የተባረከ ጋብቻ
‹‹የምድር ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ››
እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን በትንቢት መልክ የሰጣቸውን የደኅንነት ዕቅድ እውን ለማድረግ ሲያስብ ሌሎች ተጋቢዎችን መረጠ፡፡ አብርሃምንና ሣራን ከዑር እንዲወጡ በተራቸው ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ የሚለውን የተስፋ ቃል ሰጠው ይህም ሰይጣንን በማሸነፍ ለዓለም ሁሉ በረከትን የሚሠጠው አዳኝ ከአብርሃም ዘር እንደሚወለድ የሚያመለክት ታላቅ የተስፋ ቃል ነበር፡፡ የአብርሃም የሣራ ጋብቻ በእግዚአብሔር የተባረከ ጋብቻ እንደነበር ይታወቃል ተጋቢዎች ሁሉ በበረከት መንገድ ይራመዱ ዘንድ በአብርሃምና በሣራ ጋብቻ የሚገኘውን ጠቃሚ ትምህርት እንዲገበዩ ማሳሰብ እንደወዳለን፡፡
የተባረከ ጋብቻ
የቅንጅትን ሕይወት መኖር ይጠይቃል
ከሁሉ አስቀድሞ አብርሃምና ሚስቱ ሦራ (መጀመሪያ እንደተጠሩበት) ለእምነት ጉዞ በአንድነት የተነሡ ‹‹ታራም ልጁን አብርሃምንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፡፡ ዘፍ 11÷31‹‹ ሁለት ሰዎች ሳይሰማሙ አብረው መጓዝ ይችላሉ?(አሞጽ 3÷3) ባልና ሚስት በእምት መንገድ ጎን ለጎን እንዲሄዱ አስፈላጊ መሆኑን ከአባታችን ከአብራምና ከእናታችን ከሦራ ሕይወት እንማራለን፡፡ ‹‹አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ፡፡) የአበብራምና የሦራ የመጨረሻ መድረሻ ሰማያዊ አገር መሆኑ በዕብራውያን 11÷16 ተጽፏል እንግዶችና መጻተኞች ሆነው በምድር ላይ ሳሉም እንኳ እግዚአብሔር በምድራዊ ሕይወታቸው ይፈጸምላቸው የነበረውን የተስፋ ቃል ሁሉ በቅንጅት ሕይወታቸው አብረው ይካፈላሉ ነበር፡፡ ይኸውም ለምሳሌ ወደ ተስፋው አገር ወደ ከንዓን አብረው ደረሱ፡፡ እዚያም ብዙ ዓመት ከቆዩ በኋላ የተስፋው ልጅ ይስሐቅ ተወለደላቸው እንደዚሁም የክርስቲያን ባልና ሚስት ዓላማ ወደ ሰማያዊ አገር መድረስ ሲሆን በዚህ ምድር እንደ መጻተኞች ሆነው በአንድነት ሲጓዙ በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን በዚህ እናስተውላለን፡ የተባለከ ጋብቻ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግኑኝነት መመሥረት ይጠይቃል፡፡
አብራምና ሦራ በእምነት ቅንጅት ሲሄዱ ሁለቱም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ውስጥ ስለነበሩ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግኑኝነት ነበራቸው ይህም በመሆኑ እግዚአብሔር የአብራምን ስም ሲለውጥ የሦራንም ስም ደግሞ ለወጠ የወንዱ ስም ከአብራም ‹‹ ታላቅ አባት›› ወደ አብርሃም ‹‹የብዙዎችን አባት ሲለውጥ የሴቲቱ ስም ከሦራ ‹‹ልዕልቴ›› ወደ ሣራ ‹‹ልዕልት›› ተለወጠ የሁለቱም ስም መለወጥ በእግዚአብሔር ታላቅ ዕቅድ ውስጥ ሁለቱም እንደ ተያያዙ ያስባል፤ ዘፍ 17÷5-15 ፡፡ እግዚብሔር ይስሐቅ የሚፀነሥበት መድረሱን ለአብርሃም ከነገረው በኋላ ጊዜ ደግሞ ወደ አብርሃም ድንኳን መጣ በምን ምክንያት መጣ?ሣራ ራሷ ከእግዚአሔር ይህን አስደሳች ዜና ሰምታ እንድታምንበት ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ታላቅ የእምት ሥራ እንዲፈጸም የሁለቱንም እምነት አስፈላጊ ነበረ ስለዚህ በመጨረሻ በአዲስ ኪዳን ስለ ተስፋው ልጅ መወለድ ሲጻፍ በእምነት የሚለው ስለ አብርሃም ብቻ ሳይሆን ‹‹ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመጽነስ ኃይልን በእምነት አገኘች›› ተብሎ ተጽፏል ዕብ.11÷11 ማናቸውም ጋብቻ የሚፈጽመው ለእግዚአብሔር ክብር ቢሆንም እያንዳንዱ ቅንጅት ልዩ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳለበት ባልና ሚስት ማስተዋል አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሪ ባልየው ብቻ ሳይሆን ሚስቲቱም ጭምር መራመድ ይችላሉ፡፡ ጋብቻቸውም የተባረከና ለብዙ ሌሎች ሰዎች በረከት ይሆናል፡፡
የተባረከ ጋብቻ
ያለፈውን የኑሮ ሁኔታ መተው ይጠይቃል
አብርሃም ሣራ የሚኖርባትን አገር ዘመዶቻቸውንና የወላጆቻቸውን ሀብት እንዲሄዱ ተናግሯቸውን ሀብት በመተው ጌታ ወደ ሚያሳያቸውን ሀብት እንዲሄዱ ተናግሯቸው ነበር፡፡ ይህ ጉዞ እጅግ ከሚቀራረብ ቤተሰባዊ ትስስር ተላቅቆ መሄድን የሚጠይቅ በመሆኑ ቀላል ጉዞ አልነብም፡፡ ይሁን እጂ አብርሃም ሣራ ለእግዚአብሐሔር በመታዘዝ ሊሄዱ ሲነሱ ከቤተሰቦቻቸው ውስጥ የአብርሃምን አባት ታምራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን አስከትለው ወጡ፡፡ የአብርሃም አባት ታራ ዐሥራ አምስት ዓመት በኖሩበት ውስጥ ሞቱ ፡፡ አብርሃም አባት ታራ ዐሥራ አምስት ዓመት በኖሩበት ጊዜ ሎጥ ለእርሱ ጋር ነበር ሎጥ ከአብራሃምና ከሣራ እንዲለይ ያደርጉት ሁኔታዎች እስከተፈጠሩ ድረስ ከእርሱ ጋር በጉዞ ላይ ቆየ፡፡ በኋላ ግን የሁለቱ ሰዎች ማለትም የአብርሃምና የሎጥ የከብትና የበግ መንጋ ብዛት በእረኞቻቸው መካከል ጠብ እንዲፈጠር በማድረጉ በመጨረሻም በአንድነት ለመኖር የማይችሉበት ደረጃ እየቸመረ መጣ በእርግጥ አብርሃምና ሣራ ጌታ ለእነርሱ ሕይወት ያቀደውን ዕቅድ ለመከታተል ነጻነት የነበራቸው በመጀመሪያ ከታራ ቀጥሎ ከሎጥ ጋር የመጨረሻ መለያት ከተፈጠረ በኋላ ነበር ይህ ታሪክ በዘፍጥረት ም፤ 1 እና 13 ላይ ይገኛል ዘፍጥረት ም 2÷24 ‹፣ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል በሚስቱም ይጠበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ›› ስለሚል መጽሐፍ ቅዱስ የሚያዝዘው ጋብቻ ዓይነት የነበረንን ነገር ‹‹መተው›› ይታይበታል፡፡ ስለሆነም ተጋቢዎች ለጋብቻቸው ጌታ ያቀደላቸውን የተለየ ዓላማ ከግብ ማድረስ የሚችሉት አብርሃምና በሣራ መንገድ በመጓዝ ነው፡፡
የተባረከ ጋብቻ
የሥርዓትን ቅደም ተከተል ማክበርን ይጠይቃል
አብርሃምና ሣራ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ግኑኝነት ማደጉን ባች ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ለአንድ እንዴት መኖር እንደሚገባቸው የበለጠ እያወቁ መሄዳቸውንም ጭምር በጋብቻ ሕይወታቸው ከታየው ልምድ እንረዳለን፡፡ ለአብርሃምና ከሣራ እግዚአብሔር በነበረው ዕቅድ በእያንዳንዷ እርምጃ እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሚያነጋግረው አብርሃምን ነበር፡፡ ምክንያቱም ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ በቤተሰብ ውስጥ የመሪነቱን ሥልጣንና ኃላፊነቱን ለወንድ ሰጥቶ ስለነበር ነው፡፡ ይኸውም ምንም እንኳ ሣራ ከአብርሃም ጋር የማትስማማበት ሁኔታ ቢያጋጥማትም ውሳኔውን ለመከተል የመታዘዝና የፈቃደኝነት መንፈስ ማሳየት እንዳለባት የሚያመለክት ነው፡፡ ሣራ እግዚአብሔርን ስትከተል ራሷን በይበልጥ በታማኝነት ለእግዚአብሔር ማቅረብ ያለባት መሆኗን በሚገባ ተገነዘበች፡አብርሃም የተስፋውን አገር ከነዓንን ትቶ ምግብ ለማግኘት ወደ ግብጽ ለመሄድ የወሰነበት ጊዜ ነበር፡፡ በተለይ ሁኔታ ወደ ደቡብ ማለትም ወደ ጌራራ ንጉሥ ወደ አቤሜሌክ በሄደበት ወቅት እንደገና ይህ ተመሳሳይ ሁኔታ ተከስቷል እነዚህ አጋጣሚዎች በዘፍጥረትም 13 እና 20 ላይ ተጠቅሷል ፡፡
በዚህ ጊዜ አብርሃም ለሕይወቱ ሣራን እኅቴ ናት ሲል ቆየ ከዚህ የተነሣም ሣራ ከፍተኛ አደጋ ላይ ወደቀች፡፡ ሣራ ይህ ችግር ቢያጋጥማትም በባሏ በአብርሃም ላይ ዐላመጸችም በእያንዳንዱ የሕይወት ጉዞ ወቅት እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር ስነበር ሊደርስባት ከሚችል አደጋ አድኗታል ሣራ ከአብርሃም በዋሸው ግማሽ ውሸት መስማት አልነበረባትም የሚል ግምት ሊኖረን ይችላል በእነዚህ ታሪኮች ውስጥ በእርግጥ ለፈጸመው ስሕተት ውጤት በማድረግ እግዚአብሔር በአብርሃም በራሱ ላይ በተከሠተው ሁኔታ አሳይቷል እግዚአብሔር ከአብርሃም የተመረጠውን አላከናወነለትምና ዘፍጥረት 12÷14-13 ይህን በተመለከተ ኃላፊነት የወደቀው የቤተሰቡ ራስ በሆነው በአብርሃም ላይ እንጂ በሣራ ላይ አልነበረም በነዚህ ድርጊቶች ውስጥ ሣራ ከነበራት ድርሻ የተነሣ እግዚአብሔር የወቀሳት አይመስልም ምክንያቱም ለባሏ ለመታዘዝ ልቧ ቀና ስለሆነ ‹‹እግዚአብሔር ፊት እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ›› (1ጴጥ 3÷4) ስለነበራት ነው፡፡ ሣራ በእግዚአብሔር ፊት የነበራት ውስጣዊ ቁንጅና የተፈጥሮ ውበቷን በለጠው፡፡
የሆነው ሆኖ እግዚአብሔር አብርሃምንና ሣራን በድንኳ ለመጎብኘት የሄደበት አንድ ቀን ደረሰ ዘፍ 18 እግዚአብሔር ሣራ ከዓመት በኋላ ልጅ እንደምትወልድ በተናገረ ጊዜ ሣራ ቃሉን ሰምታ ባለማመኗ ምክንያት ሳቀች ቁ 10-12 እግዚአብሔር ሣራ የሣቀችበትን ምክንያት ሲጠይቅ ግን ‹‹ሣራ ስለፈራች›› አልሳቅሁም ስትል ካደች፡፡ እርሱም ‹‹አይደለም ሳቅሽ እንጂ›› አላት ቁ 15 በዚያም ወቅት ሣራ ራሷ ተጠያቂ ነበረችና እውነቱን ባለመናገሯ እግዚአብሔር ዘለፋት፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ የሚያተኩረው ግን ሣራ እውነቱን ባለመናገሯ ላይ ሳይሆን ለአብርሃም ባሳየችው ሥርዓታዊ ዝንባሌና የፈቃደኝነት ስሜቷ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ክርስቲያን ሚስቶች ሁሉ እርሷን በምሳሌነት በማየት አርአያነቷን መከተል እንደለባቸው ያሳስባቸዋል በአብርሃምና በሣራ መካከል የነበሩ ሁኔታዎች እየተዛቡ መሄድ ሲጀምሩ በመጽሐፍ ቅዱስ በተለይም በዘፍጥረት ም16 ላይ አንድ የተመዘገበ ጉዳይ አለ ዓመታት በዓመታት እየተተኩ አለፋ ለአብርሃምና ለሣራ ተስፋ የተገባላቸው ልጅ ግን ገና አልተወለደም ስለዚህ ሣራ በነገሮች ሁሉ ራሷ ወሳኝ የምትሆንበትን ወቅት እንደደረሰ ተሰማት፡፡ ወዲያውም በአካባቢያቸው ይኖር የነበሩ የአሕዝብን ሥርዓት መከተል እንደሚገባውና ከአገልጋይዋ ከአጋር ልጅ መውለድ እንዳለበት ለአብርሃም ነገረችው፡፡ ይህን በመፈጸም ባደረባት ጥርጥር የተነሣ ከነበራት የኃላፊነት ባደረባት ጥርጥር የተነሣ ከነበራት የኃላፊነት ክልል ወጥታ የቤተሰቡ መሪ ለመሆን ሞከረች፡፡ በዚህ አሳዛኝ አጋጣሚ ምክንያት አብርሃምም ከነበረው ቤተሰባዊ ኃላፊነት በመውጣት የሣራን ሐሳብ ተቀበለ፡፡ የዚህ ስሕተት አሳዛኝ ውጤቶች ዛሬም ቢሆን ከእኛ ጋር አሉ፡፡ ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ ከአብርሃም ጋር ያለውን የዘር ግንኙነት በይሰሐቅ ዐረቦች ደግሞ ከአጋር በተወለደው በእስማኤል በኩል እንደሆነ ስለሚያምኑ ነው፡፡ሐዋርያው ጳውሎስ በጋብቻ ሕይወት ውስጥ የማዘዝንና የመታዘዝ ዐበይት መርሖች ኤፌሶን 5÷21-23 ላይ ጠቅሷቸዋል ባሎች ቤተሰባቸውን እንዴት መምራት እንደሚችሉ መማርና በክርስቶስ ፍቅርም መሞላት አለባቸው ሚስቶችም ደግሞ መላበስ ይኖርባቸዋል፡፡ ባል ወይም ሚስት በቤተሰብ ውስጥ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን የኃላፊነት ድርሻ በትክክል ለመወጣት ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ በእርሱ በሌሎች ሰዎች የጋብቻ ሕይወት ውስጥ በረከትን ማስገኘት ለሚችለው ለታላቁ የእግዚአብሔር ዓላማ መኖር መሥራት እንዳለባቸው ከዚህ በላይ የተመለከትነው አብርሃምና የሣራ ጋብቻ ሁኔታ በሚገባ ያስረዳልና፡፡
ነብዩ ኢሳያስ ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ፡፡ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት. ባረክሁትም አበዛሁትም (ኢሳ. 51÷2) በማለት እግዚአብሔር የባረከውንና የሠራበትን የአብርሃምንና የሣን የጋብቻ ሕይወት በሚገባ እንድናየው ያነቃቃልናል አብርሃም ከእግዚአብሔር በረከትን እንዲቀበል ተጠርቶ ነበር፡፡ ከሣራ ጋር የነበረው ጋብቻም በእግዚአብሔር የተባረከና በመጨረሻ በክርስቶስ በኩል የተከናወነውን የእግዚአብሔርን ዓላማ ለመፈጸም ያስቻለ ነበር፡፡ ምእመናን በክርስቶስ አማካይነት የአብርሃምን በረከት አብረው ይካፈላሉ የምሥራቹን ወንጌል በቃልና በኑሮ በማወጅ ለሌሎች በረከት እዲሆኑ ተጠርተዋ ክርስቲያኖችን እግዚአብሔር ወደ ጋብቻ የሚጠራበት ምክንያት የቅንጅት ሕይወታቸው ይህንኑ ታላቅ የእግዚአብሔር ዓላማ በብቸኝነት ሕይወታቸውን ከሚከናወኑት በበለጠ እንዲፈጽሙ ነው፡፡ እስካሁን እንደተመለከት ነው በዚህ የድካም ዓለም እንከን አልባ የሆነ የጋብቻ ሕይወት የለም ነገር ግን ሁለት የትዳር ጓደኛሞች የለም፡፡ ነገር ግን ሁለት የትዳር ጓደኛሞች ምንም ዓይነት ዋጋ ቢያስከፍልም እግዚአብሔርን ለማገልገል ራሳቸውን ለእርሱ ሲሰጡና ተስማምተው አብረው ሲጓዙ እግዚአብሔር በሕይወታቸው ለሚያደርገው ሁሉ የአብርሃምና የሣራ ጋብቻ ሕያውና ቋሚ ሐውልት ነው፡፡
ቤሪ ጋዜጣ
ቁጥር2 1996
Copyright Hiyawkal © 2024
Leave a Reply