ሳምራዊቷ

ብርሃን መፅሔት ቁጥር 2 1984 ዓ.ም :

አንድ ጊዜ በዮሐንስ ደቀመዝሙርና በአይሁድ መካከል ስለመዳንት ትልቅ ክርክር ተነሳ፡፡ የዮሐንስ ተከታዮችም ወደ መምህራቸው ሄደው በዮርዳኖስ ማዶ ካተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርክለት እነሆ ያጠምቃል ብዙዎችም ተከትለውታል፡፡ ሁሉም ደግሞ ፊታቸውን ወደ እርሱ መልሰዋል ይህ ነገር ታዲያ እንዴት ሊሆን ነው አሉት፡፡ በአነጋገራቸው ደስተኞች እንዳልነበሩ ለመረዳት አያዳግም፡፡ዮሐንስም ለአፍታ ያህል ይህ ሰው በአይኑ ላይ ሽው አለበት፡፡ በአንድ ወቅት ከኢየሩሳሌም ከካህናትና ሌዋውያን ሰዎች ተልው ስለእርሱ የሰጠው ምስክርነት ትዝ አለው፡፡ ለተከታዮቹም መልሶ እኔ በውሀ አጠምቃለሁ ዳሩ ግን እናተ የማታቁት በመካከላችሁ ቆሞአል እኔ የጫማውን ጠፈር ልፈታ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣውን ከእኔ የሚከብር እርሱ ነው እያለ ባለማወቅ ልባቸው የጠጠረውን ተከታዮቹን ያስተምር ጀመር፡፡ ዮሐንስም ቀናው መንገድ የቱ እንደሆነ እያፍታታ በዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ በቤተ ረባ ሆኖ ሲያገለግላቸው ሳለ ያ የተፈራው ሰው (በዮሐንስ የሥልጣን ሽኩቻ የገጠመው) ድንገት ብቅ አለ፡፡
ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የዓለምን ኃጢያት የሚያስወግድ የዕግዚአብሔር በግ ሲል ጮኸ ይን ወሬ በአይሁድ ምድር ተናኘ ግማሽ ሲመለከተው ግማሹ ቃሉን ሲሰማ ፈሪሳውያንም በነገር ሊያጠምዱት ወደ እርሱ ይርፉ ጀመር፡፡ ይሕ ሰው ሁኔታች ሰለዋወጡ ይሁዳ ትቶ ወደ ገሊላ ተጓዘ፡፡ ከረጅምና አደድካሚ ጉዞ በኋላ ያዕቆብ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ ወደምትገኝ ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ ደረሰ፡፡
ሲካር ከጥንታዊ ከተማነቷ ባሻር በተለየ መልክ እንድትታቅ ያደረጋት ያዕቆብ በዘመኑ ለቤተሰቡና ከዛም አልፎ አስቆፍ ስለነበረ ነው፡፡ ጉድጓዱም ለሰማርያ ሕዝብ ራሱን የቻለ የራሱ የሆነ የታሪክ ምስክርነት ይሰጠው ስለነር ሰማርያዎች በዚህ ጉድጓድ ያዕቆብን የሚያወድሱበት የልብ ኩራት ነበራቸው፡፡

ይህም ተጓዥ አይሁዳዊ ድካም ስለተጫነው ሙቀቱም እየጨመረ ስለመጣ ጊዜውም የምሳ ሰዓት በመሆኑ ደቀመዛሙርተህ ምግብ ፍለጋ ወደ ከተማይቱ አቅንተው ሳሀሉ በዛች በቴምር ዛፍ በተከበበች የውሀ ጉድጓድ አተገብ አረፍ አለ፡፡
በአገሩ ልምድ መሠረት እረኞች ከብቶቻቸውን የሚያጠጡት ኮረዶችና ሴቶች ውሀ የሚቀዱበት ሰዓት ስለሆነ ከሰማርያ አንዲት ሴት ውሀ ተሸክማ መጣች፡ድካም ቢጫጫነው የራሱ የሆነ አላማውና ተልዕኮ ስለነበረው እባክሽ ውሀ አጠጭኝ አላት፡ጥያቄው መገረምን ሳያስከትል አልቀረም፡፡ ምክንያም በወቅቱ አይሁዶች ከሳምራያን ጋር አይተባሩም ነበረና ነው፡፡ ይህችው ሴት መገረምን በውጧ እንደ ያዘች እንዴት ከኔ ከሳምራቷ ሴት አውሀ ትለምናለህ አለችው፡፡የእግዚአብሔር ስጦታና ውሃ አጠጭኝ የሚልሽ መሆኑንስ ብታውቂ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውሃ ይሠጥሽ ነበር አላት፡፡የብርሀን ውጋጋን ትንሽ ፈነጠቀባት፡፡ ጌታ ሆይ አለችው ሐሳቧ እንደተበታተነ በተለይም የሕይወት ውሃ ይሰጥሽ ነበር ያላት አባባል አእምዋ በጥያቄ ሞላ፡፡ እና ስትመለከተው በእጁ መቅጃ የለም፡፡ ውሀንም ከጉድጓድ ለመጎተት አቅም ያለው አይመስልም፡፡ እንዳውም ልብ ብለው ሲያዩት መልክና ውበት የለውም፡፡ ይወደድ ዘንድ ደም ግባት አልባ የተናቀ ሰውም አይ ፊቱን የሚሰውርበት ነበር፡፡ ታዲያ ጉስቁልና ቢጎዳው ቢዝል በላብ ቢነከር ከዚህ ሰው መልካም ነገር ይገኛል ብላ ባትጠብቅም ለመሄድ ግን አልቻለችም፡፡ጌታ ሆይ አለች ማተውቀው ነገር ጌትነቱን እየገለፀላት ትክ ብላ አስተዋለችው፡፡ ከማይስበው እሱነቱ ላይ አዳኝ የሕይወት ውሃ ከውስጡ የሚፈልቅ ከነዛም ዓይኖቹ ላይ ርህራሄ የሚንፀባረቅበት በመሆኑ እሷም በተራ ግልፅ ሆነችለት፡፡ ያን አባቶቿ እና ድፍን የሰማርያ ሕዝብ የሚመካበትን የውሃ ጉድጓድ የሙሴን ሕግ ወጓንና ባህሏን አወጋችለት፡፡

አይሁዳዊው በተመስጦ ከሰማት በኋላ እኔ ግን ከምሰጠው ውሃ ለዘላለም አይጠማም፡፡ እንዳ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጅ አላት፡፡ሳምራቷ ግራ ገባት፡፡ ከበፊቱ በበለጠ አእምሮዋ በጥያቄ ተሞልቶ እንዴት ሳትል አላለፈችም፡፡ በተለይም ያን አድካሚ የእግር ጉዞ ከምትሸከመው የውሃ እንስራ ጋር መዘነችው፡፡ ኸረ ስንቱ የቤት ውስጥ ስራም የሙቀቱ ነገር ሁሉም ቤፈርጁ አድካሚ ነበር ታዲያ ከዚህ አንፃ ሲታይ ለዘላም የማያልቅ የሕይወት ውሀ ማግኘት ግልግል ነው፡፡ እንደማት ነገር በረጅሙ ተንፍሳ እባክህ አለችው ፈቃደኝነቷን በሚገልፅ ሁኔታ ያ የሲካር እንግዳ ሰው ዋዛ አልነበረም ጀም ከግቡ ሳያደርስ በእጥልጥል አይተውም ሂጂና ባልሽን ጠርተሸ ነይ አላት የሕይወቷን ጓዳ ሊያሳያት እየዘፈለገ ጥያቄው ድንጋጤ ቢያስከትልም ፈርጠም ብላ ባል የለኝም አለቸው፡፡ባል የለኝም በማትሽ መልካም ተናገርሽ፡፡ አምስት ባለሎች ነበሩሽ፡፡ አሁን ካንቺ ጋ ያለው ባልሽ አይደለም አላት፡፡

ብርሃን መፅሔት
ቁጥር 2 1984 ዓ.ም

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox