አብሪዎች ስለከፈታችሁት እድል እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ እኔም እስኪ በዚህ አጋጣሚ ትንሽ ልተንፍስ፡፡ ባለቤቴ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በጣም የተሰጡ አገልጋይ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ጥሩ የሆነ የግል ሥራ እንሠራለሁ በኑሮ ምንም ችግር የለብንም ይሁን እንጂ ከባለቤቴ ጊዜ ማጣት የተነሣ ለራሳችንም ሆነ ለልጆችን ምንም ዓይነት ጊዜ የለንም ጥሩ መልስ አይሰጠኝም ለሰው ላማክር ይሆን ብየየ ሳስብ በኋላ የባሱ ችግር ይፈጥራል ብዬ ፈራሁ እስኪ ምናልባት ችግሬን በጽሑፍ ብገልጽላችሁ መፍትሔ አገኝ ይሆናል ብዬ አሰብሁ እንግዲህ ብላችሁም በግሌ እጸልያለሁ አንድ ቀን ጌታ እንደሚመልስልኝም አምናለሁ እጠብቃለሁም፡፡ የእናንተም ምክር እናፍቃለሁ ይህንን የፈረሰውን መሠዊያችንን እናድሰው ልጆቻችንንስ እንዴት በጋራ እንርዳ
በጌታ እህታችሁ ነኝ ከአዲስ አበባ
ውድ እኅታችን የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛልሽ አገልጋይ የሆነው ባለቤትሽ ለአንቺና ለልጆቹ ‹‹በቂ›› ጊዜ መስጠት ባለመቻሉ ችግር ላይ እንደሆንሽ በመግለጽ ምክር እንድንሰጥሽ በመጠየቅሽ መልካም አድርገሻል በመሠረተ አሳብ ደረጃ አንድ ለእግዚአብሔር የተሰጠ አገልጋይ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አገልግሎት የሚያስተምረውን መሠረታዊ ትምህርት ያውቃል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አገልግሎት የሚያስተምረውን መሠረታዊ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ አገልግሎት ከቤተሰብ እንደሚጀምር በግልጽ ያስተምራል ስለዚህ አንድ መንፈሳዊ አገልጋይ ሌሎችን ከማገልገሉ በፊት ቤተሰሰቡን ማገልገልና አገልግሎቱ የራሱ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን በጋራ የሚያገለግሉት አገልግሎት እንዲህ ሆኖ እያለ በዐውዳችን ያለ ብዙ መንፈሳዊ አገልጋይዮች ለቤተሰቦቻቸው /ለትዳር አገልጋዮቻቸው/ለልጆቻቸው/ ተገቢ ጊዜ ባለመስጠት በውጭ አገልግሎት ብዙ ሄደው የቤታቸው ነገር ደግሞ ፈርሶ ይገኛል፡፡ ደብዳቤሽ ውስጥ በቤታችሁ ጥሩ ኅብረት እንዳይኖር ያደረገው የባለቤትሽ ጊዜ ማጣት እንደሆነ ‹‹ከባለቤቴ ጊዜ ማጣት እንደሆነ ‹‹ከባለቤትሽ ጊዜ ማጣት እንደሆነ ‹‹ከባለቤቴ ጊዜ ማጣት የተነሣ . . .›› የሚል አሳብ ጠቅሰሻል ለቤተሰብ ጊዜ ማጣት እርሱ ብቻ ነው ወይ ተጠያቂ? እርሱስ በቤት ሲገኝ አንቺ ትገኛለሽን? ሆን ብሎ ለቤተሰቡ ጊዜ ነላለመስጠት ፈልጎ ነው ወይስ የእርሱና የአንቺ ጊዜ አለመጣጣም? ማለትም ሁለታችሁም በቤት የምትገኙበት ጊዜ ተመሳሳይ አለመሆን ነው ችግሩ? አንችም የምትሰሪው የግል ሥራ በመሆኑና ዘመኑ ደግሞ ብዙ ውድድር ያለበት በመሆኑ ምን ያህል ለባልሽ ተገቢውን ጊዜ እንደምትሰጪ አላውቅም አብዛኛውን ጊዜ የግል ሥራን በአሳብ ወደ ቤት ይዞ መምጣት ይታያል በአካል ከቤተሰብ ጋር መሆን ቢቻልም አእምሮ ግን ሥራ ቦታ ሊሆን ይችላል ስለዚህ አንቺም ስለ ራስሽ ማሰብ ጠቃሚ ነው፡፡ ለልባችሁ መራራቅ እንደ አንድ መንሥኤ ያስቀመጥሽው አንድ ላይ አለመጸለያችሁና አለመመገባችሁ ነው ብዙ ጊዜ አብረን አንመገብም ከዚህ የተነሣ ይመስለኛል ልባችን ተራርቆዋል በንግግር አንግባባም ላናግረው ስሞክር ጥሩ መልስ አይሰጠኝም በእርግጥ አንድ ላይ መጸለይና መመገብ ለባልና ሚስት ግኑኝነት አስፈላጊ ነገሮች ናቸውው፡ ልብ ለልብ ለመያያዝ ያግዛሉ፡፡ አብራችሁ ባትመገቡም ቁርስ ምሳና ራት ቤት ነው የሚባለው አብራችሁ ባትጸልዩም ቢያንስ ጠዋትና ማታ ቤት ውስጥ ይጸለያልን? እነዚህን ነገሮች ማወቅ የችግሩን ጥልቀት ለመረዳት ያግዛል ለልብ መራራቅ ምክንያት የሚሆነው ነገሮች እነዚህ ብቻ ላይሆኑ ይችላሉ በተለይ ‹‹ በንግግር አንግባባም የሚለው አሳብ ሁለታችሁንም የየራሳችሁ ድርሻ እንዳላችሁ ያሳያል ስለዚህ በንግግር እንዳትግባቡና ስታናግሪው እንዲዘጋሽ ያደረጉ ነገሮች ምን ይሆኑ? በእርሱ በኩል ያለውን ነገር ትተሽ በአንቺ በኩል በአንቺ በኩል የሚስተካከል ነገር ካለ ያን ማስተካከል ለመፍትሔው ይረዳል በመሠረቱ ሰውን ስናናግር ጥሩ መልስ እንዳይሰጥ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል የእኛ ጥሩ ያልሆነ አቀራረብ ወይም የሰውዬው ጥሩ ስሜት ውስጥ አለመሆን ነው፡፡ አቀራረባችንና አድማጫችን ያለበት የፍልቀ ስሜት ዓውድ ሁኔታ ምላሹን ይወስናሉ፡፡
‹‹ለሰው ላማክር ብዬ ሳስብ በኋላ የባሰ ችግር ይፈጠራል ብዬ ፈራሁ›› ብለሻል በእርግጥ የራስን ችግር በግል ጥረት ለመፍታት መሞከር የሚደግፍ ቢሆንም ብቃት ያላቸውን ሰዎች በተለይ መንፈሳዊ ሰዎችን ማማከር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ከችግር ጋር ተቃቅፎ ከመኖር ይልቅ ክርስቲያን አማካሪዎች በማማከር ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ ገንቢ መፍትሔ ማግኘት ይቻላል ምሥጢርን ሊጠብቁና ለመረዳት ደግሞ ብቃት ላላቸው ሰዎች ችግርን መንገር አያስፈራም በአካባቢሽ ያሉትን መንፈሳዊ አገልጋዮች ማመን ካልቻልሽ ሌሎችን አማካሪዎች በመፈለግ ማማከር አሁንም ጥቅም እንዳለው አሳስብሻለሁ በዚህ ጽሑፍ የተሰጠውም ምላሽ ቢሆን ለግንዛቤ ያህል አቅጣጫ የሚሰጥሽ እንጂ ለችግርሽ ሙሉ መልስ ይሆናል ብዬ አላስብም አንዱ ምክንያት የመልሱ አጭርነትና ጥልቅ በመሆናች ነው፡፡ ስለዚህ በስፋትና በጥልቀት ተወያይቶ መልስ ለማግኘት አሁንም የማማከር አገልግሎት ማግኘት ይረዳል ይህ ችግር የተነሣበትን ጊዜ ተረጂ ባለቤትሽ ለአንቺ እንዲሁም ለልጆቹ ጊዜ መስጠቱን የተወው ከመቼ ጀምሮ ነበር? ችግሩ የተጀመረው ከተጋባችሁ በኋላ ተከታይነት ባለው ሁኔታ ከሆነ ባለቤትሽ አንድ የተቀበለው የተሳሳተ አስተሳሰብ መኖሩን ያመለክታል ካደገበት ቤተሰብ ወይም ማኅበረሰብ ለቤተሰብ ትኩረት መስጠት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆነ ተምሯል እንዲሁም /ወይም ከእርሱ ጋር አብረው ከሚያገለግሉት የአገልግሎት ባልደረቦቹ ‹‹ከቤተሰብ ይልቅ ለእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ቅድሚያ መስጠት አለበት›› የሚል መርሕ ተምሮ ተግባራዊ እያደረገ ይሆናል እንዲህ ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው ነገር ግን ‹‹እጅግ መንፈሳዊ›› የሚመስል የተሳሳተ ግንዛቤ ካለው የአንቺና የልጆቹን ‹‹እባክህ ጊዜ ስጠን›› ጥያቄን እንደ ጠላት ውጊያ በማሰብ አጥብቆ ይቃወማል ‹‹ሰይጣን በቤተሰቦቼ በኩል እየተፈታተነኝ ነው›› በማለት ይህን አሳብ የሚያሸንፍበትን መንገዶች ይፈልጋል በእርግጥ የባለቤትሽ ለቤተሰቡ ተገቢውን ትኩረትና ጊዜ አለመስጠት መንሥኤው የአስተሳሰብ ለውጥ ማየት አትችይም የአስተሳሰብ ለውጥ ሂደት በመሆኑ ቀስ በቀስ እየተለወጠ ይሄዳል በዚህ በአንድ ጊዜ ሁሉም ነገር ባይስተካከልም በዕየለቱ ለውጦች እንዲመጡ ጥሬ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ የየዕለቱ ለውጦች አንድ ላይ እየተረማመዱ በሂደት የሚፈልገው የለውጥ ውጤት ይገኛል ባለቤትሽ ከቤተሰብ ይልቅ ለአገልግሎት ቅድሚያ የሚሰጥበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለመረዳት ጥረት አድርጊ እርሱን ሳትኮንኚ ይህን የሚያደርግበትን መሰረታዊ መንስኤዎች ን ተረጂ ቤተሰቡን ችላ ብሎ ከቤተሰቡ ውጪ ለሆነ አገልግሎት መስጠቱ አንቺን እና ልጆቹን ለመጉዳት ሆነ ተብሎ ታቅዶ የተደረገ ላይሆን ይችላል በእርሱ ግንዛቤ እርሱ ለእግዚአብሔር የሚገባውን መሥዋዕት እያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ የእርሱን ግንዛቤ ለመረዳት መሞከር አሳፈላጊ ነው፡፡
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ የቤተሰብ ሕይወትና አገልግሎት እንዴት አድርጎ በሚዛን መጠበቅ እንደሚችል ስልቶችን የሚያስጨብጡትን መጽሐፍቶችን ማንበብ እንዲችል እንዲህ ዓይነት መጽሐፍቶችን ገዝተሸ መስጠትም ይረዳል አንቺ ደግሞ ይህን ለማድረግ የገንዘብ አቅም እንዳለሽ ደግሞ ይህን ለማድረግ የገንዘብ አቅም እንዳለሽ ማሰብ ይቻላል ምክንያቱም የግል ሥራ እንደምትሠሪና የኑሮ ችግር እንደሌለብሽ ገልጸሻል በአገልግሎትና በሕይወት እንዲሁም በቤሰብ መካከል ‹‹ሚዛን ለመጠበቅ የሚረዳው አንዱ ሚዛን የጠበቀ ሕይወትናአገልግሎት›› የሚል መጽሐፍ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ እርሱም አንቺም ብታነቢ ያግዛችኋል በሁኔታዎች ግፊት የተጀመረ በትዳር ሕይወታችሁ አብራችሁ ስትኖሩ ባለቤትሽ ለአንቺ እንዲሁም ለልጆቹ ትኩረት ሲሰጥ ኖሮ ነገር ግን በሆነ ወቅት ለቤተሰቡ የሚሰጠውን ጊዜ በመተው ለአገልግሎት ከፍተኛ ትኩረት መሰጠት ጀምሮ ይሆናል በሁኔታዎች ተጽእኖ ድሮ የሌለውን ባሕሪ እያሳደገ መጣ ማለት ነው፡፡ የችግሩ አፈጣጠር እንዲህ ዓይነት መልክ ያለው ሲሆን መንሥኤው መሠረታዊ የአስተሳሰብ መዛባት ሳይሆን በጊዜ ውስጥ የጠፈጠሩ ሁኔታዎች ይሆናሉ እነዚህ ሁኔታዎች ውስጣዊ ቤተሰባዊ ወይም ከቤተሰብ ውጭ የሆኑ ግቶች ና ስበቶች ሊሆኑ ይችላሉ ለቤተሰቡ ትኩረት ላለመስጠት የሚያቀርበው ምክንያት የአገልግሎት ብዛት ሲሆን እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ይሆናሉ፡፡
1) ውስጣዊ መንስኤ፡- የሚባለው እርሱ ለግል ሕይወቱ ደስታና እርካታ ምንጭ ማንነቱን በአገልግሎቱ ለመግለጽ ካለው ጽኑ ፍላጎት የተነሣ የሚጠበቅበትን ወይም ከሚጠበቀው በላይ በማገልገል ፍሬያማ በመሆን ‹‹ምርጥ›› አገልጋይ እንደሆነ ለሌሎች ለማስመስከር የሚያደርገው ጥረት ነው አገልግሎቱን እንደ ማንነቱ መግለጫ ለመጠቀም ያለው ፍላጎት በአገልግሎት እንዲወጠር አድርጎት ይሆናል እንደ ባል ወይም እንደ አባት ያለው ማንነት ዋጋ ያለው እንደሆነ በማይታሰብበት ዓውድ በእንዲህ ዓይነት ፍላጎት መነዳት ያጋጥማል ‹‹ጥሩ አገልጋይ ነው›› መባል ‹‹ጥሩ ባልነው›› ወይም ‹‹ጥሩ አባት ነው›› ከማለት የበለጠ ስፍራን የሚሰጥ ስም እንደሆነ ይታሰባል፡፡
2) ቤተሰባዊ መንሥኤ፡- ባለቤትሽ ለቤተሰብ ትኩረት እንዳያደርግ የሚያደርገው ሌላው ምክንያት የቤተሰብ ዓውድ ምቹ አለመሆን ነው ባልሽ ቤት ውስጥ የሚያጋጥሙ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች ከሆኑ ቤት ውስጥ ጊዜ ለማሳለፍ አይጋብዘውም በተለይ አንቺ በማወቅ ወይም ባለማወቅ እርሱ ከቤት እንዲርቅ ልታደርጊ ትችያለሽ ወደ ውጭ የሚገፉ ተገቢ ያልሆኑ ባሕሪያቶች ናቸአው እንዲህ ሲሆን ባልሽ አገልግሎት ከቤቱ ጭቅጭቅ የማምለጫ መንገድ አድርጎ ይጠቀምበታል ‹‹ለምን ቆየህ?›› የሚሉ ጥያቄዎች ሲነሱ ‹‹አገልግሎት በዝቶ ነው›› በማለት ሲመልስ አንቺ ብዙ መናገር አትችይም ምክንያቱም ‹‹አገልግሎቱን ቀንሰህ ከእኛ ጋር ጊዜ መውሰድ አለብህ›› ማለት መንፈሳዊ አለመሆንሽን እንደሚያሳይ ስለሚታሰብ ዝምታን ትመርጫለሽ ይህ ዝምታ ደግሞ ውስጥ ለውስጥ ወደ ቁጣ ይመራሽና ግንኙነታችሁ የባሰ እየጎዳ ይሄዳል፡፡
3) ከቤት ውጪ የሆኑ መንስኤዎች፡- ባለቤትሽ ከቤተሰቡ ይልቅ ወደ ውጭ እንዲያተኩር የሚያደርጉ ውጫዊ ስበቶች ሊኖሩ ይችላሉ ከቤትውስጥ ያላገኘውን ነገር ከውጪ የሚሰጡት ወይም ያላገኘውን ነገር ከውጭ የሚሰጡት ወይም እንደሚሰጡት ተስፋ የገቡ ሁኔታዎች ሲኖሩ ቤተሰብን ችላ ብሎ መናገር ግምታዊ ሰለሚሆን ለጊዜው መተው የሚሻል ቢሆንም ከሚያገለግላቸው ሰዎች ከጓደኞቹ እንዲሁም ከመዝናኛ ሁኔታዎች ጋር የተገናኙ ሊሆኑ ይችላል እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱት አሳቦች ለአጠቃላይ ግብዛቤ ከረዱሽ ከዚህ በታች የቀረቡትን ምክሮች ደግሞ ተግባራዊ በማድረግ ባለቤትሽ ለቤተሰቡ ትኩረት የመስጠት እርምጃዎች እንዲወስድ ያግዛሉ፡፡ በአእምሮ ግጭት የሚፈጠር ጥያቄን መጠየቅ ለእግዚአብሔር የተሰጠ አገልጋይ ለቤተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አይገባውምን? እንዲህ ዓይነት ጥያቄ በአሳቡ ውስጥ ሁለት የሚጋጩ ነገሮች እንዲፈጠሩ በማድረግ የራሱን ድርጊት ከአሳቡ አንጻር በማየት መፍትሔ እስኪሰጥ ድረስ ዕረፍት የሚነሣው ይሆናል ከዚህ ላይ ግን በጥያቄው ይዘት ላይ ብቻም ሳይሆን ጥያቄው ይዘት ላይ ብቻም ሳይሆን ጥያቄውን በምታቀርቢበት ሁኔታ ላይ ጥበበኛ መሆን ይገባሻል በጥበብ ያልቀረበ አሳብ ራሱን እንዲፈትሽ ሳይሆን ራሱን እንዲከላከል የሚያደርግ ሊሆን ይችላል፡፡
4) በጉዳዩላይ አገልግት እንዲሰጥ መጋበዝ፡- ‹‹አገልጋይና ቤተሰብ›› በሚል ርዕስ ላይ በቤተሰብ በሰፈር ኅብረት በአጠቃላይ አምል ወይም በሌሎች መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ላይ ምእመናንን እንዲያስተምር ሁኔታዎችን ማመቻቸት ጠቃሚ ነው፡፡ እንዲህ ማድረግ ትምህርቱን ለማስተማር ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲመረምር እንዲሁም ሌሎች መጽሐፍቶችን እንዲያነብ እድል ይሰጡታል በተጨማሪም ትምሕርቱን ሲያስተምር ሌሎች መጽሐፍቶችን እንዲያነብ እድል ይሰጡታል በተጨማሪም ትምህርቱን ሲያስተምር ሌሎች በሚጠይቁት ጥያቄዎችና በሚያደርጉት ውይቶች አዲስ ግንዛቤ ወደ ማግኘት ይመጣል ያስተማረውን ትክክኛ ትምህርት ደግሞ በሕይወቱ ለመኖር ይገደዳል በአብዛኛው ሰዎች እውነት ነው ብለው በአደባባይ ያስተማሩትን ነገር በኑሮአቸው ለመግለጽ ጥረት ያሰርጋሉ በተለይ ከእሴት ጋር የተገናኙትን ነገሮች እንደተናገሩት በማድረግ የሚመራቸው መስጠት ከፍተኛ ነው፡፡
5) ከእርሱ ጋር አገልግሎት መውጣት፡- እርሱ ጊዜ አልሰጥሽም ካለሽ አንቺ ጊዜ ስጭው ለግልሥራሽ እንዲሁም ለልጆችሽ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ከእርሱ ጋር ለተወሰነ ጊዜ አብረሽው ሁኚ አብረሽ ስትሆኚ የእርሱ አገልግሎት ምን እንዲመስል የሆነ ምሥል ታገኛለሽ እነማንም የት ቦታ በምን ጊዜ እንዴት እንደሚያገለግል ግንዛቤ በማግኘት እርሱን ለመረዳት ወይም መለወጥ ያለብሽን ነገር ለመለወጥ ትችያለሽ ሁለታችሁ እንደባልና ሚስት የሚያውቁ እርሱ የሚያገለግላቸው አማኞች እንደ ጥንድ ለማወቅ እድል ያገኛሉ ይህ ደግሞ ሰዎች ስለ ቤተሰቡ እንዲጠይቁ እድል ይሰጣል ከእርሱ ጋር ጊዜ ካሳለፍሽ አንቺም እርሱ የተወሰነ ጊዜ ካሳለፍሽ አንቺም እርሱ የተወሰነ ጊዜ አንቺ ጋር እንዲያሳልፍ መጠየቅ ትችያለሽ ‹‹እኔ የአንተን ሥራ አከብራለሁ አንተም እንዲሁ አድርግ ማለትሽ ነው
6) ለእርሱ ያለሽን መልካም እይታ መግለጽ፡- በትዳር ሕይወት ዘመናችሁ ከእርሱ ጋር ያሳለፍሽውን መልካም ጊዜ በመጥቀስ በዚያን ወቅት ስለ እርሱ ይሰማሽ የነበረውን ስሜት ንገሪው ይህ እርስ ይሰማሽ የነበረውን ስሜት ንገሪው ከዚያም አሁን ያለውን ነገር ራሱ እንዲጠይቅ ተይው አስተዋይ ልቦና ካለው አንቺ ለእርሱ ያለሽን መልካም ነገር ላለማጣት በምትፈልጊው ሁኔታ ውስጥ ይገባል፡፡
7) የራስሽን ፕሮግራሞች ለእርሱ ማሳወቅ፡- የራስሽ የዕለት ወይም ሳምንታዊ ዕቅዶችና የጊዜ ሰሌዳሽ ለእርሱ በማሳየት አስተያየት እንዲሰጥበት መጠየቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ አንቺ ለእርሱ ግልጽ መሆንሽን ሕይወትሽን ከእርሱ ጋር በመመካከር ለመምራት ማሰብሽን ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ ያቅድሽውን ጊዜ እንዲያውቅ ያግዛል በተዘዋዋሪ መንገድ ደግሞ ‹‹እኔ ከአንተ ጋር ፕሮግራም እንዳወጣሁ ሁሉ አንተም ከእኔ ጋር በመመካከር የአገልግትን ፕሮግራምህን ማውጣት ጠቃሚ ነው፡፡›› የሚል መልእክት ማስተላለፍ ይሆናል መልእክቱን በግልጽ መረዳት ካልቻለ የሳምንት ፕሮግራሙን እንዲያሳይሽ መጠየቅ ትችያለሽ ይህን በመልካም አቀራረብ ማድረግ ውጤቱን ይወስናል ‹‹የአገልግሎትህን ፕሮግራም ባውቅ እኮ በደንብ እጸልያለሁ . . .›› ብትይው አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ልጆችንም በፕሮግራም አወጣጥ ማሳተፍ ጠቃሚ ይሆናል
ለጋራ ፍላጎት እርካታ ትኩረት ማድረግ፡- ከውጭ የሚያገኘውን ደስታና እርካታ ከቤት ውስጥ እንዲያገኝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አስፈላጊ ነው፡፡ ሰው ሕይወትን የሚያስደስት ነገር ባለበት ስፍራ መሆን ይፈልጋል ቤት ያለው ነገርመቼም አገልግቴን ጨርሼ ቤት በደረስሁ የሚያስብለው እንዲሆን ማድረግ ለአንቺእና ለልጆቹ ትኩረት እንዲሰጥ የማድረግ ኃይል አለው፡፡ ለአንቺ ወይም ለልጆች ብሎ ሳይሆን ራሱም እርካታውን ለማግኘት ስለሚያጓጓው ከቤተሰብ ጋር ጊዜን ለማሳለፍ ያቅዳል እንዲህ ሚስቱ በመሆንሽና ከእርሱ ጋር አብረሽ የቆየሽ በመሆኑ (በእርግጥ የትዳር ዘመናችሁ በደብዳቤሽ ላይ ባይገለጽም ልጆች ስላሉአችሁ አብራችሁ የተወሰኑ ዓመታት እንደቆያችሁ ማሰብ ይቻላል) እርሱ የሚፈልጋቸውን ነገሮች በቤት ውስጥ እንዲገኙ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ቁሳቁሳዊ ነገሮች ላይሆኑ ይችላሉ እርሱን ወደ ቤቱ ለመሳብ ኃይል የሚኖራቸው የሕይወት ደስታና እርካታ ሊሰጡ የሚችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ጥሩ የልጆች እናት ታታሪ ሠራተኛ የቤት አስታዳዳሪና የጸሎት ሰው መሆን ጥሩ ነገሮች ናቸው፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሚስትና ጓደኛ መሆን ቅርበት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ በደብዳቤሽ እንደገለጽሽው ‹‹በግሌ ብዙ እጸልያለሁ አንድ ቀን ጌታ እንደሚመልስልኝም አምናሁ እጠብቃለሁም ››የሚለው ሀሳብ ጥሩ መደምደሚያ ይሆናል ችግር ሲያጋጥም ጠገቢ መፍትሔ ለማግኘት የሚረዳው አንድ ትልቅ ነገር ‹‹ይህ ችግር የሚፈታ አይመስለኝም›› ብሎ ተስፋ አለመቁረጥ ነው በእግዚአብሔር መታመን ሲኖር በግል ስለ ጉዳዩ መጸለይ በቀጣይነት መሠራት የሚገባውን ሥራ በመሥራት መፍትሔውን ለማምጣት ያግዛል እግዚአብሔርን በመታመን የሚጠብቅ ሰው አያፍርም ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ‹‹ስትጸልይ ምን ብለሽ ነው የምትጸልይው?››እግዚአብሔር ሆይ ይህን ሰው ለውጠው ነው ወይስ እግዚአብሔር ሆይ ለዚህ አገልጋይህ የምመች ረዳት እንድሆን ጸጋህን አብዛልኝ ብለሽ ነው? እኔ ሁለቱም አስፈላጊ እንደሆኑ አስባለሁ በተለይ ከራስ ጀምሮ ለሌላውም መጸለይ በግኑኝነት ውስጥ ያለውን ተግባር ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
አብሪ ቁጥር 4
2000 ዓ.ም
Copyright Hiyawkal © 2024
Leave a Reply