21 በትንቢት ማነፅ እና በማታለል መካከል ያሉ ንጽጽሮች

ዶ/ር ጆሴፍ ማቴራ :

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን እውነተኛ ትንቢት ቤተክርስቲያንን ያንፃል እንዲሁም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከፍ ከፍ ያደርጋል (1 ቆሮ 12፡3-7 እና 14፡3-4)። ይሁን እንጂ፣ እውነተኛ የትንቢት ስጦታ ባለበት ሁኔታ፣ የትንቢት ጸጋን ትክክል ባልሆነ መንገድ የሚጠቀሙ አይጠፉም። ለምሳሌ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነብዩ በለዓም የተሰጠውን ስጦታ ለገንዘብ ብልጽግና ሊጠቀም ሲሞክር እናያለን (ዝኁ 22፡21-39)። በዚህ የበለዓም ትረካ ውስጥ፣ ምንም እንኳ አላማው መልካም ባይሆንም፣ በለዓም ቦና ፊዴ (እውነተኛ) የትንቢት ስጦታ ነበረው።

ዳሩ ግን ዋናው ነጥብ፣ ሁሉም የትንቢት ስጦታዎች በተነሳሽነት፣ በዓላማና በዋናው የእግዚአብሔር ቃል ግብ የተመዘኑና የተቃኙ መሆን አለባቸው። ከ1980ዎቹ ጀምሮ በትንቢታዊ አገልግሎቶች እንደማገልገሌ መጠን፣ ትንቢታዊ ጸጋን ለማነፅም ደግሞ ተፅዕኖ በማድረግ ለመቆጣጠር ወይም ለማታለልም ሲጠቀሙበት አስተውያለው።በትንቢት በማነፅ እና በትንቢት በማታለል መካከል ያሉ ንጽጽሮች

  1. በትንቢት ማነፅ ቤተ-ክርስቲያንን ያድሳል፤ ማታለል ነብዩን ብቻ ይጠቅማል (1 ቆሮ 14፡4)።
  2. በትንቢት ማነፅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ማታለል የትንቢት ቃልን ለሚያካፍለው ብቻ ከፍታን ይሰጣል (1 ቆሮ 12፡3)።
  3. በትንቢት ማነፅ የእግዚአብሔርን መንግስት ያስፋፋል፤ ማታለል የነብዩን ተቋም ያሳድጋል (ማቴ 6፡33)።
  4. በትንቢት ማነፅ የቤተ-ክርስቲያኗን ራዕይ ያጠናክራል፤ ማታለል የነብዩን የሃብት አቅም ይገነባል (ዘኁ 22፣ ራዕ 2፡14)።
  5. በትንቢት ማነፅ ሰዎችን ወደ ቤተ-ክርስቲያኗ ራዕይ ይጠቁማል፤ ማታለል ሰዎችን ከቤተ-ክርስቲያን አርቆ ወደ ነብዩ ያቀርባል (ሐዋ 20፡30)።
  6. በትንቢት ማነፅ መንፈሳዊውን ሰው ይገነባል፤ ማታለል በሰሚው ስሜት ውስጥ ያልተፈቱ ችግሮችን ያባብሳል (ኤፌ 5:18-19)።
  7. በትንቢት ማነፅ ማስተዋልን ይገነባል፤ ማታለል ከአማኞች የዋሁን መጠቀሚያ በማድረግ ይጎዳል (ምሳ 1፡2-4)።
  8. በትንቢት ማነፅ በእግዚአብሔር ዕቅድ ተነሳሽነት ላይ የተመሰረተ ነው፤ ማታለል በነብዩ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ነው  (1ኛ ነገስት 22፣ ኤር 23)።
  9. በትንቢት ማነፅ ለመንፈሳዊ ስልጣን ተጠያቂ ነው፤ ማታለል ለማንም ተጠያቂነት የለውም (1 ቆሮ 4፡29)።
  10. በትንቢት ማነፅ የተገነባው በቅዱስ ቃሉ እንክብካቤ ላይ ነው፤ ማታለል የተመሠረተው በቅዱስ ቃሉን በማዛባት ላይ ነው (2 ጢሞ 3፡16፣ 17)።
  11. ትንቢት ማነፅ በእግዚአብሔር ላይ ታላቅ እምነትን ይሰጠናል፣ ማታለል በነብዩ ላይ ታላቅ እምነት ይሰጠናል (ዮሐ 7:18)።
  12. በትንቢት ማነፅ ከጌታ ምክር ይመነጫል፤ ማታለል የሚጀምረው ከነቢዩ አስተሳሰብ ነው (ኤር 23)።
  13. በትንቢት ማነፅ የእግዚአብሔር ልብ እና አዕምሮ መግለጫ ነው፤ ማታለል የነቢዩን ፍላጎት ይገልጻል (ኤር 7:24)።
  14. በትንቢት ማነፅ በፍቅር እውነትን ይናገራል፤ ማታለል ለግል ጥቅም ያሞግሳል (2 ጴጥ 2፡18)።
  15. በትንቢት ማነፅ በቤተክርስቲያን ውስጥ ላሉ ጎልማሳ ሰዎች ያግዛል፡ ማታለል ውሎ አድሮ ሰዎችን ከቤተ-ክርስቲያን ያፈልሳል (ሐዋ 15፡32)።
  16. በትንቢት ማነፅ ሰዎች ጌታን እንዲሹ ያነሳሳቸዋል፤ ማታለል ሰዎች ነብዩን እንዲፈልጉ ያነሳሳቸዋል (ኢሳ 55: 6-7)።
  17. በትንቢት ማነፅ ሰዎች የትንቢት ቃልን እንዲያረጋግጡ ይመክራል፤ ማታለል ሰዎች በራሳቸው ቃል እንዲመሩ ያስፈራራቸዋል (2 ቆሮንቶስ 13፡1)።
  18. በትንቢት ማነፅ ትሕትናን ያበረታታል፤ ማታለል ራስ ወዳድ ምኞትን ያበረታታል (ኢሳ 57:15፣ ፊሊ 2: 1-12)።
  19. በትንቢት ማነፅ የእግዚአብሔርን ክብር ብቻ ይሻል፤ ማታለል ብዙኦችን ሰውን ወደ ማሞገስ እንዲመጡ ያበረታታል (ዮሐ 7፡18)። 
  20. በትንቢት ማነፅ ዘላለማዊ ውጤት አለው፤ ማታለል ጊዜያዊ ውጤት አለው (1 ጴጥ 1፡25)።
  21. በትንቢት ማነፅ ሰሚውን ያሳድጋል፣ ማታለል በሰሚው ላይ አላግባብ ይጠቀማል (ኤፌ 4:29)።

በአጠቃላይ፣ ጌታ የትንቢት ሰዎችን ትክክለኛነት፣ ተፅእኖና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ያላቸውን ተስማሚነት መጨምርን እንዲቀጥል እንለምናለን።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox