ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው በሥራ ላይ ከተሰማሩ ከአንድ አመት በኋላ አንድ ቀን ዳኒ ከሚወዳት እጮኛው ከጃኔት ደብዳቤ አገኘ የእኔና የአንተ እጮኛምነት መተሳሰር እዚሁላ መብቃት አለበት የሚለውን ዓረፍተ ነገር እንዳነበበ ዓይኑን ማመን አቅቶት ፈዞ ቀረ ዳኒና ጃኒት ለመጀመርያ ጊዜ የተገናኙት ገና የሁለተኛ አመት ተማሪዎች እያሉ ነበር የተለያ መንፈሳዊ ስብሰባዎችን አብረው ተካፍለዋል መልካም ጊዜዎችንም በመረዳዳት አብረው አሳልፈዋል በትምሕርታቸውም እየተረዳዱ በማጥናት ጥሩ ውጤት ሲያመጡ ቆይተዋል ይህ መቀራረብና መተሳሰብ ጥሩ ጓደኛሞች እንዲሆኑ ከመረዳት አልፎ ለቁም ነገር ለመተሳሰብ ትክክለኛ ወቅትና የእግዚአብሔር ጊዜ ነው በማለት እርስ በእርስ ተጠያይቀው ተስማሙ ቃልም ተግባቡ ከምርቃ በኋላ ጃኒት አስተማሪ ሆና ወደ አንዲት የጠረፍ ከተማ ስትመደብ ዳኒ በአንድ የነዳጅ ማጣርያ ድርጅት ተቀጥሮ ወደ ሌላ ከተማ ሄደ እንደወትሮ መተያየት አብሮ ማሳለፍ እየቀረ ሲሄድ የነበራቸውም የሞቀ ጓደኝነትበመጠኑም እየቀዘቀዘ መጣ በዚህ ወቅት ነበር ጃኒት ለመጋባት የወሰኑትን ውሳኔ ያፈረሰችው ይህ ውሳኔ ዳኒን በጣም ጉዳው በእግዚአብሔርም ላይ በማጉረምረም ጌታ ሆይ ይህ ለምን በኔላይ እንዲደርስ ትፈቅዳለህ ይህ ለምን ማለት ቀጠለ ያወጣውን ገንዘብ ያጠፋውን ጊዜ ሁሉ ወደኋላ እያሰበ በሃሳብ ተመሰጠ ይህ ልክ ቤትን ሠርቶ ሲጨርሱ በእሳት ለኩሶ እንደማቃጠል ነው ኪሳራ አለ ዳኒ ለዓመታት የገነባው ነገር ሲፈርስበት ቀናት ተቆጠሩ ቀስ እያለ ስሜቱ ሲሰክን ዳኒ ብዙ ነገር ማስተዋል ጀመረ፡፡
በዩኒቨርሲቲ ወይም በኮሌጅ የተጀመረ ጥምረት በሙሉ ተሳክቶ ለሦስት ጉልቻ ይበቃል ብሎ መደምድ ከስሕተት ላይ ይጥላል ወጣት ወንዶችና ሴቶች ከተለያየ ቤተሰብና ከተለያየ አስተዳደግና አካባቢ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ በቤተሰብም ሆነ በኅብረተሰቡ ዘንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሚሰጠው ግምት የላቀ ነው ከዚህ የተነሳ ታላላቅ ውሳኔዎች እንደ የወደፊት የኑሮ ጓደኛን የመምረጥን ጉዳይ በዚህ ጊዜ የሚወስኑ አይታጡም ዳኒ በተማረበት ዩኒቨርስቲ የወደፊት የትዳር ጓደኛ አመራረጥ የሚፈጽመው እያንዳዳቸው ከሚማሩበት የትምህርት ዘርፍ (faculty) አንጻር ሲሆን የተለያየም ደረጃ ይመደብላቸዋል በሕክምና ትምሕርት መስክ የሚያጠኑ ወንዶች ሴቶች በሙሉ በእጃቸው እንዳሉ ሲያስቡ በአንጻሩ ደግሞ በዚህ የትምህርት ዘርፍ የሚገኙ ሴቶች ከራሳቸው የትምሕርት ዘርፍ ጓደኛ ካላገኙ በስተቀር በሌላ የትምህርት መስክ ከሚገኙ ወንዶች ጋር ጓደኝነት ለመፍጠር በጣም ይቸገራሉ ምክኒያቱም በሌላ የትምህርት ዘርፍ የሚገኙት ወንዶች የበታችነት በመጠኑም ቢሆን ስለሚሰማቸው ለመጠየቅ አይደፍሩምና ነው የወደፊት የትዳር ጓደኛ መምረጥ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ለማጥናት እንደሚወስድ ኮርስ አይደለም ካልሆነ እተወዋለሁ የሚባል ነገርም አይደለም ስለዚህ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡
አንዳንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ደግሞ በጣም ጥቅም ወዳድ ወደመሆኑ ያዘነብላሉ ያኔ በትምህርት ቤት ምንም ሳይኖራቸው ያለንተ ላንቺ እንዳልተባባሉ በሥራ ዓለም ሲሰማሩ ኑሮ የሞላላቸውን ኪሳቸው ዳጎስ ያለውን መጠጋት ይመርጣሉ ስለዚህ ያ የተገባ ቃል በቀላሉ ይፈርስና አንደኛው ወገን ለጉዳት ይዳረጋል በስፍራ እርቀት የቀድሞ የሞቀ ፍቅር ቀዝቅዞ ወደ ሌላ ለማየት የሚገደዱ ጥቂት አይደሉም ይህንንና ያንን በጥሞና ሲያሰላስል ከርሱ በፊትና ኋላም አብረውት የነበሩትን ጓደኞቹን ሲያስብ ቆየና ዳኒ አንድ ነገር ወደ አይምሮው መጣ ለምን ጊዜ ወስጂ አልጸልይም ብሎ በዚህ ጉዳይ ላይ አዘውትሮ በጌታ ፊት ለመቅረብና እግዚአብሔርን ለወደፊት የትዳር ጓደኛ የምትሆነውን ሰው እንዲሰጠው አጥብቆ መጸለይ ቀጠለ፡፡
‹‹ቤትና ባለጠግነት ካባቶች ዘንድ ይወረሳል አስተዋ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት››
ምሳ 19፡14
ብርሃን መፅሔት
1989 ቁጥር 32
Copyright Hiyawkal © 2024
Leave a Reply