ለምን መንፈሳዊ የንግግር ሕክምና ያስፈልገኛል /ያስፈልጋችኋል

ቤኪ ሃርሊንግ :

ሁለቱ የልጅ ልጆቼ በንግግር ህክምና ውስጥ ናቸው ፡፡ በሐቀኝነት አንዳንድ ጊዜ እኔም የንግግር ሕክምና እንደሚያስፈልገኝ ይሰማኛል! እናንተስ? አንደበታችሁ ችግር ውስጥ ያስገባችኋል? አውቃለሁ – የኔም!

የመጽሐፈ ምሳሌ ጠቢብ ጸሐፊ እንደ ጻፍው፣ “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው” (ምሳ 18፡21)፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ ጻፍው፣ “እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል
ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ” (ኤፌ 4፡29)፡፡ “ክፉ” የሚለው ቃል የተበላሸ ፣ የበሰበሰ እና ስለ ሞት መናገር
ማለት ነው ፡፡ በሌላ አገላለጽ ፣ ሕይወት የሚሰጠውን የእምነት ቃላትን እንድንመርጥ መጽሐፈ ቅዱስ
ያሳስበናል ፡፡
ክፉ ቃላት አሉታዊ፣ብልሹ ወይም ሌሎችን የሚያፈርስ ቃላት ምድብ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ ፡፡ ኢየሱስ ራሱ
እንደዳለው፣ “እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ
ይሰጡበታል፤ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ” (ማቴ 12፡36-37)፡፡
ከአንደበታችን ስለሚወጣው ተጠያቂዎች እንሆናለን ፡፡ አስፈሪ ሐሳብ ነው!

ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ አንደበታችንን ሌሎችን ወደ ህይወት ለማምጣት እንዴት እንጠቀማለን? በተናገርነው
ቃሎች ምክንያት በህይወታችን መጨረሻ ላይ እንዳናፍር አንደበታችንን እንዴት ልንጠቀም ይገባናል? በዚህ ትንሽ
ሆኖም ኃይለኛ በሆነው የሰውነታችን መሣሪያ ዙሪያ ድንበሮችን እንዴት እናስቀምጣለን?
ምሳሌ 18 በቃላታችን ዙሪያ ወሰን እንዴት ማቀናጀት እንደሚቻል የተወሰኑ ምክሮችን ይሰጠናል፡
የራስህን አስተያየት ማናፈስ አያስደስትህ
“ሰነፍ የጥበብን ነገር አይወድድም፤ በልቡ ያለውን ሁሉ መግለጥ ብቻ ይወድዳል እንጂ” (ምሳ 18፡2)፡፡
እኛ ከራሳችን አስተያየት ጋር ፍቅር ውስጥ ነን ፡፡ ይህንን ሀሳብ የምትጠራጠሩ ከሆነ በቀላሉ ማህበራዊ ሚዲያ
ውስጥ ተመልከቱ፡፡ በሁሉም ነገር ላይ ብዙ አስተያየቶች አሉ!
አስተያየቶች የተሳሳቱ አይደሉም፡፡ የእኛ ማንነት ለመግለጽ ይረዱናል፡፡ በአክብሮት የሌሎችን አስተያየት
ሳያዳምጡ የራስን ሃሳብ ብቻ ማናፈስ ግን ሞኝነት ነው፡፡ በሁሉም ነገር ላይ የእናንተን አመለካከት ማጋራት
አስፈላጊ አይደለም፡፡ አንዳንድ ሀሳቦች ሳይነገሩ ቢታለፉ የተሻሉ ናቸው፣በተለይ ግንኙነት ለመገንባት
በሚሞክሩበት ጊዜ፡፡ አመለካከቶቻቹን መስዋእት ማድረግ የለባቹም፡፡ የናንተ የራሳቹ የሆነ አስተያየት ሊኖራቹ
ይችላል፤ነገር ግን ሁሉንም ማጋራት አያስፈልግም፡፡ በሁሉም ጥቃቅን ጉዳዮች ላይ አመለካከታችንን መግለፅ
አስፈላጊ ሆኖ ሲሰማን ብዙውን ጊዜ በራስ የመተማመን ስሜት ስለማይሰማን ሌሎች ከእኛ ጋር እንዲስማሙ
ለማሳመን እየሞከርን ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር ላይ ባንስማማም ግንኙነት ሊኖረው ይችላል፡፡
ሐሜት አታድርግ
“የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥ እርሱም እስከ ሆድ ጕርጆች ድረስ ይወርዳል” (ምሳ 18፡8)፡፡
ጥሩ መመሪያ ይኸውላቹ፤በውይይቶቻቹ ውስጥ ሌላን ሰው በመጥፎ ብርሃን አትጣሉ እና ሚስጥራዊ መረጃን
አታጋሩ፡፡ ሌሎችን በአዎንታዊ ብርሃን ሳሉ፡፡ የሚያሳስባቹ ነገር ካለ ፀልዩ እና ከእግዚአብሔር ጋር ተማከሩ፡፡
አንዳንድ ጊዜ አስተዋይ ወዳጅ ወይም አማካሪ ማማከር አስፈላጊ ነው፤ነገር ግን ከሚገባ በላይ አትጋሩ፡፡
መጽሐፈ ቅዱስ በሐሜት ላይ በጣም ግልፅ ነው – ስህተት ነው፡፡ ስለዚህ አቁም፡፡

መጀመሪያ ሳታዳምጡ መልስ አትስጡ
“ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል” (ምሳ 18፡13)፡፡
ፍርድ ነው አይደል? መልስ ከመመለሳቹ ፣ አስተያየት ከመስጠታቹ ወይም ምንም ነገር ከመናገራቹ በፊት
ግለሰቡ ሀሳቡን እንዲጨርስ ፍቀዱለት፡፡ በሌላ አነጋገር ለማዳመጥ እንጂ ለመናገር አትቾክሉ (ያዕ 1፡19)፡፡
በዙሪያቹ መሰማት የሚያስፍልገው ማነው? ቀስ በሉ ና አዳምጡ፡፡
በንግግራቹ ዙሪያ ድንበር ማበጅት ይጠቅማል፤ግን እንዴት ሌሎችን በሚያንፅ እና በሚያበረታታ መንገድ
ትናገራላቹ? ብዙ ጊዜ አሞጋግሱ፡፡ አዘውትራቹ አበረታቱ፡፡ በየጊዜው አጽናኑ፡፡ እናም ያለማቋረጥ ጸልዩ፡፡
አንደበታቹ ሌሎችን ወደ ሕይወት የመመለስ አቅም ያለው መሆኑን በየቀኑ አስታውሱ፡፡ የምንኖረው ሰዎች
ብርታትን እጅግ በጣም የሚሹበት ዓለም ውስጥ መሆኑን አምኛለሁ፡፡ ስለዚህ እነሱን ለማጎልበት ዕድሉ
እንዳያመልጣቹ!
አንድ አፍታ ወስዳቹው ከእኔ ጋር ይህን ጸሎት ጸልዩ፡ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ፤ ብዙ ጊዜ በአንደበቴ እሳሳታለው፡፡
መንፈስ ቅዱስ ፤ ሙላኝ፡፡ የአፌ ቃል አንተን ደስ የሚይሰኝ እና ለሌሎችም የሚያነቃቃ ይሁን፡፡ ጌታ ሆይ ፤
በአፌ ላይ ድንበር አብጅ፡፡ ማንኛውንም ክፉ ቃል ወይም ተስፋ የሚያስቆርጥ ቃል እንዳልናገር እርዳኝ፡፡ ይልቁን
አፌን በምስጋና እና በደስታ ቃላትን ሙላው፡፡

Download Here

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox