የሚያዳምጠንን ጆሮ የሚያስተውለንንም ልብ እንፈልጋለን

ከወላጆች ከቤተክርስቲያንም :

በየትኛውም ዘመን የወጣቶች ጉዳይ ከቶም ሊዘነጋና ቸል ሊባል የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ማንም ሊስማማበት ያሻል እንደሚታወቀው በዓለማዊውም ሆነ በመንፈሳዊው መስክ የነገው ትውልድ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበትና ስኬታማ እንዲሆን የዛሬዎቹን ወጣቶች ፈር ማስጨበጥ የቤተክርስቲያ ድርሻ በተለይም የዋንኞቹ ሃላፊነት እንደሆነ ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባም መጋቢት 25 ቀን 1991 ዓ.ም ፓስተር ስለሺና ባለቤታቸው ወ/ሮ ዓለምነሽ አሰፋ በናዝሬት ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ለወጣቶች የሚሆን የጋብቻ ትምህርት አቅርበው እነዚህ ከተለየ ሥፍራ የመጡ ወጣቶች ካገኙት ትምህርትና ካላቸው መለስተኛ የሕይወት ገጠመኝ ተነስተው ወላጆችም ሆኑ ቤተክርስቲያን እንዲረዱላቸው እንዲገነዘቡላቸው እንዲሁም ልባቸውን እንዲሰጧቸው የሚፈልጉት አሳብ እንዲህ ጨምቀው አቅርበውታል ሁሉንም ከእነርሱ እንስማው ደግሞም ማላሻችንን እንስጥ የነገውን ትውልድ በአግባቡ ለመገንባት በምክርም ሆነ በተግባር ከጎናቸው እንሰለፍ ጉድለታቸውን እናርም በእግዚአብሔርም ቃል እንመከራቸው፡፡ ውድ ቤተሰቦቻችን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው አንደኛው ፈቃድ እናንተ ወደ ደረሳችሁበት ክርስቲያናዊ ጋብቻ ሊያደርሰን እንደመሆኑም ከእናነተ ከወላጆቻችን እንዲደረግልን የምንሻውን ፍሬ ሃሳብ ስንገልጥላችሁ በታላቅ አክብሮትና በልጅነት ፍቅር ነው፡፡ ያ ስለሆነም እናንተም በበኩላችሁ ያለውን የወላጅነት ግዴታችሁን እንደምትረዱልን በመንፈሳችን እናምናችኋለን፡፡ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ቀጥሎ በሰው ልጆች ውስጥ ያቀድነውና የፈጸምነው ጋብቻን ነው ይህም ፈቃዱ እንዲያው በዘፈቀደ የሚከናወን ሳይሆን እግዚአብሔር ቀድሞበት የሚፈጸም የከበረ ነገር ነው፡፡ጋብቻ በቤተክርስቲያን በሀገር በትውልዶች መካከል ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል በእግዚአብሔር ፍርሃት የተመሠረተ ጋብቻ ሲኖር ብቻ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ቤተክርስቲን እግዚአብሔርን የሚፈሩ የሀገር መሪዎችና ትውልዶች የሚኖሩት፤

1.ስለእኛ ስለልጆቻችሁ ጋብቻ እግዚአብሔር ትክክለኛ ወደ ሆነውና ፍቃዱ ወዳለበት ትዳር እንዲመራን የመጸለይ ሃላፊነት አለባችሁ አብርሃም በዘፍ. 24÷27 እግዚአብሔር መልአኩን በፊትህ ይሰዳል ሲል እግዚአብሔር ይመራሃል ማለቱ ነው፡፡ ሎሌውም በዘፍ 24÷27 እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድም ቤተ መራኝ እንዳለ እናነባለን እግዚአብሔር በመንገድ የሚያስኬድ የማይሳሳት ትክክኛ መሪ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲመራን ደግሞ መጸለይ ያስፈልግሃል ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን በትክክለኛ የእግዚአብሔር ምሪት ውስጥ እንዲሆኑ መጸለይ ያስፈልጋቸዋል ዘፍ.24÷48 በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፡፡

ብርሃን መፅሔት
ቁጥር 39 1992

2. የእግዚአብሔርን ፍቃድ መቀበል መቻል እንዲሁም እግዚአብሔር ለእኛ ለልጃቸው የሰጣትን ወይም የሰጠውን እጮኛ መባረክ እውቀት በውበት በኑሮ ደረጃ ባይመጣን ጋብቻን ጋብቻ የሚያደርገው በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል እንደ እግዚአብሔር ፍቃዱ በመተሳሰብና መቀባበል ላይ የተመሠረተ ፍቅር እን ዲግሪ ጥ ቁመና በባንክ ያለ አካውንት አይደለም የእግዚአብሔርን ፍቃድ በመተሳሰብና መቀበባበል ላይ የተመሠረተ ፍቅር እንጂ ዲግሪ ጥሩ ቁመና በባንክ ያለ አካውንት አይደለም የእግዚአብሔርን ቃል ስንመለከት ዘፍ. 24÷50 ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷል ክፉም መጥፎም ልንመለስ አንችልም ዘፍ፣24÷51 እግዚአብሔር እንደተናገረው ለጌታዬ ሚስት ትሁን የርብቃ ቤተሰቦች ለልጃቸው በመጣው በእግዚአብሔር ፍቃድ ላይ ምንም አልተናገሩም ነገር ግን ለጌታዬ ሚስት ትሁን ብሉ ተስማሙ በመቀጠልም በዘፍ 24÷60 አንቺ እህታችን እልፍ አዕላፍ ሁኚ ዘሮችሽንም የጠላቶችሽን ደጅ ይውረሱ አሉአት የርብቃ ቤተሰቦች እንደተስማሙ ወላጆችሽም እንዲሁ እግዚአብሔር ለልጃችሁና የሰጣትን እጮኛ ወዳችሁና ፈቃዳችሁ የወደፊት ኑሮአቸውን እግዚአብሔር እንዲባርክ ሃላፊነት አለባቸው፡፡

‹‹የተባረከ ትዳር የተባረከን ትውልድ ያፈራል››

3. ስለ ጋብቻ ግልጽ ውይይትና ከልምዳችሁ ማካፈል ዕብ. 13÷4 መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውምንጹህ ይሁን ወላጆች እኛ ልጆቻችሁ ወደፊት ልንመሠርት ያለው ብቻ ክቡር እንደሆነና ልናከብረውም እንደሚገባን የመናገር ሃላፊነት አለባቸው በእኛ በኢትጵያውያን መካከል ስለጋብቻ በልጆች ፊት ማውራት እንደ ነውር ስለሚቆጠር ልጆችም ፈርተው ከወላጆች ስለሚደበቁ በዚህ ጉዳይ ወላጆች ለልጆቻችሁ ወደደፊት ልንመሰርት ያለው ብቻ ክቡር እንደሆነና ልናከብረውም እንደሚገባ የመናገር ሃላፊነት አለባችሁ፡፡ በእኛ በኢትዮጵያውያን መካከል ስለጋብቻ በልጆች ፊት ማውራት እንደ ነውር ስለሚቆጠር ልጆችም ፈርተው ከወላጆች ስለሚደበቁ በዚህ ጉዳይ ወላጆች ለልጆቻችሁ የቅርብ አማካሪ ብትሆኑን መልካም ነው፡፡ መድረሳችንን ማወቅ መቻል እና በምክር መርዳት አለባችሁ፡፡

4. የልጆቻችሁን እጮኛ ለመተዋወቅ ፈቃደኛ መሆን አለባችሁ ከባህል የወረስነው ተጽዕኖ ስላለ በእጮኛሞችና በቤተሰብ መካከል መቀራረብ ግልጽነትና ነፃነት የለም ያ በመሆኑ ክርስቲያን ቤተሰብ በዚህ ረገድ ቀደምት ምሳሌ ሊሆን ይገባል ምክንያቱም ልጃቸው ወደ ፊት ቤተሰብ ስለምትሆን (ስለሚሆን) እንደልጃቸው የማቅረብ እና ቤተሰብነት እንዲሰማው (ስንዲሰማት) ማድረግ መቻል አለባቸው፡፡

5. የባህልና የዘርን ተጽዕኖ ማስወገድ የእግዚአብሔር ቃል በራዕይ 5÷9-10 ታርደሃልና በደምህ ለእግዚአብሔር ከነገድ ከቋንቋ ከወገንም ከህዝብም ሁሉ ሰዎች ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደርግሃቸው እንደሚል፡፡ ኢየሱስ የሞተው በደሙ ሰዎችን ከኃጢአት አንጽቶ ሁሉን ለአንድ መንግሥት አንድ ለማድረግ እንጂ በዘርና በቋንቋ ለመለያየት አይደለም ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ያፈረሰውን የጥል ግድግዳ እኛ አንገንባው ገላ. 3÷28 አይሁድ ወይም የግሪክ ሰው የለም ባርያ ወይም ጨዋ የለም ሁላቸው በክርስቶስ አንድ ናቸውና በእኛ በኢትዮጵያውያን መካከል የተለመደ አንድ ነገር አለ፡፡ ይህም የተጫጩት ቤተሰብ የመጀመሪያ ጥያቄ የማን ዘር ነች? በማለት ወንዱ ወይንም ሴቷ ይጠይቃሉ ክርስቲያን ቤተሰቦች ማስተዋል ያለብን ትልቅ እግዚአብሔር ብቻ ነውው፡ የትልቁ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ /ኗ/ እንጂ የምድር ሰዎች ዝና እና ክብር ከመቃብር ሃውልት ላይ ካለጽሑፍ አያልፍም ነገር ግን ደስ ሊለን የሚገባው በ1ኛ ጴጥ 1÷23 የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው የእግዚአብሔር በህያውና ለዘለዓለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ዳግመኛ መወለዳችን ነው ፡፡

6. በተደጋቢዎእ የኢኮኖሚ እቅድ ውስጥ ጣልቃ አለመግባት ሁለት ተጋቢዎች ወደፊት ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው የራሳቸውን ኑሮ ለመመሥረት በዝግጅት ላይ በመሆናቸው የሚያስፈልጋቸውን የኑሮ ቁሳቁሶች ለመግዛትም ሆነ ወደፊት ሕይወታቸውን ለማቀድ እንደ ኢኮኖሚያቸው ነው መራመድ የሚችሉት ስለዚህ ወደፊት ወላጆቻችን አብራቹን ስለማትኖር ጣልቃ ገብታችሁ መመርያ ለመስጠት ባትሞክሩ፡፡ ዘፍ. 2÷ 24 ስለዚህ ሰው አባትና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናለሁ አንድ ሥጋ የሚሆኑት ሁለቱ ብቻ እንጂ ከወላጆቻችን በዚህ ላይ ትኩረት ቢያደርጉ ተጋቢዎች ወደ ጋብቻ ፈጥነው እንዲደርሱ ቢያበረታቱ እጮኛሞች ከጋብቻ የሚያዘገያቸው ብዙ ጥያቄዎች ወይም ጎዶሎ የሚመስሏቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ ቤት አልሠራሁም ሠርግ ነደገሻ የለም ወዘተ በዚህ ሁሉ ውስጥ ወላጆች ተጠግተው በጸሎት ሊደግፏቸው ወይን ሊያበረታቷቸው ይገባል፡፡

7.ቢቻል በኢኮኖሚ ከሌሎች ጋር ፉክክር ማድረግን መተው በእግዚአብሄር ቤት በኑሮ ደረጃ የማይመጣጠኑ የተለያዩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ስለዚህ ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን እንደ ምሳሌ አድርጎ በመጥቀስ የግድ እንደእነርሱ መደገስ አለበት በማለት የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን ልጆቻችሁን ታስጨንቁን፡፡

ጋብቻ የሚመሠረተው በእግዚአብሔር ፍቃድ እና በድግስ ብዛት አይደለም

ጌታ ይከፍላል እያሉ ተጋቢዎች ለብድር ከመዳረግና ያላቸውን ጥሪት ከመጨረስ መቆጠብ እግዚአብሔር መክበር የሚፈልገው ባለን ነገር እን ተበድረን ባመጣነው እዳአይደለም፡፡ተበድረን እዳ ገብተን ባዘጋጀነው ነገር እግዚአብሔር ከበረ ብንል የኑሮአችን ፍሬ ደግሞ መርገምን ያውጃል ስለዚህ ልጆቻችን ወደ ባን ዕዳ የምትጋብዙ ወላጆች ለልጆቻችሁ ትዳር መፍረስ ምክንያት እንዳትሆኑ መቆጠብ መቻል ጠቃሚ ነውው፡ ወላጆች ባለፋችሁበት ምንገድ የግዴታ ተጋቢ ልጆቻችሁን እንዲያልፉ አትገፋፉን ወላጆች ቤተሰብ ተጽእኖ ውስጥ አልፋችሁ ሊሆን ይችላል የግዴታ ግን እናንተ ባለፋችሁበት ውጣ ውረድ እኛ ልናልፍ አይገባንም ውጣ ውረድ እኛ ልናልፍ አይገባ ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው የሚያልፋችሁበት እኛ እንድናልፍ ተጽዕኖ ማድረግ ለሌላ አደጋ ስለሚያጋልጠን ከወዲሁ ነገሩን ብታጤኑት መልካም ሆኖ ይታያል ፡፡

ለቤተክርስቲያን

ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ጢሞ 3÷1 ልጁን ጢሞቴዎስን ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ በማለት ይመክረዋል እንግዲህ በዚህ መጨረሻ ለተባለው ዘመን እጅግ ለተጠጋን በአሁኑ ዘመን ያለን ወጣቶች የታቀፍንብሽ ከሰንበት ትምህርት አንስቶ እስከ ጋብቻ ትምህርት ድረስ እስካሁን ማስተማርሽ በእግዚአብሔር ዕቅድና ዓላማ እንድንገባ ሁሌም መኮትኮትሽ ያየነውና ያለፍንበት እንዲሁም ገናም የምናድግበት ስሆነ ጌታን ስለ አንቺ እንባርካለን፡፡ ወጣት ምዕመኖችሽ እርስ በርስ በመንፈሳዊ ቋንቋ የምናማርበትን የምንተያይበትንና የምንተዋወቅበትን ፕሮግራሞች ብታዘጋጂልን ወጣት ምዕመኖችሽ በጾታ በመክፈል ነጻ ሆነው አንድንወያይ ከበሰሉ የጋብቻ አማካሪዎችና አስተማሪዎች ጋር ብታገናኚን ወጣት ምዕመኖችሽ ለጋብቻ ደርሰን እጮኛችንን ካስተዋወቅንሽ በኋላ በዐይኘቁራኛ መመልከት ሳይሆን አስፈላጊውን ትምህርትና ጥንቃቄ ብታደርጊልን ምክንያቱም እኛም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ ታጭተናልና በአግባቡ ብትይዥን ወጣት ምዕመኖችሽ ብዙዎቻችንን ብዙ ጠይቀንና የእግዚአብሔርም ፍቃድ ግራ ገብቶን እንደ ኢትዮጵያውያን ልማድ በተለይም ሴት ልጆችሽ ዕድሜያችን በቃ አለቀ ሄደ ከእንግዲህ ማን ያገባናል ብለን አለንና በስፍራሽ ምንገኘውን የምትመለከቺውን ጠጋ ብለሽ ብታነጋግሪንና ችግራችንን ተረድተሸ ብትመክሪን በቤተክርስቲያን ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ማለትም በዘመኑ ወግ በቬሎና ከአቅም በላይ በጆነ ድግስ ለቪድዮ ካሜራ የማይጨነቁ ተጋቢዎችን ለማበረታታት ብትተጊ መልካም ይሆንልናል ውድ ቤተክርስቲያን እኛ የናዝሬት ሙሉ ወንጌል ወጣቶች ብቻችንን ሳንሆን ከሌሎች አብያተክርስያናት ወጣቶች ጋር በመሆን በትምህርትና በውይይት ጨምቀን እነሆ ይህን ቁምነገር አስፍረናልና እንደገና እንድታስቢበት ልብሽንም እንድታሰፊልን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን፡፡

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox