አስተምህሮተ እግዚአብሔርና ሥነ-ሰው ከቅደሳት መጻሕፍት አንጻር

ብርሃን መፅሔት 1989 ቁጥር 29 :

1.የእግዚአብሔር ሕልውና(መኖር)

በመጽሐፍ ቅዱስ ገና የመጀመሪያው ምዕራፍ የመጀመሪያው ቁጥር ላይ የምናነበው ‹‹በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ›› የሚለውን ነው ከዚህ ቁጥር እንደምንረዳው ሰማይና ምድር ከፈጠራቸው በፊት እግዚአብሔር መኖሩን ነው ከዚህም የተነሳ ሁሉም ነገር አንድም ሳይቀር ከእነርሱ ሕልውና የመነጨ እንጂ በራሱ ሕላዊነት ያገኘ ነገር እንደሌለ እንረዳለን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በጊዜው ለነበሩት ሰዎች የተጻፈው እግዚአብሔርን ያምኑ ዘንድ ሳይሆን እግዚ አብሔርን ስላመኑ ነበር አምኖ በጠማማው መልኩ ለመቅረብና ለማምለክ ከመኖር አልፎ የእግዚአብሔርን ሕልውና ጨርሶ መካድ የዚያን ዘመን ትውልድ ባሕርይ አልነበረም ይህ አለ ብልን የምንለው እግዚአብሔር ያልነበረበት ጊዜ አልነበረም ወደፊትም የማይኖርበትም ጊዜ አይኖርም ለእንዲህ አይነቱ እግዚአብሔር መኖር አጽናፈ ዓለሙ ምስክር ነው ‹‹ሰማይት የእግዚአብሔር ክብር ይናገራሉ የሰማይም ጠፈር የእጁን ስራ ያወራል ››መዝ.(19፡1) ስለ እግዚአብሔር ሕልውና ስናወራ በራሱ ሕልውና የሆነ እንደሆነ የሆነው እንደሆነ መዘንጋት የለብንም እንዲህም ዓይነት ሕልውና ያለው በመሆኑ ፍጥረት ሁሉ የእርሱ ተደጋፊ ነው እርሱ ሕያው ብቻ ሳይሆን ለአጽናፈ ዓለሙ ሁለተናዊ ሕይወት ምጭ እና መሠረት ነው እግዚአብሔር በማንኛውም አይነት መልኩና መንገድ ቢገለጥ ለዚያ ለተገለጠበት ነገር ጥገኛ ተደጋፊ አይሆንም አይደለምም እግዚአብሔር ለሰው ሁለተኛ የሚያስፈልገው ረቂቅ ግዙፍ ነገር ሁሉ ሰጪ እንጂ ለሕልውናው ከሰው ወይም ከሌሎች ፍጥረቴ ድጋፍ ጠያቂ አይደለም እርሱ ግን ድጋፍ ሰጪና ፍጥረትን አጽኚ ነው ‹‹እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው›› አይደክምም አይታክትም ማስተዋሉም አይመረመርም (ኢሳ40፡28) እርሱ ሰጪሲሆን ፍጥረት ሁሉ (ሰውንም ጨምሮ) ተቀባይ ነው

2. የእግዚአብሔር ባሕይ

እግዚአብሄር በባሕርይው ህጸጽ የሌለበት ንጹሕ መንፈስነው ገና ከመጀመሪያው የፍጥረት ባለቤትነቱን ሲረጋግት ከጨለማ ብርሃን የሚወጣወ መንፈስ ሆኖ ነው ‹‹ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበር….. እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ ብርሃንም ሆነ››(ዘፍጥ 1፡2-3) ይህን አይነቱንየእግዚአብሔር የባሕሪ መገለጥ ጌታኢየሱስ ክርስቶስ የአምልኮ ማረፊያ ማን መሆን እንዳለበት ለሳምራዊቷ ሴት ሲናገር እንዲህ ብሏል‹‹እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል›› (ዮሐ.4፡24) በዕብራውያን 12፡9ላይ ደግሞ የመንፈስ አባት ይለዋል እንዲህ ማለት ግን እግዚአብሔርና መንፈሳዊያን ፍጥረቱ አንድ ናቸው ማለት አይደለም እግዚአብሔር መንፈስ ነው ማለታችን በግማሹ መንፈስ ሆኖ በግማሹ ደግሞ የሰው አይነት አካል ያለውነው ማለትም አይደለም እግዚአብሔር በቅርጽና በክፍል ሳይመዳደብ ያለቁሳዊ ሕልውና የሚገኝ መንፈስ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ሰውኛ (anthropomorphic) በሆነ መልኩ የሚገልጣቸው ማለትም እግዚአብሔርን እንደ ባለዓይን ባለጆሮ ባለእግርና እጅ አድርጎ የሚገልጠው ለሰው ልጆች ባሕርይውንና አድራጎቱን ተመልካችነቱንና ሰሚነቱን ለማስተማር እጂ በውኑ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ዓይነት ገላ ኖሮት አይደለም በእንዲህ ዓይነት መልኩ ስለ እግዚአብሔር ባይገለጽ ኖሮ ስለእግዚአብሔር ጨርሶውኑ ምንም መናገር አይቻልም ነበር እግዚአብሔር መንፈስ ሆኖ ያለ ቁሳዊ አካል መኖሩ በማንነቱ ላይ ያለውን ብቃት አይቀንስም፡፡ እግዚአብሔር የማይመረመርና የማይወሰን መንፈስ ነው ስንል ይህግንዛቤ ከእኛ የእውቀትና የልምምድ አድማስ ፈጽሞውኑ የራቀ መሆኑን መዘንጋት የለብንም እኛ በግዜና በቦታው በእውቀትና በኃይል የተወሰንንና ገደብ ያለብን ነን እግዚአብሔር በመሰረቱ የማይወሰን ነው ከጌዜ አንጻር ሲታይ ዘላለማዊ ከቦታ አንጻር ሲታይ በሥፍራዎች ሁሉ የሚገኝ በእውቀትም ቢሆን እርሱ ብቻ ሁሉን አዋቂ በኃይሉ ችሎት ደግሞ ብቻውን ሁሉን ቻይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ውሱን አለመሆን ደግሞ በፈጠረው አጽናፍ ዓለም ላይ (over the universtranascendent) ሆኖ መገኘቱን ያስገነዝባል ይህም ደግሞ ከፍጥረቱ ሁሉ ተለያይቶ በራሱ ሕልውና ያለ መንፈስ መሆኑን ያሳያል እርሱ እና ተፈጥሮ ብላን በምንጠራው ነገር ተዘግቶ ያለአምላክ ሳይሆን አንድም ሳይቀር በፍጥረታት ሁሉ ላይ ከፍብሎ የሰለጠነ ነው‹‹አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም››በአጽናፍ ዓለም የሚፈልገው እያንዳንዱ ታሪክ እግዚአብሔር በዕቅዱ ያዘጋጀው ነው ነገር ግን የዚያኑ ያህል በጣምራ አብሮ ሊጤን የመገባው እግዚአብሔር ምጥቁና ከፍጥረታት የራቀ ብቻ ሳይሆን በምጥቀቱ ያለው ማንነት ሳይጎድልና ሳያንስ በቅርብ በፍጥረቱ የሕልውና ሥርዓት ውስጥ ጣልቃ እየገባ ነፍስ ያላቸውንና ግዑዛን የእጆቹን ሥራ መቆጣጠሩም ማጽናቱም ነው ስለዚህ ምጥቀቱና ቅርበቱ በእኩል ካልታዩ በቀር ትክክለኛውን የእግዚአብሔር ግንዛቤ ማግኘት አይቻልም(ኢሳ.57፡15)

3.የእግዚአብሔር ጠባይ

የእግዚአብሔር ጠባይ ስንል በግብር/በተግባር የተገለጠው ግብረገባዊ ማንነቱን ማለታችን ነው ይህም አካላዊነቱን የሚያረጋግጥልን ነው በራሱ ሕሊና ያለውና በራሱ የሚወሰን ግብረገባዊ ህላዌ ያለውመሆኑን አብረን እናስባለን የእግዚአብሔር ጠባይ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ከመግባቱ አኳያ ሲታይ ደግሞ ፍጹምና ሙሉ በሆነ መልኩ የተገለጠው ክርስቶስ መገለጥ በኩል መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሔር ከፍተኛውን የህሊና አቅም የያዘ እርሱ ብቻ በመሆኑ ለሰው ልጆች ምክኒያታዊነት (rationality) ሁሉ ምንጭ ያው እርሱ ብቻ ነው እንደ አካለዊ አምላክነቱ እራሱን በመግለጡም አኳያ ሆነ ከሰው ልጆች ጋር ደረገው ግንኙነት በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ተጠቅሷል እንግዲህ ከሰው ልጆች የኑሮ ሁኔታ አንጻር የሚገለጠው እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ባሕርይ እርሱ ለሰው ልጆች እራሱን የገለጠበት የማንነቱ ማስረጃ ነው በመከራ ጊዜ ርኅራኄ ለበደለኛነት ጸጋ ለንሥሐ ይቅርታመስጠቱን ለፈለጉት ሁሉ የመገለጡን ጠባይ ያስረዳል እግዚአብሔር በሁሉም ዓይነት ጠባዩ እራሱን ለሰው ልጆች እንደአስፈላጊነቱ ይገለጣል ይህ ሲሆን አንደኛው ጠባዩ ከሌላኛው ጠባዩ ሳይበላልጥ ነው ከእያንዳንዱ ጠባዩ ጋር በቀዳማይነት ሊጠቀስ የሚገባው ልዩ ጠባዩ ግን ቅድስናው ነው ከዚህም የተነሳ ፍቅሩን ስናስብ ቅዱስ ፍቅሩን ፍትሑን ስናስብ ቅዱስ ፍትህ ርኅራኄውን ስናስብ ቅዱስ ርኅራኄ በማለት የዚሕ አካላዊ አምላክም ጠባይ እንረዳለን እንገልጻለንም የእግዚአብሔር ጠባይ ዝርዝር ከመግለጫችን አስቀድሞ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር የእግዚአብሔር ጠባይ በሁለት ሊከፈል መቻሉን ነው ይህም የሚወረስ ጠባይና የማይወረስ ጠባይ ነው እነዚህ ሁለት የጠባይ ክፍሎች እግዚአብሔር ከእኛ በምን ይለያል የሚሉትን ሁለት ዓይነተኛ ጥያቄዎች የሚመልሱ ናቸው እነዚህን ሁለት ጥቄዎች በሚገባ መመለስ እግዚአብሔርን ያለማወቅ ምክኒያት ከሚሆን ትልቅ ስህተት ይጠብቀናል እርግጥነው የእግዚአብሔር የማይወረስ ጠባይ (incomunicableattributes) ከሚወረስ ጠባዩ (comunicableattributes) ለይቶ ለማቅረብ በምናደርገው ሙከራ ውስጥ የማይወረስ መስሎ የማይታየው የሚወረስ በተቃራኒው ደግሞ የሚወረስ መስሎ የሚታየው የማይወረስ መስሎ የሚታይበት አጋጣሚ ብዙ እንደሆነ እንገነዘባለን ይህ ሊሆን የቻለበት ምክኒያት የሚወረሰውም ሆነ የማይወረሰው ጠባይ መቶ በመቶ የሚወረስ ወይም የማይወረስ ባለመሆኑ ነው ይህንን በዚህ የጥናት ሂደት ውስጥ ተብራርቶ እናገኘዋለን፡፡

3.1 የማይወረሱ የእግዚአብሔር ጠባያት

ሀ. ነፃነው (በራሱ ሕልውነው)

እግዚአብሔር ነፃነው ስንል ለምንም ነገር መቸውንም ቢሆን ጥገኛ አለመሆኑን መግለፃችን ነው ለእርሱ ሕልውና እኛም ሆንን ሌሎች ፍጥረታት አናስፈልገውም ሆኖም ግን እኛም ሆንን ሌላ ፍጥረታት እግዚአብሔርን ልናከብረውና ደስ ልናሰኘው እንችላለን ይህ ጠባዩ የፍጹምነቱ ምልክት ነው የሕልውናው መሠረት ያረፈው በሌላ አካል ላይ ሳይሆን በራሱ ነው ለእርሱ የሕልወናውመሠረት ያረፈው በሌላ አካል ላይ ሳይሆን በራሱ ነው፡፡ ለእርሱ መኖር ሌላ ሰበብ አይፈልግም ለሌሎች መኖር ግን እርሱ ሰበብ ነው (uncaused cause) በምግባሩ በሕጉና በሥራው ሁሉ ነፃ ነው በራሱ ለራሱ የበቃ ሐዋርያው ጳውሎስ ለአቴናውያን ፍልሱፋን ይህንኑ ነው የነገራቸው‹‹ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሰራው መቅደስ አይኖርም እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስ ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም (የሐዋ 17፡24-25)እንግዲህ በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ከህግ በላይ ያለና ሕግን የሚሠራ የሕግ ጌታ እግዚአብሔር ለሰው ሕግን ይሰራል እንጂ በሕግ አይገዛም እርሱ በሉዓላዊነቱ መንቀሳቀሻና የመኖርያ ሕግ ያወጣል ለእርሱ ግን ሕጉ ራሱ ነው ‹‹ከሰማይ በታች ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው ታድያ እንድመልስለት ለእኔ ያበደረ ማነው››(ኢዮ. 41፡11 አዲሱ ትርጉም) አንዳነድ ሰዎች እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረበትን ዓላማ ሲናገሩ እግዚአብሔር ብቸኝነት ስላጠቃው ከሰዎች ጋር ሕብረት ለማድረግ ል ፈጠራቸው ይላሉ ይህ እውነት ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር የፍጥረቱ ጥገኝ የሆነ የሕልውናው ሙሉነት በሌሎች የሚወሰን ሊሆን ነው ሆኖም ግን በሦስትነትና በአንድነት ሕልውናው የተረጋገጠ እግዚአብሔር ብቻ የመሆን ችግር ያለበት አይደለም፡፡

ለ. የማይለወጥ ነው

እግዚአብሔር የማይለወጥ ነው ስንል በማንነቱ በፍጹምነቱ በዓላማውና በሚገባው ተስፋ የማይለወጥ ነው ማለታችን ነው ሆኖም ግን እግዚአብሔር ለተለየ ሁኔታዎች የተለያ ድርጊትና የስሜት ምላሾች ያደርጋል፡፡

ቅዱሳን መጻሕፍት ስለዚህ ምንይላሉ

በመዝሙር(102) ላይ ሁለት ነገሮች በተቃርኖ ሲነበቡ እንመለከታለን በአንድ በኩል እጅግ ጽኑ መስለው የሚታዩት ሰማይና ምድር በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር፡፡ መዝሙረኛው እንዲህ ይላል አቤቱ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማያት የእጅህ ሥራ ናቸው እነርሱ ይጠፋሉ አንተ ግን ትኖራለህ ሁላቸው እንደልብስ ያረጃሉ እንደ መጎናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ ይለውጡማል አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዓመታቶችህ ከቶ አያልቁም መዝ(102፤25-27) ይህን ብሎይ ኪዳን ለያሕዌሕ የተሰጠው የአይለወጤነት ባሕርይ ባዲስ ኪዳን ደግሞ በቀጥታ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቶት እንመለከታለን (ዕብ 11፡ 12)እንዲሁም ዕብ 13፡ 8 ይመለከቷል ስለዚህ እግዚአብሔር ወልድ የአለመለወጥ መለኮታዊ ባሕርይውን ሙሉበሙሉ እንደሚካፈል ማስተዋል እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ከሰማይ ከምድር በፊት ሕልው ነው ሰማይና ምድርም ከጠፉ በኋላ ሕላዌው ይቀጥላል እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን ለውጥ ይዳርገዋል እርሱ ግን ለምንም ለውጥ አያደርግም፡፡ስለነጻነቱ ስለምሕረትና ትዕግስቱም ራሱ እግዚአብሔር በቃሉ ሲናገር እንዲህ አለ ‹‹እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም እናንተ የያቆብ ልጆች ስለዚህ የጠፋችሁ እንዳይደላችሁ (ሚል 3፡6)ደግሞም በአዲስ ኪዳን ያዕቆብ የመልካም ስጦታ ሁሉ ምንጭ እራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ሲናገር በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ(ያዕ 1፡17) ይላል የማይለወጥ የሰማይ አምላክ የማይለወጥ የበጎ ስጦታ ምንጭ ነው፡፡

እስካሁን በተሰጠው የእግዚአብሔር አለመለወጥ የትርጉም ማብራሪያ እኛ ይለወጣል ወይም አይለወጥም ብለን ባሰብንበት የትርጉም አቅጣጫ ሳይሆን ቅዱሳት መጻህፍት በገለጹት መሰረት እግዚአብሔር አይለወጥም ስንል ጠባዩና ሕልውናው ከፍጹምነቱ አንጻር ሲታይ አይለወጥም ማለታችን ነው ይህንን እውነታ ጠንቅቆ መረዳት ደግሞ በፈጣሪና በተፈጣሪ መካከል ያለውን መሰረታዊ ልዩነት አውቆ እራስን ለአምልኮ እግዚአብሔር ለማዘጋጀት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡የእግዚአብሔር አለመለጥ ከፍፁምቱ አንጻር ሊሰተዋል ይገባል የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው(መዝ 33፡1) ይህ ስለ እግዚአብሔር ጠቅለል ያለ ዓረፍተ ነገር ሲሆን እግዚአብሔር በዘላለም ውስጥ ስላሰባቸው ዕቅዳችና ስለዓላማው የሚያብራሩ የሚያብራሩ በርካታ ጥቅሶች አሉ(ማቴ 13፡35 25፡34 ኤፌ 1፡4፡11 3፡9፡11 2ኛ ጢሞ.2 ፡10 1ጴጥ 1፡20 ረእ 13፡15) እግዚአብሔር አንዴ አንድን ነገር ለመፈጸም ከወሰነ ዓላማው ሳይለወጥ ግቡን ይመለከታል በእርግጥ በዚህ ዓይነት ባሕሪው እርሱ ይመለታል በእርግጥ በዚህ ዓይነት ባሕሪው እርሱን የሚመስል ማንም እንደሌለ በነብዩ ኢሳያስ በኩል እንዲህ ብሎ ተናግሮአል ‹‹ እኔ አምላክ ነኝና ሌላ የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም እንደሌለው ያለ ማንም የለም በመጀመርያ መጨረሻውን ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ ምክሬ ትፀናለች ፍቀዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን ከሩቅም አገርም ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጣራለሁ ተናግሬያለሁ እፈጽማለሁ አስቤዋለሁ አደርግማለሁ (ኢሳ 46፡9-11) ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሔር በተስፋውም የማይለወጥ ነው እግዚአብሔር አንዴ ለአንድ ነገር ተስፋ ከገባ ለዚያ ተስፋ በፍጹም ታማኝ ነው፡፡ ‹‹ሐሰትን ይናገረ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም››ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም እርሱ ያለውን አያደርገውም የተናገረውንስ አይፈጽመውም (ዘኃል 23፡19) ‹‹የእስራኤል ኃይል እንደሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትም አለው›› (1ኛ ሳሙ 15፡29)

ብርሃን መፅሔት
1989 ቁጥር 29

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox