አለማችሁን እስከዘለቄታው የሚቀይሩ አምስት የትንሳኤ ቱርፋቶች

ዶክተር ኤዲ ሂያት :

በካናዳ አገር በሚገኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ውስጥ በመነቃቃት ዙሪያ አንድ ሳምንት የሚፈጅ ትምህርት በማስተምርበት ወቅት አንድ ቀን ከ ለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ራሴን ነቅቼ አገኘሁት። በአእምሮዬ በክርስቶስ ትንሳኤ ሰይጣን ላይ የድረሰበትን ፍጹም የሆነ ሽንፈት እያሰላሰልኩ ነበር፤ ይህንንም እውነት የዛኑ ቀን ጠዋት ክፍል ውስጥ ማካፈል እንዳለብኝ ተሰማኝ።

ብዙዎች ሰይጣንን አጉልቶ በሚያሳይ እና የእግዚአብሔርን ልጆች ለፍርሃት በሚሰጥ የመንፈሳዊ ውጊያ ስልት እና አስተምህሮ የተያዙ መሆናቸውን ስለማውቅ፤ ይህንን ማድረጉ ተገቢ ነበር። ይህ አይነቱ አቀራረብ በብሉይ ኪዳን ላይ የሚያተኩር እና የክርስቶስ ትንሳኤ በሰማይ እና በምድር ለውጥ የማምጣቱን እውነታ ወደ ጎን የሚያደርግ ነው።ከዚህ ቀጥሎ ከሕይወታችን የሰይጣንን ፍርሃት የሚያስወግዱ እና የምንኖርበንትን አለም የሚያናውጡ አምስት የትንሳኤ እውነታዎች ቀርበዋል፥

የመጀመሪያ የትንሳኤ እውነታ

ኢየሱስ የሰይጣንን እራስ ቀጥቅጦ የ ዘፍጥረት 3፥15 ቱን ትንቢት ፈጽሟል።

ዘፍጥረት 3፥15 እንዲህ ይላል “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”

እነዚህ ቃላት እግዚአብሔር ከመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ውድቀት በኋላ ለእባብ የተናገራቸው ናቸው። በዚህ ክፍል “የሴቲቱ ዘር” የተባለው ወደፊት ከሔዋን ዘር ስለሚመጣው እና እባቡን ድል በመንሳት በተንኮሉ ያመጣውን እርግማን ሊቅለብስ ስላላው ስለእርሱ የተነገረ ነው።

በዚህ ትንቢት መሰረት “የሴቲቱ ዘር” ከሰይጣን ጊዜአዊ ቁስልን እንደሚቀበል “አንተም ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ” በማለት ይናገራል፤ ነገር ግን “የሴቲቱ ዘር” ሰይጣንን በማይድን ቁስል እንደሚመታው “እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል” በማለት ይናገራል።

“የሴቲቱ ዘር” የሚለው ይህ የመሲሁ ተስፋ የመጀመሪያ ክፍል ኢየሱስ ያለወንድ ከድንግል ማርያም ሲወልድ ተፈጽሟል፤ ሁለተኛው ትስፋ ድግሞ በትንሳኤ ጊዜ “የሴቲቱ ዘር” የሰይጣንን ራስ ቀጥቅጦ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ድል ሲያድርገው ያኔ ፍጻሜን አግኝቷል።

የሰይጣንን ሽንፈት ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።”(ማቴዎስ 28፥18) ብሎ ሲያውጅ በግልጽ ይናገራል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት በነበርኩበት ጊዜ አንድ ተጋባዥ አስተማሪ ይህንን ክፍል ካነበበ ብኋላ የጠየቀውን ጥያቄ አልረሳውም “ስልጣን ሁሉ የኢየሱስ ከሆነ፣ የሰይጣን ስልጣን ምን ያህል ነው?”

ከሞት የተነሳው ጌታ ስልጣን ታላቅነት ለዮሃንስ በፍጥሞ ደሴት በግልጽ ታይቶት ነበር።ዮሃንስ በገናናው ሃይሉ እና ክብሩ ባየው ጊዜ እንዲህ ነበር ያለው “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ።”(ራዕይ 1፥17) ከዚያም ኢየሱስ ዮሃንስን በእጆቹ ዳስሶ እንዲህ አለው “አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።” (ራዕይ 1፥17-18)

ሁለተኛው የትንሳኤ እውነታ፥

አማኝ አሁን ከክርቶስ ጋር ከ ከአለቆች እና ሃይላት በላይ ተቀምጧል።

ለጳውሎስ የክርስቶስ መስቀል የእግዚአብሔር የመጨረሻ ታላቅ ፍቅሩ የተገለጠበት ከሆነ፤ የክርስቶስ ትንሳኤ ደግሞ የእግዚአብሔር የመጨረሻ ታላቅ ሃይሉ ያተገለጠበት ነው። የክርስቶስ ትንሳኤ ፍጥረታት ሲፈጠሩ ከተገለጠው በላይ ዓለም ያየው የመጨራሻ ታላቅ ሃይል የታየበት ነው፤ ትንሳኤ፥ ሕይወትን ከሞት አምጥቷልና በትንሳኤ እንደ ሰይጣን እና ሃጢያት ያሉ መንፈሳዊ የእግዚአብሔር ጥላቶች ድል ተነስተዋልና።

ክርስቶስ በሰይጣን ላይ የተቀዳጀውን ታላቅ ድል ጳውሎስ በኤፌሶን 1፡15-23 እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው “. . . . ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። . . . .”

“ቀኝ” በመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣንን እና ሃይልን የሚወክል ነው። ለምሳሌ በመዝሙር 98 ፥ 1 ላይ ስለ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ብሎ ይናገራል “ቀኙ የተቀደሰም ክንዱ ለእርሱ ማዳን አደረገ።” ጳውሎስም ኢየሱስ አሁን በእግዚአብሔር “ቀኝ” ተቀምጧል ሲል እጅግ ከፍ ካለው እና በመጨረሻው የስልጣን እና የሃይል ቦታ ተቀምጧል እያለ ነው። 

ጳውሎስ ሲናገር አሁን ክርቶስ የተቀመጠበት ቦታ “ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ”(ኤፌሶን 1 ፥ 21) ነው፤ የተኛውም ስልጣን እና ሃይል ቢሆን፣ ሰይጣንም እንኳን እራሱ ቢሆን ክርስቶስ አሁን የተቀመጠበት ስፍራ ከእነርሱ ሁሉ በላይ ነው።ደስ ያሚለው ነገር ደግሞ ይህ ነው! በኤፌሶን 2፥5 – 6 ጳውሎስ እምነታቸውን በክርስቶስ ያደረጉ ከእርሱ ጋር በዚያ በከፍታ ስፍራ አብረው እንደተቀመጡ ይናገራል። ሰይጣን በክርስቶስ ያለበትን ቦታ እና የተሰጠውን ስልጣን የሚያውቅን አማኝን ቢፈራ አያስደንቅም።

ሶስተኛው የትንሳኤ እውነታ፥

የክርስቶስ የትንሳኤ ሃይል አሁን በእናንተ እየሰራ ነው።

ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ በሚናገርበት ኤፌሶን 1፥19 ላይ እንዲህ ይላል ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው ያ መንፈስ “ለምናምን” እዚህ ጋር በግሪኩ “ኢስ” የሚል ቃል ጥቅም ላይ ውሏል ትርጉሙ “ለምናምን ለእኛ” ወይም “በምናምን በእኛ ውስጥ” የሚል ትርጉም ይኖረዋል። 

ስለዚህ እኛ የክርስቶስ የትንሳኤ ሃይል ለእኛ ተስጥቶናል በእኛ ውስጥም ይኖራል ማለት እንችላለን። ይህንንም ጳውሎስ በሁለተኛ ቆሮንቶስ 4፥11 ላይ እንዲህ ይጠቅሳል “የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።” በሌላ አገላለጽ ምንም እንኳን መንግስተሰማያት ባንሆን እዚሁ ሞት በሚሰለንበት በወደቀ አለምም ሆነን የትንሳኤው ሕይወት በእኛ ውስጥ ይሰራል ማለት ነው።

በጋብቻችን የመጀመሪያ ቀናት ባለበቤቴ ሱ እና እኔ ሕይወታችንን እና አገልግሎታችንን የሚፈትን ውጊያ አጋጥሞን ነበር። ተሸነፍን ራዕያችንም ሞተ ባልንበት ጊዜ ጌታ እግዚአብሔር በቀጥታ እንዲህ ነበር የተናገረኝ “ሞትን አትፍራ እኔ ትንሳኤ ነኝና።”

እኛም እምነታችንን ከቀድሞው በበለጠ በጌታ ላይ አኖርን እርሱም ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው፣ እና ባላቀድነው ሁኔታ ራዕያችንን ወደ ሕይወት ሲያመጣ አይተናል፤ የትንሳኤው ሕይወት በሞት መካከል እንኳን ሲሰራ ተመልክተናል።

ከዚያ ቀን ጀምሮ ኢየሱስን የማውቀው ቁስላችንን እንደሚፈውስ ብቻ አይደለም ንገር ግን የሞተን ህልም፣ ራዕይ፣ እና ተስፋ ወደ ሕይወት ማምጣት እንደሚችልም ነው። አሁን ትንሳኤ ያለፈ ጊዜ ክስተት እንዳልሆነም ተረድቻለሁ፤ ትንሳኤ ማለት በመንፈሱ በእኔ የሚኖረው ክርስቶስ ማለት እንደሆነ ተረድቻለሁ። 

ትንሳኤ እና ሕይወት የሆነው እርሱ በእኛ ውስጥ ይኖራልና የትኛውንም አይነት ሞት ልንፈራ አይገባም። ዮሃንስ ይህ ስለተገለጠለት ነበር እንዲህ ያወጀው ፥ “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።” (1 ዮሃንስ 4፥4)

አራተኛው የትንሳኤ እውነታ፥

ሰይጣን ውሸቱ ብቻ የሚሰራ የተሸነፈ ጠላት ነው። 

ሁሉም ስልጣን ተወስዶበታልና ሰይጣን አሁን በምድር ላይ የሚሰራው በመዋሸት እና በማታለል ነው።እሱ አሁን በከህደት ትከሶ ፍርዱን እየተጠባበቀ እንዳለ በከንቱ እንደሚጮህ የጦር አዛዥ ነው፤ ስልጣኑ ተሰስዶበታል፣ ተዋርዷል፣ ከአገልግሎትም ተባሯል።

አሁን ይህ የጦር አዛዥ ከስልጣን መባረሩን የማያውቁ ወታደሮችን ካገኘ በእነርሱ ላይ ይሰለጥናል፤ እውነቱ ሲገለጥ ግን ተራ ወታደር እንኳን በትዕዛዝ ሊያባርረው ይችላል። የሰይጣን እና የአጋነንቶቹ እውነታ ይህ ነው።

ለዚሀ ነው ራእይ 12፥9 ላይ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ “ ተብሎ የተጠራው። ኢየሱስ ስለ እሱ እንዲህ ነበር ያለው “ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” (ዮሃንስ 8፥44) ሰይጣን የአሁኑን አለም የተቆጣጠረው በውሸት እና በማታለል ነው። 

ለዚህ ነው ኢየሱስ በዮሃንስ 8፥32 ላይ ይህን ያለው “እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።” የኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል እውነት እና በሞቱና በትንሳኤው የሰራው ስራ የሰይጣንን ውሸት ያባርራል፤ ብራሃን ጨለማን እንደሚያባርር። ውሸቱ ከተጋለጠ ሰይጣን መስራት አይችልም፤ ስለዚህ ይህንን ውሸትን የሚያጋልጠውን የእግዚአብሔር ቃል እውነት በቤተክርስቲያንም ሆነ በግል ሕይወታችን የሚተካ ነገር ሊኖር አይችልም።

አምስተኛው የትንሳኤ እውነታ፥

የትንሳኤውን እውነት ስናውቅ ለፍርሃት ቦታ አይኖረንም።

አሁን በሕይወት የሌለው ዶክተር ቲ ኤል ኦስቦርን በአንድ ወቅት በአፍሪካ ክሩሴድ ላይ ያገለግል ነበር፤ በዚያ አገልግሎት ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጠንቋዮችን ጨምሮ በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታድመው ነበር።

ወደ መድረኩ ከመሄዱ በፊት ይረዱት የነበሩት አገልጋዮት ከሰይጣን እንዲጠበቅ እጃቸውን ጭነው ሊጽልዩለት ፈልገው ነበር፤ ኦስቦርን ግን አይሆንም በሚል ተቃወመ እንዲህ ሲል “በዚህ የጌታዪን ክብር አላዋርድም”። ያን ቀን የኦስቦርን ስብከት ያተኮረው የክርስቶስ ትንሳኤ መልካም ማወጅ ላይ ነበር፤ ብዙዎች ወደ ክርስቶስ መጡ፣ ብዙዎች ከልዩ ልዩ አይነት ህመም እና እስራት ነጻ ወጡ። እነዚያ ክርቲያን መጋቢዎችም ሰይጣንን መፍራት እንደሌለባቸው ተረዱ።

ስሚዝ ዊግልስዎርዝ በውድቅት ለሊት ከቤቱ ስር የጩህት ድምጽ ይሰማል ምን እንደሆነ ለማየትም ወደ ስፍራው ሻማ እያበራ ይሄዳል በቤቱም ጥግ ሰይጣን ተገልጦ አየው፤ እስሚዝም “ውይ አንተ ነህ እንዴ” ብሎት ነበር ወደ መኝታ ክፍሉ የተመለሰው። 

አንድ ወቅት ዘመድ ለመጠየቅ በሄድንበት ቤት ህጻን ልጃቸው በጸና ታሞ ነበር። እኛም ጸለይን ሆኖም ምንም የሚለወጥ ነገር አልነበረም። በኋላ ላይ ደረጃ በመውረድ ላይ ሳለሁ ህመሙ የመናፍስት ውጊያ እንደሆነ ተረዳሁ ምንም ነገር ሳናደርግ ህመሙ በዛን ጊዜ ሄዶ ነበር። ብርሃን ጨለማዉን አባረረው።

በእውነት እና በንቃት ልንዋጋው እንጅ ሰይጣንን ፈጽሞ ልንፈራው አይገባም።

ማጠቃልያ

የኢየሱስን ትንሳኤ ሳታቋርጥ መስበኳ የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን የስኬት ሚስጥር ተድርጎ ሊወሰድ ይችላል።ለእነርሱ ትንሳኤ በአመት አንድ ጊዜ የሚያከብሩት በዓል አልነበርም ይልቁንስ እለት እለት የሚኖሩበት፣ የሚራመዱበት፣ እና የሚተነፍሱበት እውነታቸው ነበር፤ ኢየሱስ ተነስቷል የሚለው እውነት።

የሕይወት መለዕክት፥ የትንሳኤ ሕይወት እንዳለን በማወቅ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን ወንጌልን ለሌሎች ከማካፈል ወደ ኋላ አንበል። ምክንያቱም በትንሳኤ ሃይል ከሞት የተነሳው እና የሚኖረው እርሱ የዕብራውያን ጽሃፊ እንዳለው “ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” (ዕብራውያን 7፥25) 

በዚህ ዘመን የኢየሱስን እና የትንሳኤውን መልዕክት ማዕከላዊነት እንደገና መረዳት ይሁንልን። ይህ በቤተ‑ክርስቲያንም ሆነ በብዙ ግለሰቦች ሕይወት መነቃቃት ለማየት እውነተኛው ቁልፍ ነው። 

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox