ኢየሱስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርትን ከእርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደ ምትባል ሥፍራ ወሰዳቸው። እነርሱም እየሱስ በታቦር ተራራ በተለወጠ ግዜ አብረዉት የነበሩት ናቸው። ኢየሱስ በብርታት ከእርሱ ጋር በፀሎት እንዲቆሙ የፈቀደው ሦስቱ፤ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ነበሩ። እነርሱም ከኢየሱስ ጋር ቅርበት ነበራቸው። በልጆች ጫወታ ሲስቅ ሰምተውታል እንዲሁም በአልዓዛር መቃብር ስፍራ አምርሮ ሲያለቅስ አይተውትም ነበር።
መልካም ሥራን ብቻ ከሚያደርገው ሰው ጋር ተዓምራትን አድርገዋል። እነሱም አስተማሪያችን፣ ጓደኛችን እና የእግዚአብሔርን ልጅ ብለው ነበር የሚጠሩት። ያለ ምንም ጥርጥር፤ እርሱ ማን እንደነበረ ያውቁ ነበር። ነገር ግን በዚህች ምሽት፣ በገትሰመኔ፣ ኢየሱስ ሲፀልይ፡ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ተኝተው ነበር። ኢየሱስ ደም ሲያልበው፣ ታላቁ ትራምቭሬት ያንኮራፋ ጀመር።
ኢየሱስ በጥልቅ ሲያለቅስ፣ እርሱ ያመናቸው ሦስቱ ጓደኞቹ ግን አሸልቧቸዋል። ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ጭካኔ በተሞላበት የሞት ፍርድ እንደሚሞት ያውቁ ነበር። ነገር ግን እነርሱ አሁንም ያንቀላፉ ነበር። ርህሩህ ልባቸው የት ገባ? ታማኝ ጓደኞች ወይንም በሩቁ የሚተዋወቁ ሰዎች ነበሩ?
ሦስት ጊዜ ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ቢመጣ፣ ሦስቱንም ጊዜ ተኝተው አገኛቸው። ኢየሱስ በሥቃይ ለወደፊት ግቡ ሲታገል፣ እነርሱ ግን ዓይናቸው ላይ የተርከፈከፈውን አሸዋ እንኳ ሊያራግፉ ተስኗቸው ነበር። ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንዲኖሩ ኢየሱስ በጭካኔ መገደል ነበረበት። ሆኖም ለኢየሱስ የእንቅልፍ ጊዜአቸውን እንኳ አሳልፈው ሊሰጡት አዳገታቸዉ። ምን ዓይነት ጓደኝነት ነው?
የጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ግድ የለሽ ድርጊቶች በጣም እንበሳጨናለን፣ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ስሜን ሲጣራ፣ ምን ያህል ጊዜ ነዉ በስንፍና ጠባይ ስመላለስ የተገኘሁት?
“ኬሮል … ከእኔ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ትችያለሽ?”
መጸለይ የነበረባቸው ጸሎቶች እያሉ ቴሌቪዥን ላይ እጣዳለው።
“ኬሮል … ላንቺ ያለኝን፣ ቃሌን ልታነቢ ትችያለሽ?”
መወደድ የሚገባቸው ሰዎች እያሉ ልቦለድ አነባለው።
“ኬሮል … እኔን ታመልኪኛለሽ?”
ባህሌና ልማዴ ሲቀጭጭ እኔ ግን አንኮራፋው።
ልክ አዳኙ፣ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስን እንደፈለገው፣ አዳኛችን እናንተን ይፈልጋል። የኔ አዳኝ ይፈልገኛል። እርሱ የጸሎት ኃይል በአደራ ሰጥቶናል። እርሱ ታላቁን ተልዕኮ በአደራ ሰጥቶናል። ወንጌልን በአደራ ሰጥቶናል።
በዚህ የአትክልት ቦታ፣ ኢየሱስ እንዲህ በማለት ጸልዮ ነበር፣ “አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን።”
ህይወታችሁ ሊጎሳቆል ባለበት ጊዜ ጸሎትን ለመፀለይ ሞክረዋል? ሰቆቃ በተሞላበት ሁኔታ ላይ ይህንን ጸሎት ጸልየው ያዉቃሉ? “ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤”።
በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ከተከሰቱት ክስተቶች፣ ቢያንስ ፣ ሌሎች ሲተኙ መፀለይ እንዳለብን እና ከሁሉም ይልቅ የአባታችንን ፈቃድ መሻት እንዳለብን እንማራለን።
በመጨረሻ ኢየሱስ ሦስቱን ከእንቅልፋቸው ሲያነሳቸው፣ በዚያ በጨረቃ ብርሃን ዉስጥ በምዕራባዊው ደብረ ዘይት በኩል ወታደሮችና ፈሪሳውያን በይሁዳ ተመርተው ሲምጡ ተመለከቱ። እነርሱም እየሱስን ይዘው ከሄዱ ባኋላ ጴጥሮስ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተጠልሎ ቆይቶ ነበር። በዚያም ስፍራ ጴጥሮስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ካደው።
ጴጥሮስ ከመተኛት ይልቅ ፀልዮ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስን ይኮደው ይሆን ብዬ አስቤ ነበር። በህይወቴ ከማንቀላፋት ይልቅ መጸለይ ብችል ኖሮ ሕይወቴ ምን ያህል የተለየ ይሆን ነበር? ብዬ አስባለሁ። ይህንኑ ደግሜ አስባለሁ።
Copyright Hiyawkal © 2024
Leave a Reply