም ሞት ነበር የዳነችው ስለዚህ በደስታ ሰከርኩ ከጠዋት የጀመረው ጸሎት እስከ ምሽቱ ስድስት ሰዓት ዘለቀ ሰውም ደከመ እስካሁን አልተነሳም ወንጌልን ከፍቼ መናገር ጀመርኩ በዚያ ቅጽበት ሞቷል የተባለው ልጅ ብድግ ብሎ ተነሳ ዳነ ቤቱ እንደገና በእልልታ ተሞላ ከዚያ በኋላ እናቴን ማስተማር ቀጠልኩ አጠመቅኋትም ዛሬ ከሁለቱ እህቶቼ በስተቀር የተቀሩት እህትና ወንድቼ በሙሉ በጌታ ናቸው ብዙ ዘመዶቼም እንዲሁ ከእዚህ መካከል ቤተክርስያንን የሚመሩ በእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምሩና የሚማክሩ አሉበት፡፡
መቼም ይሕ ሁኩ ያለምን ውጊያና የሰይጣን ተግዳሮት ተመርቶ ተከናወነ ማለት አይቻልም ብዙ ብዙ ችግሮችና የሰይጣን ውጊያዎችን አልፈን ነው እንዲህ ያበብነው ያፈራነው አዲስ ዐይንአማባ ለምትባለው ከተማ ሸክም ስለነበረኝ ወደዚያ ሄድኩ አንድ ቡት ገብቼ ወደ ጌታ ልባቸውን መመለስ ጀመሩ በዚህ ጊዜ ቤተዘመድ የሆነ አንድ ታጣቂ ካልገደልኩ በማለት ክላሹን አቀባብሎ አፈሙዙን ወደ እኔሀ ሰጠሁ መስዋዕት ለመሆንም ተዘጋጀሁ ይሁንና በመሃል የሆነውን ባላውቅም ክላሹን አስቀመጠ እኔም ወጥቼ በአካባቢው መስበኬን ቀጠልኩ ብዙ ሰዎችን ባላንጣ አድርጎ አስነሳብኝ ዳግመኛ ወደ ከተማው ስመለስ የቀበሌ አስተዳደሮች ከመንገድ ጠበቁኝና ሊያስሩኝ ፈለጉ እግዚአብሔር በዚያ ሥራ እንዳለው በማሰብ ሳላንገራግር ሄድኩ የቀበሌው ሕዝብ ቄሶች ሽማግሌዎች ሼኪዎች እና ሕፃናት ተሰባስበው ጴንጤው ተያዘ በማለት ከተማውን አናውጦ ቢሮ ይዘውኝ ከገቡ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቀረቡልኝ ሕፃናት ከደጅ ይሰድቡኝ ጀመር ያኔ ነበር የጌታን ነገር ያሰብኩት እንዲያስችልለኝም ጸለይኩ በመጨረሻም ያለ ሕግ ፈረዱብኝ እስር ቤት እንድገባ ተደረገ ወደ ውስጥ ስገባ አልፈተሸኩም ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱሴን ይዤ ገባሁ ብዙ እስኞች አጋጠሙኝ ወንጌልን ለመስበክ ምቹ አጋጣሚ ነበር ሆኖም እስረኞቹ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ሸሹኝ መጸለይ ጀመርኩ ከዚያም በድፍረት የወንጌልን እውት ነገርኳቸው ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ባለሥልጣናቱ አስጠሩኝና ለምንድነው እዚህ አካባቢ መጥተህ የምትበጠብጠው? እንደሚያስቀጣህ አታውቅም? ሲሉ ተናገሩ አካባቢዬ ነው በማለት ከቤተክርስቲያን የተሰጠኝን ደብዳቤ አሳየኋቸው ማኅተም አርፎበት እያዩ ሕጋዊ አይደለም ካሉ በኋላ ኪሳቸው ከተቱት ከዚያም ሃምሳብር ተቀጥተሃልና ክፈል አሉኝ የለኝም ስል መለስኩ አንድ ሰው ጴንጤ ስታደርግ ይከፈልህ የለ? በድጋሚ ጠየቁኝ ገንዘብ እንደሌለኝ ገለጥኩላቸው ጴንጤ ካደረግሃቸው ሴቶች ተበድረህ አምጣ ጥያቄአቸው ቀጠለ እንደማላደርገው ገለጥኩ ጥለውኝ ሄዱ ወይ አልፈቱኝ ወይ አላሰሩኝ ተከትያቸው ወጣሁና ወንድች ጋር አደርኩ ነገ ስለሚሆነው ነገርም ጸለይን፡፡
ጠዋት ላይ አስተዳዳሪው ወደ እኔ እየሮጠ መጣ ትላንት የወሰደብኝም የቤተክርስቲያን ደብዳቤ በእጁ ይዞታል እንካ አለኝ እጁን ወደእኔ እየዘረጋ አክሎም ማታ ሲያስጨንቀኝ ነው ያደረው እንካ ተቀበለኝ ሲል አጣደፈኝ የእ ወረቀት የሰላም ደብዳቤ እንጂ የሚያስጨንቅ አይደለም ካልኩ በኋላ ተቀበልኩ በዚያ አካባቢ የተለያዩ ችግሮች ቢደርሱብኝም እግዚአብሔር ግን ብዙ ምርኮ ሰጥቶኛል ብዙ ወንድሞችና እህቶች አፍርቶልኛል ዛሬ ራቅ ወዳሉት ማትም ሱዳን ከኢትዮጵያ ወደምትዋሰንባቸው ድንበሮች ወንጌልን ይዞ የመሄድ ትልቅ ጥማት አለኝ አንድ ጊዜ እዚያው አካባቢ ካለችው አንድ አጥቢያ አገልግዬ ስመለስ የከባድ መኪና ሾፌርና ረዳቱ ከመንገድ አጋጠሙኝ ገቢና ነበር የተሳፈርኩት ሾፌሩ በእድሜ ጠና ያሉ ሲሆን ረዳቱ ደግሞ ጎረምሳ ነው ሲበዛ ያጨሳል ንግግሩ ትዕቢቱን ይገልጠዋል ጎዞአችን ረጅም የሆነ ረጅም የሆነ የበርሃ አካባቢን አቋርጦ ነው የሚያልፈው ጸሎት ጀመርኩ እግዚአብሔር ሆይ በዚህ መኪና ውስጥ ያሉትን ሰዎች አሳልፈው ጸሎት ጀመርኩ እግዚአብሔር ሆይ በዚህ መኪና ውስጥ ያሉትን ሰዎች አሳልፈህ ስጠኝ ገቢና በሲጋራ ጢስ ታፍኗል ጭሱን እየጠጣሁ መንገዴን ቀጠልኩ ጸሎቴ ግን አልተቋረጠም ረዳቱ ሲጋራ በሲጋራ ላይ ያቀጣጥላል መኪናው ይጓዛል ሾፌሩ ዝምታውን ጥሰው ወሬ ጀመሩ ‹‹ከየት ነው የምትመጣው?ለመሆኑ ዲማ የሚባል ቦታ ረገጠህ ታውቃለህ በማለት ጥያቄያቸውን ደረደሩ እዚህ ቦታ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የመጣሁትን ባየሁትም ነገር ተደንቄያለሁ ሰው ሁሉ በመጠጥ ኃይል አይደለም እንዴ የሚንቀሳቀሰው በዚያ ላይ የማየው ሁሉ አስደንግጦኛል አሉኝ መንገድ ከፈቱልኝ ስለዚህም ስለዘመኑ ክፋትና ርኩሰት መጠቃቀስ ጀመርኩ ለመሆኑ የት ሄደህ ነው የምትመጣው ጥያቄያቸውን ቀጠሉ ለወንጌል አገልግሎት ወጥቼ እንደምመለስ ነገኳቸው ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ነህ? አክለው ጠየቁኝ እንዴ እርሶ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያንን ያውቃሉ? በመገረም ጠየቅኋቸው ድሮ ቀጠና ሁለት የሚባል ቦታ እሄድ ነበር አሁን እዚህ ፕሮጀክት ከመጣሁ ወዲህ ትቻለሁ አሉኝ የእግዚአብሔር ቃል ስለ መዳን የሚያስተምረውን ትምህርት መተንተን ጀመርኩ ረዳቱ በቁጣ ተሞላ መኪናው ይጓዛል ሽፍቶች ይኖሩበታል ተብሎ ከሚታሰበው ክልል ገባን ለመሆኑ ከአባታችን ጋር የምንነጋገረው ጉዳይ ገብቶሃል? ረዳቱን ጠየቅሁት እየሰማሁ ነኝ መልስ ሰጠኝ አንድ ምሳሌ ወደ ልቤ መጣ አሁን ይሕ መኪና እንደተጓዘ አይከርምም አንድ የሚቆምነት ቦታ አለው ሕይወትም ደግሞ እንዲሁ የሚያከትምበት ቦታ አለው ታዲያ የእግዚአብሔርን መንገድ ያላወቀ ሁሉ ደግሞ የዘላለምን ፍርድ ይጠብቀዋል በማት ማብራራቴን ቀጠልኩ ጆሮውን ሰጥቶ አደመጠኝ ልቡ መቅለጥ ጀመረ መጽሐፍ ቅዱሴን ገልጬ በደንብ አስረዳሁት ከዚያም አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን መግባት አለብህ በማለት ገለጥኩለት አልተቃወመም ቀጥሎም እጅህን አንሳና እኔ የምለውን በል በማለት ነገርኩት እጁን ዘርግ ጌታን ተቀበለ መኪናው አሁንም ይጓዛል እጄን ልቡና ጭንቅላቱ ጭኜ ጸለይኩለት መኪናው ወደ መዳረሻችን ተቃረበ አድራሻዬን ሰጠሁት በአቅራቢያው ወዳለው ቤተክርስቲያን በመሄድ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰማ መከርኩት ተለያየን፡፡
ይኼ አንደኛው ገጠመብ ቢሆንም በተለያዩ ሥፍራዎች ሰዎች ጌታን ያገኘሁበትን ሁኔታ ሳስብ ደግሞ ሁሌም ይገርመኛል ከብት የሚጠብቁ እረኞች ከብትየሚጠብቁበት ሜዳ ላይ እንዲሁም መንደሮችን አቋርጬ በምሄድበት ወቅት ባለፍኩበት ቦታ ብዙ ምርኮዎችን ጌታ ሰጥቶኛል፡፡ በአካባቢዬ ወንጌልን መዝራት ስጀመር ቃሉ የደረሳቸው ጥቂት ሰዎች በላይ የሚያመልከው አምላክ ነጻ ያወጣል እያሉ ከመናገራቸው የተነሳ እንዲሁም የአባቴን የውቃቢ እቃዎች ማጋየቴ ተደምሮ ጓደኞቹ የሆኑ ባላባቶች እንዲሁም ከዘር የሚተላለፍ መንፈስ ያረፈባቸው ባለውቃቢዎች ገለውኝ ክብራቸውን ሊያስመልሱ አስደበደቡኝ ሊያጠፉኝም ተማማሉ አጥብቄ ጸለይኩ ወደ እግዚአብሔርም ጮህኩ ስማቸውን ማንሳት ባያስፈልግም እኒህ ዝናቸው ጎልቶ የነበረና ተሸጋጋሪ መንፈስ ያላቸውን ሰዎች ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በከታታይ አለቁ እኛም ተሰባስበም መንፈሱ በማንም ሰው ላይ እንዳይወርድ አጥብቀን በመቃወም ጸለይን እስከዛሬ አንድም ሰው ላይ ሳይመጣ እንደተመታ መቅረቱ ደግሞ የእግዚአብሔርን ብርቱ ክንድ አመላክቶናል ብዙ የማወራውና የምተርከው ቢኖረኝም ከጊዜው አንጻር ሁሉንም የማዳርሰው አይመስለኝም ዛሬም ቢሆን የበለጠ በቃሉ ተሞልቼ ራቅ ወዳሉ ሥፍራዎች ወንጌልን የማድረስና ቤተክርስቲያንን በቃሉ የማሳደግ ሸክምና ጥማት አለኝ፡፡ ጌታም እንደሚረዳኝ አምናለሁ ደግሞም በዚያ የሚከናወነው የጌታን ድንቅ ሥራ ለወደፊት እተርከዋለሁ፡፡
ብርሃን መፅሔት
ቁጥር 39 1992
Copyright Hiyawkal © 2025
Leave a Reply