በእስራኤልና በዮርዳኖስ አካባቢ ከ100 በላይ የሚሆኑ ጥናታዊ ምክራቦች የተገኙ ሲሆን ብዙዎቹም በገሊላ አውራጃ የተገነቡ ነበሩ የሥነ ቅርስ ጠበብትም ምኩራቦችን እንደይዘታቸው ከፋፍለው አስቀምጠዋል የምኩራቦቹ ፊት ወደ እየሩሳሌም አንጻር ሆኖ ብዙዎችም ባለሦስት በር ነበሩ የመቅደስ ሥፍራ ከሚታይባቸው የገሊላ ምኩራቦች መካከል በቅፍረናሆም ያሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ቅፍረናሆም ቴስሁም በሚባል ቦታ ከገሊላ ናሕር በስተሰሜን ምዕራብ ትገኛለች ኢየሱስም ምድራዊ አገልግሎቱን በሰጠባቸው ዓመታት የአካባቢውን ንግድና እንቅስቃሴ ማዕከል ነበረች ሶሪያና ፍልስጤምን በሚያገኘው አውራ ጎዳና ላይ የምትገኘው ቅፍረናሆም ቀረጥ የሚቀረጥባት የሮም ሠራዊት የሰፈረባት ከተማ ጌታ ኢየሱስ ከናዝሬት መጥቶ የጴጥሮስን ቤት እንደ ቤቱ ተገልግሎበታል ማቴዎስም የተጠራው በዚህች ከተማ ሲሆን ከመስበክና ከማስተማርም አልፎ ተአምራቱን ፈጽሞባታል፡፡ ክርስቶስ የፍቅረናሆምን መፍረስ አስቀድሞ እንደተነበየው ዛሬ የከተማው ፍርስራሽ በገሊላ ባህር ዳርቻ እስከ አንድ ተኩል ኪሎ ሜትር ይሸፍናል በአካባቢውም የቀድሞው ውበታቸውን የለቀቁ ሕንጻዎች እዚህና እዚያ ይታያሉ ከመካከላቸው ትኩረት የሚሰጠው ባለስምንት ማዕዘኑ የጴጥሮስ መኖርያ ቤት ነው ሥፍራው ምናልባትም ለሐዋርያው ጴጥሮስ መታሰቢያ እንዲሆን ታስቦ የተሠራ ሊሆን ይችላል ሕንጻው በገሊላ ከሚገኙ የተዋቡ ምኩራቦች አንዱ ለመሆኑ ፍርስራሾቹ ይጠቁማሉ፡፡
በቦታው የተደረገው ቁፋሮ ያነጣጠረው ባለሁለት ደርብ በሆነውና ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር በሆነው በዚህ ምኩራብ ላይ ነበር ምኩራቡም በምስራቅ ያማረ በረንዳ የሚገኝ ሲሆን ውስጡ ሕጻውን ደግፈው የያዙና ለሴት አምላኪዎች የተሠሩ በሁለት መደዳ የተሰለፉ ዓምዶች ይገኛሉ በውስጡም የተለያዩ ማስጌጫዎች የተቀመጡ ሲሆን ከእነዚያም መካከል የእጽዋት የእንሰሳት የአእዋፍና የተለያዩ ጥንታዊ ፍጥረታት ምስሎች ይገኙበታል የአይሁድ ምልክቶች የሆኑትን ባለ ሰባት አንጓ መቅረዝና ባለ ስድስት ራስ ኮከብ (የዳዊት ኮከብ) በውስጡ ተገኝተዋል፡፡ በውስጡም እስራኤላዊያን በምድረበዳ ይጓዙ በነበሩበት ወቅት ከፊት ለፊታቸው ይጓዝ የነበረውን ታቦት የሚመስል ምስል ተቀርፆ ይታያል ከእምነበረድ ከተሰሩት ነጫጭ ዓምዶች በአንደኛው
የዘቢድያ ልጅ የዮሐናን ልጅ ይህን ዓምድ ሠራ›› የሚል የአረማይክ ጽሑፍ ተገኝቷል ደ/ር ግሉክ የተባሉ አጥኚ ስሞች በአዲስ ኪዳን በኢየሱስ ደቀመዛሙርት ዙሪያ ከተጠቀሱት ዘብዴዎስና ዮሐንስ ጋር የተመሳሰሉ እንደሆኑ ተናግረዋል(ማርቆስ 3፡17-18)
ብዙዎች ይህ በኢየሱስ የተጎበኘው መቶ አለቃ ያሠራው ምኩራብ እንደሆነ ቢያምኑም በርካታ የሥነ- ቅርስ ተመራማሪዎች ደግሞ ክርስቶስ በተመላለሰባቸው ቦታዎች በሦስተኛው ወይም በአራተኛው ምዕተ ዓመት የተገነቡ እንደሆኑ ያስባሉ ሐሳባቸውም የመሰረቱት ነሕንጻው ይዘት በተለይም ደግሞ በጌጣጌጦቹ ላይ ነው፡፡ የምኩራቡ ምንነት በማያሻማ መንገድ ሊቀመጥ ባይችልም የመጽሐፍ ቅዱስ ቅፍረናሆም ግን በትክክል ለመኖር ግን ቁፋሮው ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል የኢየሱስ ማንነት የተገለጠባቸው ሥፍራዎች ከያሉበት በቁፋሮ መገኘታቸው የያዝነው እውነት የተደላደለ ለመሆኑ እማኝ ሲሆን በማየት መመላለስ የሚሹም የሚያወላዳ ማስረጃ ነው በምህረቱ ያገናኘን፡፡
ናሁሰናይ አፈወርቅ
ብርሃን መፅሔት … ቁጥር 32
Copyright Hiyawkal © 2024
Leave a Reply