እግዚአብሔር ስለምን በቅዱስ መንፈሱ ሊያጠምቃችሁ ይፈልጋል?

ቻሪቲ ካያምቤ :

ኢየሱስ ከሞተ፣ ከተቀበረ፣ ከሞትም ከተነሳ በኋላ ለደቀመዛሙርቱ የመጨረሻ ትእዛዛትን ሰጥቶ ነበር።ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት የነገራቸው ነገር አብ ቃል የገባውን እንዲጠባበቁ ነበር። አንድ ሰው ከመሄዱ በፊት የሚናገረው ነገር በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። የኢየሱስ የመጨረሻ ንግግሩ “በመንፈስ ቅዱስ ከመጠመቃችሁ በፊት ወዴትም እንዳትሄዱ” የሚል ነበር።

ለምንድን ነው እነደዚያ እንዲሆን ያስፈለገው? ይህ ልምምድ የእርሱ ምስክሮች ለመሆን የሚያሰፈልጋቸውን ሃይል እንደሚሰጣቸው ጨምሮ ነግሮአቸዋል። “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ሃይልን ትቀበላላችሁ፥በኢየሩሳሌም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”(ሃዋ 1 ፥8)

ምን?

ሃይል በጣም ጥሩ ነገር ነው፤ ግን ለምን ሃይል አስፈለገ? ምስክሮች ለመሆን። ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች ምስክርነትን በአንደበት የሚደረግ ነገር እንደሆነ ያስባሉ፤ ብዙዎች ግን ምስክርነትን የሚያያይዙት ከማየት ጋር ነው።የቅሉ ትርጉም እንደዛ ነው፥ በግላችን እናያለን እንታዘባለንም። የአይን ምስክር ነገሩን የሚነግረን ጉዳዩን በቀጥታ ባየበት ሁኔታ ነው። በፍርድ ቤት ምስክር እንድንሆን ከተጠራን ወንጀሉ ወይም አደጋው ሲፈጸም በይናችን አይትን ነበር ማለት ነው። ውይም ደግሞ ዘጋቢው “ታሪክ ሲሰራ መስክሩ” ካለን በዓይናችን ፊት አስገራሚ እና የማይታመን ነገር ተከስቶአል ማለት ነው። ምስክር ለመሆን ያየን እና የታዘብን መሆን አለብን።

ማን?

ማንን ነው እምናየው ማንንስ ነው እምንመለከተው? ኢየሱስን። ጥሩ ወደ ሰማይ እየሄደ ከሆነ እንዴት አድርገን ነው እሱን ማየት የምንችለው? እዚህ ጋር ነው የመንፈስ ቅዱስ ሃይል የሚመጣው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እየሱስን እንድንመለከት የማይታየዉንም እናይ ዘንድ ያስችለናል።(እብ 12፥2። 2ቆሮ 4 ፥ 18) የመንፈስ ቅዱስን ሃይል የምንቀበለው የኢየሱስ ምስክሮች እንድንሆን ነው። የተቀባነው እሱን እንድናይ እንድንመለከተዉም ነው። ኢየሱስ የእርሱን ሕይወት የሚመሰክርለት ይፈልጋል ፤ አሁን እየኖረ ያለውን ሕይወት።

በመጀመሪያ ኤደን ገነት መንግስተ ሰማያትን በምድር ላይ ትገልጥ ነበር። ሃጢያት፣ በሽታ እና ሞት አልነበረም። ሰይጣንም ስልጣን አልነበረውም (እኛ እስከምንሰጠው ድረስ)። ከእግዚአብሔርም ጋር ፍጹም የሆን ሕብረት ነበር። ወደፊት ሄደን የራዕይን መጽሃፍ ብናይ ሰማያዊ ቤታችንም እንደዚሁ እንደሆነ ይነግረናል። በዚያ እምባ የለም፣ ህመም የለም። (ራዕይ 21፥4)።

ሰማይን ለመለማመድ እስክንሞት መጠበቅ አይገባንም። ኢየሱስም እንደዛ ነው ያለው! ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ እንዲጽልዩ ነበር ያዘዛቸው ፤ “መንግስትህ ትምጣ ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” (ማቴ 6 ፥ 10)።

መቼ?

ሃዋርያት 1 ፥ 8 መቼ ነው የኢየሱስ ምስክሮች እና ተመልካቾች ትሆናላችሁ ያለን? ኢየሱስ ሰው ሆኖ በምድር ላይ የተመላለሰው ለ 33 አመት ነው። ኢየሱስን በስጋ በተገለጠበት ሁኔታ እንድናየው ከሆነ ያሰፈለገን ያ መሆን የነበረበት ከ 2000 አመት በፊት ነበር።

ኢየሱስ ግን ምስክሮቼ ትሆናላችሁ ነው ያለው፤ ይህ ደግሞ ቃል የገባልንን እና ለምስክርነት የሚያስፈልገንን የመንፈስ ቅዱስ ሃይል ወደ ፊት የሚመጣ እንደሆነ ያሳያል፤ ወደ ፊት ማለት ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ እና ካረገ በኋላ ማለት ነው። ኢየሱስ ያን ጊዜ በእስራኤል ያደረገውን ድንቅ እና ተአምራት መመስከር እና ማየት ሳይሆን ከዛ በኋላ እስከ አሁንም ድረስ እያደረገ ያለውን መመስከር እና ማየት ነው።

የት?

ኢየሱስ በምድር ላይ በስጋ ተገልጦ በነበረበት ጊዜ አጋልግሎቱ በጥቂት ቦታ የተወሰነ ነበር። አገልግሎቱ በ እየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣ እና በሰማርያ እንጅ ከዛ ውጭ ያለውን ስፊውን አለም ያጠቃለለ አልነበረም። በእርግጥ ኢየሱስ ከተውልድ ስፍራው ከ 200 ማይል በላይ ርቀን አልተጓዛም ነበር።

ሃዋርያት 1፥ 8 ግን በአለም ዙሪያ እስከ ምድር ዳርቻ ሁሉ የእርሱ ምስክር ስለመሆን ይናገራል። ይህም የእርሱ ምስክሮች የምንሆነው እና እርሱንም የምንመለከተው ወደ ፊት እንደሆነ ያረጋግጥልናል፤ ምክንያቱም እርሱ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እስከ አለም ዳርቻ አልተጓዘምና።

ኢየሱስ እንዴት እርሱን ማዬት እና መመልከት የእርሱም ምስክሮች እንደምንሆን እያስረዳን ነው። ምክኛቱም አሁን እርሱ በሁሉም ቦታ አለና ስራውንም ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከ ምስራቅ እስከ ምእራብ እየሰራ ይገኛልና። እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ።

ለምን?

ምክንያቱም ጥሪው አሁንም አልተቀየረም፤ ኢየሱስ አሁንም እንደ ጥንቱ “ተከተሉኝ” ነው የሚለው።

ይህ ደረቅ ሃይማኖት፤ የአስተምህሮ እና የስነ መለኮት ከምርም አይደለም። ሕብረት ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው ይህን ነው፤ የተፈጠርነውም ለዚህ ነው። እኛ ራሳችን ነን የህግ እና ትዕዛዝ ሳጥን ሰርትን በዛ ውስጥ ካልኖርን የምንለው።

ህጻን አባቱን ወይም ደግሞ የሚበልጠውን ወንድሙን እየመሰለ እንደሚያድግ፤ እኛም ሰማያዊውን አባታችንን እናያለን እንመስለዋለም። እኛ ታላቅ ወንድማችንን ኢየሱስን እናያለን የእርሱንም ምሳሌ እንከተለለን። የኛ እምነት ለህጻናት ቀላል መሆን አለበት፤ በእውነትም ደግሞ እንዴት ቀላል እንደሆነ አሁን ገብቶናል። ከኢየሱስ ጋር ጊዜ እናሳልፋለን መሪያችን እርሱ ወደሚሄድብት እንከተለዋለን።

ንዴት?

ምስክር መሆን ማለት ተመልካች መሆን ማለት ነው፤ ምስክር መሆን የምንችልበትን ህይል የሚሞላን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ትምቀት ነው። አሁን ኢየሱስን እንድናይ፣ እንድንመለከት፣ የእርሱም ምስክሮች እንድንሆን።

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መንፈሳዊውን አለም እንድናይ፣ የኢየሱስን ስራ እንድንመለከት ምሳሌዉንም እንድንከተል የልቦናችንን አይኖች ይከፍታል። የጊዜው የኢየሱስ ምስክሮች እንድንሆን ከእሱም ጋር አብረን እንድንሰራ የሚቀባን መንፈስ ቅዱስ ነው። ስራችሁ፣ አገልግሎታችሁ፣ ጨዋታችሁም ከእርሱ ጋር ይሁን። ሕይወታችሁም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሁን።

ሳናይ እና ሳንሰማ እንዴት ሕብረት ማድረግ እንችላልን? የእግዚአብሔር የልብ አሳብ ጥልቅ የሆነ ሕብረት ውስጥ ከእርሱ ጋር እንሆን ዘንድ ነው። የህ ነው ታልቁ ግብዣ።

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox