በመንፈስ አለም ውስጥ ቀን ወይም ሌሊት እንደሌለ ታዉቃላቹ? እንዲያውም፣ መንፈሳቹ ሁል ጊዜ ንቁ ነው፣ ሰውነታቹ ተኝቶ ሳለ እንኳ።
ከሙሉ ለሊት እንቅልፍ ዉስጥ በጦርነት እንደዘመተ ሰው ድካም እየተስማቹ ነቅታቹ ታዉቁ ይሆናል። እውነታው ግን እናንተ እንቅልፍ ብላቹ ምትሰይሙት፣ እንዲያውም መንፈሳቹ ከመንፈሳዊ አለም ጋር የሚጣመሩበት ልዩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ከዛ ባለፈ ግን፣ አጽናፈ ሰማይን የፈጥረ፣ ለእናንት ህይወት በእጅጉ ግድ የሚለው፤ እርሱ ሊያናግራቹ ፈልጎ ይሆናል።
ሁላችንም በታላቅ መገለጥ መጓዝ እንድንችል፣ ለሕልማችን የበለጠ ትኩረት የምንሰጥ ከሆነ ለህይወታችን ግንዛቤ እና ታዕምራዊ ስልት እንድናገኝ አስባለው። ደግሞም ከሕይወታቹ አንድ ሦስተኛ ያህሉን በማንቀላፋት ታሳልፋላቹ። እግዚአብሔር ሕያው ቃል ነው፣ እና እርሱ ሁል ጊዜም እየተናገረ ነው። እርሱ የእናንተን እንቅልፍ እንደባከነ ጊዜ አይመለከተውም እናም እናንተን ለመናገር ሊጥቀምበት ይችላል።
ሕልም ሙሉውን ህይወታቹን ሊቀይር ይችላል
ከእግዚአብሔር የመጡ ሕልሞች፣ ልክ ጌታ በሌላ መንገድ እንደሚያናግረን ሁሉ፣ በህይወታችን ዉስጥ ታዕምራትን ለመክፈት የሚጠቅሙ መለኮታዊ ቁልፎች ሊሆኑ ይችላሉ። ጌታ ብዙውን ጊዜ በሕልም ይነግረኛል፣ እና ባለፈው ዓመት፣ የምወዳቸውን ጥቂት ሰዎች በእኔ በራሴ የስኬታማነት ስሜት እየተገፉ ከነበረበት እውነታ እኔን ያነቃኝ ሕልም አየው። ሕልሙ ልክ እና ስፍራ እንዳላቸው የማይሰማቸው ሰዎች እንዴት በጥሩ ሁኔታ እንደሚገባቸው እና ወደ ባለቤትነት መጠራታቸውን በጠለቀ ግንዛቤ ያሳያል።
ስለ ሕልሞች ሃይል፤ ውስጣዊ ማንነታቹን የሚያነቃው ምስክርነት
አንድ ጓደኛዬ የወንድ ልጁ ጋብቻ እንዴት በሕልሙ እንደተመለሰ የሚገልጽ አንድ ታሪክ ነገረኝ። ወንድ ልጁና ምራቱ ለአንድ ዓመት ያህል በአንድያ ልጃቸው የአሳዳጊነት መብት ለማኘት አስቀያሚ ውጊያ ተዋግተዋል። ትዳራቸው አበቃ፣ እናም ባሏ የልብ ለውጥ ስላደረገ ከባለቤቱ ጋር ለመታረቅ ቢፈልግም፣ እሷ ግን ተጎድታ፣ ተቆጣና ተማርራ ነበር። እርሷም ማንኛውንም አማካሪ አልተቀበለችም እና ከቤተሰቧ ጋር ያላትን ግንኙነት ሁሉ በማፍረስ ከማናቸውም ጋር ምንም ግንኙነት እስከማይኖራት ድረስ ተቆራረጠች።
ለመፋታት ከመሄዳቸው በፊት በነበረው ምሽት ላይ፣ የጓደኛዬ ምራት ህልም አየች። እሷም ውብ በሆነ የግጦሽ ጫፍ ላይ ቆማ እራስዋን አየች። ባልዋም በእርሻው መካከል ቆሞ ነበር፣ በድንገት ኢየሱስ በስፍራው ተገለጠ። እሱም ወደእርሷ ተመለከ፣ በፈገግታም እርሻው ውስጥ በመጓዝ ወደ ባሏ በኩል ተሻግሮ በእርሱን አቀፈዋለሁ። ከዚያም ተዕይንቱ ተለወጠ።
አማቷ በአሁኑ ጊዜ በእርሻ መሃል ቆሞዋል፣ እና ጌታ በድጋሚ ተገለጠ። ለሁለተኛ ጊዜ ወደእርሷ ተመለከተ እና አማቷን እያቀፈ ፈገግ አለ። በቀጣዩ ትዕይንት፣ በአበባ ማሳዎች ላይ ራሷን ቆማ አየች። ኢየሱስ በእርሻው ውስጥ በእግር እየተራመደ ከርቀት ወደ እርሷ ሲመጣ ተገለጠ። ልክ ጌታ ሊቀበላት እጁን ሲዘረጋ፣ ከእንቅልፏ ነቃች።
ወዲያውኑ ከባለቤቷ ጋር የነበራትን ግንኙነት ለማደስ የሚያስፈልገውን ጸጋ ጌታ እየሰጣት እንደሆነ ተገነዘበች። ከጠዋቱ 11 ሰዓት ላይ ከአልጋ ተነስታ ለባሏ ስልክ ደወለችለት፣ እናም በዚያኑ ቀን እርቅም አወረዱ፣ በደስታም አብረው መኖር ቀጠሉ!
ሳይስተዋሉ እንዲሄዱ አትፍቀዱላችው
ስለ ምስጢራዊው የሕልም ዓለም ብዙ ሚታወቅ አለ። ኢዮብ ስለ ሕልሞች ተፈጥሮ እና ስለ ዓላማቸው የተወሰነ ግንዛቤ ይሰጠናል፡
እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም። በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል፥ በተግሣጹም ያስደነግጣቸዋል፥ ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሰው ዘንድ ከሰውም ትዕቢትን ይሰውር ዘንድ፤ ነፍሱን ከጕድጓድ፥
በሰይፍም እንዳይጠፋ ሕይወቱን ይጠብቃል። (ኢዮብ 33፡ 14-18)።
ኢዮብ የአምላክ ሕልሞች ብዙውን ጊዜ ሳይስተዋሉ ያልፋሉ አለ። እርሱ እግዚአብሔር አመለካከታችንን ለመለወጥ ብዙ ጊዜ ህልሞችን እንደሚጠቀም ማብራራቱን ቀጥሎበታል። ነፍሳችን ጌታን ቢቃወም፣ እኛ እራሳችንን ሳናውቅ እስክናንቀላፋ ድረስ ይጠብቃል፣ ከዚያም ልባችንን በለሊት ራእይ ያቀናል። እንዲያውም የእኩለ ሌሊት መገናኘታችን ከሲኦል ሊያድነን እንኳን እንደሚችልም ይናገራል!
አንዳንድ ጊዜ እኛ የሚለውጡን ህልሞች እኛ የምናስታውሳቸው ህልሞች አይደሉም። ኢዮብ ያየው ሕልም እርሱ ያላስታወሰዉን ሕልም ነበር፣ ቢሆንም ግን፣ አመለካከቱን እንደለወጠ ያውቅ ነበር። አንዳንድ ሰዎች በጭራሽ ሕልም አናልምም ሊሉ ይችላሉ ነገር ግን ምናልባት እያለማቹ እና ማስታወስ እያቃታቹ ሊሆን ይችላል። ይበረታቱ-እግዚአብሔር አሁንም ታሪካችሁን ይቀይራል፣ ውስጣዊ አለማችሁን የለወጠውን ሕልም ባታስታውሱም እንኳን አሁንም ታሪካችሁን ሊቀረጽ ይችላል።
ሕልሞች እንደዛ በጣም ኃይለኛ ከሆኑ፣ ህልም እጣፈንታቹ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር፣ ልባቹን ወደ እግዚአብሔር ማዞር፣ ሁኔታን ግልፅ ማድረግ እና ተስፋ ቢስ መስለው በሚታያቹ ህይወት ውስጥ ያሉ ችግሮችን እንኳ ማስተዋል እና ማጥራት እንደሚችሉ አስባለው።
4 ህልማችሁን ለመረዳት የሚረዱ ቁልፎች
ምናልባት ካመለጠዎት፡ ህልሞች እግዚአብሔርን ለመስማት የሚደንቁና አስገራሚ መንገዶች ናቸው! በህልም ህይወታችዉ ውስጥ ለማደግ ለሚፈልግ ማናቸውም አማኝ አራት መሠረታዊ እውነቶች እዚህ አሉ፡
የህልም ጉዞን የበለጠ ማራመድ
እግዚአብሔር ለሰዎች ህልሞችን በትኩረት የምናከብራቸው፣ እና የምንንከባካባቸው አይንት ሰዎች እንሁን! ስለ ሕልሞች እና ራዕዮች ለማወቅ የሚቻል ብዙ ነገሮች አሉ። ጆን ፖል ጃክሰን፣ ጀምስ ጎል እና ሲንዲ ጄኮብስ ሁሉ የዚህን የእግዚአብሔር ቋንቋ ጥልቅ ግንዛቤዎች ስለ ርዕሰ-ጉዳይ የሚገልጹ አስደናቂ መጽሐፍቶች አሏቸው።መጽሐፎቻቸውን እንድታነቡ በጣም እመክራለው።
የምሽት ሕልም ከሌላቹ ግን ይህን ስጦታ የምትፈልጉ፣ ዛሬ እባርካቿለው። እግዚአብሔር ከእንቅልፍህ ጋር እንደሚገናኝህና የመንፈስ አለም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ እጸልያለሁ። በምሽት የእግዚአብሔር ድምፅ ሲያሰማ፣ በጥልቅ መገለጥ እና በግልጸት ከህልማቹ የምትነቁ ሰው ያድርጋቹ።እናንት ሓላሚ ናቹ? ሕልማችሁን ለመንከባከብ ምን እያደረጉ ነው? ሕልም እያንዳንዷን ህይወታቹን ለውጦታል? በአስተያየቶቹ ውስጥ ስለሂደቱ መስማት እፈልጋለሁ!
Copyright Hiyawkal © 2024
Leave a Reply