7 ኢየሱስ በመጨረሻ ትምህርቱ ላይ ያስተማራቸው ጠንካራ ነጥቦች

ሮን አለን :

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ለእያንዳንዷ እስትንፋስ በከፍተኛ ስቃይ እየታገል ሣለ፣ እርሱ ማን እንደነበረ እና በወቅቱ ምን እየሆነ እንዳለ የሚያሳዩ ሰባት አጫጭርና ኃይለኛ ንግግር ተናገረ። እርሱንም በነዚህ ቃላት፣ እርሱን የሚከተሉን ሰዎችን በሙሉ ያበረታታል። ይህ የእርሱ የመጨረሻ ስብከት ነበር።

  1. “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” (ሉቃ 23:34)

ኢየሱስ በሄደበት ለሰዎች ይቅርታን በመስጠት ብቻ ሳይሆን በመስበክም አገልግሏል (ማቴ 5፡44)፣ ለሃጥያት ይቅርታ በማድረግ መለኮታዊ ጌታ መሆኑን አውጇል (መዝ 103፡3)። ከዛም ባለፈ፣ እርሱ በስሩ ሃጥያታችን ይቅር የሚባልበት የአዲሱን ኪዳን ጅማሬ አስተዋውቆናል (ኤር 31፡33፣34)።

2. “እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው” (ሉቃ 23፡43)

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለወንጀለኛው ህይወትን ቃል መግባቱ፣ በገነት ላይ ስልጣን እንዳለዉ ያሳያል (መዝ 115፡16)፣ ሞትን ድል ይነሳል (መዝ 16፡10) ደግሞም በርሱ እኛ ሕያዋን እንሆናለን (ዮሐ 14፡19)። ከቶ በማይጠፋው ህይወቱ ምክንያት እርሱ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን ነው (ዕብ 7፡16-17)።

3. “አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ … እናትህ እነኋት አለው” (ዮሐ 19፡26፣27)

ኢየሱስ የእናቱን ጥበቃ፣ የሚወድደውን ደቀ-መዝሙር ዮሐንስን በማመን ሰጠው፣ በመዝሙር 69፡8፤ ከወንድሞቹ እንደባዳ ተቆጠረ ይላል፣ በዚህም ቃል እግዚአብሔር፣ ቤተሰቦቻቸንን ማክበርና ቦታ መስጠት ከኛ እንደሚጠበቅ እያስተማረን ነው (ማር 7፡10-13)። ኢየሱስ “የሴቲቱ ዘር” እንደሆነም እናስታውሳለን፣ ይህንንም ከድንግል የሚወለደው አዳኝ በዘፍጥረት 3፡15 ላይ ቃል ገብቶልናል።

4. “አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ?” (ማቴ 27፡46)

ይህን የኢየሱስ ቃል የሰሙ አብዛኛዎቹ ሰዎችና ብዙ አስተያት ሰጪዎች እስካሁን ያልተረዱት ነገር፤ ኢየሱስ መዝሙር 22ን እየጠቀሰ መሆኑን ነው። ከ1000 አመታት በፊት በእርሱ ላይ እንደሚሳለቁበት፣ የዘባቾቹ ቃል እንኳ ሳይዛነፍ በትንቢት እንደተነገረ ሊያሳየን ነው ኢየሱስ ወደ መዝሙር 22 የመራን (መዝ 22፡6-8)። በአንድ በኩል በተሳለቁበት ላይ እየተሳለቀ ነበር ማለት ይቻላል። በስቅላቱም እጅና እግሮቹ እንደተቸነከሩ (መዝ 22፡16)፣ በልብሶቹ ላይ እጣ እንደተጣጣሉ (መዝ 22፡18) እና ሊናገር እንደከበደው (መዝ 22፡15) ተገልጾአል።

ሆኖም መዝሙር 22 የተስፋ መቁረጥና የመጣል ምልክት ሳይሆን፣ ድልን የማብሰሪያ አዋጅ ነው። ጌታ፣ የኢየሱስን ስቃይ አይቶ ቸል አላለም (መዝ 22፡24)። ነገር ግን የዘላለምን ህይወት ሊገዛ ተጠቀመበት (መዝ 22፡26) ደግሞም አህዛብ ወደ ኢየሱስ እንዲመጡ ቃል ገብቶልናል (መዝ 22፡27፣28)። ኢየሱስ፣ ሊከፈል ያለውን ዋጋ እንደሚያውቅና በደስታም እንደከፈለው ሊነግረን ወደደ።

5. “ተጠማሁ አለ” (ዮሐ 19፡30)

በስቃይ ያለው አዳኝ ለጥሙ ኮምጣጤን ሲሰጡት፣ ይህ ሌላው የትንቢት ፍጻሜ ነበር (መዝ 69፡28)። በህመምና በሰቀቀን ውስጥ ጌታን የሚፈልጉ በህይወት እንደሚኖሩ ሊያመለክተን መዝሙር 69፡12ን ተጠቀመ። እናም እግዚአብሔር የሕዝቡን ሥቃይ ተመልክቶ ቸል አይልም (መዝ 69:33)። ደግሞም ሕዝቦቹ ይሁዳን ዳግመኛ መልሰው እንደሚገነቡ የተነገረ የተስፋ ቃል አለ (መዝ 69:35፣ 36)፤ ይህም ተመልሶ እንደሚመጣ የገባውን ቃል በግልፅ የሚያስታውስ ነው።

6. “ተፈፀመ” (ዮሐ 19፡30)

ይህን ቃል በደንብ ለመረዳት፣ የነብዩ ዳንኤልን መጽሐፍ ማየት ይጠበቅብናል። ከ 483 አመታት (69 ጊዜ 7) ብኋላ ማለትም ኢየሩሳሌምን ዳግም ለመገንባት ከወጣው አዋጅ (458 ዓ.ዓ) ወይም በ 26 ዓ.ም በኋላ ፣ የተቀባዉን መምጫ አስቀድሞ ተናግሯል። ከዚያም ደግሞ በሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት መካከል እንደ ሚገደልም ተናግሯል (ዳን 9:25፣ 26)። ኢየሱስ በዳንኤል ትንቢት፤ ኃጢአትን እንደሚያጠፋ፣ ለክፋት ስርየት እንደሚያደርግ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን እንደሚያመጣ፣ ትንቢትን በማተም እና ቅዱሱን እንደሚቀባ (ዳንኤል 9፡24) ያለውን ቃል እንደፈፀመ እያስተማረን ነው። ይህ በመስቀል ላይ የተፈፀመው የኢየሱስ ሥራ ነው።

7. “አባት ሆይ፤ መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ” (ሉቃ 23፡46)

የኢየሱስ በመስቀል ላይ የተናገራቸው የመጨረሻ ቃላት ከመዝ 31 የተወሰዱ ናቸው። እርሱ ወደ እግዚአብሔር መሰደድ እንደምንችል እየነገረን ነው (መዝ 31፡1-4) እና እግዚአብሔርን በህይወታችን ልናምነው እንደምንችልም ጭምር (መዝ 31፡15)። ጊዜአችን በእርሱ እጅ ነው (መዝ 31፡19-22)። እንዲሁም የሚታመኑትን እርሱ ይጠብቃል (መዝ 31፡23-24)።

ኢየሱስ በመጨረሻ ትምህርቱ፣ እያደረገ ያለውን ነገር ልክ እያደረገው ሣለ በግልፅ አስተማረን።“አባት ሆይ፤ መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ” በማለት ከእርሱ ጋር መቀላቀል ትችሉ ይሆን?

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox