ሁሉም ኃጥያት በ አምላክ ዕይታ እኩል ነውን ?

ቢል ዊዝ :

አንዳንድ ሰዎች አምላክ ሁሉን ኃጥያት በ እኩል ያያል ሲሉ ይናገራሉ ። አንዱ ኃጥያት ከሌላው አይከፋም ። እነዚህ አረፍተ ነገሮች በ
እውነት ልክ አይደሉም አማኝ ያልሆኑ ሰዎች ልብ ሊሉ የሚገባው ነገር እግዚአብሔር ሁሉንም ኃጥያቶች አንድ ዓይነት አድርጎ
እንደማይመለከት ማወቅ አለባቸው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ የኃጥያት እና የቅጣት ደረጃዎችን ያስቀምጣል፡፡

በክፋት ደረጃ ቀዳሚ የሆነ ኃጥያት አለ ፣ ስለሆነም ከበድ ያለ ቅጣት ይገባዋል። የኃጥያት ደመወዝ ሞት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ
ይናገራል ፡፡ ሮሜ 6፥23 በሀሳብ ፣ በቃልም ሆነ በተግባር ስለ ኃጥያትን ያወሳል፡፡

እግዚአብሔር እየሱስን በመላክ መለኪያውን ከፍ አደረገ ፡፡ ኢየሱስ በአዲሱ ኪዳን ውስጥ አንድን ሰው ጥፋተኛ ያደረገው የውጭ
ኃጢአት ብቻ አለመሆኑን ሲናገር ግልፅ አድርጎታል ፡፡ ኃጥያት በሰው ልብ ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ ውጫዊ መግለጫ ነው ፡፡
ስለዚህ የሚሰሯቸው ነገሮች ብቻ አይደሉም ኃጥያት የሚባለው በልብዎ ውስጥ የሚያስቡትም ጭምር ነው ፡፡

በጣም ማወቅ የምፈልገው ጥያቄ “ኃጥያታችን ወደ ገሃነም ያስገባናል?” የሚለው ነው ፡፡ ለዚ መልሱ ሊያስገባን አይችልም
የሚለው ነው ፡፡ እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በጸጋ ድነናል ምንክያቱም እግዚአብሔር ስለሚወደን ኢየሱስን ስለ እኛ ኃጥያት
በእኛ ምትክ እንዲሞት እና በድል ወደ ሕይወት እንዲነሳ ላከው ፡፡


ወደ ሲኦል የሚወስደን ኃጥያታችን ብቻ አደለም ፣ አንድ ሰው ለኃጥያታችን የተከፈለውን ብቸኛ ነገር ካልተቀበል ወደ መንግ
ሰማይ አይገባም ፡፡ በመስቀል ላይ የተጠናቀቀውን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ አለመቀበል ሰውን ወደ ገሃነም ያመራዋል ፡፡ ይህም
ይቅር የማይባል ኃጥያት ነው ፡፡ ኢየሱስ ወደ መስቀል የወጣው የኃጥአትን ኃይል ለማውደም እና ከ እኛ ከክርስቲያኖች ሕይወት
ላይም ለማጥፋት ነው ፡፡ ሰዎች ከኃጥያታቸው ንፁህ ሆኖ እንዲገኙ ኢየሱስን መምረጥ አለባቸው ፡፡

Download Here 

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow by Email
YouTube
YouTube
Set Youtube Channel ID
Telegram

ማሕደር

Language
WordPress Image Lightbox