መጽሐፍ ቅዱስ አውግስጦስ ቄሳርን መጥቀሱ ለምን ግድ ይለናል?

ማርክ ዲሪስኮል :

“በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች” (ሉቃስ 2: 1)።

የሉቃስ 2 የመክፈቻ ዓረፍተ-ነገር ጸሐፊው ለታሪካዊ ዝርዝር ሁኔታ ታላቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ያሳያል። ሉቃስ፣ ኢየሱስ በተወለደበት ጊዜ ላይ ገዢ ከነበረዉ ከአውግስጦስ ቄሳር ጋር ያስተዋውቀናል። አውግስጦስ ቄሳር በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ የፖለቲካ መሪ ነበረ። በወቅቱም በአለም ከነበሩ ግዛቶች መካከል ረጅም ዘመናት የቆየች፣ ታላቅ፣ ታዋቂ እና ሰፊ የሆነችውን የሮሜን ግዛት ተቆጣጥሮ ነበር። እሱም የጁሊየስ ቄሳር የጉዲፈቻ ልጅ ነበር። “አውግስጦስ” የሚለው መጠሪያው “ግርማ የተላበሰ ወይም የተከበረ” ማለት ነው።

የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት፣ አውግስጦስ ቄሳር ወደ ስልጣን ሲገሰግስ ጨካኝ ሰው ነበረ፣ ነገር ግን አንዴ ስልጣንን ከተቆናጠጠ በኃላ ግን ተቀይሮ በጎና ደግ ሆነ። በእሱ ዘመን ከነበሩ፣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እርኩስ፤ ልክ እንደ ንጉሥ ሄሮድስ አይነት ሰዎች ጋር ሲነፃፀር በይበልጥ ቸር ነበረ።

አውግስጦስ ቄሳር ስር ሆኖ የሚሠራው ቄሬኒየስ የተባለ ገዢ ነበር፣ እሱም ከንጉሠ ነገሥቱ ፖሊሲዎችና ውሳኔዎች ተፈጻሚ ያደርጋል። ሉቃስ የኢየሱስን ልደት በአንድ በተወሰነ ጊዜ ታሪካዊ የጊዜ ሰንጠረዥ ውስጥ በመቁጠር እነዚህ ገዥዎች በተሰጡት የሕዝብ ቆጠራ ትዛዝ ወቅት እንደተከሰተ ይነግረናል።

አውግስጦስ ቄሳር በመላው የሮማን ግዛት ላይ ነግሦ የነበረ ሲሆን, ቄሬኔስ፡ ልክ እንደ ካቢኔ አባል ሆኖ ከፍተኛውን አመራር አገልግሏል። ቄሳር አንድ እርምጃ እንዲወስድ ይጠይቃል፣ እንደ ቄሬኔስ ያለ ሰው ትዕዛዙን ይፈጽማል። በዚህ ሁኔታ ሉቃስ የሚነግረን የህዝብ ቆጠራ ሊወሰድ ነበረ፣ ይህም ቄሳር ያለዉን ታላቅ ሥልጣን ለመገምገም እና ከፍተኛ ግብር ለማዘዝ እንዲሁም የሕዝቡን ወታደራዊ ተሳትፎ ለመጨመር ነበር።

በሌላ ታሪክ በተቃራኒው፣ ሉቃስ ትኩረታችንን ዮሴፍንና ማርያምን ነው። እነርሱ፣ ቄሳር እና ቄሬኔስ ያልሆኑትን በሙሉ ናቸው፡ ድሆች, አቅመ-ቢስ, በገጠር የሚኖሩ, እግዚአብሔርን እንደ አማልክት ከመመለክ ይልቅ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ነበሩ። የሆነ ሆኖ፣ ሁለቱም እርስ በርስ ይዋደዳሉ፣ በእግዚአብሔር ይታመናሉ፣ እናም የእግዚአብሔርን ጥሪ በህይወታቸው ላይም ተቀበሉ። አሁን, ማርያም በእርግዝናዋ መገባደጃ አከባቢ ናት፣ የሕዝብ ቆጠራውም ባልና ሚስቱ ወደ ቤተልሔም እንዲጓዙ ይጠብቅባቸዋል።

ዮሴፍ ከዳዊት የዘር ሐረግ ሲሆን ዳዊትም በቤተልሔም አቅራቢያ ነው ያደገው። ለቆጠራው ሁሉ ሰው ወደየ ትውልድ ሀገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል። ሕጉን ለመታዘዝ፣ ዮሴፍ ከናዝሬት ወደ ቤተልሔም በሚያስኬደው በግምት 100 ማይል(160ኪ.ሜ) ያክል በሚርቀው መንገድ ላይ ነፍሰ ጡሯ ማርያምን ማድረስ ነበረበት። ካሰቡበት በጣም አስደንጋጭ ነገር ነው፣ ከማንኛውም ሐኪም የራቀ፣ የህክምና እንክብካቤ ወይንም ማንኛውንም እርዳት ከቶ ከሌለበት፣ ከመንገድ ዳር ጌታ ሊወለድ ይችል ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በሉዓላዊው የአገዛዝ ስልጣኑ ታሪክን አስተካከለ፤ እነዚህን ጥንድ ከናዝሬት ወደ ቤተልሔም ለመውሰድ ከዚያም የሚክያስ 5፡2፤ ስለ መሲሑ ትውልድ ስፍራ ሚያወራው ትንቢት ይፈፅም ዘንድ ነበረ። 

ምንም እንኳ ረጅም ጉዞ እና ከእንስሳት በረት በቀር ሚያርፉበት ቦታ ባይ ባይኖራቸውም፣ ዮሴፍና ማርያም ኢየሱስ ሊወለድ ልክ በሰዐቱ ወደ ቤተልሔም ደረሱ። የአለም ፈጣሪ እና የነገስታት ንጉስ ለእንስሳት መመገብያ እቃ ሆኖ ቀረበ። በእዚህ ትሁት ቅንነት ግን፣ እግዚአብሔር በመንግሥታትና በታሪክ ሂደት ላይ ያለውን የመለኮታዊና ሉዐላዊ ኃይል ይመለከታል። እግዚአብሔር ዝርዝር ነገሮች በሙሉ ከኃያላን (ቄሳር አውግስጦስና ቄሬኒየስ) እስከ አቅም አልባዎቹ (ዮሴፍ እና ማርያም)፣ እርሱ ይቅርና በብዛታቸው ለቁጥር እንኳ የሚያዳግቱ ነፍሳትና እስከ ፍፃሜው ድረስ የተከናወኑ ክስተቶች፤ ቃሉ ይፈፅም ዘንድ እና የእርሱን አምላክነት በሁሉ ዘንድ ይታይ ዘንድ ነው የሆኑት።

ወደኋላ መለስ ብላቹ ስታስቡት፣ እግዚአብሔር ለህይወትዎ ያለው እቅድ ይቀጥል ዘንድ፣ ባልተጠበቀ ግንኙነት እና ክስተቶች አማካይነት እንዴት ሠርቷል?

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox