መገለጥን በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን፥ 1) ጠቅላላ መገለጥ፥ ይህ መገለጥ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ጊዜ እና ቦታ ሳይለይ ራሱን የገለጠበት ነው። 2) ልዩ መገለጥ፥ ይህ መገለጥ እግዚአብሔር በሆነ ጊዜ ለመረጠው ሰው ራሱን የሚገልጥበት የመገለጥ አይነት ነው።
መገለጥ በአሁን ውስጥ የእግዚአብሔርን ልብ የሚያሳየን ነው። ክስተት ደግሞ ያንን መገለጥ በተጨባጭ የሚያስረግጥልን ነው።መገለጥ እና ክስተት የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፤ ይህ ማለት ከመንፈሳዊ ክስተት ውጭ የሆነ መገለጥ የለም፣ ከመገለጥ ውጭ የሆነም መንፈሳዊ ክስተት የለም። በምድር ላይ ክርስቶስ እንደተመላለሰው ለመመላለስ ሁለቱም ያስፈልጉናል።
በመንፈሳዊው አለም ያለችሁ ልምምድ በገሃዱ አለም ተገልጦ ተጸእኖ መፍጠር አለበት።
መገለጥ የእግዚአብሔርን ሃይል ለማሳየት አስፈላጊ ነገር ነው ብዬ ስናገር ተራ መረጃ እና ከንቱ እውቀት የሰውን ሕይወት እንደማይለውጡ አጽንኦት በመስጠት ነው። መገለጥን የማያመጡ ነገሮት በሰው ሕይወት ውስጥ ለውጥን ማምጣት አይችሉም ምክንያቱ ደግሞ በዛ ሁኔታ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ሃይል በሙላት መስራት ስለማይችል። ከዚህ በመቀጠል እንደምንመለከተው ግን እያንዳንዱ የመንፈሳዊ አለም እውነታ በመገለጥ ጉልበት ወደ ገሃዱ አለም መምጣት እንደሚችል እናያለን።
እስከ አሁን ድረስ በቤተ ክርስቲያን የምናያቸው ብዙዎቹ መለኮታዊ ክስተቶች ከእግዚአብሔር ሉኣላዊነት የሆኑ እንጅ ያንን ሃይል ለማሳየት መገለጥን ከመቀበላችን የተነሳ የሆኑ አይደሉም።በቤተ ክርስቲያን መገለጥ እስካልመጣ ድረስ የእግዚአብሔርን ሃይልን በሙላት በሕይወታችን መለማመድ እንችላለን ብዬ አላምንም። የእግዚአብሔር ቃል እውቀት እና ስነ መለኮታዊ መገለጥ ያስፈልገናል።ለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን እነዚህን እውነቶች እንድንገልጥ እና የእግዚአብሔርን ሃይል በምድር ላይ እንድላማመድ።
የቃሉ መገለጥ ባለበት ነው መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊውን ሃይል በሙላት የሚገልጠው።
በአንተ እግዚአብሔር እንዲሰራ ፈቅደህለታል?
የእግዚአብሔር ሃይል በሕይወታቸው በሙላት እየሰራባቸው ያሉን አማኞች ከሌሎች የሚለየው የመገለጥ ጉዳይ እንደሆነ በእውነት ልንረዳ ይስፈልጋል። ብዙዎች የተአምራት፣ የፈውስ፣ ነጻ የማውጣት፣ እና የመስጠት ስጦታዎችን አሏቸው፤ በሕይወታቸው ግን አይገለጡም ምክንያቱም እንዴት መግለጥ እንዳለባቸዉ ስለማያውቁ።ይህ ትዉልድ መለዕክት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ሃይል መገለጥ ያይ ዘንድ ያስፈልገዋል። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ሃይል መግለጥ ችላ ስትል የሚሰራ እምነት የሌላቸውን አማኞች ትፈጥራለች። . ለዚህም ነው ዛሬ ብዙ የእግዚአብሔር ልጆች የእርሱን ሃይል በመለማመድ እርሱን የበለጠ ከማወቅ ይልቅ እውነትን የሚያመቻምቹ እና ሰዎችን ለማስደስት የሚሞክሩ የሆኑት። የምጠይቃችሁ ይህንን ነው፥ እግዚአብሔር በእናንተ እንዲሰራ ፈቅዳችሁለታል? በእናንተ እውሩን እንዲያበራ ጆሮው የማይሰማውን እንዲከፍት።
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ራዕይን ወደ መገለጥ የሚያመጡ መንገዶች ናቸው
በእግዚአብሔር ሃይል መንቀሳቀስ!
ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ “እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድርስ በእየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።” (ሉቃስ 24፥ 49) ሲል መንፈሳዊ እውቀትን እና ሃይልን ቃል እይገባላቸው ነበር። በግሪኩ እስክትለብሱ የሚው ቃል ‘ኢንዱ’ ይባላል፥ ኢንዱ ሃይልን፣ ችሎታን፣ እና እውቀትም መልበስ ያጠቃልላል።
የጴንጤ ቆስጤ እለት እግዚአብሔር አምላክ የኢየሱስን ተከታዮች በሃይል ብቻ አልነበረም የሞላቸው፤ በመገልጥም ነበር ያስታጠቃቸው፤ ምክንያቱ ደግሞ ሃይሉ በስጋዊ መረጃ እንዲሰራ ስለማይፈቅድ ነው። የእግዚአብሔር ሃይል የ ኢየሱስ ምስክር መሆን ለሚፈልጉ ለእነርሱ ነው፤ እርሱን ማወቅ ደግሞ ሃይሉን እነዴት መጠቀም እንዳለብን እንድናውቅ ያስችለናል። “እነርሱም ወጥትው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሰራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።” (ማርቆስ 16 ፥20)
Copyright Hiyawkal © 2024
Leave a Reply