ትንቢት: ጊዜው ጨለማን ዘልቀን የምንገባበት ነው

ዋንዳ አልገር

አዎ ምድርን ከቧት የሚገኘውን ከባድ ጨለማ በመለማመድ ላይ ነን እኛ ሁላችንም እየተካሄደ ያለውን የብጥብጥ ማዕበል፣
የሙስና ደመና እና የሚለዋወጠው የክህደት ጥላ ውጤት እየተሰማን ነው።
ጨለማ የሴጣን መገኘት ብቸኛ ማሳያ እንዳይመስልክ አስተውል እሱ ብቻውን ትልቅ የጨለማ ጌታ የሆነ አለ።
“ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ
ነበር”። (ዘፍጥረት 1፥2)
ብርሀን ከመሆኑ በፊት ጨለማ ነበር እናም ሁለቱም የተፈጠሩት በተመሳሳይ ፈጣሪ ነው። ጨለማ ሁልጊዜ የእግዚሀብሄር
አለመኖር ማሳያ አይደለም የሰራው እርሱ ስለሆነ። ግን እግዚአብሄር ብቻ አይደለም በጨለማ ላይ የሚሰፍፍው እርሱ አላማውን
ለማስፈፀም በጨለማ ላይ ይንሳፈፋል።
ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ፥ ወረደም፤ ጨለማም ከእግሩ በታች ነበረ።በኪሩብም ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ ሆኖ ታየ፤
መሰወርያውን ጨለማ፥ በዙሪያውም የነበረውን ድንኳን፥ በደመና ውስጥ የነበረ የጨለማ ውኃ አደረገ።

በፊቱም ካለው ብርሃን የተነሣ ፍም ተቃጠለ። እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።(2ሳም22 :10
፥14)
እያያችሁት ነው ? የሰራዊቱ አለቃ በእጁ የሚገባንን ቅጣት ይዞ በጨለማ ላይ እየጋለበ ነው፣ በአይኖቹ ዉስጥ እሳት እና በሆዱ ሳቅን
የያዘ ነው። ጌታ በጨለማ ውስጥ በደስታ እንደሚደረግ ጉዞ በሀጥያተኞች እና አስቸጋሪ ሰዎች ላይ ለመፍረድ ያልፍል። ጠላት እንደ
ጭስ የሚጠቀምበት የለሊቱ እርዝማኔ ለእርሱ ምንም ማለት አይደለም ጌታ እንደ መጓጓዣ ይጠቀምበታል።
ሻምፒዮናችን በጨለማው አይስፈራራም ወይም አይገታም ፣ ምክንያቱም ሁሉም ነገር ከእግሩ በታች ስለሆነ ጨለማም ለእርሱ
እንቅስቃሴ እና ፍቃድ መገዛት እና እጅ መስጠት አለበት። ይህ እውነታ ተስፋችንን ማጠንከር እንዲሁም እምነታችንን መገንባት
አለበት እርሱን ለሚከተሉት ሁሉ እርሱ ያዘጋጀው ታላቅ ጥሪ አለ።
እርሱ በእውነቱ ከእርሱ ጋር ወደ ጨለማው ይጋብዘናል። ሙሴ ነጎድጓድ ፣ መብረቅና ጭስ ወደነበረበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ
ሕዝቡን ባቀረበ ጊዜ ፣ ​​በመካከል እንዲመጣ ጥሪ ቀረበ ፡፡
“ሙሴም ለሕዝቡ፦ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ፥ ኃጢያትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በልባችሁ ይሆን ዘንድ መጥቶአልና
አትፍሩ፡ አለ፤ ሕዝቡም ርቀው ቆሙ ሙሴም እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ቀረበ”። (ዘጸአት 20:20-21)
ሕዝቡ ለፍርሃታቸው በሰጡበት እና ጨለማውን በሚርቁበት ቦታ ሙሴ ወደ ውስጥ በመግባት የጌታውን ድምፅ አውቆ በእርሱ
መታመንን ተማረ ፡፡ በሥራ ላይ ሌላ የማይታይ እውነታ እንዳለ ያውቅ ነበር ፡፡ ጨለማው ከጌታ ፊት አይወስደንም በእውነቱ ወደ እኛ
እንድንቀርብ ያደርገናል እንጂ፡፡
“ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው”። (መዝሙረ ዳዊት 97:2))
ቤተክርስቲያን አሁን እየኖርንበት ባለው ጊዜ ይህን መረዳት አለብን። ጨለማው እየተቃረበ በመጣ ቁጥር መገኘቱም እየቀረበ
ይመጣል። ደመናው የከበደ ሲመስል ክብሩ በትልቅ ይገለጣል። እግዚአብሔር ፅድቅን እና ፍትህን ለማምጣት እኛን ለማሳወር እና
ለመጨቆን የሚፈልግ ነገርን ሁሉ ይቆጣጠራል።

ጠላታችን በእውነቱ ሞኝ ስለሆነ ታላቁ ማታለያ አይሰራም ፡፡ ለክፉ ዓላማ እያስተናገደው ያለው ጨለማ ሰማይ ከተፈጥሮ በላይ
የሆነ አብዮት ለማምጣት እየተቆጠረ ነው ፡፡ መገለጥ ብቻም አደለም አብዮት ከጨለማው ውስጥ አንድ ክብር እየተገለጠ ሲሆን
ሰማይ ብቻ የሚያስተዳድረው ህዝብ ስልጣን ተሰጥቶታል። አሁንም ቢሆን የጠላት ሰራዊት የሰፈሩባቸው ቦታዎች ለክብር እየተዘጋጁ
ያሉ ስፍራዎች ናቸው ።
የእግዚሐብሄር ቅዱሳን እና የእግዚሐብሄር መንፈስ በጨላማው ላይ እያንዣበበ እና እየተንሳፈፈ ነው። በፊታችን ያለውን ባዶነት
ባልታየ ድንቅ እና ግርማዊነት ይሞላዋል። ይህንን ሰፊ በሆነው ከነዛ ጥላዎች ሁሉ የፈጠረው የእርሱን ድንቅ ስራ ለመግለጥ
ከበስተጀርባ ሆኖ እየሰራ ነበር፡፡ በድፍረት የተነሱ እና ከእርሱ በስተቀር ምንም የማይፈሩ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ናቸው።
ህይወትን ፣ ብርሀን እና ክብሩን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለምድር የማሳየት የኤደን ቃልኪዳን ነው። ከእያንዳንዱ የጨለማ
ደመና ጀርባ ለመወለድ የሚጠብቅ የመንግስተ ሰማይ ቁራጭ እንዳለ ይወቁ!
ግን ምርጫ አለን። ይህን ጨለማ በምንጋፈጥበት ወቅት ምላሾቻችንን ማወቅ አለብን። በድጋሚ የእግዚሐብሄር ህዝብ በተራራው
ፊት ነው። በድጋሚ ከማይታየው ግዛት የሚመጣው መንቀጥቀጥ እና ማዕበል እየተሰማን ነው። ነገር ግን ይህ ተራራ የጌታ ተራራ
ነው እርሱን የምናገኘውም ጌታን በመፍራት ብቻ ነው (ኢሳ 2፡2፥4 ተመልከቱ) ። በጀግንነቱ ወደ ሚያዝበት እና ድፍረቱ ወደ
ተሰበሰበበት ወደዚህ ስፍራ እንድንመጣ እንደገና እየጋበዘን ነው ፡፡
እንደ ድሮ ሰዎች ተመሳሳይ ስተትን አትስሩ። ጨለማን አታስወግዱ ወይም ከእርሱ ዞር አትበሉ። እርግጠኛ ወዳለመሆን አታፈግፍግ ።
ሚስጥሮቹን የሚያጋራው እና ልቡን የሚገልጠው በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ስለሆነ ወደ ጨለማው የመሮጥ ጊዜው አሁን ነው!።
ልክ ከሙሴ ጋር እንዳደረገው ፣ አገልጋዮቹን እና ለእኛ አሁን ላለው ለዚህ የመዳን ወቅት የተለዩትን ወደ እርሱ እንዲመጡ እና
ከመንፈሱ ጋር ህብረት እንዲሆኑ ጥሪ እያቀረበ ነው። እውነተኛ ኃይል እና ስልጣን የሚገኘው በዚህ በነበልባል ተራራ ውስጠኛው
መቅደስ ውስጥ ብቻ ነው ፡፡
አስተውሉ ይህ ሚስጥራዊው ቦታ እንደ ግጦሽ መሬት ወይም እንደ ተሰወረው ዋሻ የሚገኝ አይደለም ። ይህ ሚስጥራዊው ቦታ
በጨለማ፥በማዕበል፥በመንቀጥቀጥ ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው። በእውነት ምን እንደሆነ የምናየው ጨለማውን ዘልቀን ወደ
ውስጥ ስንገባ ነው።
ይህ ማለት የሰውን ፍራቻ እና የሚመጣውን ክፉ ነገር መፍራት እና ማየት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ መታመን ማለት ነው ፡፡
ወገብዎን ጠበቅ አርገው ወደ ፊት ይንቀሳቀሱ! ጊዜው የፈራችሁትን የምትጋፈጡበት ነው። ወዳለመዳችሁበት የምቾት አቅጣጫ
ወይም መንገድ አትመለሱ ። ያየችሁት እና የሰማችሁት ጠላት ከሚደበቅበት እና ጌታ ከሚነግስበት የጨለማ ግብዣ እንዲመልስዎ
አይፍቀዱለት። የጨለማ ፍራቻዎ መንግስተ ስማያትን ከመውረስ እና በመንፈስ ከማደግ እንዲያስተጋጉልዎ አይፍቀዱ።
እምነት እየበሰለ እና እግዚአብሔርን መፍራት እየተጠናከረ ነው ፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ የመዳን ቀናት ውስጥ ከጌታ ጎን ያሉት
በደህና ሁኔታ መጠበቃቸው እና በጨለማው ውስጥ ዘልቀው የመግባት ድፍረታቸው አይታወቅም ፡፡

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox