ለተረኛው ባለ-አደራ ፣ ብርሃን መፅሔት 1991 ቁጥር 32

ከመላኩ ሲሳይ :

ሕይወት ጉዞ ነው የጎዳና ላይ ጉዞ ታዲያ በዚህ ጎዳና ላይ ብዙ ነገር ያጋጥማል ብዙ ይኮናል ሰው በማሕጸን ጎዳና በኩል ደግሞም በሞት መንገድ አልፎ ወደ እግዚአብሔር አደባባይ ይደርሳል ከዚህ ነባራዊ ሕግ የተነሳ መወለድ ማደግና መሞት የማያቋርጡ የዕለት ተዕለት ክስተቶች ናቸው፡፡ ከፅንስ ጀምሮ የሰው ልጅ ብዙ ነገሮች ይገጥሙታል በዚያው በማህጸን እንዳለ ውርጃ ቀድሞት ከሚቀጨው ጀምሮ አርጅቶ እድሜን ጠግቦ እስከሚሞተው ድረስ በረዥሙ የሕይወት መንገድ ላይ አደጋ በሽታ ሀዘን ደስታ ኪሳራ ትርፍ መበልጸግ መደህየት ወዘተ….. ይገጥሙታል አንዱ ሀኪም ሌላው ወታደር ወይ ገበሬ አለበለዚያም አስተማሪነት የልዩ ልዩ ሰዎች እጣ ፈንታ ናቸው፡፡

ጊዜ ሰውን ኃላፊነት ግዴታና አደራን ያሸክመዋል ሀኪም በታማኝነት ከበሽተኞች ጋር ሥራውን ያከናውን ዘንድ ኃላፊነት ግዴታና አደራ አለበት ሌላውም በሙያው እንዲሁ፡ አንድ አብይ እውነት ደግሞ አለ ሁሉም ሰው ሀኪም የአንድ አገር ዜጋ እንዳለ አስተማሪ ወይ ገበሬ አልያም ነጋዴ አይሆንም ታይቶም አጋጥሞም አያውቅ ይህ የዓለም የውል ሕግ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሌላ ሰማያዊ ሕግ አለ ሁሉም ሰው ዳግም የተወለደ የክርስቶስ ደቀመዝሙር የእግዚአብሔር ሠራተኛ ሊሆን ይገባዋል ይላል በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና (ዮሐ 3፡16) በሕይወት ጎዳና ላይ በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር የመዳን ዕድል የገጠመን ሁሉ ደስ ሊለን ይገባል በዚህ ዓለም እለን የእግዚአብሔር በር ተከፍቶልናል የእግዚአብሔርም ልጅ የመሆን ሥልጣን ተሰጥቶናል (አደራም) ኃላፊነትም ተሰጠው ግን ገና ከማለዳው ወደቀ ሳይሆንለት ቀረ፡፡ ኖህንም እንዲሁ በሕይወት መንገድ ላይ ሳለ እግዚአብሔር ትልቅ አደራ አሸከመው በድንቅ ሁኔታ አደራውን ተወጣ (ዘፍ.6-9)፡፡

አብርሃም ይሳቅና ያዕቆብ ሙሴና ኢያሱ ነገስታት ነቢያትና ካህናት በኋላም ሐዋርያት በየተራቸው የእግዚአብሔርን ሁሉ ን ትተው ዋጋ ከፍለው ያለፉት በማያልፈው ሥፍራ ናቸው አደራቸውን የረሱ ግዴታቸውን ያልተወጡ በተገላቢጦሽ እግዚአብሔርን ክደው ወደአልታሰበውና ወዳልተዘጋጀላቸው ሥፍራ ሄደዋል (ለዲያብሎስ ብቻ ተዘጋጅቶ ወደነበረው) የእግዚአብሔርን ሥራ ትውልድ ለትውልድ እያቀበለ ቆይቶ ዛሬ በዚህ ዘመን ላለነው ባለአደራዎች ደርሷል ለመሆኑ ተረኞቹ በዚህ ዘመን እኛ ብቻ መሆናችንን ተገንዝበናል አደራው ኃላፊነቱ ግዴታው ገብቶናል ለእያንዳንዳችን በግል የተሰጠንን የሥራ ድርሻ አውቀናል ወደኋላ መለስ ብለን ያለጦርነትያለውጊያ ያለ ተቃዋሚ የእግዚአብሔርን ሥራ ያከናወነ የለም ሁሉም በየተራቸው ተዋግተዋል ተጋድለዋል የተለየ ነገር ቢኖር በየዘመናቸው የሚገጥማቸው የውጊያ ዓይነት የተለያየ መሆኑ ነው፡፡የአብርሐም ፈተናው ከሚወዳቸው መለየት በመገንዘብ ላይ መጨከን በልጁ ላይ ቢላዋ መሰንዘር ነበሩ ሙሴ ከፈርኦንንና ሠራዊቱ ጋር አስማተኞችና ጠንቋዮች ጋር መታገል ነበረበት በሐዋርያት ላይ ዲያብሎስ ቄሳሮችን አይሁድ ካህናትና አረመኔዎች አሳልፎ ባቸዋል ሁሉም ግን እያሸነፉ አለፉ ምክኒያቱም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነበርና ለዛሬዎቹ ባላደራዎች ሠይጣን እንዲሁ ስስ ጎናችንን እየፈለገ ሊዋጋን አያንቀላፋም አይቦዝንም አይደክምም አይታክትም፡፡

ዛሬ እንዳለፈው ዘመን የድንጋይ ወገራ የጦርነት የጎራዴ ስንዘራ አያጋጥመን ይሆናል ግን ከመገረፍም ከመወገርም ከመታረድም ያላነሰ ፈተና ሰይጣን አለው ለዲያብሎስ ትልቁ ዓላማው የእግዚአብሔርን ሠራተኛ ከሥራው መለየት ነው ለአሁኑ ተረኛ ባለአደራ ምቾትን ገንዘብን ሥልጣንን በመጠቀም ለመጣል ይዞ መሰለፉን ተረኛው ባለአደራ አወቆ ይንቃ…… ዛሬ በየቦታው ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ምቾታችንን ቀድሞ ድርድር ውስጥ ይገባል የዛሬዎቹ ተረኛ ባለአደራዎች የእግዚአብሔርን ቃል ታዘን ካገለገልን በኋላ ክብሩን ሁሉ ለእግዚአብሔር መስጠት አለብን የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ልንለውጠው አልተፈቀደልንም፡፡ የተጠራው የእርሱን ማንነት ለማወጅ ነው ሳናውቀው ክብሩን እየተሻማን ይሆን? የዲያብሎስ የውጊያ ዓይነቱ ብዙ ነው በሥልጣን ከፍ ከፍ ማድረግ አዲስ ዘዴው ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ ዋና መሥሪያው ነው ከእኔ በላይ ማን አለ ብቁ መሪ እኔ ብቻ ነኝ እኔ ከሌለሁ ቤተክርስቲያን አትቆምም በማሰኘት ለመጣል ኃብረትን ለማፍረስ እየተሯሯጠ ነው::ምቾትን ትቶ ለጌታ ማደር ቀላል አይደለም እንግዲህ የእግዚአብሔር ሥራ ሲሰራ ኖሯል ዛሬ በዘመኑ ፍጻሜ ላይ ተራ የደረሰን ባለአደራዎች የተቀበልነውን ኃላፊነት አንዘንጋ የተሰጠንን አደራ እንፈጽም ግዴታችንን እንወጣ የቀደሙት አባቶች የሄዱበትን ምንገድ እንይ የክርስቶስን ፈለግ እንከተል የተሰጠንን አደራ ለይተን እንወቅ የዛሬውን ባላደራና የዛሬው ተረኛ በሕይወት መንገድ ላይ ስንጓዝ ከእግዚአብሔር የተሰጠህን ኃላፊነት አትዘንጋ በየሰዓቱ በየቀኑ ምን እያደረክ እንደሆነ ራስህን መርምር ጊዜው ፈጣን ነው የሥራው ባለቤት ከደጅ ነው ወንድሜ ተዘጋጅ እህቴ ተዘጋጂ፡፡

ብርሃን መፅሔት
1991 ቁጥር 32

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox