15 ለሕልም አተረጓጎም የሚጠቅሙ ቁልፎች

!5 Keys for Dream
!5 Keys for Dream

ዶር. ጄምስ ጎል :

በሕልም ቋንቋ ውስጥ መመላለስ እና የእግዚአብሔርን አእምሮ እና ልብ መንካት አስገራሚ እና አስደሳች ጉዞ ሊሆን
ይችላል። ነገር ግን እርሱ በሕልም ዉስጥ የሰጠውን ራዕይ መረዳት እና መተርጎም ብዙውን ጊዜ ውስብስብ ብሎም ግራ የሚያጋባ ሂደት የሚሆንበት ጊዜ ይኖር ይሆናል።
እነዚህ 15 ቁልፎች የሕልም አተረጓጎም ሂደትን ቀላል እንዲሆንላቹ ለማድረግ ይረዳሉ፡

  1. በአብዛኛው፤ ህልሞች በመጀመሪያ በግለሰብ ደረጃ መተርጎም አለባቸው (ዮሐ 10፡3)።
  2. አብዛኛዎቹ ህልሞች ቃል በቃል (በጥሬው) መወሰድ የለባቸውም፤ ትርጓሜ ያስፈልጋቸዋል (ዳን 1፡17፤ ዘፍ 40፡8)።
  3. እግዚአብሔር እናንተ የምታውቋቸውን የተለመዱ ቃላት ይጠቀማል (ማቴ 4፡19)።
  4. በሕልሙ ወይም በራዕዩ ላይ አሰላስሉ እናም መንፈስ ቅዱስን እንዲረዳችሁ ጠይቁ (ዳን 7፡8፤ 8፡15- 16፤ ሉቃ 2፡19፤ 1ቆሮ 2:10-12)።
  5. መንፈስ ቅዱስን ማዕከላዊ ሃሳቡ ምን እንደሆነ፤ ቃል ወይም ጉዳይ በመገለጥ ውስጥ ምን እንደሆነ ጠይቁ። ህልሙን በጣም ቀላል ወደ ሆነው ቅርጽ ቀይሩት። ዋናው ሐሳብ ምንድን ነው?
  6. በቃሉ ዉስጥ ፈልጉት፤ ከእግዚአብሔር የመጡ ሕልሞች ፈፅሞ ከቃሉ በተቃርኖ አይመጡም (ምሳ 25፡2)።
  7. ከህልሙ ምን ስሜት ተሰማዎት? ጥሩ ወይም ክፉ መገኘት ነውን? ቀዳሚና ዋነኛው ስሜት ምን ነበረ?
  8. ህልሙን ከእርስዎ ሁኔታ እና የተጽዕኖ ምሕዋር ጋር ያዛምዱት።
  9. ተከታታይ የሆኑ ህልሞች ብዙውን ጊዜ ተመሳሳይ ፍችዎች አሏቸው (ዘፍ 41፡1-7)። እግዚአብሔር ከአንድ በላይ በሆነ መንገድ ተመሳሳይ መልዕክት ከአንድ ጊዜ በላይ ይናገራል።
  10. ቀለሞቹ ምንድናቸው? ሁሉም ነገር ጥቁር እና ነጭ ክአንድ ዋና ነገር በቀለም ነውን?
  11. ትርጓሜዎች በሶስት ደረጃዎች ላይ ሊገኙ ይችላሉ: የግል፤ ቤተ-ክርስቲያን ወይም ብሔራዊ እና አለምአቀፋዊ።
  12. ከአንድ በላይ ትርጉም በአንድ ህልም ውስጥ ሊወጣ ይችላል። ልክ እንደ መጻሕፍ ቅዱስ፤ ታሪካዊ ዐውደ-
    ጽሑፍም አለ፤ እንዲሁም በግላዊ፤ ወቅታዊ አንድምታ አለው። ስለዚህ በህልሞች ነው። ምናልባት ለራስዎ (ወይም ሌሎች) የተወሰኑ መተግበሪያዎች ላላቸው ቤተ-ክርስቲያን አጠቃላይ ቃል ሊሆን ይችላል።
  13. አንዳንድ ህልሞች ለወደፊቱ ብቻ ሊረዱት የሚችሉት ሊሆኑ ይችላሉ። ከጊዜ በኋላ ይገለጣሉ። ዝርዝር
    ነገሮች በመንገዱ ላይ ትርጉም ይሰጣሉ።
  14. ማስታወሻ ላይ ማጠቃለያውን ይጻፉ፤ ቀኑን ያካትቱ፤ የት እንደነበሩ ያስገቡ፤ ሰዐቱን (ከሕልሙ
    የነቃችሁበትን)፤ ዋና ስሜቶችን፤ እና ሊሆን የሚችለውን ትርጓሜ ይፃፉ።
  15. ለትክክለኛ ትርጓሜ ቁልፉ ጥያቄዎችን፤ መጠየቅ፤ መጠየቅ፤ መጠየቅ ነው።

ሁሉም ሰው-ሁሉም ህብረተሰብ፤ ባህል፤ እምነትና ቀለም ህልም አላሚዎች አሉት፤ ሕልም ትልቅ ስፍራም አለው።
ሕልሞች እግዚአብሔር ከልቡ እና ከአዕምሮ ውስጥ መለኮታዊ አላማን በማነሳሳት በእኛ ታሪክ ውስጥ እዉን ንዲሆን
የሚጠቀምበት መድረክ ነው።
ሕልሞች ቦታ እና ጊዜ የሚገፉበት፤ እግዚአብሔር በውስጣችን ያለዉን ማንነታችንን ከዉስጣዊ ንቃት ጠረፍ ባሻገር
ብሎም በስትጀርባ እንዲያይ የሚፈቅድበት እንዲሁም እድል እና ተስፋ፤ ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው እምነቶቻቸን ሳይቀር ወጥተው የሚታዩበት ስፍራ ነው።

አባት ሆይ፤ ሕልሞችና ትርጉሞቻቸው የአናንተ እንደሆኑ እናውቃለን፤ ክታላቅ ክብር ጋር በተጣመረ ጥልቅ ረሃብ፤ ከአንተ የሚመጡ ሕልሞች፤ ለምታሳየን ነገር ትክክለኛውን ትርጓሜ እና በኢየሱስ ስም ላይ በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ጥበብን እንድትሰጠን እንጠይቃለን፤ አሜን።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox